4 Aug 2024, 18:47 UTC≈3,700 viewsread 6 August 2026 ስትሄጅ ስም አትስጪኝ
የልቤ ነሽ ብየ ያኔ የነገርኩሽን
እምነቴን ሰጥቼ ያወያየሁሽን
የሽንፈቴን ታሪክ ያን ጥቁሩን ጠባሳ
ዛሬ ፊት ስትነሺኝ
እንደተራ ነገር በየደረስሽበት አነሳሽውሳ
እምነት ልኩ እንዲ ነው?
ሚስጥር ወጉ እንዲ ነው?
ላጠፋሽው ጥፋት
ለመሄድሽ ሰበብ ብትልኪ ይቅርታ
የላክሻቸው ሰዎች
እኔን ሊያስማሙልሽ ቢሉኝ በርታ በርታ
ያሁኑን ጥፋትሽን ችየ ባልፍልሽም
ፍቅርና ክብርሽን ብመልስልሽም
የናድሽው እምነቴን
ላይድን ሰብረሽዋል ፈጽሞ አልሰጥሽም
ደግሜ ባገኝሽ
(እንዳዲስ ተዋውቀን)
እንኳንስ የልቤን ስሜን አልነግርሽም💔
ሐምሌ 2016
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! Share x100
@desitanafiker
@desi…
Signed Nafii Habesh 🇺🇸
2 Jul 2024, 02:44 UTC≈2,920 viewsread 6 August 2026 ስትዘንቢልኝ እፋፋለሁ!
(ታደሰ ደምሴ)
እኔ ማለት ቲኒሽ አጸድ፣
የዘር ፍሬ ያበቀለኝ
ገር አፈሩ የደገፈኝ
አንቺ ማለት የኔ ሰማይ፣
ፀሓይ ዝናም በመዳፍሽ
ችለሽ ሁሉን የምትለግሽ!
ወየው እቴ ወየው ወየው፣
ለምዶሽ መራቅ የታከተው፣ የኔን እጣ ማን ባወራው!
ማን ባወራሽ ጸአዳሽን፣ እርጥብ ገላ ማቃጠሉን
ማን ባወራሽ ስለ ጥላሽ፣ ደረቅ ነፍሳት ማለምለሙን!
ስሚኝ እቴ የኔ ሰማይ፣
በእምነት ሆነሽ የመም ቃሌን
የሀዘን ዳስ እንዳይውጠው፣
በቸልታሽ ጎጆ አለሜን!
ዝቅ ብለሽ ወደመሬት፣
በምሕረት አይን ብትፈልጊኝ
ከእግሮችሽ ውስጥ የማልጠፋ፣
የመዓዛሽ ቡቃያ ነኝ።
በይ ልንገርሽ ፣ በይ አድምጭኝ ከእውነት ወዴት እሸሻለሁ?!
ያባራሽ ለት ነው ሲቃየ፣ ስትዘንቢልኝ…
Signed Nafii habesh
18 Jun 2024, 18:34 UTC≈2,400 viewsread 6 August 2026 ጊዜ
ጊዜ እንደ ውሀ ነው ወራጅ እንደ ወንዝ
እውነቱም ሀሰቱም ይጠራል ሲጓዝ
ጊዜ ንፋስ ነው ሲጓዝ በፍጥነት
መቅመስ እንጂ ማጣጣም የሌለበት
ምንም ያህል ቢዋደዱ አይቀርም መለያየት
ያሻው ቢሰራ አይቀርም መመንዳት
ሺ አመት ቢኖር አይቀርም ሞት
ጊዜ ቂጣ ነው ይገለባበጣል
ሲስቅ የዋለው ሲያለቅስ ያድራል
በጉልበቱ የተመካው በትንኝ ይሞታል
በሀብቱ የተመፃደቀው ሚበላውን ያጣል
በውበቱ የኮራው ተሸፋፍኖ ይሄዳል
ደረቱን የነፋው አንገቱን ይደፋል
በስልጣኑ የተማመነው በስጋው ይወጋል
ፈሪ የተባለው ገድል ይሰራል
ድሀ የተባለው በፎቅ ይወዳደራል
ሰነፍ የተባለው አለም ይቀይራል
ብቻ ጊዜ ገራሚ ነው ሁሉን ያሳያል
ለጊዜው ዝቅ ያለው በጊዜው ይነሳል
N-🎢
ከወደዱት ለወዳጅዎ …
Signed Nafii habesh
17 Jun 2024, 04:53 UTC≈2,230 viewsread 6 August 2026 .........-------....የዝምታው ጩኸት....-------.........
አንተን ከመሰለህ፣ የፍቅር መግለጫው፣
በል በደንብ ኩራ፣ እስከ ዓለም ዳርቻው፣
ግን ይህን አስብ፣ ከቶ እንዳትዘነጋው።
ነገር ተገልብጦ፣ አንተኑ ብመስል፣
አስተማሪው ጎበዝ፣ ልጅቱ ነች በሳል።
ብጠፋ በድንገት፣ ከዓይንህ ብሰወር፣
ውሎዬን ብቀይር፣ ከቶ እነዳትሰኝ ቅር።
በፈገግታዬ ውስጥ፣ ከባድ ሀመም አለ፣
በዝምታዬም ውስጥ፣ ትልቅ ጩኸት አለ።
አሁን ግን------------
የውሸት መሳቁ፣ ህመሙ ከብዶኛል፣
የዝምታው ጩኸት፣ አቅሌን አስቶኛል።
ከቶ ሳላሳብቅ፣ ምንም ሳልል ዘመም፣
ጥርሴን እያሳየሁ፣ ብዙ ደበቅኩ ህመም።
አሁን ግን ይበቃል፣ ምላሽ ፈልጋለሁ፣
ጠልቶኝ ይሆን እያ…
Signed Nafii habesh
16 Jun 2024, 19:38 UTC≈1,980 viewsread 6 August 2026 እመኝኝ
""""""""""""""""""""''"""""'''"""""""""Yikirta le koyitachin be adiss melk matenal
ምኔን አይቶ ልብሽ ፈራ
አደረግሽው ፍቅሬን ተራ
ጎንሽ ልሁን ሁሌም ካንቺ
አንቺም ብትሆኝ ሳትሠለቺ
እመኝ እኔን ፍርሀቱን ተይ
ምን ይሆናል ከዛም አትበይ
ሁሌም ልሁን ካንቺ አጠገብ
ለደይቃ እንኳን አንዴ አላስብ
ፍቀጅልኝ ልብሽ ይስከን
የአፌን ቃል ከቶ አይመዝን
አልዋሽሽም ለምን ብዬ
ፍቅር አልሻም አታልዬ
ሁሉን ሁኜ እንደ ሁሉም ልሸፍነው ክፍቱን ቦታ
አለሜንም ላሳምረው ቤቲ ፍቅሬ ባንቺ ደስታ
እባክሽን የኔ ቆንጆ አሳምኝው ውብ ልብሽን
እውን አድርገሽ አሳውቂው በኔ ያግኝ ሙሉ እምነቱን
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
…
Signed Nafii habesh
1 Dec 2022, 06:17 UTC≈5,000 viewsread 6 August 2026 አንዳንድ የሰው ልጅ ልብ ልብነቱን ያጣ...
ሰውነቱን ያጣ
ጥምም አፈቃቀር ተምሮ የመጣ ...
የፍቅርን ሞገስ ተነጥቆ የተቀጣ ...
ልብ አይሉት ባዶ ልብ ለዙፋን ተሰርቶ የረከሰ ነገር
ሰርክ ሚያሸበሽብ ጥምም አፈቃቀር
.
.
.
.
.
ሊያስተምር ሲቃጣ ስለፍቅር ተግባር
አይናችን ይታዘብ የዚን ልብ ተግባር
...
አስተማሪ አይደለም ተናጋሪ ሁሉ
መሪም ከቶ አይደለም ከፊት ያለ ሁሉ!
@desitanafiker
Share share argulin
Signed Nafii habesh
13 Jul 2022, 04:23 UTC≈5,780 viewsread 6 August 2026 #መስታወት_ልግዛልሽ
:
:
መቼስ በዚች ዓለም፤
አምናለው አልክድም፣
የሰው ፍፁም የለም።
፡
፡
ሰው ስህተት ይሰራል፤
ከዚያም ይታረማል፤
ከስ'ተቱ ይማራል።
፡
፡
ያንቺ ግን ፍቅርዬ መሳሳትሽ ወዛ፤
በ'ኔና አንቺ መሀል ደርሶ ሰው ሳይበዛ፤
እየው ዕድሜ ላንቺ ፍቅራችን ጠነዛ።
፡
፡
ከሰራሺው ስህተት ትማሪያለሽ ብዬ፣በተስፋ ስጠብቅ ወይ ዛሬ ወይ ነገ፤
እንኳን ልትማሪ ጥፋትሽ ስር ሰዶ፣ቅርንጫፍ አውጥቶ ይባሱን አደገ።
፡
፡
እናምልሽ ፍቅሬ...
ትናንት በመቅረዜ ድንግዝ ብርሃን ይዤ፤
ሁሉን ላ'ምላክ ጥዬ እሱን ተመርኩዤ፤
አጣጥቤ ልኬሽ ጨቅይተሽ ስትመጪ፤
ፍቅርሽ እንዳይርቀኝ ከልቤ እንዳትወጪ፤
መውደድ አስገድዶኝ ዳግም እንደገና፤
አምጥቼልሽ ነበር ውሀና ሳሙና።
፡
…
Signed Nafii habesh
8 Jun 2022, 17:46 UTC≈4,640 viewsread 6 August 2026 የደመናው እንባ
አጠፋህ ዝም አልኩኝ ካድከኝ ፊትህ ቆሜ
ፈልጌ እንዳልመረጥኩ ያኔ እጅህን ስሜ
ፍቅር ፍቅር እንዳላልክ ዛሬ ተለውጦ
ክብሬ ይሻለኛል የሚያኖር አብልጦ
ስትቀየር በሀብት መደበቅ ከበደኝ
ከቃላቴ በፊት እንባዬ ቀደመኝ
አሳዘንኩት መሰል ደመና አለቀሰ
ህመሜን ተረድቶ እንደውሀ ፈሰሰ
የደመናው እንባ ከእንባዬ ጋራ ገብቶ ሲቀላቀል
እንዳይከፍልህ ፈራው የበደልከኝ በደል የሰጠኸኝ ቁስል።
✍✍✍ሰላም (Selito)
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@desitanafiker
Signed Nafii habesh
7 Jun 2022, 19:04 UTC≈4,640 viewsread 6 August 2026 #የኔ አዳም
ካወኳቸው ሁላ ልቤ አንተኑ መርጧል
ማንነትህ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል
ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ
አይኔም ሌላን ላያይ ምሏል ተገዝቶ
እግሮቼም ካንተ ውጭ ከቶውን ላይሄዱ
ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ
ከንግዲህ ለኔ ጎን ያለኸው አንተ ነህ
ብዬ ምፅፍልህ የኔ አዳም ወዴት ነህ
@desitanafiker
@desitanafiker
Signed Nafii habesh
28 May 2022, 07:36 UTC≈4,480 viewsread 6 August 2026 . አንቺን ሳገኝሽ ነው!
ተራ ሰው ነበርኩኝ
ልክ አንቺን ሳገኝሽ
ከእድለኛ ተርታ ባንዴ ተሰለፍኩኝ
አንቺን ሳገኝሽ ነው
ዘንበል ያለ ጎኔ
የዘመመ አካሌ መስመር የያዘልኝ
አንቺን ሳገኝሽ ነው
ልፍስፍሱ ልቤ
ብኩኑ መንፈሴ በሳቅ የሞቀልኝ
አንቺን ሳገኝሽ ነው
የህይወትን ዳዴ በእርምጃ የጀመርኩት
አንቺን ሳገኝሽ ነው
ህይወት የሚባልን
የሰው ልጅን ማዕድ ልጎርስ የቆረስኩት
አንቺ መግበሽኝ
ህይወትን ቀመስኳት ጣፈጠችኝ በጣም
ለራሴው ማልኩለት
ቅዠት ቢመስል እንኳ ከዚ'ስ ህልም አልወጣም
አንቺን ሳላገኝሽ
ያባከንኩት እድሜ ሊቆጨኝ አሰኘው
ረጋ በል አልኩት
ረፈደ እንጂ አልቀረም እሰየው
ካንቺ ጋራ ያለምኩት
አምሯል ጎዳናየ ሂዱብኝ እ…
Signed Nafii habesh
31 Jan 2022, 15:29 UTC≈4,850 viewsread 6 August 2026 ♨ሰዎች ምክንያት እየፈለጉ ጥፋተኛ ካደረጉህ ሊርቁህ እንደፈለጉ እየነገሩህ ነውና ከአንደበትህ አልፎ ውስጥህን የሚያዳምጥ አምላክ መቼም የትም እንዴትም ካንተ ጋር ነው።
♨በህይወት ውስጥ ፈተና ከበዛብህ አትዘን ታገስ...የጨረቃ ውበት የሚጨምረው ጨለማ በዙሪያዋ በጨመረ ቁጥር ነውና።
♨ወዳጄ ሆይ እራስህን ብዙም ግልፅ አታርግ ምክንያቱም ግልፀኝነትህን ተጠቅሞ ወዳጅህም ጠላትህ ይሆናልና!
♨ ቀን ጠብቆ የወጋህን እሾክ ጊዜ ጠብቀህ እስክትነቅለው ድረስ ታገስ እንጂ አውጡልኝ ብለህ ቁስልህን ለሰው አሳልፈክ አትስጥ ምክንያቱም የባሰ ያቆስልሀልና!
♨. እንደ እኔ አንዴ እንደምትኖር አውቀህ ጊዜህንና ጉልበትህን በማይጠቅም ቦታና ማንነት ውስጥ አታባክን።
♨መቆጣጠ…
Signed Nafii Habesh
28 Jan 2022, 02:09 UTC≈4,180 viewsread 6 August 2026 አፍቃሪ ይትረፈው
በድህነቴ ወቅት ያቺን ሴት ሳፈቅር
ትዝ ይለኛል ያኔ ኪሴ ባዶ ነበር
መውደዴን ለመግለፅ ውብ ቃላት ደርድሬ
ላሳምናት ብጥር በአፍቃሪ ተግባሬ
አትምጣብኝ አለች አትድረስ ከበሬ
ነገሩ ልክ ናት እኔ አልፈርድባትም
ኪሴ ከጎደለ ፍቅረኛ አልሆናትም
የተትረፈረፈ ከሌለኝ እንጀራ
ሀብቴ ካልዘነበ ላፍታ ሳያባራ
ተቸግራ ልትኖር ልትልስ ፍቅፋቂ
ሴት ወደኔ አትመጣም ለሷ ነኝ ውዳቂ
ቅዳሜን ጠብቄ ክለብ ካልወሰድኳት
ሪዞርት ለሪዞርት ካላንሸራሸርኳት
በስጦታ ብዛት ካላጨናነኳት
እንዲሁ በባዶ አፈቀርኩሽ ብላት
በሉ እስቲ ፍረዱ ምን ፍቅረኛ ሆንኳት
እና ስነግራችሁ ያየሁትን እውነት
አፈቀርኩኝ ያለ ፍቅሩን እንዳያጣት
አስንቆ ሳይጥለው ያ ክፉ ድህነት
ፍቅር እቃ ሆኖ…
Signed Nafii Habesh
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @desitanafiker. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.