21 Jun 2026, 09:27 UTC360 views6 reactionsread 8 August 2026 Photo
ትናንት የአባቶች ቀን ነበር።
ብዙኀኑ ስለአባቱና አባትነት በቻለው መጠን ሲገልጽም ነበር።
ብዙዎች ስለአባታቸው መግለጽ ከሚችሉት በላይ ሲናገሩ ማየት ደስ ይላል።
አንድ አንዶች ደግሞ ይኽንን የአባት ጣዕም እንዴትም ብትነግሯቸው የማይሰማቸው አሉ። አባትነት ትርጕሙን እንኳን የማያውቁት ጥቂት አይደሉም።
እናታቸውን እንደአባት የሚቆጥሩም አሉ።
እናትነትንም ካላወቁ ደግሞ የኾነ ሰው ወይም እግዚአብሔር ብቻ ይኾናል አባታቸው።
ብቻ ኹላችንም የሚያስማማ የማያልፍ፣ የማይከዳ፣ የማይተወን የዘለዓለም እውነተኛ አባት አለን፤ እግዚአብሔር። ሊቁ ''አንተ አቡነ ወአንተ እምነ /አንተ አባታችን ነኽ፤ አንተም እናታችን ነኽ/'' (ቅዱስ ያሬድ) ያለውም አንድ የሚያደርገን ፍጹም …
❤6
6 Mar 2026, 21:20 UTC751 views6 reactionsread 8 August 2026 Photo
ሲነሳ
ሲወድቅ
ሲጥር ~ ሲለፋ፤
ሲጠላ
ሲወድድ
ሲስቅ ~ ሲከፋ፤
የሐዘን ገበሬ
አንጀቱን ሲያርሰው
የፍቅር ንፋስ ሲያስጎነብሰው ፤
የሕይወት ንዳድ
ሲያንቀለቅለው ~ ሲያተራምሰው፣
የውበት አምላክ ~ ሲኩል ሲያፈርሰው፣
ገና ጅምር ነው ...
ያለቀ አይደለም እያንዳንዱ ሰው ።
© ቴዎድሮስ ካሳ
@Chokhmah3
@Chokhmah3
❤5👏1
Channel photo removed
5 Feb 2026, 09:47 UTC334 views5 reactionsread 8 August 2026 What a decent human being!
አንድ ቀን ስምህን የሚያስታውሰው የመጨረሻው ሰው ይሞታል፤ and in that moment, it will be as if you never existed ይላሉ፤ ያኔ ሞት ድል ያደርጋል።
ሞትን የመታገያ ብቸኛ መሳሪያ፨
ትዝታ ነው።
መታወስ ነው።
መዘከር ነው።
ከፒያሳዋ ጁስ ቤት ተጀምሮ፤ በእውቅና፣ በዝና፣ በህመም፣ በጉዞ መሀል የማውቀውን ነፆነትን ዘክሬ ለዛሬ ሞትን በጥፊ ላጮለው ግድ ነው።
ነፆነት ትሁት ነው!
ምርጥ ስብእና ያለው መልካም ተግባቢ እና እጅግ ጨዋ ሰው ነው። በትንሽ እውቅና ብዙ መባለግ በሚቻልበት ሀገር ውስጥ እየኖረ ትሁት መሆንን የመረጠ የፀዳ ሰው። እኔ በማውቀው ልክ የውሸት ያልሆነ ትህትና ያለው …
❤3👏2
5 Feb 2026, 09:05 UTC238 viewsread 8 August 2026 Video
@Chokhmah3
@Chokhmah3
1 Feb 2026, 11:26 UTC895 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
ከኒቼ እብደት ጀርባ፣ ከቻርሊ ቻፕሊን ድብርት ጀርባ፣ ከኒዛር ቃባኒ ንዴት ጀርባ፣ ከሾፐን ሃወር ተቺነት ጀርባ፣ ከሶቅራጠስ ፈላስፋነት ጀርባ፣ ከማክሲም ጎርኪ ሀዘን ጀርባ፣ ከሄሚንግዌይ ራስን ማጥፋት ጀርባ፣ ከዶስቶቭስኪ መከራ ጀርባ፣ ከካፍካ መሰበር እና ከቶልስቶይ ለውጥ ጀርባ..
አንዲት ሴት ነበረች 🙌🏽🙂
© ሞገስ ዘአምድ
@Chokhmah3
@Chokhmah3
🤔2😢1
2 Dec 2025, 02:12 UTC332 viewsread 8 August 2026 Forwarded from @Light_Book_Delivery
🔥 ልዩ ድግስ!🔥
📖 ኦሮማይ 📖
⏳ እሁድ ማታ 3:00 ላይ
እንዳትቀሩ ቤተሰብ!
👇👇👇👇👇👇👇
2 Dec 2025, 02:12 UTC382 views5 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @bestletters
Weekly book review session
Guys ማርያምን ረስቼዋለኹ።(ይቺ ልጅ እኮ ልቤን ጥፍት አደረገችው እናንተዬ።)
...ቀጣይ book review እኛ ቤት ነው።እንኳን ደስ አላችሁ። እኛ የተቀደደው ማስታወሻ members ደግሰን ልንጠራቸው ነው።በቤታችንም የጥበብን ማዕድ በበአሉ ግርማ የሚጣፍጥ እንጀራ ከገፀ ባህሪዎቹ እየጨለፍን ብሉልኝ በሞቴ ልንል ነው። እድምተኞቹ ቤታችንን ከመሙላታቸው በፊት ፤ የምናቀርበው አጥተን እንዳናፍር...የበአሉ ግርማን ደራሲውን ለዚህ ሳምንት አንብበን ጨርሰን እንጠብቅ።
የመወያያ መፅሐፍ፦ደራሲው
ደራሲ ፦ በአሉ ግርማ
የዝግጅቱ ቀን፦ እሁድ ማታ 3:00
የዝግጅቱ ቦታ: የተቀደደው ማስታወሻ channel live stream…
❤5
21 Jul 2025, 20:44 UTC≈2,350 views8 reactionsread 8 August 2026 Video
በኾነ የድሮ ቀን .. በልጅነት ልቡና ወሬ ጀመርን። ልክ እንደሚተዋወቅ ሰው።
ነፍስና ልብ እየተዋዋስን በጋራ የምንጠቀም ጽኑ ጓደኛሞች ኾንን።
ኖርን። አደግን።
የኾነ ቀን ነፍሴን ወሰድኹ፣ ልቡን ወሰደ — ተጣጣን።
የኾነ ቀን አብረን ተቀምጠን ወሬ ጠፋብን። ማዶ ማዶውን ማየት ጀመርን።
የኾነ ቀን የምንገናኝበት ቆይታ እየተራራቀ መጣ።
የሆነ ቀን ደክሜ ሊደርስልኝ ሲገባ ዝም አለኝ ፣ "እንዴት ነኽ?” ልለው ሲገባ በኩርፊያ አለፍኹት።
የኾነ ቀን ስልክ መደዋወል አቆምን፣ አጉል ፉክክር ያዝን።
የኾነ ቀን «ሰላም ነው?» ተባብለን ተጨባብጠን ተላለፍን።
የኾነ ቀን መጨባበጡም ቀረና በቅንድባችን ከፍ ዝቅ ብቻ ሰላም ተባባልን።
የኾነ ቀን ዝም ተባብለን …
❤7🥰1
11 Jul 2025, 15:15 UTC896 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
The Art of War ይህ ነው። አለም ስለእናንተ ስሜት ግድ የላትም። ስላወጣነው ሳይሆን ስላለንና ስላስቀመጥነው ነገር የማጤን አባዜ አለባት። አለም ስለመልክ እና ባህሪያችን ግድ የላትም ይልቅ የምንሸከምበትን ልብ ትመረምራለች።
አለም ምርጫ አላት ነገር ግን ፍትሐዊ አይደለችም። አስመሳይነቷ ማንም ቢያጣና ቢነጣ ዞር ብሎ የማያይ ስነ ልቦናን መሸከሟ ነው። ሙሉ ህይወታችንን ትንሽ እና ደካማ ነኝ ብለን ብናለቃቅስ ከእኛ በተሻሉ ጠንካራ ሰዎች ተሸንፈን እንበላለን።
አለም በእናንተ ላይ አታሴርም ወይም አትደግፋችሁም ብቻ እስከምታሸንፉ በፍፁም ችላነት ውስጥ ታመላልሳችኋለች። የምንበላው ከሌን የሚበላን ይሰለጥንብናል። የምንሰጠው ከሌለን የሚነጥቀን ይመጣል። በወ…
❤3
3 Jul 2025, 19:45 UTC475 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
"ይመስላል : ዘላለም......
ሰው ሰውን : ሲወዱት፣
ዐይን ዐይኑን ሲያዩት
ይመስላል ፡ ዘላለም
አድማስ አልፎ ፡ አድማስ ጠፈር አልፎ ጠፈር
ይመስላል ዘላለም ሰው ባካል የሚኖር።
በመቃብሯ ውስጥ
ጢስ እንጨት ይጨሳል
ከርቤ ብርጉድ ዕጣን ፣ መቃብሯ ሽቱ
ጣፋጭ መዓዛ አለው ፣ አጥንቷ ታቦቱ
መቅደስ ቤተልሄም ፣ ቅኔ ማህሌቷ
ዕጣኑ ይጨሳል ፣ ይታጠናል ቤቷ
ልዩ መዓዛ አላት
በመቃብሯ ውስጥ ፣ ጢስ እንጨት ይጨሳል
በመቃብሯ ውስጥ ፣ አበባ ተኝቷል
.
.
.
ከሞተች ቆይቷል
© ገ/ክርስቶስ ደስታ
@Chokhmah3
@Chokhmah3
❤2
26 Jun 2025, 19:09 UTC≈1,010 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
በ'ውቄ 🖤
@Chokhmah3
@Chokhmah3
👏1
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @chokhmah3. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.