13 Jun 2025, 19:26 UTC≈1,740 views1 reactionsread 8 August 2026 👋
ቤቶች ጊዜው ከሆነ ወቅት ወደዚህ ነው😀 እና ከዚያ ወዲህ የሆነ ነገሬ በሆነ ነገር ከተመታ ጀምሮ “ሰላም እንዴት ናችሁ?” ብሎ ሰውን ተቀላቅሎ ወሬን መጀመር ነገር ፍለጋ እየመሰለኝ ስለመጣ ከተውኩት ሰንበትበት ብያለሁ☺ እርግጥ ባለፈው አንድ ወዳጀ በዚህች ሀገር “ሰላም በሰላም ብቻ አይመጣም!” ካለኝ ወዲህማ ይሄ የመመታት ነገር የኔ የግል ጣጣ ብቻ አልመስልህ እንዳለኝ ነው ያለሁት።
መገናኘት ደግ ነው፤ እንግዴክ ይሄን ስርጭት እንዲህ ያሉ ነገሮችን የማድቀቂያ ስለሚሆን የስነልቦናችሁን ትጥቅ እንድታጠባብቁ ትለመናላችሁ ጓዶች
{ጋርናቾንና ራሽፎርድን} ካልሸጥን አሁንም ቢሆን ምንም ተስፋ የለንም!... እግረኛው መንገድ ላይ የቆሙ 2 ወጣቶችን አልፌያቸው ስሄድ…
😁1
29 May 2025, 02:36 UTC≈1,660 viewsread 8 August 2026 👋 በአመቱ ካሉን 13 ወራቶች መካከል እንኳን ለዛሬው (ጉንበት 21) አደረሰን!
ቤቶች፤ አካሄዳችንን ካያችሁት ከዛሬም የሚያስረፍድ ነበርኮ፤ ግን የማያሸልበው የጦጲያ አምላክ ወየት ሄዶ! ስለዚህ እንኳን አደረሰን😀
ኧረ ደሞ ትላንት ምን እንደሆንሁ…
ቤሄራዊ መታሰቢያ የድል በአል የነበረው “ጉንበት 20” ወደክልል ወርዶ በክልል ብቻ ታስቦ ውሎ የለም? ይህንኑ በአፍሪካችን ያለውን {ትግል የብዙዎች፣ ድል ደሞ የጥቂቶች ነው} የሚለውን መሪር ሃቂቃ ዘንግቸው ኖሮ.. እንግዴክ ታሪኩም፣ መታሰቢያ የድል በአሉም፣ ቀኑም የመንግስት ብቻ ከሆነ ዜጋው ምን ተረፈው?
እሺ መንግስት ቀኑን ሰርዞ ተገላገለ እኔስ እለቱን ምን አባቴ እያሰብኩበትና እንዴት አድርጌ ልገላገለው? በ…
10 Feb 2025, 05:37 UTC≈1,470 views3 reactionsread 8 August 2026 👋 (ወንድ ስሜቱ እንጅ ጆሮው ደንቆሮ አይደለም!)
ጓዶች፣ ችግርም ምክርም በቤትና ጓዳችን በሽ በሽ አይደል? ጎሽ አልጠፋችሁም ማለት ነው! በዚህ ልዩ የምክርቤቱ መሰናዶ ግን ከአሌክሶ ጋር በልዩ አርዕስት ልዩ ቆይታ እናደርጋለን! እንቀጥላ…
የእኔ እህት! ስሜት ስሜት ነው... ዘመናዊ ስሜት ኋላ ቀር ስሜት የሚባል ነገር የለም! ስሜትን መቆጣጠር እንጅ በሌለ ስሜት ቀይሮ ማስመሰል ጨዋም ስማርትም አያስብልም! በምሳሌ ላስደግፈው ወይንስ ገብቶሻል? ይሄ ሳይገባሽ ነው ዝም ብለሽ ፍቅር ውስጥ የተዘፈቅሽው? ምናይነት ጣጣ ነው!
እሽ በቃ ስሚ ! አፈቀርሽ እንበል...ያፈቀርሽው ሰው ከልቡ አፍቅሮሻል። እና ምን ላምጣልሽ፣ ወይም ምን ልግዛልሽ የኔ ቆንጆ አለሽ…
👍3
14 Nov 2024, 05:47 UTC≈2,080 viewsread 8 August 2026 👋 ቤቶችየ ከመጠፋፋታችን የተነሳ ላሁኑ ቆይታችን ርዕስ አልተከሰተልኝም😀 እስቲ እየሄድን አየት እናደርጋለን🙂👌
ድሮ ልጅ ስለነበርኩ ነው መሰል በጦጲያ ሀገራችን ብሎም በሰፈራችን፣ ለመሳቅም ለመብሸቅም እንደምርጫችን የተመቻቸ እድል ነበር ያለው🤭አሁን ሳይቸግረኝ ካደግሁ ብኋላ ግን..
ባለፈው፣ በጁመዐው ደህና ተሸሽጌ ውየ ከቤቴ መዝጊያ በፊት ጦጲያ ራዲዮን ከፈትሁ.. "በደማችን ተከብሮ የቆየው ሉዓላዊነታችን በላባችን ፀንቶ ይቀጥላል" - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት” የሚል መግለጫ አጉል ቦታ አገኘኝ😬
በራሱ መንግስት ስለተከበብሁ ነው መሰለኝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሚለው ላይ መጨመር ቸግሮኝ በጨዋ ደንብ የተገኘውን አጉሌን እያሻሸሁ ወደኋላ አፈግፍ…
28 May 2024, 07:01 UTC≈2,280 views1 reactionsread 8 August 2026 👋 (ከመፈክር ጀርባ) ። _ቤቶችየ😊ያሁኑ አመጣጣችን ከጉንበት 20ጋ በተያያዘ ለመነጋገር ሳይሆን ከዚያ በመለስ ባሉ ጉዳዮች ለመንጎዳጎድ ነው አከሳሰታችን😆ያው ነገሩን ከስሩ እያጠራን እንሂድ በሚል ነው😁ወደተገናኘንበት ፈሮግራም👌 _“_እንግዴክ፣ ከመፈክር ጀርባ” ምን አለ? እምትሉኝ ከሆነ እኔና ወሬየ ነን ያለነው🤣 እርግጥ ነው ሰሞኑን መንግስትም አማረልኝ ብሎ ጽዱ ኢትዮጲያ የምትል መፈክር አምጥቶ እየበጠበጠን ይገኛል።
መቸ ቀን ነው እሱ፤ በነጻነትና በጸጥታ ለተፈጥሮ ምላሽ መስጠት ወደማልችልበት መጸዳጃቤት ተጣድፌ ገባሁ።
በዚሁ መጸዳጃ ቤት ፊትለፊት ከ90 ሳንቲ በማይበልጥ ርቀት ላይ ያለን ቤት የሆነች ሸግየ ልጅ ተከራይታዋለች።
ደሞ ያጋጣሚ ነገር እኔ ሳልሆን…
❤1
24 May 2024, 01:50 UTC≈2,060 viewsread 8 August 2026 👋!።
👨🎤 እኅኅምሕም___ ኣሁን፥ ጥሩ እሰማለሁ ልቀጥል🙆♀️
ቤቶችየ ☺️ በመጀመሪያ እንኳን ከጠፋሁበት በደህና መጣሁ!😎 በመቀጠል እናንተም እንኳን ባላችሁበት ቆያችሁኝ! ለማለት እወዳለሁ😊
አልነበርክም እንዴ? በማለት ሊነጅሰኝ እሚፈልገኝ ካለ እድል እሰጠዋለሁ፤ ግን ይህችን አውርቸ እስክመጣ ወደዛ ፈቀቅ በማለት እየተንጎራደደ ታግሶ እንዲጠብቀኝ ይሁን🙈
እናማ ጓዶች ልነግራችሁ እንደጀመርሁት በሚዲያ አልተዘገበም እንጅ ጠፍቸ ነበር😀 ወዲህ ወደናንተ ከመምጣቴ በፊት የጠፋሁበትን ምክኒያት ዘርዝሬ በዛውም የመመለሴን ዜና ለማብሰር የቸኮልኩት ለሚስትነት ወዳጨኋት ልጅ ነበር፥ ያውም ትንፋሽ እያጠረኝ እያለከለክሁ።
ወገን ደሞ እያለከለክሁ ስላችሁ የሆነ ነገር አሳ…
23 Apr 2024, 22:53 UTC≈2,040 viewsread 8 August 2026 👋 (ያንድ ምሽት ሀሳብ) .
እህህህህም! ኦንላይን ላለህ ብቻ! ብየ በሙድ ኣላቦዝንህም😳 ብቻ ወገን! ኣሁን የሰማኸው ኣባኮዳ ከመሬት ለመነሳት ሲያኮበኩብ ሳይሆን፤ እኔ የሰውየው ልጅ ድምፄን ስጠራርግ ነው🙈 ጌታየ መቸም በዚህ ሰኣት ተገጣጥመን ኣትነጫነጭብኝም ኣ? በዚህ ጠራራ ሌት ልብን ሰዋሪ የሆነ ድምፅ የሚያወጡት የተመረጡ ሰዎች ብቻ ስለሆኑ እባክህን ኣንተም ወደ 8 32 W ብለህ ቴክስት ኣድርግ ብትፈልግ😀 ወዳመጣኝ ሃሳብ ላሳልፍህማ.
ልማድ ሆኖበት፥ ሌቱ ቢገፋ
ምን ሊጠቅመኝ፥ ነው የማንቀላፋ
ህልም ሸክም ነው፥ ፈቺው ከጠፋ፤
ሳይጎድለኝ ለዛ
ሳያንሰኝ ውበት
የቀን ጨረቃ፥ ላይንሽ ሆኘበት፥
ቀልብን የማይስብ፥ የሳር ቀለበት
መወደዴ ብላሽ
ምኞቴ ዘበት፤
የ…
13 Jan 2024, 15:39 UTC≈2,150 views2 reactionsread 8 August 2026 👋 (ጭር አይበላችሁ) .
ቤቶችየ ምክርቤቱ ገጠር መገጠሩን መቸም ያልሰማ የለም ኸዚህ ቤት ውጭ😁 እዚህ የቦለጢቃና የመኪና ጭስ ይናፍቅሀል! ንፋስና ጸሃይ ከተማ እንዳሉት መብራትና ውሀ እየተቆራረጡ ብዙም አያማርሩም ተመስገን ነው 😳 የትም ሁን የተፈጥሮ ግዳጅ አይፋታህም አይደል? ቅድም ጽድት ያለ ሸኖ ቤት ተዝናንቸ ሳበቃ ነገሩ ደንቆኝ ፋዙካን.. ሽንትቤቱ የተዋጣለትና ንጹህ ነው፤ እዚህ ላይ ጥሩ ሰርታችኋል አልሁት. ባክህ ከቅጣት ለመዳን በግዳጅ ነው የቆፈርነው፤ እሚጠቀምበትም የለም አለኝ። እንግዴክ የመጸዳጃው ንጽህና ከአገልግሎት ውጭ በመሆኑ ነው.
የሰው መሰልጠን ለከብት በተረፈበት ዘመን፤ እዚህ እኛ ግድም ግን የለም የለም አኗኗራችን ከከብት ያራቀና እን…
👍2
1 Jan 2024, 18:31 UTC≈2,500 views2 reactionsread 8 August 2026 👋 (አልሞትም!)
ቤቶቻችንየ😊 መጠፋፋታችንን እንዲሁም አዲሱን 2024 አመት በማስመልከት የሚከተለውን ዛቻ ቀረሽ ምኞትና ፍላጎትን ገላጭ ግጥም በመያዝ ነው ለሰአቱ የተገናኘነው😊 እዚህጋ ጫ እንልና ወደግጥሙ እናተኩራለን👌
ስሚ፤
እኔ በዚህ ዓለም፣ ብዙ ብሰቃይም አንድ ሀሙስ የቀረው፣ አክየ ብታይም አምሮቴን ሳላገኝ፣ ሱሴን ሳላከትም በመሬት ከርስ ውስጥ፣ ገላየን አልከትም
አልሞትም!
ማንም ባልደፈረው፣ መንገድ ሳልገሰግስ እንደ ንጉሥ ኣይዘር”፤ ግማሽ ቀን ሳልነግስ በጠገበው ሳልስቅ፣ ለራበው ሳልደግስ
አልሞትም!
ዝማሜን ሳላውቅ፣ ያንደበቴን ግድብ
ዙፋን ላይ ሳልሸና፣ ጌቶችን ሳልሰድብ
ከድሃ ሳላብር፣ ካገሬው ሳልወግን
ከምድር በረከት፥ ድርሻየን ሳልዘግን
አልሞት…
👍2
4 Dec 2023, 19:15 UTC≈2,210 views1 reactionsread 8 August 2026 👋(የቋንቋ ነገር) .
ቤቶችየ😊 የፊታችን ላይ እስክንደርስበት ባለፈው ፈገግ እንበላ ዛሬም☺️ ማሳሰቢያ! እምታነቡት ወግ ገና ስትጀምሩት አልገናኝ ብሎ እንዳያስቸግራችሁ አሁን ካላችሁበት 3 አመት ወደኋላ እንድትንደረደሩ ይሁን👌
ለአዲሳባ ከንቲባነት ልወዳደር ወይስ ለክቡር ገና ልተውለት? ምን ያንሰኛል? ሌላው ቢቀር ሁለት ቋንቋ እችላለሁ - የአራዳና የገጠር አማርኛ አቀላጥፌ እናገራለሁ፤
የዛሬ አመት ገደማ ይመስለኛል: በካፒታል ሆቴል ጀርባ ባለው አቋራጭ መንገድ ሳልፍ ሁለት ጎረምሶች ይተናነቃሉ፤ ገባሁና ገላገልኩ፤ ሳጣራ አንዱ በቅርቡ ከታክሲ ረዳትነት የተቀነሰ ከተሜ ሲሆን ሁለተኛው ከገጠር የመጣ መፅሀፍ አዙዋሪ ነው፤ ምን እንዳጣላቸው ጠየኳቸው ፤
…
👍1
24 Nov 2023, 19:03 UTC≈2,530 views3 reactionsread 8 August 2026 👋 [ስለአህያና አቧራው]
ወገኖቸ😊 በጁመአ አመሻሻችን ደሞ ይህንን እንጨት እንጨት የማይል አሪፍ ወሬን እናካሂዳለን😳👌
ከትላንት ወዲያ ረቡ እለት፤ ላለፉት 5 አመታት እምመገብበት ቤት ቁርሴን እንቁላልበስጋ አዝዠ መጥቶልኝ እያጣጣምሁ፤ ስራ በፈታው እጀ ደሞ ከስልኬ ላይ ያደረ ወሬ ሳምስ... "የአህያ ስጋ በሰፊው ለገበያ እየቀረበ ነው እሚል ጥርጣሬ" ... ዜናውን ሳልጨርሰው ተውኩትና ተጣራሁ... ቤቲ! ወይ፤ ይሄ ቁርስሽ የጣፈጠኝ ለመሆኑ የስጋው አድራሻ ከየት ቢሆን ነው?
ከምናምን ጠጅ ቤት 5 ኪሜ ገባ ብሎ ልበልህ? ይልቅ ተጨማሪ ይሰራልህ? አለችኝ.. ተስማማሁ።
😂እሚያስቀኝኮ፣ የምግብ ዝርዝር ገልጦ ከማንበብ ተጣርቶ በያይነቱ ስንት ነው? ማለት እሚቀለው.…
👍3
23 Nov 2023, 22:02 UTC≈2,270 views2 reactionsread 8 August 2026 👋 (ወደ ምንም የሚያደርሰው መንገድ(
ወገኖቸ! እንዲሉ እነ-😊 ወገኖቸ ለጁመአችን መዳረሻ እምትሆነን ስንኝ ናት👌
ቸኳይ የሚመስለው፣ ፈጣን የሚመስለው
በውልውል መኪና፤ በፋሽን መጫሚያ
ወይም በባዶ እግሩ
ሽው እልም የሚለው
ይኼ ሁሉ ምሁር፤ ይኼ ሁሉ ማይም መንገዱን የሞላው፤ ከታችም ከላይም፤ ሲመላለስ እንጂ ሲደርስ አይታይም። "በእውቀቱ ስዩም የእሳት ዳር ወጎች".
ቤቶችየ☺️እንደዝግጅታችን ሰላም እንሁን አቦ❤️✋
😁2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @dan9yemlew. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.