5 Apr 2025, 06:48 UTC402 views2 reactionsread 7 August 2026 #የጌታ_ስቅለት_በአበው
"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" #ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የ…
❤2
Signed Keruvim כְּרוּבִים
9 Mar 2025, 09:19 UTC345 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Mr.Morale
9 Feb 2025, 08:12 UTC423 views1 reactionsread 7 August 2026 ጾመ ሰብአ ነነዌ 2017
‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው (ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪)፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶ ነበር (ዮናስ ፬፥፲፩)፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ዮናስ የስሙ ትርጓሜ ‹ርግብ› የሆነ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይን ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ …
❤1
Signed Kiru
19 Jan 2025, 07:21 UTC345 views1 reactionsread 7 August 2026 እንኳን ለጥምቀት በአል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
መልካም በዓል!
🥰1
Signed Kiru
18 Jan 2025, 08:54 UTC348 views0 reactionsread 7 August 2026 ከተራ ምንድን ነው?
ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአ…
Signed Kiru
5 Jan 2025, 16:38 UTC382 viewsread 7 August 2026 Photo
ሕፃን ሔራኒ ተሾመ እና ሶልያና ተሾመ የመዝገበ ጸሎት መጽሐፍን ወደ ብሬል ቀይረው አስመረቁ።
ሕፃን ሔራኒ ተሾመ እና ሶሊያና ተሾመ የመዝገበ ጸሎት መጽሐፍን ወደ ብሬል በመቀየር በዛሬው እለት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን፣ ካህናት፣ መምህራንና እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡
📷 ጆኒ ቪዲዮ
Signed Kiru
2 Jan 2025, 08:19 UTC352 viewsread 7 August 2026 Photo
"በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ፡፡ ያን ጊዜ ለዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ፡፡"
🖊️አቡነ ሺኖዳ
Signed Kiru
30 Dec 2024, 08:13 UTC357 viewsread 7 August 2026 በሕይወት ውስጥ መጀመሪያ ከፊት የሚመጡት ሰዎች "ሔዋንህ" ወይም "አዳምሽ" ላይሆኑ ይችላሉ።
ልክ አዳም ከተፈጠረ በኋላ መጀመሪያ በእርሱ ፊት እንስሳትን እንዳገኘ እና ለእነርሱም የሚገባቸውን ስም እየሰጠ እንዳሰናበታቸው፣ አንተም አንዳንዴ በኑሮህ ቀድመህ የምታገኛቸው አካላት "ጎረቤት፣ የሥራ ባልደረባ፣ ጓደኛ" እያልክ ስም የምታወጣላቸው ብቻ ይሆናሉ። ለምን? "እንደ አንተ ያሉ (የሚመቹ) ረዳቶች" አይደሉማ። አዳም ለእንስሳት፣ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ስም ካወጣላቸው በኋላ መጽሐፉ "ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር" ይላል።(ዘፍ 2፥20)
አዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት ከእንስሳቱ መካከል ፈልጎ በማጣቱ "በቃ የምን መኩራት ነው?…
Signed Kiru
14 Dec 2024, 07:20 UTC340 viewsread 7 August 2026 በሕይወት ዙሪያ፡፡
ራስን መግዛት መላ ሕይወትን ያጠቃልላል፡፡ መንፈሳዊው ሰው ምቾትንና ድሎትን አስመልክቶ ራስን መግዛት አለው፡፡ እርሱ ሰዓቱን በትክክል ይጠቀማል፡፡ በመሆኑም ጊዜውን ለሚሠራው መንፈሳዊ ሥራ ያከፋፍላል፡፡ ቀጠሮ ያከብራል፡፡ በተሰደበ ወይም በተጠቃ ጊዜ ለራሱ ሊበቀል እንዳይነሳሳ ራሱን ይገዛል፡፡ ገንዘብን በተመለከተም ስለሚቀበለውና ስለሚሰጠው ገቢና ወጪ ላይ ራሱን ይገዛል፡፡ ከሌሎች ጋር የሚያደርገው ግንኙነት እስከ ምን ድረስ መሆን እንዳለበት ይረዳል:: ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ እንዳያጋድል የልቡን ስሜታዊነትና ፍላጎት ይቆጣጠራል፡፡ ሌላው ቢቀር በአምልኮ፣ በአገልግሎት፣ሌሎች በመቆጣጠርና _ ሌሎችም ባሉበት ኃላፊነቶች ውስጥ ራሱን በሚገባ ይ…
Signed Kiru
13 Dec 2024, 12:16 UTC220 viewsread 7 August 2026 ታዛዥነትና ቃል መግባት፡፡
ራሱ ቃል በመግባት፣ በታዛዥነትና በተሸናፊነት ውስጥ ራሱን ይገዛል:: ምክንያቱም ዛሬ አንዳንድ ሰዎች በነፃነት፣በግል ክብርና በራስ መተማመን ስም ስለ ሥነ ሥርዓት፣ ስለ ወግና ስለ ሕግ ሳይጨነቁ የወደዱትን ስለሚያደርጉ ነው:: በዲሞክራሲ ብናምንም የምናምነው በገደብ ውስጥ ባለ ዲሞክራሲ ነው:: ለዚህ አባባል ወንዝ ጥሩ ምሳሌ ሊሆነን ይችላል፡፡ ወንዝ ከግራና ከቀኙ ባሉት ሁለት ከፍ ያሉ የምድር አካላት ተገድቦ ይፈሳል፡፡ ሰዎች ወንዙን ከሚፈስበት አቅጣጫ በማስቆም ነጻነቱን ሊነፍጉት ባይችሉም ከፍሳሹ ወጥቶ የጎርፍ አደጋ እንዳያስከትልና አካባቢውን ረግረግ እንዳያደርግ ግን ሊቆጣጠሩት ይችላሉ፡፡
መንፈሳዊው ሰው ቃሉን ይጠብቃል፤ ግብረ…
Signed Kiru
13 Dec 2024, 12:16 UTC249 views1 reactionsread 7 August 2026 ምኞትና የበላይነት፡
መንፈሳዊው ስው ምኞቱን፣ ደስታውን መውደዱንና የበላይነቱን አስመልክቶ ራስን መግዛት አለው:: በራሱ ዓይኖች ፊት ራሱን አዋቂ አድርጎ ሲያገኘው ወይም በአመለካከቱ ውስጥ ራሱን አጽድቆ ሲመለከት ወይም ደግሞ ራሱን ከሚያስበው በላይ ከፍ አድርጎ ሲያስብ ራሱን ለመግዛት ይጥራል። ሮሜ 12:3:
ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔር ከሰጠው ጸጋ በላይ ራሱን ሊያልቅ አይሞክርም፡፡ ዲያብሎስ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ ብሎ በትዕቢት የተነሣው ራሱን መግዛት ባለመቻሉ ስለሆነ ወድቋል:: ኢሳ 14:14።
መንፈሳዊው ሰው ራሱን የሚገዛው ውዳሴ ከንቱን አስመልክቶ ብቻ ሳይሆን ስጦታዎችንም በተመለከተ ነው:: ወ…
👍1
Signed Kiru
12 Dec 2024, 16:09 UTC275 viewsread 7 August 2026 ምስጋና የተመላሽ ድንግል ሆይ ማን በመሰለው፥ ማንስ በተመሰለበት ምሳሌ እንመስልሽ?....... ድንግል ሆይ ቅዱሳን ነቢያት ትንቢት የተናገሩልሽ ፥ ምሳሌ የመሰሉሽ አንቺ ነሽ።
[ቅዱስ አባ ሕርያቆስ ]
https://t.me/chralaiso
Signed Kiru
Showing the 12 most recent of 17 posts we hold for @chralaiso. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.