11 Jul 2026, 10:32 UTC95 views4 reactionsread 7 August 2026 ጠላሽኝ አሉ😔
ጠላሽኝ አሉኝ እውነት ነው ወይ ወሬው?
ልቤ ለአፍታ እንኳን ካንቺ የማይርቀው፤
ይህን ክፉ ወሬ በሰማበት ቅጽበት፣
በአሳብ ተመታ ጠፋበት መውጫው።
ሳይሽ የምፈዝዘው ያንቺው አፍቃሪ ትላንት፣
ዛሬ "ጠላሽኝ" ሲሉኝ የት ይግባ የልቤ እውነት?
የሰዎች አሉባልታ ከንቱ ይሁን ወሬው፣
የኔማ ፍቅር ለአንቺ ነው ጽኑ የነበረው።
ካንቺ መለየትማ ለኔ ጨለማ ነው፣
ይህን የመርዶ ቃል ማን ነው የፈጠረው?
እስኪ በአፍሽ ንገሪኝ እውነቱን ልስማው፣
ልቤ ዛሬም ድረስ ያንቺው አፍቃሪ ነው!
🥰@fekerenagetemoch❤️
👍2❤1😍1
Signed Yova🙃
9 Jul 2026, 10:19 UTC108 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
9 Jul 2026, 10:17 UTC95 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
9 Jul 2026, 10:12 UTC81 views3 reactionsread 7 August 2026 ንገሪኝ በሞቴ
አንቺን ለመውደዴ ፍቅር ትሩፋቴ ፤
በምን ልግለፅልሽ ንገሪኝ በሞቴ ።
ያሻሽን ጠይቂኝ ላረጋግጥልሽ፤
ከጉድጓድ ወጥቼ ሰማይ ላይ ልውጣልሽ ፤
ማፍቀሬን ስነግርሽ ሁሌ እንደማስብሽ ፤
አፌን ተጠራጥርሽ ካላመነኝ ልብሽ ።
እኮ በይ ንገሪኝ እምነቴን ልወጣ ፤
ጨረቃን ሰብሬ ሽራፊዋን ላምጣ ።
ፍቅሬ ሆይ አትፍሪኝ ንገሪኝ በድፍረት ፤
ጎኔን አልጋ አይንካው ልደፋ ከመሬት ፤
ሀሞት እንደ ወይን ልጎንጭልሽ እሬት ።
የልቤን የውስጤን ፍቅሬን ያሳይሽ ፤
በፀሀይ ስባሪ መነፅር ልስራልሽ ፤
ንገሪኝ ውዴ ከቶ ምን ላድርግልሽ ፤
እውነተኛ ፍቅሬን በምን ልግለፅልሽ ።
ግን አደራ ውዴ ............
አንቺን ለመውደዴ…...........
ሙትልኝ አትበይ ስቃይን ፈ…
👍3
9 Jul 2026, 10:10 UTC82 views2 reactionsread 7 August 2026 Photo
ሳይሽ የምፈዝዘው ቃላት ከላዬ ጠፍቶ፣
አይኔ ካንቺው ገጽታ ላይነቀል ተመትቶ፤
ፈገግታሽ ልብ ገዝቶ ውስጤን ሲማርከው፣
ያለሽ ልዩ ውበት ከቶ ምንድን ነው?
አጠገቤ ስትሆኚ ሰዓቱ ይፈጥናል፣
ልቤ በአንቺ ፍቅር ክንፍ አውጥቶ ይበራል፤
አንቺን ላየሽ እኮ መፈዘዝ ግድ ነው፣
የፈጣሪ ጥበብ ባንቺ ነው ጎልቶ የታየው
ከወደዱት ለውዳጆ ያጋሩ 🙏
@fekerenagetemochu
👍2
9 Jul 2026, 10:05 UTC81 viewsread 7 August 2026 ❤️ፍቅር ብቻ🥰
ናፍቆትሽ ያስከፋኝ ተኝቼ ማልተኛ
አይንሽን ናፋቂ የቅፍሽ ራብተኛ
የእጅሽ አሳሽ ነኝ የድምጽሽ ፈላጊ
አይንሽን ለማየት ቀን ተሌት ጓጊ
አንቺን ማጣት ገሎ ፍቅርሽ የሚያድነኝ
ባለመኖርሽ ውስጥ ተስፋሽ የሚያኖረኝ
እኔ ማለት
ዛሬ እንዳጣሁሽ ያለው ጨልሞብኝ
ነገ እንደማገኝሽ አስቤ ያለሁኝ
እኔ ማለት
የሌሽበት ዛሬ ያስረጀኝ
የምትኖሪበት ነገዬ ህጻን ሚያረገኝ
እኔ ማለት በቃ አንቺ ነኝ
ከወደዱት ለወዳጆ አጋሩ 🙏
@fekerenagetemochu
28 Jun 2026, 20:38 UTC131 views2 reactionsread 7 August 2026 ታገስ!
ሁልጊዜም በህይወት መነሻህና መድረሻህ ስታስበው ቀላል ነው፤ መሀሉ ግን አይነገርም! አየህ ፈተናው፣ ተስፋ መቁረጡና ከባዱ ጊዜ ያለው መሀሉ ላይ ነው። ይሄን ወሳኝ ጊዜ በጥበብ ልታልፍ የምትችለው በአንድ ነገር ብቻ ነው 'በትዕግስት!' ወዳጄ ታገስ አለበለዚያ ምንም ብትለፋ ህይወትህን አትቀይርም!
@fekerenagetemochu
❤2
Signed Yova🙃
26 Jun 2026, 13:35 UTC146 viewsread 7 August 2026 ሐዘን በጥርስ ይደበቃል😔
ውስጡ እየቆሰለ በሐዘን ተመትቶ
ሰው ይስቃል እኮ መከራውን ውጦ
የነፍሱን እንባ በፈገግታ ከልሎ
ቀኑን ያሳልፋል የውስጡን ደብቆ
ከንፈር ይገለጣል በጥርስ ብርሃን
ለመሸሸግ ሲባል የልብን ስብራት
በሰው ፊት ስቆ መታየት ይቻላል
እውነት ነው ሐዘን በጥርስ ይደበቃል
@fekerenagetemochu
4 Jun 2026, 10:22 UTC211 views4 reactionsread 7 August 2026 የነፍሴ ዜማ❤️
አይኖችሽ ሲያዩኝ፣ ልቤ ይረታል፣
የቃላት ድርደራው፣ ከአንደበቴ ይጠፋል፤
አንቺ እኮ ለእኔ፣ የህይወቴ ትርጉም ነሽ፣
ብቸኝነቴን አጥፍተሽ፣ በደስታ የሞላሽ።
ሩቅ ብትሆኚ እንኳ፣ ከእኔ ተለይተሽ፣
ሀሳቤ ሁልጊዜ፣ ይበርራል ወደ አንቺው ዘንድ፤
ያለ አንቺ መኖርማ፣ ትርጉም የለውም ለእኔ፣
አንቺ ነሽና ብርሃኔ፣ የዓይኔ ማረፊያ፣ የልቤ እረፍት
@fekerenagetemochu
❤4
Signed Last Seen
4 Jun 2026, 10:18 UTC196 viewsread 7 August 2026 የልቤ ማረፊያ🥰
ካንቺ መለየትማ መቼ ይቻለኛል፣
ውበትሽ በህልሜ ቀን ማታ ይታየኛል፤
አንቺ እኮ የነፍሴ፣ የልቤ ሙቀት ነሽ፣
ጨለማውን ህይወቴን በፈገግታሽ የምታበሪው ነሽ።
እንደ ወንዝ ፈሳሽ፣ እንደ ንጹህ አየር፣
ፍቅርሽ በደም ስሬ ሁልጊዜ ሲመላለስ ይኖራል፤
በአለም ላይ ካሉት ውድ ነገሮች ሁሉ፣
ላንቺ ያለኝ ፍቅር ልዩ ሆኖ ይበልጣል፤
አጠገቤ ሁኚልኝ፣ የኔ ውድ እመቤት፣
ካንቺ ጋር ብቻ ነውና የህይወቴ ሙሉነት
Signed Last Seen
14 Dec 2025, 20:25 UTC606 views11 reactionsread 7 August 2026 አስተውዪ
ከኋላሽ ያሉትን መጥፎ ትዝታዎች የምትመለከቺ ከሆነ ከፊትሽ ያሉትን ትላልቅ በረከቶች እና ስኬቶች አታዪም።
ስለዚህ ወደኋላ ሳይሆን ሁልጊዜ ወደፊት ተግባባን ጀግኒት!!
👍7❤3🫡1
Signed መንፈሳዊ ግጥም የናዝሬት ቦኩ ደ/ም/ቅ/ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ቤት
17 Oct 2025, 19:22 UTC669 views3 reactionsread 7 August 2026 መልስ
አትዘን ግድ የለም አንገትህን አትድፋ
ዳግም እንዳትጠለፍ ከዚህ ቦታ ጥፋ
በዝንጀሮ ቦታ ዝንጀሮ የሆኑ
አራዊት ሞልተዋል የማይታመኑ
ሴትና ህፃናት ሽማግሌም አይለዪም
ሰው እየገደሉ እነርሱም አይቆዪም
በእረጅና ዘመንህ ምንም ባትዋጋ
ለፈጣረህ አመልክት በፀሎትህ በረታ
❤️@fekerenagetemochu🥰
Like🥰
Share
🥰3
Signed መንፈሳዊ ግጥም የናዝሬት ቦኩ ደ/ም/ቅ/ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ቤት
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @fekerenagetemochu. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.