7 Aug 2026, 14:48 UTC100 views16 reactionsread 7 August 2026 የሰው ልጅ ታማኝነትና ውለታ እንደ ደመና ተለዋዋጭ ቢሆንም፣ የእግዚአብሔር ኪዳን ግን እንደ ዐለት የጸና ነው። እኛ በጉዞአችን ብንደክም፣ መንገዳችንም ቢጠባብ እንኳ፣ እርሱ ስለ ታላቅ ስሙና ስለ ታማኝነቱ ሲል በሕይወታችን የጀመረውን መልካም ሥራ በድል ይፈጽመዋል።
“በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤”
— ፊልጵስዩስ 1፥6
የሕይወታችንና የዘላለም መዳናችን ዋስትና የራሳችን ጥንካሬ ወይም መልካምነት ሳይሆን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠው የማይለወጠው የእግዚአብሔር ታማኝነትና ጸጋ ብቻ ነው።
ይህ ደግሞ ብርታታችን ነው 🙏
❤🔥9🥰5🔥2
6 Aug 2026, 05:38 UTC273 views19 reactionsread 7 August 2026 ቅጥሬ አልፈረሰም መጠበቂያዬ
አለሁ ይለኛል ደጉ ጌታዬ
ቀና ብዬ ሳይ ቀለላት ነፍሴን
ፍቅሩ ስጠራኝ አየሁት እራሴን።
🎶 ደረጄ ከበደ🙏
❤15🥰4
3 Aug 2026, 03:47 UTC508 views12 reactionsread 7 August 2026 File
አንነቃነቅም እንቆማለን
መሠረታችን ዓለት ነው
ዓለቱም ኢየሱስ ክንደ ብርቱ
❤12
2 Aug 2026, 06:06 UTC≈3,190 views36 reactionsread 7 August 2026 ከሳምንቱ ድካም ይልቅ ከቅዱሳን ጋር የሚደረግ ህብረት ነፍስን ያድሳል፤ መንፈስንም ያረካል። ዛሬ ወደ አባታችን ቤት ጎራ ብለን በምስጋና፣ በጸሎትና በፍቅር የምንታደስበት ልዩ ቀን ነው። በህብረት ውስጥ ሰላም አለ፤ በህብረት ውስጥ በረከት አለ።
እንኪያስ ጉዟችንን ወደ ቅዱሳን ህብረት እናድርግ!
❤29💯7
1 Aug 2026, 07:06 UTC719 views28 reactionsread 7 August 2026 ክርስትና የብቸኝነት ጉዞ አይደለም፤ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረውና ያዳነው ለኅብረት ነው። እንደ አንድ አካል ክፍሎች እርስ በእርስ ሳንደጋገፍ፣ በክርስቲያናዊ ህይወታችንና አገልግሎታችን ሙሉ ልንሆን አንችልም። እውነተኛ የአማኞች አንድነት የሚመጣው በጥቅም ወይም በዘር ሳይሆን፣ በክርስቶስ ደም በተመሠረተው መለኮታዊ ቃል-ኪዳን ነው። በአንድነት ስንቆም የጨለማውን ኃይል የሚያሸንፈው ታላቁ የመለኮት ኃይል በመካከላችን ይገለጣል።
❤21🔥3❤🔥2🤝2
31 Jul 2026, 02:01 UTC879 views29 reactionsread 7 August 2026 ወዳጆቼ፣ እግዚአብሔር ያያል! 🥹
አንዳንድ ጊዜ ሕይወት የሚጭንብን ፈተናና መከራ ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ከአቅማችን በላይ ሊሆንብን ይችላል። የሚገጥመን ማዕበል አቅም የሚያሳጣ፣ በሩ ሁሉ የተዘጋና መውጫ የሌለው መስሎ ሊታየን ይችላል። "ለእኔስ ማን አለ? ይህስ መከራ መቼ ያልፋል?" እያልን የተስፋ መቁረጥ ስሜት በውስጣችን ሊመላለስ ይችላል።
ነገር ግን በዚህ ሁሉ መካከል ልባችን በጽኑ ሊይዘው የሚገባ አንድ ትልቅና አጽናኝ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት አለ፦ እግዚአብሔር አያይም፣ አይመለከተኝም፣ አልሰማኝም ብላችሁ በጭራሽ እንዳታስቡ!
እሱ በሰው ዘንድ የተሰወረውን፣ በምስጢር በውስጣችሁ የሚያለቅሰውን የሕመም እንባ፣ ማንም ያላየውንና ያልተረዳችሁን የልባችሁን …
🙏21❤5😢3
29 Jul 2026, 12:17 UTC681 views21 reactionsread 7 August 2026 መጽሐፍ ቅዱስን በነገረ መለኮት ወይስ ነገረ መለኮትን በመጽሐፍ ቅዱስ?
የክርስትና እምነትና ትምህርት የመጨረሻና የበላይ ባለሥልጣን እግዚአብሔር በመንፈሱ መሪነት ያስጻፈው ቅዱስ ቃል ብቻ ነው (Sola Scriptura)። ጤናማ ነገረ መለኮት (sound theology) የእግዚአብሔርን ቃል በጥበብ ለመረዳትና ለማደራጀት የሚረዳ መሣሪያ እንጂ፣ ከተሳሳተ ቅድመ-ግምት በመነሳት መጽሐፍ ቅዱስን አጥምዞ የራሱ ባሪያ የሚያደርግ ገዥ መነጽር ሊሆን አይገባም።
መጽሐፍ ቅዱስን በተጣመመ ነገረ መለኮታዊ መነጽር ከማንበብ ይልቅ፣ ነገረ መለኮትን ሁልጊዜም በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር መመዘንና ማረም እጅግ አስፈላጊ ነው።
የትርጓሜ አቅጣጫ፡ Exegesis vs Eisegesis
…
❤16💯5
23 Jul 2026, 09:35 UTC807 views26 reactionsread 7 August 2026 በገዛ ሥጋዊ ጥረታችንና አቅማችን ኃጢአትን ለማሸነፍና ጽድቅን ለመገንባት መሞከር፣ በገዛ እጃችን አየሩን ጨብጠን ወደ ላይ ለመውጣት የመታገል ያህል ከንቱና ባዶ ስራ ነው። እውነተኛና ዘላቂ የሕይወት ለውጥ የሚጀምረው ከመለኮታዊው የመንፈስ ቅዱስ ስራ ነው።
መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ ሲሰፍን፣ በመንፈሳዊ ሁኔታ የሞተውን ልባችንን ሕያው ያደርገዋል፤ ለጽድቅ ሕይወት የሚሆን መለኮታዊ ፍላጎትንና የማድረግን አቅምም ይተክላል። እርሱ አሮጌውን በደልና የኃጢአት አኗኗር ደረጃ በደረጃ እያቃጠለና እያደከመ፣ እኛንም በዕለት ተዕለት የቅድስና ሂደት (Sanctification) ወደ ክርስቶስ መልክ የሚለውጥ መለኮታዊ እሳት ነው።
ይህ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ግን ለስንፍ…
❤18🥰8
20 Jul 2026, 15:53 UTC≈1,560 views32 reactionsread 7 August 2026 በሕይወት ጉዞዬ ላይ ማዕበሉ ቢበረታ፣ መንገዱ ቢጠብብ፣ እና በምንም ነገር ውስጥ ባልፍ እንኳ ፣ በአንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ፦
እግዚአብሔር ያበረታኛል፣
እግዚአብሔር ያጽናናኛል፣
እግዚአብሔር ይጠብቀኛል።
የልቤ ስብራት ሳይሆን፤ የእግዚአብሔር ታማኝነት ታሪኬን ይጽፈዋል።
“እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።”
— መዝሙር 34፥18
ስለዚህ ዛሬም ሆነ ነገ በምንም ውስጥ ባልፍ፣ የታሪኬ ብዕር ያለው በታማኙ አምላኬ እጅ ስለሆነ የወደፊቱ ሕይወቴ በምስጋናና በድል የተሞላ መሆኑን ሙሉ በሙሉ አምናለሁ!
🙏24❤6👍1🔥1
19 Jul 2026, 05:05 UTC996 views26 reactionsread 7 August 2026 ቤተክርስቲያን
ቤተክርስቲያን ማለት ድንጋይና አሸዋ፣ ቀለምና ጣራ አይደለችም። የማንነታችን መገለጫ ናት፥ የህያውያን ጉባኤ ናት፥ የሰማይ ዜማ ማስተጋቢያ ናት፥ የነገው ብርሃን ማሳያ ናት። እኛ ነን! በአንድ ልብ የተሰበሰብን፣ በፍቅር የተገመድን፣ በደሙ የተዋጀን ህያው ቤተሰቦች ነን።
ለእያንዳንዱ የተሰበረ ልብ፣ በሕይወት አውሎ ንፋስ ለቆሰለችና ለዛለች ነፍስ ሁሉ እውነተኛ ፈውስና መጽናኛ የሚገኝባት ተስፋ የተሞላች ይህች የቅዱሳን ኅብረት ናት። በኃጢአት፣ በኀዘንና በጭንቀት ለደከሙ፣ በውስጥ ጩኸት ለታወኩ ሕይወት ሁሉ መታደስንና አዲስ የብርታት ምንጭን የምታበስር የእግዚአብሔር የጸጋ ማኅበረሰብ ናት።
በዚህ ጉባኤ መካከል፣ የሰውን ልጅ ውድቀትና ድካም …
❤22🥰4
18 Jul 2026, 12:20 UTC964 views28 reactionsread 7 August 2026 የክርስትና ሕይወት ጉዞ ከሲኦል ፍርሃት ያወጣናል። የጸጋው ጥልቀት ግን ከዚያ በላይ ይወስደናል፤ ኃጢአትን ራሱን እንድንጸየፈው ያስተምረናል። ስለዚህ ኃጢአትን የምንሸሸው እኛን ወደ ሲኦል እንዳይወስድ በመፍራት ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ሰማይ የወሰደንን አምላክ ልብ ስለሚሰብር ነው። ያኔ ኃጢአት የቅጣት ምንጭ ብቻ ሳይሆን፣ የአምላክ እንባ ምክንያት መሆኑን እንረዳለን። የበሰለ ልብ የሲኦልን እሳት ሳይሆን፣ የመስቀሉን ፍቅር እያሰበ ኃጢአትን ይጠላል።
🥰14❤6🔥6❤🔥1🙏1
17 Jul 2026, 05:49 UTC≈1,900 views29 reactionsread 7 August 2026 የእምነት ጉዞ
ብዙዎቻችን ስለ እግዚአብሔር ማወቅ እና እግዚአብሔርን በግል ሕይወት ማግኘት አንድ ይመስሉናል። ነገር ግን በሁለቱ መካከል የባሕርይ ልዩነት አለ።
👉ስለ እግዚአብሔር ማወቅ (Knowledge)፦ ይህ ደረጃ አእምሯዊ ነው። መጻሕፍትን ማንበብ፣ ታሪኮችን ማጥናት፣ ዶክትሪኖችን በቃል መያዝ እና በሃይማኖታዊ ክርክሮች ላይ ማሸነፍ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይህ እውቀት ወደ ልብ ካልወረደ የሃይማኖት "ሳይንስ" ወይም "ፍልስፍና" ብቻ ሆኖ ሊቀር ይችላል።
👉እግዚአብሔርን ማግኘትና መለማመድ (Intimacy)፦ ይህ ደግሞ የልብና የሕይወት እውነተኛ ልምምድ ነው። መለኮታዊውን ፍቅር በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በተግባር መለማመድ፣ በፈተናዎች መካከል …
❤🔥16❤10🔥3
Showing the 12 most recent of 21 posts we hold for @christcentered7. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.