28 Dec 2022, 04:46 UTC≈1,370 viewsread 6 August 2026 Photo
እያንዳንዱ ሰው የገነባው ምድራዊ መንግሥት ፈራሽ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ያቋቋመው መዋቅርም በስባሽና ወዳቂ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰጠን መንግሥቱ ግን የማትዝግ፣ የማትጠፋ ወይም የማትወረዛ መንግሥት ለእኛ አቆይቶልናል፡፡ ይህቺ መንግሥቱ የማትበሰብስና የማትጠፋ ዘራፊ ሌቦች ሰብረው ገብተው የማይሰርቁባት ናት፡፡
✍️@Natinaelbeki
@Daily_breads
Have a wonderful time ☕️
Signed Natinael Beki
19 Dec 2022, 04:10 UTC≈1,130 viewsread 6 August 2026 Photo
በመጀመሪያ ጊዜ እውነት ተናገር፣ ከዚያ በኋላ ምን እንደተናገርክ አታስታውስም፡፡" ይህን ቃል የተናገረው ታዋቂው የምክር ቤት አባል ሳም ራይበርን ነው፤ አባባሉ ለዘመናችን ሰዎች እንደ መድኃኒት ነው፤ ውሸትን መናገር ለጊዜው የሚያስደስት ይሆናል፤ ከዚያም በርካታ ጣጣዎችን ያመጣብናል፤ በዚህም የተነሳ የተናገርነው ምን እንደ ሆነ ለማስታወስ እየሞከርን ለምን እንደተናገርነውም እናስባለን፡፡ እውነት ጽኑ ነው፤ ሐሰት ግን ለጊዜው የሆነ ቅዠትና የሚያቃጥል እሳት ባለበት ወጥመድ ውስጥ የሚከተን ነው፡፡
መልካም ቀን‼️☕️
@Daily_breads
Signed Natinael Beki
15 Nov 2022, 05:40 UTC≈1,010 viewsread 6 August 2026 Photo
Day#28 Devotion
ኢያሱ እኔ የምወደው የመጽሐፍ ቅዱስ ጀግና ነው፡፡ እርሱ ለሙሴ ታላቅ አገልጋይ ነበር፡፡ ሕዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር ለማስገባት ሲመራ የቅርብ አቻዎቹም ጭምር ይቃወሙት ነበር፡፡ የታላቁን መሪ ዱካም በመከተል እርሱም ታላቅ መሪ ሆኗል፡፡ ይህ ቀላል ተግባር አይደለም! ኢያሱ እድሜው ከገፋ በኋላ እንኳን ንቁና ብርቱ ነበር፡፡ ኢያሱ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አድርጓል፡፡ ሁሉንም የእግዚአብሔር ትእዛዛት ፈጽሟል፡፡ ሙሴን እግዚአብሔር ያዘዘውንም እርሱም ማድረግ ነበረበት፤ በሌላ አባባል ኢያሱ ታማኝ ነበር!
Have a wonderful time ‼️
@Daily_breads
Signed Natinael Beki
14 Nov 2022, 05:02 UTC818 viewsread 6 August 2026 Photo
Day #27 Devotion
እግዚአብሔር በእኛ ላይ የሚሠራውን ታላቅ ድል እየተጠባበቅን ባለንበት፣ በጦርነት ውስጥ እንዳለንም ልንረዳ ይገባል፡፡ እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ይህንን ጦርነት ድል ይነሳልናል፡፡ የመጨረሻውም ውጤት ግልጽ ነው፡፡ ክርስቶስ ይህን ወሳኝ ጦርነት አሸንፎልናል፡፡ ይሁንና ግን ሞኞች አንሁን፡፡ ክፉው ሰዎችን ሁሉ ለማታለልና የጠፉትን ግራ ለማጋባት ማድረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጋል፡፡ ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር እንጣበቅ፤ የእርሱን እውነት እንኑር፤ በቃሉ ውስጥ ያለውን ድምጽ እንስማና የመንፈሱን ምሪት እንከተል፡፡
Have a wonderful Time‼️
@Daily_breads
Signed Natinael Beki
13 Nov 2022, 20:46 UTC666 viewsread 6 August 2026 https://youtube.com/shorts/xhAUOHUyrrA?feature=share
Signed Natinael Beki
12 Nov 2022, 06:13 UTC645 viewsread 6 August 2026 Photo
Day#25 Devotion
ጥበበኛ ሰዎች ሌሎችን በማንጓጠጥና በማዋረድ የእነርሱን ጥበበኛነት ሊያረጋገግጡ አይሞክሩም፡፡ በዚህ ምትክ፣ አንደበታቸውን በመግዛትና መልካም ቃል አክብሮት፣ ሕይወታቸው ጽድቅና እውነተኛነትን ይናገራል፡፡ ፌዘኝነት በበዛበት ዓለምና ሰዎችን በማዋረድ በሌሎች ዘንድ አክብሮትን ለማግኘት የሚፈጥኑ ሰዎች አንደበታቸው እንደ ስለታም ምላጭ ነው፡፡ እኛ በአንደበታችን ቃል በረከትን ልናመጣ የተጠራን ሰዎች ነን (ኤፌ. 4፡29)፡፡
ብሩህ ቀን ይሁንላችሁ‼️
@Daily_breads
Signed Natinael Beki
29 Oct 2022, 16:07 UTC658 viewsread 6 August 2026 https://www.clubhouse.com/room/mZg2p7n0?utm_medium=ch_room_merc&utm_campaign=xf7SGlVE9xHqQu114OPYhQ-433924
Signed Natinael Beki
14 Jul 2022, 19:07 UTC870 viewsread 6 August 2026 ──━━─━━ ⊱✿⊰ ━━━━━━──
➲ ፍቅር ዕውር ነው
አንድ ሰው ቆንጆ ልጃገረድ አገባ፡፡እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡አንድ ቀን የቆዳ በሽታ ያዛት፡፡ቀስ እያለች ውበቷን ማጣት ጀመረች፡፡በቀን በአንደኛው ባልዋ ለጉብኝት ራቅ ወደላ ስፍራ ሄደ፡፡በሚመለስበት ጊዜ አደጋ አጋጠመውና እና ዓይኑን አጣ፡፡ሆኖም የጋብቻ ህይወታቸው እንደተለመደው ቀጠለ፡፡ግን ቀናት እያለፉ ውበቷን ደረጃ በደረጃ አጣች፡፡
ዓይነ ስውር ባል ይህንን አያውቅም እናም በትዳራቸው ሕይወት ውስጥ ምንም ልዩነት አልነበረም፡፡እሷም እሱን መውደዷን ቀጠለች እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡አንድ ቀን በድንገ…
Signed Natinael Beki
14 Jul 2022, 11:38 UTC758 viewsread 6 August 2026 Photo
✍️ውድድር✍️
"ከውሻ እና ከአቦሸማኔ የቱ ሊፈጥን ይችላል?" ተብሎ በዓለም ላይ ካሉ ፈጣን የውሻ ዝርያዎች ተመርጠው ከአንድ አቦሸማኔ ጋር የውድድር ፕሮግራም ይደረጋል።
ውድድሩ ሲጀመር ውሾቹ ተፈትልከው ሲሮጡ አቦሸማኔው ስንዝር ያህል እንኳአ ለመሮጥ ፍላጎት አላሳየም።
በዚህ የተገረሙት ታዳሚዎች የውድድሩን ሀላፊ "አቦሸማኔው ለምን ሊሮጥ አልሞከረም?" አሉት።
ሀላፊውም "አንዳንዴ ምርጥነትህን_የማይገባ (የማይመጥንህ) ቦታ ላይ ለማሳየት መሞከር የስድብ ያህል ነው" አላቸው።
Don't prove your self every where' ማንነትህን በማንኛውም ቦታ ላይ ለማሳየት አትሞክር።
ምክንያቱም እንደ አቦሸማኔ የሆነ አቅምህን ከውሾች ጋር አውርደህ አትፎካከር።…
Signed Natinael Beki
12 Jul 2022, 06:53 UTC671 viewsread 6 August 2026 Singer Bikila Kebede Live worship
https://youtu.be/Gl2O-arVMag
Signed Natinael Beki
9 Jul 2022, 08:00 UTC795 viewsread 6 August 2026 ሸቶኛል ያንተ መገኘት ይትባረክ ታምሩ
https://youtu.be/W34vxejFImM
Signed Natinael Beki
27 Apr 2022, 05:18 UTC≈1,060 viewsread 6 August 2026 Photo
አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው። ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።
መዝሙር 46:1-2
እግዚአብሔር ከለላችን ብቻ ሳይሆን ረዳታችን ነው፡፡ ዓለም አፏን ከፍታ ልትውጠን በመሰለን ጊዜ እግዚአብሔር ከጎናችን ይቆማል፡፡ በሞት መካከል አሳልፎ ያስመልጠናል፡፡ ከሰይጣን እስራት ነጻ ያወጣናል፤ ሰይጣንንም የምናሸንፍበት ኃይል ይሰጠናል፡፡ እኛ ማወቅ ያለብን በማዕበሉና በአውሎ ነፋሱ ውስጥ ብቻችንን የማይጥለን አምላክ እንዳለን ነው፡፡
መልካም ቀን ይሁንላችሁ።
✍️ናትናኤል ቤኪ
@Daily_breads
Signed Natinael Beki
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @daily_breads. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.