25 Sept 2024, 05:04 UTC≈24,200 views310 reactionsread 28 August 2026 + #አምናለሁ_እና_አላምንም +
ልጁ የታመመበት አባት ነው። ጌታን " #ቢቻልህስ_ልጄን_ፈውስልኝ " አለው:: ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡ አለው።
ይህን ጊዜ ሰውዬው " #ወዲያውም_የብላቴናው_አባት_ጮኾ ፦ #አምናለሁ_አለማመኔን_እርዳው፡ አለ" ማር. 9:24
የዚህ ሰውዬ ንግግር ፍቺ የሚፈልግ ቅኔ ይሆንብኛል " #አምናለሁ_አለማመኔን_እርዳው "
ይኼ ሰውዬ ያምናል ወይንስ አያምንም❓
ያምናል እንዳንል " #አለማመኔን " ይላል ፤ አያምንም እንዳንል " #አምናለሁ " ይላል። የቸገረ ነገር ነው❓ ሁሉን አዋቂው መድኃኔዓለም ምን ለማለት እንደፈለገ ገብቶት ልጁን ፈወሰለት:: እኔ አላዋቂው ግን " #አምናለሁ_አለማመኔን_እርዳው " የሚ…
❤192🙏56😭18💯15🥰14👎7😡5👏3
Signed Bini
24 Sept 2024, 03:31 UTC≈17,300 views99 reactionsread 28 August 2026 +++ የዘመኑ ፈተና... +++
የራስ ጸጉሩን በመጠኑ ለመስተካከል አንድ ሰው ወደ ጸጉር ቤት ያመራል፡፡ የጸጉር ውበት ባለሙያውም ያለመጠን ብቅ ብቅ ያሉ የጸጉር ዘለላዎቹን ከማረም ጋር ጥቂት ጨዋታ ቢጤ ይጀምራሉ፡፡
ጸጉር ቆራጭ- ወንድሜ በእግዚአብሔር መኖር ታምናለህን?
ተቆራጭ- እንዴታ?! ምን ጥርጥር አለው፡፡
ጸጉር ቆራጭ- እኔ ግን በእግዚአብሔር መኖር አላምንም፡፡ ያንተም እምነት ልክ እንደሆነ አላስብም፡፡ እስኪ አስተውል! ዓለምን እና በውስጧ የሚኖሩትን የፈጠረ በጎ ፣የፍጥረቱንም መጎዳት የማይሻ መልካም አምላክ ቢኖር ኖሮ ዓለም እንዲህ በጥፋት ባልታመሰች፡፡ አሁን ወደ ጎዳናው ብትወጣ አሳዳጊ አጥተው በደዌ ተይዘው በየሜዳው የተበተኑ …
🙏58❤33🥰6😡2
Signed Bini
23 Sept 2024, 04:36 UTC≈13,000 views54 reactionsread 28 August 2026 +• ጊዜው ገና ነው •+
አንድ ምንጩ የማይታወቅ አስተማሪ የሆነ አፈ-ታሪክ አለ። በዚህ አፈ-ታሪክ መሠረት፥ ከዕለታት በአንዱ ቀን አጋንንት ስብሰባ አደረጉ ይባላል። ይህንን ስብሰባ የጠራው የአጋንንቱ አለቃም “ዓለምን ሁሉ ከእኔ ጋር ለማሰለፍ እፈልጋለሁ። ምን ይደረግ? ማንንስ ልላክ?” ብሎ ጠየቀ። ከሥሩ ያሉትም አንድ በአንድ እየተነሱ አሳቦችን ማቅረብ ጀመሩ።
አንዱ ተነሳና፥ “እኔን ብትልከኝ፥ ፈጣሪ የለም ብዬ ሰዎችን ማሳመን እችላለሁ!” ብሎ ተናገረ። የአጋንንቱ አለቃ ግን፥ “እርሱ አይሠራም። ብዙዎቹ አያምኑህም። ፈጣሪ እንዳለ ያውቃሉ።” ብሎ መለሰ።
ሌላኛው ተነሳና፥ “እኔን ከላክኸኝ፥ ገነትም ሆነ ሲኦል የሚባል ቦታ እንደሌለ አሳምናቸዋለሁ!” አለ።…
🙏37❤12🥰5
Signed Bini
20 Sept 2024, 03:54 UTC≈9,440 views78 reactionsread 28 August 2026 አንዲት በትዳሯ በባሏ ሐይለኛነት ሞገደኛነት ትእግስት አልባነት የተጨነቀችና የተማረረች
ሴት ወደ ንስሐ አባቷ ሔዳ እያለቀሰች "አባቴ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ባላውቅም አሁንስ
በቃኝ ከዚህ ሰውጋር መኖር አልችልም "ስትል ትናገራቸዋለች።
ንስሐ አባቷም እንዲህ ሲሉ ይመክሯታል ። "ልጄ በአንድ አፍ ውስጥ የሚኖሩትን ጥርስንና
ምላስን አስታውሺ። እነዚህ አካላት ተፈጥሮአቸው የተለያየ ነው። ጥርስ ነጭ ነው ምላስ
ቀይ ናት። ጥርስ ጠንካራ ስለታም ነው ምላስ በጣም ለስላሳ ናት። አፍ ሲከፈትላት ምላስ
ትወጣለች። ሲከደን በገዛ ጎረቤቷ ላለመጎዳት ትሸሻለች። ጥርስ ያደማውን እጅ ምላስ
ትልስለታለች። ጥርስ ሲያኝክ ምላስ ታርስለታለች። የፊት ጥርስ ማኘክ ሲከብደው ወደ መንጋ…
❤56🙏19👏2👎1
Signed ༒︎𝔚𝔢𝔫ø𝔫 𝔚ℯ𝓃𝒶
19 Sept 2024, 04:01 UTC≈11,400 views83 reactionsread 28 August 2026 💀 የሰይጣን ለቅሶ 💀
አንድ ለመመንኮስ የፈለገ ወጣኒ ወደ አበመኔቱ ይሄድና እንዲያመነኩሰው ይጠይቀዋል አበመኔቱም እንዳመነኩስህ ከፈለክ ሂድና በእስክንድርያ አደባባዮች እኔ ዘማዊ ነኝ እያልክ ለመንገደኛው ሁሉ ንገር ይለዋል ይህም ወጣት እንደታዘዘው ሲያደርግ ውሎ በነጋታው ጠዋት ቤተክርስቲያን ሲገባ በዚያ የተሰበሰቡት ሁሉ "አንተ ዘማዊ እያሉ አፌዙበት
አበመኔቱም "አዎ አንተ ሀጢያተኛ ነህ" ብሎ አስወጣው ወጣቱም ምንም ሳይናገር ወጣ ይህ ወጣት ከወጣ በኋላ ግን አበመኔቱ ለተሰበሰቡት ምዕመናን እንዲህ አላቸው
👉"በትክክል ለምንኩስና የታጨች ነፍስ ይህቺ ናት እናንተ ስትስቁበት አጋንንት ግን ሲያለቅሱ አያቸው ነበር፣ እኛ ሀጢአቱን ስንዘረዝር መላእክት ግን ስሙን …
❤47🙏31💯5
Signed Bini
18 Sept 2024, 03:23 UTC≈7,960 views94 reactionsread 28 August 2026 Photo
በዝምታው ፥ በቅድስና ሕይወቱና በብቸኝነት የሚታወቁት ጻዲቅ ዝምተኛው መነኩሴ "አባ ዮስጦስ" በገዳመ እንጦስ ከተናገሯቸው በጥቂቱ፦
<ስለ ዝምታ>
☞ ከማድረግ መናገር ይቀላል ነገር ግን ልብ ወደ ሰማይ የሚወጣው በመናገር አይደለም ፤ ወደ ጌታችን መቅረብ የምትችለው በቃላት አይደለም፡፡
☞ አንዳንድ ጊዜ ዝምተኛ ነኝ ነገር ግን ዝምታዬ ከእንባዬ ይልቅ ኃይል እንዳለው ይሰማኛል፡፡
☞ ዝምተኛ ብሆንም ልቤ ግን በቃላት የተሞላ ስለሆነ እግዚአብሔር ሳልናገር ይሰማቸዋል ፤ የእግዚአብሔር ልብ ግን የርኅራኄ ፏፏቴ ነው፡፡
☞ ቅድስና ቆሽሾ ከመታየት ጋር የማገናኘው ነገር የለም ፤ ከልብ ንጽሕና ጋር እንጂ፡፡
☞ ማናችንም በራሳችን መልካም አይደለንምና ፤ የእግዚአ…
❤64🙏30
Signed Bini
17 Sept 2024, 04:05 UTC≈6,730 views42 reactionsread 28 August 2026 የምንለወጠው ምን ስናደርግ ነው❓
በታመምህ ጊዜ ድካም ይሰማሃል፤ ብርታት ያንስሃል፤ ፊትህም ይገረጣል፡፡ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህን በአግባቡ ማከናወን ይሳንሃል፡፡ በዚህ ጊዜም ሕመምህ ምን ያህል እንደ በረታ ሰዎች ያስተውላሉ፤ መታከም እንደሚገባህም ይነግሩሃል፡፡ ስለዚህ ወደ ሐኪም ትኼዳለህ፡፡ ወደ ሐኪም የምትኼደው ግን ሐኪሙ ምን እንዲያደርግልህ ነው? አሁን ለሚሰሙህ ስሜቶች የሚሽሩ መድኃኒቶችን እንዲሰጥህ ነው፡፡ ኾኖም ይሰ'ሙህ የነበሩ ስሜቶች ቢሻሉህም ሰውነትህ አሁንም እንደ ደከመ፣ ፊትህ እንደ ገረጣ ከቀረ፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህንም በአግባቡ ማከናወን ከተሳነህ በተሰጠህ ሕክምና ደስተኛ ትኾናለህን? አትኾንም !
“እውነታው ምንድን ነው?” ስንል ወደ…
❤29🙏13
Signed Bini
16 Sept 2024, 04:03 UTC≈9,020 views53 reactionsread 28 August 2026 ክርስቲያናዊ አለባበስ
አንብቡት ይጠቅማቹሃን👇
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
“ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፡፡” ዘዳ. 22፡5
ስለ አለባበሳችን እንወያያለን ዛሬም እህቶቻችን ላይ እናተኩራለን አበዛኸው ምነው እኛን ብቻ እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለው፡፡
ስለ አለባበስ መነጋገር ያስፈለገን እውነተኛ ክርስቲያን በአነጋገሩ፣ በአረማመዱ፣ በአመጋገቡ፣ በአለባበሱ፣ ብቻ በሁሉ ነገሩ የተለየ መሆን ስላለበት ነው ይኸውም ሁሉን በአግባብና በሥርዓት ስለማድረግ ነው እህቶቻችን ላይ ማተኮር ያስፈለገው ደግሞ በአብዛኛው በዚህ ረገድ ትችት …
❤33🙏12💯5🥰3
Signed Bini
14 Sept 2024, 03:05 UTC≈7,790 views78 reactionsread 28 August 2026 አንተ ሰው ይሔንን ጹሑፍ አንብብ
ከዓለም አታላይ እንቅልፍ ይነቃል 👇👇
ሰው የሆነ ሁሉ ያንብበው
ሰው ሆይ እሞታለሁ ብለህ ታስባለህ❓
ለመኖር ብለህ ትዋሻለህ
ለመብላት ብለህ ትሰርቃለህ
ለእርካታ ብለህ ትዘሙታለህ
ሀብታም ለመሆን የማትፈነቅለው ድንጋይ የለህም
እኖራለሁ ብለህ ግንብ ትገነባለህ ቤት ትሰራለህ
አውቃለሁ ብለህ ትማራለህ
እወልዳለሁ ብለህ ታገባለህ አልመች ሲልህ ትፈታለህ
በእግሬ አልሄድም ብለህ መኪና ትገዛለህ
ሚስት ከቤት እያለችህ ከውጪ ትመኛለህ
አንድ ወልደህ ከሆነ ሁለተኛ ታስባለህ
ዲፕሎማ ካለህ ለዲግሪ ትማራለህ
ድግሪ ካለህ ለማስትሬት ትማራለህ
ማስትሬት ካለህ ለፒአች ዲ ትማራለህ
አንድ ቤት ካለህ ሁለተኛ ቤት ታስባለህ
አንድ መኪና ካለህ ሌላ …
🙏46❤27🥰3😭2
Signed Bini
12 Sept 2024, 03:42 UTC≈7,210 views40 reactionsread 28 August 2026 . አሰልቺ የክርስትና ህይወት❗️
ሦስት ሰዎች ድንጋይ ይፈልጣሉ። አንደኛው በሥራው ስለሚያገኘው ደስታ ሲጠየቅ «ድንጋይ መፍለጥ ምኑን ደስ ይላል❓» ሲል መለሰ። ኹለተኛው ፈላጭ ደግሞ «ሥራው ደባሪ ነው። ነገር ግን ብዙ ገንዘብ አገኝበታለኹ» ሲል መለሰ። ሦስተኛው ፈላጭ ደግሞ «እኔ ሥራዬን በጣም ነው የምወደው! ይገርምሃል ፥ እያንዳንዱ ድንጋይ ከሌላው የተለየ ነው። ልክ እንደ ሰው ጠባያቸው ይለያያል። አፈላለጥኽም የተለየ መኾን አለበት። የተሠሩበት ነገርም ልዩነት አለው። ውበታቸውም ይለያያል። የእኔ ድንጋናዮች በዚኽ ኹኔታ አምረው ቤተ ክርስቲያንና ቤተ መንግሥት ሲኾኑ ይታዩኛል። እኔ በያንዳንዱ ሕንጻ ላይ ፊርማዬን እያሳረፍኩ ነው» ሲል ተናገረ። ይህ…
❤27🙏12👏1
Signed Bini
10 Sept 2024, 03:58 UTC≈9,060 views27 reactionsread 28 August 2026 እንኳን ለ2017 ለዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ ዓመተ ምህረት በሠላም አደረሳችሁ >>
መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን _
የዘመን መለወጫ
ዘመን መለወጫ ምንድ ነው.❓
እንቁጣጣሽ ምንድነው..❓
አዲስ ዓመት ለምን ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል❓
ኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
ዘመን መለወጫ
ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያት “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ሌሊቱ ከቀኑ …
🙏13❤11😭2👎1
Signed Bini
9 Sept 2024, 03:48 UTC≈6,480 views22 reactionsread 28 August 2026 አዲስ ዓመት
ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመት ሲመጣ መደሰት፣ ብዙ መብልና መጠጥ ማዘጋጀት፣ አዲስ ልብስም መልበስ ጥቅም የለውም፡፡ ነፍሳችን በኀጢአት እየተጨነቀች፣ ነፍሳችን ተርባና ተጠምታ ሳለ፣ የተዳደፈ የኀጢአት ልብስም ተጆቡና ሳለ አዲስ ዓመት ማክበር ለእኛ ምን ጥቅም ይሰጠናል❓ እንዲህ ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመትን ማክበር ማለት ለእኔ እንደ ልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው፡፡
ክርስቶስ ከዚሁ ሥራ አውጥቶናል፡፡ ከሕፃንነት አዕምሮ ወደ ማወቅ አሸጋግሮናል፡፡ ከምድራውያን ለይቶ ከሰማያውያን ጋር ደባልቆናል፡፡ ስለዚህ “መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” እንደ ተባለ አፍአዊ ሳይ…
🙏15❤4😭3
Signed Bini
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @eotcy. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.