19 May 2026, 19:27 UTC218 viewsread 23 August 2026 ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሉ የሆነ ህይወት የለም። በጎች እረኛቸው ከሌለ ሁሌም ተቅበዝባዥ ናቸውና
ህይወት ትርጉም የሚኖራት ፈጣሪዋን ስታገኘው ብቻ ነው። btw ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ከነ ድካማችን የሚወደን የሙሴ እናት እንኳን በዛ ዘመን ልጇን ከሞት የሸሸገችው "መልካም እንደሆነ አይታ" ነበር። ከኛ ምንም መልካም ነገር ሳይፈልግ በበደላችን ለሞትነው ለኛ ደካማውን ማንነታችንን በመስቀል ላይ የተሸከመልን ውዱ እረኛችን ኢየሱስ ነው።
ምንም ብትደክሙ ምን ያህል እንደወደዳችሁ፤ ይህም ፍቅሩ የወረት እንዳይደለ እወቁ።
Signed N-ZION
15 May 2026, 11:14 UTC112 viewsread 23 August 2026 Forwarded from @beteafework
በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው።
(ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ -የኤፍራጥስ ወንዝ ገጽ 87)
Signed N-ZION
14 May 2026, 08:02 UTC191 viewsread 23 August 2026 እጃችን በጠጠር የተሞላ ከሆነ እንዴት አድርገን ወርቁን መቀበል እንችላለን ?
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
ጠጠር የተባለውን የልምድ ሀጥያት ትተን ከወርቅም በላይ የሆነውን በደሙ የገዛንን ክርስቶስ ኢየሱስን ወደ ህይወታችን እንጥራው 🙏😊
Signed N-ZION
9 May 2026, 18:26 UTC212 viewsread 23 August 2026 የዛሬ አመት እዚው Chanel ላይ የተለቀቀ በደንብ ይነበብ ።
Signed N-ZION
9 May 2026, 18:25 UTC103 views1 reactionsread 23 August 2026 የግንቦት ፩ ትዝብት !!
ትላንት እና ማለትም አርብ የእመቤታችንን የልደታ ለማርያም የተወለደችበትን ቀን ግንቦት አንድ በዓለ ልደቷን አክብረናል እንደሚታወቀው የእመቤታችንን በዓለ ልደት የምናከብረው ማታ ላይ ሰብሰብ ብለን የቤታችን በረንዳ ላይ በመብላት እና በመጠጣት ነው የምናሳልፈው ይሄንን ለምንድነው የምናደርገው ሰፊ እርዕስ ነው እዚህ ውስጥ አልገባም ሀሳቤም ይሄ አይደለም : እናም ለአመታት የታዘብኩትን እና ቅር የምሰኝበትን ነገር መሆን የለበትም መቅረት አለበት ብዬ የምለውን ነገር እንደሚከተለው በተወሰኑ መስመሮች ላይ ለማስቀመጥ ልሞክር ምን መሰላችሁ :- ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት የእመቤታችንን የልደት በዓል የምናከብረው ውጪ ላይ በመብላት እና በ…
❤1
Signed N-ZION
9 May 2026, 04:23 UTC144 views1 reactionsread 23 August 2026 Photo
ነብያት ትንቢት የተናገሩለትን ፃድቃን በሱባኤ ይወርዳል ይወለዳል ያሉትን ሙሴ ፊቱን ማየት ፈልጎ ለማየት ያልቻለውን በሲና ተራራ ላይ በሚያስፈራ ግርማ የተገለጠውን አምላክ የወለደች ንፅህተ ንፁሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ዛሬ ተወለደች የአምላክ እናት Theotokos ለማንም የሌለ ሱራፌል እና ኪሩቤል ሊሸከሙት ያልቻላቸውን አምላክ ድንግል ማርያም የመለኮት ማደሪያ ልትሆን ዛሬ ተወለደች 🥰
❤1
Signed N-ZION
8 May 2026, 19:49 UTC130 viewsread 23 August 2026 “ዛሬ በዓለም ሁሉ ደስታ ሆነ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር እናት ተወለደች።”
ዩሐንስ ዘደማስቆ
Signed N-ZION
5 May 2026, 08:49 UTC179 viewsread 23 August 2026 የኔ መድኃኔዓለም ሆይ እኔን ይስቀሉኝ ያኔ አይሁድ መራራውን ሀሞት አጠጡህ ለኔ ብለህ ÷ መድኃኔዓለም ሆይ ከኔ በላይ ሀሞት አለ ? ከዚያ መራራ ሀሞት ይልቅ እኔ አላስመረርኩህም እኔ አላሰቃየሁክም አንተ እንዴት ለኔ ትሞታለህ ? እኔን ይስቀሉኝ እንጂ ያኔ ጎንህን በጦር የወጋህ እኮ የሮም ወታደር ነው ምን ያውቃል ስላንተ ከጎንህ የፈሰሰውን ውሃ ሲያይ ወዲያው አይደል የተመለሰው ÷ እኔ ግን ምንድነኝ ጌታ ሆይ ከጎነህ በፈሰሰው ደም ድኜ እንዴት ነው እድሜ ልኬን ስወጋህ የምኖረው እንዴት ለኔ ተሰቀልክ እንዴት ለኔ ዋጋ ከፈልክ ነፍስህ በምትወጣበት በዛች ቅፅበት እጅህን በችንካር ለቸነከሩህ ለፈረዱብህ ለሰደቡህ ላንገላቱህ ሁሉ ይቅርታን የምትሰጥ እንዴት ቸር ብትሆ…
Signed N-ZION
4 May 2026, 13:55 UTC149 viewsread 23 August 2026 ከጉያው አውጥቶ ማነው የሚገድለን
ጠላት የማይደፍረን የንጉስ ልጆች ነን
🎧🎧
ጌታ ኢየሱስን እርሱን ተጠግተን ማንም አይደፍረንም 🥰
Signed N-ZION
4 May 2026, 12:02 UTC167 views1 reactionsread 23 August 2026 ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል። ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
ራዕ 22:4-5
ጌታ ኢየሱስን ይዘን የትኛውም ጨለማ አያስፈራንም የትኛውም ማዕበል አያስደነግጠንም ምክንያቱም የበጉ ስም በግንባራችን አለና። የበጉን ደም በግንባራችን የምንጽፈው በአንድ ነገር ነው ከ ቅዱሱ ሚስጢር ቶሎ ቶሎ በመካፈል እና ስጋ እና ደሙን ቶሎ ቶሎ እየተቀበልን አደራ 😊
❤1
Signed N-ZION
2 May 2026, 22:59 UTC172 viewsread 23 August 2026 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ኢሳ 41-10
Signed N-ZION
1 May 2026, 05:01 UTC198 viewsread 23 August 2026 እስቲ ይሄንን የቅዱስ ጊዮርጊስን መዝሙር ተጋበዙልኝ 🥰
Signed N-ZION
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @ethiopa_liturgy. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.