6 Aug 2026, 17:32 UTC74 views9 reactionsread 7 August 2026 ክረምት
በዚህ ቅዝቃዜ ውርጭ ባጠቃኝ ቀን
ብርድ ልብስ አልወጣም ሮቆኝ ያንች ዘቀን
ወይኔ ነሽ የኔ ውድ የልቤ ንቅሳት
የፍቅርሽ ትዝታ ይሰጠኛል እሳት
ክረምቱ በርትቶ ምን ብከናነብም
እጅሽ ካልዳበሰኝ ብርድ አልቋቋምም
ጃል በጊዜ ጠብሰህ ከሆን ለክረምት ማለፊያ ጥሩ ነው
በሌላ አታስቡ በቆሎ ለማለት ነው😊
♡ˢʰᵃʳᵉ
✍️የሙሂቡን ግጥም
አብረን እናጣጥም
https://t.me/byetiLhadorat
😁6👍3
6 Aug 2026, 12:27 UTC156 views9 reactionsread 7 August 2026 ሙሀመድﷺ
የኔን ውድ
ስሙም ይናገራል ንግስና ማዕረጉን
አህመድ ብቻ ደርሷል የምስጋና ጥጉን
ሙሀመድ ብቻ ነው የበላዩ ምስጉን
ይመስላል
ፊታቸው ጨረቃ ሙሉ የወጣች ቀን
እንየው ይገለጥ ለምንስ ይራቀን
ፈገግታቸው ኑር ነው ተስፋን የሚዘራ
ከሁሉ ያማሩ
የውበት ተምሳሌት የመካው ሙሽራ
አሏሁመ ሰሊ ወሰሊም ዓላ ሰይዲና ሙሀመድ።
በዱዓችሁ ኸሚስ ሙባረክ❤️💚
♡ˢʰᵃʳᵉ
✍️የሙሂቡን ግጥም
አብረን እናጣጥም
https://t.me/byetiLhadorat
❤9
5 Aug 2026, 20:59 UTC144 views14 reactionsread 7 August 2026 ያፈቀረ ለካ አይተኛም?
በመልካምነት ዜማ መውደድሽ እያሸነፈኝ
በለዘብታ ቃል ተከሽኖ ፀባይሽ እያከነፈኝ
ከልቤ ወደድኩሽና ቀስቅሶ ስንኝ አፃፈኝ
የኔ ሀዩ❤️💚
የሙሂቡን ግጥም
አብረን እናጣጥም
https://t.me/byetiLhadorat
❤12😘2
5 Aug 2026, 13:14 UTC177 views26 reactionsread 7 August 2026 Photo
መብሩክ❤️💚
ኡስታዝ አብዱ ሶመድ ማድህ ፉአድ ሸምሱ
#የትዳርን_ጣዕም_ሰሞኑን_ቀመሱ
አሚን በሉ💍
ሊቃአችሁ አምሮ ፈክቶ ትዳራችሁ
በፍቅር በደስታ ሞቅ ይበል ጎጇችሁ
ጀግና በሳል ልጆች በኸይር ወልዳችሁ
የምናይ ያድርገን ሞልቶ ሙራዳችሁ
አሚን በሉ💍
አሽራር የተባለ የትዳር ማነቆ
ትርኪ ምርኪው ሁሉ ከናንተ እርቆ
እስከ ጀነት ይዝለቅ አምሮና ሸብርቆ
ይሁን በል💍
ሰዓደተ ዳረይን ለናንተ ተመኘን
ኡስታዝ የኛ ዕንቁ እንወዳችኋለን
መብሩክ ብያለው🌹🌹🌹
አዩሀል አሂባ ለምን አትነቃም ክረምት እንኳ ያንቃህ😁
የሙሂቡን ግጥም
አብረን እናጣጥም
https://t.me/byetiLhadorat
❤19🥰5😁2
5 Aug 2026, 11:42 UTC170 views7 reactionsread 7 August 2026 File
ይድረስ ለሙሂቡ ገጣሚው
የነቢን ማድህ ገጣሚ የሚገልፅ መደድ
✍በወንድም ዘሪሁን ኮቦልቻ ቁርቁር
የሙሂቡን ግጥም
አብረን እናጣጥም
https://t.me/byetiLhadorat
❤7
4 Aug 2026, 19:06 UTC185 views15 reactionsread 7 August 2026 ሞት ቅርብ ነው
የምትወዱትን ሰው ፍቅራችሁን ሳትገልፁለት ሞት እንዳይቀድማችሁ!
ነገሮችን ለነገ አታሳድሩ
ማድረግ የምትፈልጉትን ዛሬ አድርጉለት መናገር የምትፈልጉትንም ዛሬ ተናገሩ።
ከሞተ በኋላ ቁጭት አይጠቅምም።
ዛሬ እንተሳሰብ
ዛሬ እንደማመጥ
ዛሬ እንከባበር
ዛሬ እንተዋወቅ...ወዳጃችሁን በወረትና በተረት አትቀይሩት #ውደታ የአካል ጥምረት ሳይሆን የመንፈስ ውህደት ነው።
የሙሂቡን ግጥም
አብረን እናጣጥም
https://t.me/byetiLhadorat
👍15
4 Aug 2026, 13:06 UTC186 views9 reactionsread 7 August 2026 #ሙሀመድ
ካኢናቱን
እሱ ነው የሞላው በማዕናው በሱራው
ወዳጅ አርጎ መርጦ ጌታችን የሰራው
መልኩም አጋር የለው ልቆ በዛት በስም
የሱ ውበት ጀውሃር ሞልቶ አይገመስም
وَجَوْهَرُهُ الْفَرْضُ مَا لا يَقْبَلُ الاِنْقِسَامَ
የኔ ነቢ ጀውሃር ፈርድ (Indivisible particles) መገመስ የማይችል ብቸኛ ጀውሃር ነው
✍ #ሙሂቡ_ገጣሚው❤️💚…………
❤9
3 Aug 2026, 11:47 UTC212 views16 reactionsread 7 August 2026 Photo
#የኔ ሸይኽ
ውዴታን በመግለፅ ስለሚያዘን ዲኑ
በናፍቆትሁ ብዛት ሳይጠፋኝ ውጥኑ
እስኪ ልሞጫጭር ባይኖረኝም ፈኑ
የዳንዩ ሳኒ የአብረከት ቁራጭ
የበሻሻው ፍሬ የአሏህ ተመራጭ
የልጅ ልጅ ሆንኩና ደረበብሁ ግርማ
አድርጎ መረጠሁ የፊቅህ አውድማ
የዚክር የአውራድ የቋንቋወች ካስማ
ሸይኽ ሙሀመድ ሚፍታህ አዳንይ አልጓጉርይ
የኔ ሸይኽ 2 አመት አብሪያቸው ስኖር ፊታቸው ከፈገግታ ውጭ አያስተናግድም፣መመረጥ እንደዚህ ነው
ሀያት በሉልኝ💚❤️
የሙሂቡን ግጥም
አብረን እናጣጥም
https://t.me/byetiLhadorat
❤16
3 Aug 2026, 07:23 UTC185 views5 reactionsread 7 August 2026 አሏሁመ ሶሌ ዓላ ሙሀመዴ መዲና ያለሁቱ ጠናብኝ ናፍቆቱ
ይድረሰው ምስጋና አሏህ ላለው ኩንቱ
ኡመት ላደረገን ለሙሀመድ ላንቱ
ሳያቋርጥ ዳኢም ጎርፎ ሶለዋቱ
በመዲናው ጀንበር በወወዳጄ ባንቱ
ያንቱን ኡመትነት ፈልጎ አጣው ስንቱ
ባንቱ ላይ ይንቧቧ የጌታ እረህመት
በፈጠረው አደድ በወርም ባመት
ቢአደዲ ረምሊ ወከዘ ነባት
ሀጀር ወላ ሸጀር ቢማዒል ቀጥራት
በለገሰ ቁጥር ፈይዱ በየወቅቱ
ኩሌው ትዝ እያለኝ ናፍቆት አብሰልስሎት
የውዱ አገር ርቆ እሩሁን ሀይሮት
ሀራራው ጠንቶበት መንፈሱን አስሎት
ትኩር ብሎ ያያል ሁሉም እሱ መስሎት
አካቦት ኸያሉ በኋላም በፊቱ
ሙሀባ እንደዚህ ነው በቃ ውድ ማለት
ቆራረጠኝ…
❤4👎1
2 Aug 2026, 20:30 UTC168 views9 reactionsread 7 August 2026 በምቶዱት መጠቃት
የወጥመድ መጀመሪያው የምትወደው ነገር ነው።
ሰው በመሆን ታሪካችን ውስጥ ጀግኖች ተጠልፈው የሚወድቁት ከክብር ማማ ላይ የሚዋረዱት ወደው ቀርበው ሚስጥረኛ ባደረጉት ሰው ነው።
ለዛም ነው የኔ ህዝብ #ወሎየ ሲገጥም
ጌታየ እርዳኝ ብየ እማፀንሀለሁ
ከወዳጀ አድነኝ ለጠላቴ እኔ አለሁ
.....ይላል.....
ከወጥመዳቸው ለማምለጥ ከፈለክ የማትገመት ሁን ብየ አልመክርህም ...ሰው የሚጎዳው በሚወደው ከሆነ .....ለሚወደው ካልታመነ..አይሆንማ....እንደት ይደረጋል.....መቼም ለምትወደው ድብቅ ሁን አይባል ነገር...!!
ስማ
እንደ እርግብ የዋህ እንደ እባብ ልባም ሁን ማለትኮ...እግርህን ሰብረውት በደረትህ እየተሳብክ ተጓዝ ማለት አይደለም…
❤9
2 Aug 2026, 11:48 UTC197 views11 reactionsread 7 August 2026 የኔ ቢጤ ላጤወች
ክረምት እንደት ይዟችኋል ቤተሰብ?😊
❤8😍3
2 Aug 2026, 11:24 UTC219 views8 reactionsread 7 August 2026 Video
መወለድስ ገጠር
የክረምት ትዝታ
በጧት በማለዳ ልቤ ተከፈተ
በገጠሩ ህይወት በሀሳብ ሸፈተ
ዛሬም አለቀቀኝ የትዝታ አባዜ
የገጠሩ ህይወት የልጂነት ጊዜ
ሀምሌ እና ነሀሴን ምድጃ እሳት ሙቆ
መስከረም ጥቅምትን ሳይቀር አረፍቆ
ዝናብ የጣለ ቀን በዚች በሳር ጎጆ
ትዝታ ያለበት ጎበዝና ቆንጆ
ልጅ እንደሆኑ አይቀር እንደት ይደረጋል
ገጠር የለመደ ከማን እንደት ያድጋል
ቀኑ እንደት መሽቶለት ሌቱ እንደት ይነጋል
ወደ ጫካ ሂደን ፍየሎች ለማልቀም
በሰማይ ላይ አይተን ጉሙ ሲጠራቀም
ደመናው ሲወጠር ሰማዩ ሲጠቁር
ዋሻ እንፈልግ ነበር መጠለያ ሽንቁር
ወይ ደግሞ በፍጥነት ፍየሉን አካለን
ቁጥር አረጋግጠን በግልፅ አደላድለን
በሩጫ በጩኸት ጉዞ እንጀምራለን
መንገድ እ…
❤8
Showing the 12 most recent of 19 posts we hold for @byetiLhadorat. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.