7 Aug 2026, 17:04 UTC48 views6 reactionsread 8 August 2026 😘ነፍስ ስታፈቅር😘
🔥 ክፍል 15
.
.
///
በዚህ ምድር ላይ ዝም ብሎ ከመኖር ውጭ ምንም ሌላ ማደርገው የረባ እና ትርጉም ያለው ነገር የለም፡፡በዚህም የተነሳ ሰው በመሆኔ እየተገረምኩ አለው እልሻለሁ ››
‹‹ ላንተ ሰው ምንድ ነው?››
‹‹ሰው ለእኔ የማይረባ እንስሳት ነው፡፡እንስሳት እንኳን አይደለም ተሳስቼያለው፤ እንስሳት ቃሉ ለስለስ ያለ ነው፡፡የዋህ የሚል ስሜት ያለው ትርጉም ነው የሚሰጠው፡፡ሰው እንደዛ አይደለም እንስሳ ነው ብለን እንኳን ብንል ያ እንስሳ ግን ትልቅ ውቅያኖስ የሚያህል ጥልቅና ስውር ሆድ ያለውና በዛ ሆድ ውስጥ ጥፍራም ያደፈጠ አውሬ ተሸክሞ የሚዞር ፍጡር ነው፡፡››
‹‹ስለሰው ጭለምተኛ ምልከታ ነው ያለህ ልበል?፡፡››
ቀስ በቀስ እ…
❤6
6 Aug 2026, 17:04 UTC72 views9 reactionsread 8 August 2026 ነፍስ ስታፈቅር
#ክፍል 14
.
.
///
ዛሬ እራሱ ነው የመጣው.ለዛውም ገና በጥዋት ስራ ለመሄድ እየተዘጋጀው ሳለ፡፡
‹‹እትይ››
‹‹አቤት ተዘራ››
‹‹ሰውዬሽ መጥቷል›
ደንግጣ በፍጥነት ወደሰሎን በራፍ ተንደረደረች..ምን ተፈጥሮ ነው ?ሳይደውልልኝ በዚህ ጥዋት››ስትል አሰበች፡፡በራፉን ስትከፍት ግን በአንድ ሜትር ርቀት በረንዳው ጠርዝ ላይ የቆመው ያሰበችው ፍቅረኛዋ ሄኖክ ሳይሆን እብዱ ነው፡፡ፅድት ያለ ልብስ ለብሷ ፅድት ብሏል፡፡በእጁ ባለፈው በራሱ ፍቃድ ይዞት ሄዶ የነበረውን መፅሀፍ ይዞል፡፡
በደመቀ ፈገግታ‹‹እ አንተ ነህ እንዴ?››አለቺው፡፡
‹‹አዎ እትይ እሱ ነው….ስራ ልትሄድ ነው ብለውም ያው እንደተለመደው አልሰማኝም››
‹አይ ግድ የለም ስራው ይ…
❤9
5 Aug 2026, 17:00 UTC78 views6 reactionsread 8 August 2026 ነፍስ ስታፈቅር
🔥ክፍል 13
.
.
.
ሲፈን እራት ላይ ከሽማግሌውም ሆነ ከነኄኖክ ብዙ ጫወታ እና የቤተሰብ ወሬ ጠብቃ ቢሆንም አንድም ንግግር አልነበረም፡፡እሷና ሄኖክም እራት በልተው ስለመጡን እንደነገሩ ነበር የነካኩት ፡፡
ሽማግሌው ድንገት ከመቀመጫቸው ተነሱና ..መጀመሪያ የሄኖክን ግምባር..ቀጥሎ የልጅቷን ግንባር ከዛ ደግሞ የእሷን ጉንጭ ሳሙና ምንም ሳይናገሩ ወደውስጥ ገቡ ..ወደመኝታቸው፡፡
ሲስሟት የከንፈራቸው ልስላሴ እና የፂማቸው መዋጋት እና ደግሞ የትንፋሻቸው ሙቀት ከእሷ ጋር ነበር የቀረው፡፡
ልክ እሷቸው ቦታውን ለቀው ወደውስጥ እንደገቡ ሄኖክ በረጅሙ ተንፍሶ‹‹ይገርማል?››አለ
‹‹ምኑ…?››እህቱ ነች ተንቀልቀል የጠየቃችው፡፡
‹‹ልዕልት አለሽ …
❤3👍3
4 Aug 2026, 17:04 UTC95 views7 reactionsread 8 August 2026 ነፍስ ስታፈቅር
🔥ክፍል 12
.
.
‹‹ቁርጥ ቦንጋ የሚኖሩትንአጎቴንይመስላ ስትል ››አሰበች፡፡
‹‹ሄኖኬ ያልኩህን ሰምተሀል ….ውጡና እራት አዘጋጁ፡፡››
‹‹እሺ እራቱን እናዘጋጃለን…ግን በዚህ ለሊት በረንዳ ላይ…..››
‹‹እተነጫነጭ››
ወጣ..እህቱም ተከተለችው፡፡
‹‹ተነሽ በረፉን ዝጊው፡፡››
‹‹እ ምን አሉኝ..?››ደንግጣ
‹‹ተነሽ በራፉን ዝጊው፡፡››
በዝግታ ከተቀመጠችበት ተነሳችና እንደታዘዘችው በራፉን ዘግታ ተመልሳ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹ቁርጥ እሷን ነው የምትመስይው፡፡››
‹‹ማንን?››
‹‹እናቱን..የሄኖክ እናት››…
‹‹የእውነት.እሱ ግን እንደዛ ብሎ ነግሮኝ አያውቅም››
‹‹እርግጥ ህፃን እያለ ስለሞተች ጥርት ባለ ምስል አያስተሰውሳትም…
❤7
3 Aug 2026, 17:05 UTC94 views4 reactionsread 8 August 2026 ነፍስ ስታፈቅር
🔥ክፍል 11
.
.
እንዳላያት እርግጠኘ ነች ፡፡ቢያያት ኖሮ መኪናውን አቁሞ የሆነ ነገር ይላት ነበር ፡፡ላፍቶ ሲደረሱ አራት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ይገርማል በአየር ላይም ቢሆን ፍቅር ፍቅር መጫወት ከጀመሩ አንድ አመት አልፎቸዋል፡፡አንድ ቀን ግን እቤትህ የት ሰፈር ነው ብላ ጠይቃው አታውቅም ፡፡ግቤው ደርሶ የመኪናውን ጡርንባ አስጩሆ ዘበኛው ሲከፍትለትና ወደውስጥ ሲገባ እሷም ተከትላው ገባች ..አቁሞ ከመኪናው ሲወርድ እሷም በተመሳሳይ ከመኪናዋ ስትወርድ ሲያያያት በጣም ነው የደነገጠው
‹‹እንዴት?››
‹‹እንዴት ምን?››
‹‹እንዴት መጣሽ..ማለቴ ለምን?›
‹‹የሰማውትን ሰምቼ መሄድ አላስቻለኝም፡፡››
እሷን በዚህ ሰዓትና በዚህ የጭንቅ ጊዜው ጊ…
👍4
2 Aug 2026, 17:02 UTC90 views6 reactionsread 8 August 2026 ነፍስ ስታፈቅር
🔥ክፍል 10
.
.
///
ከፍቅረኛዋ ጋር ያላትን የእራት ቀጠሮ አክብራ ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል በሰዓቱ ተገኝታለች፡፡
ረጅም ነው..በጣም ረጅም፡፡ ደግሞም ፈርጣም….ወደቀይነት ያደላ የሰውነት ቀለም ያለው….ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት ፀጉር ..ልቅም ያለ ቆንጆ..በዛ ላይ ሽክ ብሎ ዘንጧል፡፡በአቅራቢያው ያሉት እንስቶች ዓይን ማረፊያ ሆኗል ፡፡
እንደደረሰች ጎትቶ ከደረቱ አጣበቀትና ትንፋሽ እስኪያጥራት ሳማት፡፡ተሳምችለት እንጂ መልሳ አልሰመችውም፡፡ወንበር ስቦ ከፊት ለፊቱ አስቀመጣት፡፡
አዎ ሴት መንከባከብ እና በፍቅር ማቅለጥ ይችልበታል፡፡ግን ይህ ችሎታ ው በአሰበው መጠን ሲፈን ላይ እየሰራለት አይደለም፡፡በዚህ ምክንያት በችሎታው ላይ ያለው በ…
❤6
1 Aug 2026, 17:31 UTC95 views5 reactionsread 8 August 2026 ነፍስ ስታፈቅር
🔥ክፍል 9
✍ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ
.
.
.
አንድ የምታውቀው ብቸኛ ነገር ቢኖር ከዛች ቀን ጀምሮ ቢሮም ቁጭ ብላ ሆነ ከሰራ
ወደቤቶ ገብታ ስትተኛ ምስሉ በአዕምሮዎ ፊት ለፊት ስፍራ ላይ በግዙፍ
እንደተለጠፈ መቅረቱን ነው፡፡
ቆይ ያውና ….››አለች፡፡.ከፊት ለፊቴ አንገቱን ደፍቶ በዝግታ እየተራመደ
አየችው….ደረሰችበትና መኪናዎን አቆመች….አንገተቷን በመስኮት አሰገገችና
‹‹እ…እንዴት ነህ?፡፡››አለችው ….ስሙን እንኳን አታውቅም አኮ ….አይገርም፡፡
በግማሽ ቀና ብሎ አያትና መልሶ አቀረቀረ፡፡
‹‹አንተን እኮ ነው….አላወቅከኝም?››
እርምጃውን ገታ አደረገና መልሶ እያያት‹‹..አንቺን አላወቅኩሽም ነፍስሽን ግን
..››
‹‹ነፍሴን ምን?››
‹‹…
❤5
31 Jul 2026, 17:00 UTC140 views4 reactionsread 8 August 2026 ነፍስ ስታፈቅር
🔥ክፍል 8
.
.
.
‹‹አበቃልሽ…ሲፈን…፡፡››ደግማ አልጎመጎመች….ወላጆቾ በሀዘን ተራ በተራ
ሲሞቱ ታያት፡፡
‹‹እና ዛሬ ካማን ጋር ትደር?››ሌላ አጀንዳ ከአንደኛው ሽፈታ ተነሳ፡፡
‹ዛሬም የመጀማሪያ ቀን ስለሆን አምስታችንም በየተራ እናደርገዋን፡፡››
‹‹ይሻላል..?››
‹‹አዎ ይሻላል፡፡››
‹‹መጀመሪያ እንደቡድኑ መሪነቴ እኔ ልግባ…››
‹‹ግባ ..ግባ ..››በአንድ ድምፅ ፈቀዱለት
ከተቀመጠችበት ተነስታ ከተቆለለው የእህል ማደበሪያ ስር ተወሽቃ
ተደበቀች..ቢጨንቀት እንጂ እነሱ የማይደርሱበት ተሸሽጋ የምታመልጥት ምንም
ከለላ እደሌላ በደንብ ታውቃለች… የመጀመሪያ ደፋሪዎ የዋሻዋን በራፉ አልፎ
ከአሁን አሁን ገባና አነቀኝ ብላ በምትጠባቅበት …
❤4
31 Jul 2026, 17:00 UTC140 views4 reactionsread 8 August 2026 እንደውም ገና ስትወለድ ጀምሮ በግዘፍ ችግር የታጀበ ነው፡፡ይህ ችግሯ ችግር
አልባ መሆኗ ነው፡፡
እናቷ እሷን ማርገዟን ተጠራጥራ ሆስፒታል ሄዳ ተመርምራ መፀነሷን
የሚያረጋግጥ ወረቀት ይዛ መጥታ ማታ እራት ከተበላ ብኃላ ለአዛውንቱ አባቷ
ስታሳየው ….
‹‹ዳግመኝ እንድፈጠር አደረግሺን…››ብሎ በቦርጩ ወደፊት የተወጠረውን ሱፍ
ኮቱን ቁልፍ ከፈት በማድረግ የውስጥ ኪሱ ገብቶ ቼክና እስኪሪብቶ
አውጥቶ….አንድ ሚሊዬን ጻፈበትና ለእናቷ አቀበላት…
በወቅቱ የሲፈን እናት እየተፍለቀለቀችም እየተገረመችም‹‹ምን
ላድርገው…?››ብላ ጠየቀችው፡፡
‹‹ሽልማት ነው…››የፈለግሺውን አድርጊበት ማለቴ ልጄን የሚያስደስተውን …
ጤነኛ ሆኖ እዲወለድ ሚረዳውን ነገር ሁሉ ሀኪም እያማከርሽ…
❤4
30 Jul 2026, 17:00 UTC154 views4 reactionsread 8 August 2026 ነፍስ ስታፍቅር
🔥ክፍል 7
.
.
.
///
* ፍቅር
➶
የህይወት ጣዕም መዓዛን-አመንጭቶ ያተናል
በናርዶስ ሽቶ አውዶ-በደስታ ልብን ያሰክራል
ደግሞም ትንሽ ስቃይ አለው…ያስጨንቃል ያስተክዛል
ፍቅር ሲይዝ እንደዛ ነው…ሁሉ ነገር ግራ ያጋባል
…………..ያስፈግጋል…….
……………ያስፈዝዛል……..
///
ሰማያዊ ቀለም በተቀባች ላንድኩሩዘር መኪና በእሷ ሹፌርነት እየተጓዙ ነው፡፡ከጎኗ ሄኖክ ቁጭ ብሏል፡፡በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል ከአዲስ አበባ ከ400 ኪ.ሜትር ገደማ ርቀው ይገኛሉ፡፡ወደ ቦንጋ እየተጓዙ ነው፡፡ጥቅጥቅ ባለው ደን ውስጥ ሰነጥቆ በሚያልፈው ፒስታ መንገድ ላይ በሰዓት 80 ኪሎ ሜትር እየነዳች ነው፡፡ከፒስታው መንገድ እየተሸረፈ የሚነሳው አቧራ ሰማዩን …
❤4
29 Jul 2026, 17:02 UTC151 views6 reactionsread 8 August 2026 ነፍስ ስታፈቅር
🔥ክፍል 6
.
.
‹‹እንዴ ወደየት ነው.…?››
ቆም አለና ፊቱን ብቻ ወደእሷ ዞሮ ከእብድ ይልቅ የጅላጅል በሚመስል
በተንቀረፈፉ ቃላት‹‹እ..ማዬ ጋር ››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹እማዬ ጋር .ልብስህን ልበሰና ትሄዳለህ፡፡››
‹‹እኮ ሰውነቴን ታጥቤ የለ …የምቀይረውን ልብስ እረስቼ ስለመጣውእኮ
ነው..ልብሴ እማዬ ጋር ነው ያለው፡፡›
ሳቋ ሊያመልጣት ነበር..እንደምንም ስሜቷን ተቆጣጥራ‹‹ቆይ ቆይ.እንደእሱ
አይደለም …እኔ ንፅህ ልብስ እሰጥሀለው፡››
‹‹ይሻላል …?››
‹‹አዎ …ና ተከተለኘ ››አለችና እንዳይጠጋት አምስት እና ስድስት ሜትር ከእሱ
ርቃ ወደላይ ወደፎቅ ለመውጣት ደረጃውን መንደርደር ጀመርች
ምንም እንደልተፈጠረ .ረጋ ብሎ ..ደረቱን ነ…
👍4❤2
28 Jul 2026, 17:01 UTC146 views5 reactionsread 8 August 2026 ነፍስ ስታፈቅር
🔥ክፍል 5
.
.
ሸፍኗት የቆየውን ፤ የስጋ ልብሷን አውልቃ
ነፍሴ እርቃኗን ቀረች፤ በፍቅር አይን ስር ወድቃ
///
እቤቷ ያስገባችው ጥቁር እንግዳ ታጥቧ ከጨረሰ ቡኃላ የሚቀማምሰው ምግብ
ፍለጋ ኪችን ገብታ መንጎዳጎድ ጀመረች….ከቁርሷ የተረፈ ምግብ ስለነበር እሱን
አሙቃ አሰናደችና ወደሳሎን ይዛ ሄደች….፡፡የምግብ ጠረጳዛ ላይ በማስቀመጥ
ሶፋ ላይ ጋደም ብላ ቻናል እየቀያየረች ቲቪ ለማየት ሞከረች ግን ትኩረቷን
የሚስብ ፕሮግራም አላገኘችም….ከፕሮግራሞቹ የጥራት ችግር ይሁን ወይሰ የእሷ ቀልብ እቤቷ ውስጥ ባለው እብድ ተብየ ልጅ መሳብ አልገባትም፡፡
በግምት 15 ከሚሆኑ ደቂቃዎች ቡኃላ ከቴሌቭዝን ድምፅ ጎላ ያለ ድምፅ
ሰማችና ከተጋደመችበት በር…
👍4❤1
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @ber191. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.