7 Dec 2025, 15:44 UTC≈2,250 views19 reactionsread 8 August 2026 ያኮረፉ ግዜ-
ለማማረር ሲባል ስምህ ትዝ የሚለው፣
ለማቀፍ ካልሆነ፣
ለመገፍተር ክንድህ የማይቸኳኩለው።
የፍቅር ዐይኖችህ-
ከፍርድና ቁጣህ ተስማምቶ የሚኖር፣
ምህረት መቅሰፍትህ፣
ሲመጣ ተዋርሶ ለልጅ ልጅ የሚቀር።
ግዜ የማይቀድምህ-
ከሯጭ እኩል ባትሮጥ መቅደም የተካንከው፣
በፍጥረት አንደበት፣
በልብም በአፍም የምትመለከው።
አሁን ባለህበት-
ስንት ጆሮ ኖሮህ ስንቱን ልትሰማነው፣
ጠያቂን አጥፍተህ፣
ምድር'ና ሰማይን የማትበታትነው?
(የሞገሴ ልጅ)
@eyadermoges
@eyadermoges
❤13🕊4👏2
Signed እያደር ሞገስ [የሞገሴ ልጅ]
15 Nov 2025, 11:29 UTC727 views13 reactionsread 8 August 2026 ቢሆንም ባይሆንም፡-
መልካሙን እናድርግ - ደግ ደግ እንሥራ፣
እኛ ምን አገባን፣
ነጋዴን ይጭነቀው - ትርፍ እና ኪሣራ።
@eyadermoges
👏8❤3🕊2
Signed እያደር ሞገስ [የሞገሴ ልጅ]
Eyader Moges pinned «ራሱ’ንደማይጠጣ - የውሃ ማሰሮ፣ መሆን ላልተቻለው - ክው ያለ ጉሮሮ፤ አስመሳይ ደጋጎች - ውሃ ሰጡት’ና፣ የሞት ሞቱን ሲኖር - ችግሩ እንደጠና፤ ጉሮሮ ማሰሮ - ተመሳስሎባቸው፣ ያጠጡትን ቀድተው - መውሰድ ላቃታቸው፤ ረሃብ አንጎራጉሮ - ለለመደው ውሃ፣ ሰጥቶ ተቀባዮች አስቀየመልሃ! (የሞገሴ ልጅ) @eyadermoges»
2 Nov 2025, 10:13 UTC≈2,640 views12 reactionsread 8 August 2026 ቤት እማ ጨዋ ነሽ፣
እንኳን ሌላ ሌላ እኔንም አታይም፣
ግን እድሜ ለሱሱ፣
ወተሽ ወዳጅ ካየሽ አታልፊም አትተይም።
የሸመገለን ወንድ፣
በሰለቸ ዐይንሽ ዕያየሽ ወጠምሻ፣
የሱን መድሃኒት፣
አርገሽ ለቀን ያዝሽው የኔን ማስታገሻ። @eyadermoges
😁10🕊2
Signed eyader Moges [የሞገሤ ልጅ]
26 Oct 2025, 13:11 UTC≈2,230 views13 reactionsread 8 August 2026 ሁለቱም ይኑሩ!
(የሞገሴ ልጅ)
አለመተዋወቅ..
አለመቀራረብ..
አለመነጋገር..
አለመደራረብ፤
ዶግማ ይሁን እና-
ብዙ ይራራቁ፣
አይነፋፈቁ፣
አይተዋወቁ፤
አንድ አይሁኑ እንጂ-
ችግር እንዳይመጣ፣
ኁለቱም ይኑሩ፣
ዐይን’ና ሚጥሚጣ።
ሼር ማድረግ ጥሩ ነው😁
@eyadermoges
❤11🕊2
Signed እያደር ሞገስ [የሞገሴ ልጅ]
25 Oct 2025, 15:47 UTC556 views6 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @socialworkforallVideo
Social work is as much an art as it is a science. You might wonder how—well, art is one of the most powerful ways to influence society. That’s why we are always delighted to see our students engaging in artistic activities alongside their academic pursuits.
We are pleased to share a selection of poems by our talented and courageous student, Eyader Moges, who performed these pieces at the inauguration of the renovati…
❤3👏2🕊1
Signed እያደር ሞገስ [የሞገሴ ልጅ]
25 Oct 2025, 15:47 UTC477 viewsread 8 August 2026 እኔም ግቢዬን እና የትምህርት ክፍሌን አመሠግናለሁኝ። በዚሁ አጋጣሚ ለሦሻል ወርክ ልባችሁ የሚያደላ ቻናሉን ብትቀላቀሉ እላለሁ።
Signed እያደር ሞገስ [የሞገሴ ልጅ]
24 Oct 2025, 18:32 UTC≈2,200 views4 reactionsread 8 August 2026 ሰማሽ ወይ...
ያደለው ለሃገር - ጥይቱን ይጠጣል፣
ያላደለው ደግሞ - ቢራ ያማርጣል፤
ያገኘ ላምላኩ - እጁን ይዘረጋል፣
ተስፋ ያጣ ሃገር - ጥሎ ይጠረጋል፤
ታዳጊው ጎርምሶ - ለትዳር ይታጫል፣
ያመለጠው ኖሮ - በትላንት ይቆጫል፤
ኁሉም የየራሱን - እያነሳ ጣለው፣
ያንችን እና የኔን..........እኔስ ምን ልበለው?
በቅንነት ሼር
@eyadermoges
❤4
Signed እያደር ሞገስ [የሞገሴ ልጅ]
18 Oct 2025, 18:22 UTC≈3,880 views8 reactionsread 8 August 2026 ያላንቺ ይቅርብኝ!
(የሞገሴ ልጅ)
ዐየሽ የኔ ናፍቆት-
ካንቺ በፊት እኔ - ኖሬአለሁ ለናቴ፣
ቆንጥጣ አባራኝ - በሚናፈቅ ቤቴ።
ያኔ ግን - ልጅነት-
ከጎኔ ስትለይ - ናፍቆት ቢቀጣኝም፣
አቅፋኝ እየተኛች፣
በናፍቆቷ መራብ - - ጭራሽ አያውቀኝም።
ጭራሽ አደግ ስል...
እሷን መውደድ ሳልተው - አንቺን በልብ ይዤ፣
አጠገቤ ሆነሽ፣
ናፍቆትሽን ፃፍኩት - ማግኘቴን ሰርዤ።
እንደው ግን የምልሽ?
እለት እለት ጾሜ፣
ያለኝን መፅውቼ፣
ከገነት ለመግባት - የምጠባበቀው፣
ካንቺ ጋራ ስሆን፣
ከሚሰማኝ ምቾት - እንዴት ነው ሚልቀው?
እንጃ ያሳስባል-
ካንቺ በላይ ናፍቆት የሚያስይዝ ቢመጣ፣
ከሆነ ነው እንጂ፣
አንችው ሰማይ ሆነሽ - ልቤ በልብሽ ላይ ገነት ተቀምጣ።
…
👏4🥰4
Signed እያደር ሞገስ [የሞገሴ ልጅ]
14 Oct 2025, 19:02 UTC≈1,800 views5 reactionsread 8 August 2026 ባቀፈሽ ካልቀናሁ፣
ካላማርሽ ካልከፋኝ፣
የያዝሽውን ካልያዝኩ - የጣልሽው ካልጠፋኝ፤
ሲአቅፉሽም ሲአሻሹሽ - ፊቴ ካልዳመነ፣
ደግ አረግሽ ብቻ ምኑን ፍቅር ሆነ?
@eyadermoges
👏5
Signed እያደር ሞገስ [የሞገሴ ልጅ]
Eyader Moges pinned «ውድ ቤተሠቦቼ ቻናሉን ለሌሎችም በማድረሥ እናሣድገው! @eyadermoges»
9 Oct 2025, 16:39 UTC619 views6 reactionsread 8 August 2026 ውድ ቤተሠቦቼ ቻናሉን ለሌሎችም በማድረሥ እናሣድገው! @eyadermoges
❤6
Signed eyader Moges [የሞገሤ ልጅ]
Showing the 12 most recent of 19 posts we hold for @eyadermoges. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.