29 Jul 2026, 07:33 UTC106 views4 reactionsread 8 August 2026 ዛሬ የምታየው ሁኔታ የሕይወትህን መጨረሻ አይወስንም። እግዚአብሔር የሚናገረው ቃል ከሁኔታዎች ይበልጣል፣ የእርሱ ዓላማም ከሰዎች ፍርድ ይልቃል። ሰዎች የዛሬን ውድቀት ሊያዩ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን የነገን ክብር ያያል። ሰዎች በተዘጋ በር ፊት ይቆማሉ፤ እግዚአብሔር ግን ማንም ሊዘጋው የማይችለውን በር ይከፍታልና ዛሬ የህይወትህ መጨረሻ እዳልሆነ በማመን የእምነት ጉዞህን ቀጥል።
አብርሃም የተስፋውን ፍጻሜ ወዲያውኑ አላየም፤ በእምነት ተራመደ። ኖኅ ዝናብ ሳይዘንብ መርከብ ሠራ። እነርሱ በዓይናቸው ከሚያዩት ይልቅ በእግዚአብሔር ቃል አመኑ። ዛሬም ጌታ የሚጠራህ በሚታየው ሳይሆን በማይታየው ተስፋ እንድትኖር ነው። ዛሬ የህይወትህ መጨረሻ አይደለምና በእግዚአብሔር…
❤3👍1
Signed 🙏 🙄
11 Jul 2026, 16:19 UTC213 views2 reactionsread 8 August 2026 ሁሉም ነገር ከንቱ ነው። የከንቱ - ከንቱ።
ገንዘብ፣ እውቀት ሁሉም ነገር ከንቱ።
.
ይህ ጠቢቡ ሰለሞን የእውቀትን ጫፍ - የገንዘብን የሀብትን ጫፍ ተመልክቶ የተናገረው ነገር ነው። ሁሉም ነገር ከንቱ ነው። ከፀሀይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም። ሰዋዊ፣ ምድራዊ እና ቁሳዊ የሆኑ ነገሮች ያለ እግዚአብሔር ሲታዩ ባዶ ናቸው።
.
ሀብት እና ንብረት ጊዜያዊ እርካታን እንጂ የነብስን ዘላለማዊ ጥማት ሊያረኩ አይችሉም። በነገራችን ላይ.. ምድራዊ ስኬትን ብቻ ማሳደድ ንፋስን በእጅ የመጨበጥ ያህል ነው። የሰው ልጅ አቅሙ ሳይደክም፣ አማራጮቹ ሳይጠቡ በፊት በጉብዝናው ወራት እግዚአብሔርን ማሰብ አለበት።
👍2
Signed 🙏 🙄
1 Jul 2026, 12:36 UTC347 views6 reactionsread 8 August 2026 ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በ94 ዓመታቸው፣ ለናይጄሪያውያን የጻፉት ልብ የሚነካ መልእክት
ውድ የአገሬ ልጆች፣
ሰዎች ሕይወት ረጅም ናት ይላሉ። “አትቸኩል፤ ጊዜ ብዙ አለ” ይላሉ። እኔ ግን አሁን 94 ዓመት ሆኜ፣ ይህ እውነት እንዳልሆነ በእርግጠኝነት ልነግራችሁ እችላለሁ። ሕይወት ረጅም አይደለችም፤ በዓይን ጥቅሻ ታልፋለች። ከዚህ ዓለም ለመለየት እየቀረብኩ ስሄድ፣ ልቤ ጥቂት ትምህርቶችን ትቶላችሁ ለመሄድ ይፈልጋል። ሀብት ሰበሰብኩ፣ ተጽዕኖ አገኘሁ፣ ክብርና እውቅናም አተረፍኩ። ነገር ግን ዛሬ እነዚህ ሁሉ በክፍሌ ጥግ ላይ እንደተከማቸ አቧራ ይመስሉኛል። አሁን እጄን ብዘረጋ፣ ከእነሱ አንዳቸውም ከእኔ ጋር ሊሄዱ አይችሉም።
ትምህርት አንድ፡ ሕይወትን እየጠበቅክ …
❤6
Signed 🙏 🙄
30 Jun 2026, 11:53 UTC256 views5 reactionsread 8 August 2026 እግዚአብሔር መልካም ነው። ❤️
መንገዶች ሁሉ የተዘጉ ሲመስሉ፣ ነገን ማለም ቅንጦት ሲሆን፣ ተስፋዎች ሁሉ ፈትነው በሚያስጨንቁበት ሰአት እንኳን እርሱ ታማኝ ነው..!
❤5
Signed 🙏 🙄
27 Jun 2026, 04:39 UTC332 views4 reactionsread 8 August 2026 አንዳንድ መውደቆች ለበጎ ናቸው። ነገ ደግሞ ትነሳለህ። ነገ መነሳትህ አይቀርም። በመውደቅ ውስጥ ግን ብዙ ነገር ትማራለህ። ትሁት ትሆናለህ፣ የሰው ችግር ይገባሀል፣ ትልቁን የህይወት ጥንካሬም ታገኛለህ። ሁሌ ስኬት ብቻ ከሆነ ትእቢተኛ ልትሆን ትችላለህ። ትእቢተኛ ከሚያደርግህ ስኬት ይልቅ ትሁት የሚያደርጉህ አንዳንድ መውደቆች ለህይወትህ ወሳኝ ናቸው። አንድ ሰው ሁልጊዜ ስኬትን ብቻ ሲያይና ሲያከማች ሳያስበው "እኔ ፍፁም ነኝ - ከእኔ በላይ ማንም የለም.." የሚል የትእቢት ስሜት ውስጥ ሊገባ ይችላል። ትእቢት ደግሞ የአእምሮን አይን ይጋርዳል ፤ አዳዲስ ነገሮችን የመማር አቅምን ሙሉ በሙሉ ያጠፋል። ወድቆ መነሳት በጣም ፀዴ ነገር ነው። ስትወድቅ በዙሪያህ ያሉት…
❤2👍2
Signed 🙏 🙄
15 Jun 2026, 13:47 UTC383 views9 reactionsread 8 August 2026 ሁሉም ነገር ከንቱ ነው። Everything in Life come to an End anyways. የአሁኑ ቅፅበት ብቻ ነው በእጃችን ያለው። ትናንት አልፏል፣ ነገ ደግሞ ገና አልመጣም። ነገሮች ሁሉ የሚያልቁ መሆናቸው.. ዛሬ በእጃችን ያለውን ጊዜ በአግባቡ እንድንጠቀምበት ይገፋፋናል። የምንወዳቸውን ሰዎች መውደድ፣ በምናደርገው ነገር ደስታን መፍጠር፣ እና የህይወትን እያንዳንዱን ደቂቃ ማጣጣም የምንችለው ጊዜ እንደሚያልቅ በማወቅ ነው። ህይወት እጅግ በጣም አጭር ናት።
❤8👍1
Signed 🙏 🙄
21 May 2026, 15:57 UTC519 views5 reactionsread 8 August 2026 አለመ-ኖር ግን ምን አይነት ስሜት ያለው ይመስላችኋል..? Exist አለማድረግ ፤ ወይም አለመፈጠር ምን አይነት ስሜት አለው? እኛ እዚህ ምድር ላይ ከመምጣታችን በፊት አለም ለብዙ አመታት ያህል ቆይታለች። ላለፉት 7,500 አመታት በላይ ደግሞ እኛ በህይወት አልነበርንም። ከ 80 እና 100 አመት በኋላ ደግሞ አንኖ-ርም። አለመ-ኖርን መግለፅ ግን በጣም ይከብዳል። አለመ-ኖርን ወይም Non-existence በአእምሮ መገመት ከባድ ነው ፤ ምክንያቱም እኛ የምናውቀው ብቸኛው ነገር “ማሰብን እና መኖርን..” ብቻ ስለሆነ። በነገራችን ላይ.. በመፅሀፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሰረት እኛ ከመፈጠራችን በፊት እዚህ አለም ላይ ባንኖርም በእግዚአብሔር እውቀትና እቅድ ውስጥ ግን…
❤3🔥1🥰1
Signed 🙏 🙄
18 May 2026, 13:56 UTC456 views7 reactionsread 8 August 2026 በአለማችን ውስጥ.. በየአመቱ 30 ሚሊየን ሰዎች በካን-ሰር ህ-መም ይያዛሉ። 173,000 ሰዎች ደግሞ በየእለቱ ይሞ-ታሉ። አለማችን ላይ ከሚገኙ ህዝቦች 90 ሚሊየን የሚሆኑት መራመድ አይችሉም። 300 ሚሊየን የሚሆኑ የአለማችን ህዝቦች ደግሞ Color Blind ናቸው [ ቀለማትን መለየት አይችሉም ] ... 430 ሚሊየን መስማትም መናገርም የተሳናቸው ሰዎች አሉ።
.
በአለማችን ውስጥ 45 ሚሊየን ማየት የተሳናቸውም ሰዎች አሉ። 160 ሚሊየን ፓራላይዝድ የሆኑ [ እጃቸውንም፣ እግራቸውንም፣ ሰውነታቸውንም ማዘዝ የማይችሉ ] ሰዎች በምድራችን ላይ ይገኛሉ። My Brother.. ያንተ የእለት እለት ኑሮ ለእነዚህ ሰዎች ህልማቸው ነው። your ordinary life…
👍4❤3
Signed 🙏 🙄
17 May 2026, 14:26 UTC426 views10 reactionsread 8 August 2026 ከ 100 አመት በኋላ - ማለትም በ 2118 ዓ.ም ሁላችንም በህይወት አንኖ-ርም። ዛሬ የተወለደ ህፃን ልጅ ራሱ በ 2118 ዓ.ም የለም። ጓደኞቻችንም፣ ቤተሰቦቻችንም ሁላችንም ሂያጅ ነን። ከ 200 አመታት በኋላ ደግሞ - በ 2218 ዓ.ም እኛ እዚህ አለም ላይ መኖራችንን ወይም Exist ማድረጋችንን እንኳን ማንም ሰው አያውቅም። Exist ማድረጋችን ራሱ ተረስቷል። የገዛ የልጅ ልጅ ልጅ ልጆቻችን ራሱ ስማችንን ላያውቁት ይችላሉ። አብዛኛዎቻችን የቅም አያታችንን ስም እንደማናስታውሰው ማለት ነው።
.
አሁን አሳካን የምንለውን ስኬት & አፈር ድሜ ግጠን ያመጣነውን Our all Achievements ጭምር፣ ከፍታችንን ዝቅታችንን ማንም አያስታውሰውም። There …
❤10
Signed 🙏 🙄
9 May 2026, 10:27 UTC497 views7 reactionsread 8 August 2026 የዐዲስ ኪዳን ዳሰሳ
🔥ሐዋርያው ዮሐንስ ማን ነው?🔥
1. ዮሐንስ ተብለው በተመሳሳይ ስም የሚጠሩ ቢያንስ ሦስት ሰዎች አሉ። መጥምቁ ዮሐንስ፣ ማርቆስ ዮሐንስና ሐዋርያው ዮሐንስ ናቸው። አንዳንድ ሰዎች መጥምቁ ዮሐንስንና ሐዋርያው ዮሐንስን እንደ አንድ ሰው ሲያስቧቸው ተመልክቼ አውቃለኹ። ኾኖም በቅዱሱ መጽሐፍ ልዩነታቸው በግልጽ ተቀምጧል። አኹን ታሪኩን ለማየት የምንወደው የሐዋርያው ዮሐንስን ነው።
2. ሐዋርያው ዮሐንስ በጌታ ከተመረጡት አሥራ ኹለት የበጉ ሐዋርያት ውስጥ አንደኛው ነው። አባቱ ዘብዴዎስ እናቱ ደግሞ ሰሎሜ ትባላለች። ወንድሙ ደግሞ ሐዋርያው ያዕቆብ ነው። እነዚኽ ኹለት ወንድማማቾች ከ12ቱ የበጉ ሐዋርያት በጌታ ጸጋ የተቀላቀሉ ናቸው። ሐዋርያ…
❤7
27 Jan 2026, 09:50 UTC733 views7 reactionsread 8 August 2026 ኧረ ምኑን ሰጠን?!
(አሌክስ አብርሃም)
አማኝ ከሆንክ ለፈጣሪህ፣ ካልሆንክም ለተፈጥሮ በግንባርህ ተደፍተህ የምትሰግድበትን በቂ ምክንያት ልንገርህ። በመጀመሪያ ሰው ሆነህ በመፈጠርህ እንኳን ደስ አለህ ወዳጄ! "ኑሮ ተወደደ፣ ምን ጥቅም አለው?" እያልክ ከመነጫነጭህ በፊት ይህንን አንብብ። በእርግጥ ይህን ማንበብህ ኑሮን አያረክስም፣ የአንተን ዋጋ ክብደት ይነግርሃል እንጅ!
በአሁኑ ወቅት "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ" (AI) ሲባል ሰምተህ ይሆናል። ሰውን በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ተአምራዊ ረቂቅ ነገር አድርገን እያየነው ነው። ነገር ግን የኔ ጌታ... AI ከሰው ልጅ አፈጣጠርና አጠቃላይ ስሪት ጋር ሲወዳደር እጅግ ደካማ ነው። የሰው ልጅ አስገራሚ ፍጥረት …
❤6🥰1
3 Dec 2025, 13:25 UTC839 views7 reactionsread 8 August 2026 ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና የትኛው ነው?66 ,73 ወይስ 81?
ማነው ትክክል ወንጌላዊያን ኦርቶዶክስ ወይስ ካቶሊክ?
ቀኖና የሚለው ቃል ካኖን κανών ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ቀጥትኛ ትርጉሙ የመለኪያ ዘንግ እንደማለት ነው። መመሪያ ወይም መለኪያ በሚል ቃል ሊተረጎም ይችላል። ወደ እኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አውድ ስናመጣው ደግሞ በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት የተጻፉ ለእምነት እና ለተግባር ስልጣን ያላቸው የቅዱሳት መጽሐፍት ስብስብ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና እንዋለን።[1] የተለያዩ አብያተክርስቲያናት የተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና አላቸው። ስለዚህ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ የመጨረሻ ሥልጣን እንደሆነ የሚያስተምር እምነት የትኛው መ…
❤7
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @biblequiztobest. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.