7 Aug 2026, 03:03 UTC260 views4 reactionsread 9 August 2026 Forwarded from @christcentered7
የእምነት ጉዞ
ብዙዎቻችን ስለ እግዚአብሔር ማወቅ እና እግዚአብሔርን በግል ሕይወት ማግኘት አንድ ይመስሉናል። ነገር ግን በሁለቱ መካከል የባሕርይ ልዩነት አለ።
👉ስለ እግዚአብሔር ማወቅ (Knowledge)፦ ይህ ደረጃ አእምሯዊ ነው። መጻሕፍትን ማንበብ፣ ታሪኮችን ማጥናት፣ ዶክትሪኖችን በቃል መያዝ እና በሃይማኖታዊ ክርክሮች ላይ ማሸነፍ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይህ እውቀት ወደ ልብ ካልወረደ የሃይማኖት "ሳይንስ" ወይም "ፍልስፍና" ብቻ ሆኖ ሊቀር ይችላል።
👉እግዚአብሔርን ማግኘትና መለማመድ (Intimacy)፦ ይህ ደግሞ የልብና የሕይወት እውነተኛ ልምምድ ነው። መለኮታዊውን ፍቅር በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በተግባር መለማመድ፣ በፈተናዎች መካከል …
❤4
Signed Chirstian Abeni
6 Aug 2026, 05:46 UTC276 views5 reactionsread 9 August 2026 ወደቅኩ፣ ደከምኩ፣ በኃጢአት ደቀቅሁ፣ እግዚአብሔርን አሳዘንሁ ብለን የእግዚአብሔርን ጸጋ ከምንለምንባቸው ቀናት እኩል "ዛሬ ጥሩ ቀን አሳለፍኩ" በምንልባቸውም ቀናት የእግዚአብሔር ምህረት እና ጸጋ ያስፈልገናል። የምህረቱ መድረክ፣ የጸጋው ዙፋን ፊት የምንቀርበው የደከምን ቀን ብቻ አይደለም። የወደቅን ቀን ብርቱ ከሆንበት ቀን የበለጠ ጸጋ አስፈልጎን አይደለም፣ የበረታን ቀንም ከደከምንበት ቀን ያነሰ ጸጋን አይደለም የምንሻው።
ለክርስትና ሕይወት የእግዚአብሔር ጸጋ ሁልጊዜ ያስፈልገናል። ያለ እግዚአብሔር ጸጋ የምንበረታበት ቀን የለም፣ ያለ ምህረቱ ከውድቀታችን የምንነሳበት ቀን አልተመቻቸልንም።
ጸጋው ስንደክም ብቻ ሳይሆን ስንበረታም ያስፈልገናል። ሲጀመር በ…
❤4👏1
Signed Chirstian Abeni
3 Aug 2026, 17:35 UTC233 viewsread 9 August 2026 መዝሙር 101:1-4 NASV
[1] ስለ ምሕረትና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአንተ በምስጋና እቀኛለሁ።
[2] እንከን የማይገኝባትን መንገድ አጥብቄ እይዛለሁ፤ አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? በቤቴ ውስጥ፣ በንጹሕ ልብ እመላለሳለሁ።
[3] በዐይኔ ፊት፣ ምናምንቴ ነገር አላኖርም። የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ ከእኔም ጋራ አይጣበቅም።
[4] ጠማማ ልብ ከእኔ ይርቃል፤ ለክፋትም ዕውቅና አልሰጥም።
Signed Chirstian Abeni
2 Aug 2026, 17:23 UTC238 viewsread 9 August 2026 ዮሐንስ 17:24 NASV
[24] “አባት ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ እኔ ባለሁበት እንዲሆኑ፣ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝንም ክብሬን እንዲያዩ እፈልጋለሁ።
Signed Chirstian Abeni
2 Aug 2026, 17:18 UTC227 views1 reactionsread 9 August 2026 ዓለም ከመፈጠሩ ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሔር ልጁን ይወድዳል ይህንንም ፍቅሩን በመንፈሱ በኩል ያፈስሰዋል። እግዚአብሔር ፈጥሮ "ፈጣሪ" ተብሎ ከመጠራቱ በፊት ከዘላለም ልጁን በመንፈሱ የሚወድድ አባት ነበር። ፍጥረትንም ሲፈጥር ይህንን በሥላሴ መካከል ያለውን ጥልቅ ፍቅር ለፍጥረቱ ለማጋራት እንጂ እግዚአብሔር ማንነቱን ለመሆን ፍጥረቱ አስፈልጎት አይደለም። "እግዚአብሔር ፍቅር ነው" ለመባል ፍቅሩን የሚገልጥባቸው ፍጥረታት አያስፈልጉትም። ፍቅር የዘላለም ማንነቱ ነው ይህም የሆነው አፍቃሪነቱ የሚጀምረው ከፍጥረቱ ሳይሆን ከዘላለም ልጁ ስለሆነ ነው። እግዚአብሔር በዘላለም ፍቅር ያልነበረበት ወቅት የለም ምክንያቱም ልጁን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ይወድድ ነበርና፤ ስለዚ…
👍1
Signed Chirstian Abeni
30 Jul 2026, 03:22 UTC195 views5 reactionsread 9 August 2026 1 ነገሥት 8:57-61 NASV
[57] አምላካችን እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ጋራ እንደ ነበረ ሁሉ ከእኛም ጋራ ይሁን፤ አይተወን፤ አይጣለንም።
[58] በመንገዱም ሁሉ እንድንሄድ፣ ለአባቶቻችን የሰጣቸውን ትእዛዞች፣ ሥርዐቶችና ደንቦች እንድንጠብቅ ልባችንን ወደ እርሱ ይመልስ።
[59] በየዕለቱም ባሪያውንና ሕዝቡን እስራኤልን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ እንዲረዳቸው፣ ይህች በእግዚአብሔር ፊት ያቀረብኋት የራሴ ልመና በቀንና በሌሊት ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ፊት ትቅረብ። [60] ይኸውም የምድር ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ እንደ ሆነና ከርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ ነው።
[61] ስለዚህ እንደ ዛሬው ዕለት ሁሉ፣ በሥርዐቱ እንድትኖሩና ትእዛዙን…
❤5
Signed Chirstian Abeni
26 Jul 2026, 05:11 UTC197 views4 reactionsread 9 August 2026 2 ሳሙኤል 23:5 NASV
[5] “የእኔስ ቤት በአምላክ ዘንድ ትክክል አይደለምን? ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፣ ከእኔ ጋራ ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ አይደለምን? ድነቴን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፣ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን?
❤4
Signed Chirstian Abeni
22 Jul 2026, 02:40 UTC241 views7 reactionsread 9 August 2026 ሚክያስ 6:8 NASV
[8] ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣ በአምላክህም ፊት በትሕትና ትራመድ ዘንድ አይደለምን?
🙏6❤1
Signed Chirstian Abeni
19 Jul 2026, 15:47 UTC266 views0 reactionsread 9 August 2026 Pray
Signed Chirstian Abeni
27 Jun 2026, 21:08 UTC362 views1 reactionsread 9 August 2026 Unparticular repentance is a clever way to avoid particular conviction.
🤔1
Signed Chirstian Abeni
24 Jun 2026, 03:15 UTC382 viewsread 9 August 2026 ሉቃስ 15:17-24 NASV
[17] “ልብ በገዛ ጊዜ ግን እንዲህ አለ፤ ‘ስንቱ የአባቴ ሠራተኛ ምግብ ተርፎታል፤ እኔ ግን እዚህ በራብ ልሞት ተቃርቤአለሁ
[18] ተነሥቼ ወደ አባቴ ልሂድና፣ እንዲህ ልበለው፤ አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በአንተ ፊት በድያለሁ፤
[19] ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም፤ ከተቀጠሩት አገልጋዮችህ እንደ አንዱ ቍጠረኝ።’
[20] ስለዚህም ተነሥቶ ወደ አባቱ ሄደ። “ነገር ግን፣ እርሱ ገና ሩቅ ሳለ፣ አባቱ አይቶት ራራለት፤ ወደ እርሱም እየሮጠ ሄዶ ዐቅፎ ሳመው።
[21] “ልጁም፣ ‘አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በአንተ ፊት በድያለሁ፤ ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም’ አለው።
[22] “አባቱ ግን ባሮቹን እንዲህ አላ…
Signed Chirstian Abeni
21 Jun 2026, 15:38 UTC300 views9 reactionsread 9 August 2026 "እግዚአብሔር ብቻ ስለ ራሱ ሲናገር ያምርበታል።"
መጋቢ ሳሚ ቱራ
❤4🔥4🤝1
Signed Chirstian Abeni
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Biblicall_Way. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.