28 May 2025, 19:44 UTC72 viewsread 10 August 2026 ✍✍ወልደህ ቅጣ✍✍
ድንገት ሳላስበው በድካም በዝለት
ወድቄ ቢያገኘኝ ከመንገዱ ስስት
የቅጣት በትሩን በእኔ ላይ ሊዘረጋ
በወደኩበት ስፍራ ክሱን እያወጋ
ሊቀጣኝ በፍርዱ ድንገት ተነሳ
ጠበቀቃዬም በጥበብ ክሴን አነሳ
ማነህና የማንን ልጅ ትቀጣለህ
ወልደህ ቅጣ ርህራሄ የት ታውቃለህ
ቀን ሚጠብቅህ ለራስህ ፍርደኛ
ዳግም የወለድኩትን እንዳታይ ዳግመኛ
አለውና ክሴን አባትነቱ ሻረልኝ
ወልደህ ቅጣ ብሎት እኔን ቀና አደረገኝ
“ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር ሳይሆን ሕያው በሆነና ጸንቶ በሚኖር፣ በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ከማይጠፋ ዘር ነው።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥23 (አዲሱ መ.ት)
Signed እግዛአብሔር ዛሬም ይወደኛል
27 Apr 2025, 01:54 UTC73 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @akiyaneh
✍✍መቼ ትመጣለህ🙌🙌
ሩቅ ከሄድክበት ሰው ከማያየው ማዶ
በሙላት ልታኖረኝ አውጥተህ ከባዶ
ሩቅ ሄደሀል እኔ ወደ ማልደርስበት
እዚህ ጋር ነህ ብሎ ከማትገመትበት
በተስፋ ቃልህ ልቤን አሙቀህ
ብቸኛ እንዳልሆን አፅናኝ አኑረህ
ውዴ ሄደሀል ለነገ ህይወታችን
ደፋ ቀና ልትል ልታንፅ መኖሪያችንን
ባልደከምኩበት ላይ እኔን ልታኖረኝ
ሩቅ ሄደሀል ስትጨርስ ልትወስደኝ
ታዲያ ውዴ በእነዚህ ቀኖች መሀል
ልቤ በናፍቆት አንተን አንተን ይላል
የሰጠኸኝም አፅናኝ ወዳንተ ይመራኛል
ሁኔታዎች ሲጋርዱኝ ቶሎ ይመልሰኛል
ነፍሴ ተጨነቀች ለፍቅርህ ሸፍታ
ለአንተ ትነቃለች ለዓለም ተኝታ
የሚያያት ሁሉ ሞኝ ያደርጋታል
ከንፈሩን መጦ በትዝብት ያያታል
እርሷ ግን እርሷ ግን
እርሷ ነጉዳለች…
Signed እግዛአብሔር ዛሬም ይወደኛል
24 Feb 2025, 10:52 UTC78 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @akiyaneh
💥💥💥ፀጋው ነው💥💥💥
ብ...ዙ ብ...ዙ እጅግ ብዙ
የዚህ ዓለም ነገር መዘዙ
ትርፍ የማያውቃት ኪሳራን አንግባ
ብቅ ብቅ ትላለች ሆዴን ልታባባ
አንድ ሁለት ብላ መቁጠር ትጀምራለች
የሌላትን እንዳላት አድርጋ ታቀርባለች
የሚጠፋውን ነገር እንደማይጠፋ
መሬት የማይነካ የአንደበት ተስፋ
ያላረፈችበትን እንዳረፈችበት አድርጋ
በክረምት ያገኘኝኝ ልታስለቅቀኝ በበጋ
በስውር ወጥመድ ትጋረፋለች በአለንጋ
በፀጋው ሙላት የምኖረውን እኔ
የራሷን ጉድለት አምጥታ ወደ እኔ
የሌላትን እንደ መጠየቅ የለህም ትለኛለች
ተዋናብዳ ልታወናብደኝ ትሞክራለች
ነውረነቷን እያፀደቀች ፅድቄን ሸፍና
የሌሎችን ዕብደት አድርጋ ንፅህና
ና ና ና ትለኛለች ነውሯን ሸፋፍና
ከዘመኑ ጋር እንድሄድ እግሬ…
Signed እግዛአብሔር ዛሬም ይወደኛል
25 Nov 2024, 17:30 UTC87 viewsread 10 August 2026 ፨ የጲላጦስ ማስታወሻ ፨
ይህን ማስታወሻ ለማግኘት በዘመናት መሀል በብዙ ተለፍቷል በብዙ ተስፋም ተቆርጦበት በብዥታ መሀል እንደገና እያንሰራራ ዛሬ ላይ በእግዚአብሔር ዕርዳታ አግኝቼዋለሁ። በዚህ ማስታወሻ ብዙ ምክርን አግኝታችሁ ገንዘባችሁ እንደምታደርጉት ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ፤ በጲላጦስ ማስተወሻ ውስጥ እራሳችንን እንድናየው የወንድማዊነት ምክሬን እለግሳለሁ።
፨ ልቤ አልረጋ አለ ፨
በቤቴ ቅጥር ውስጥ እየተዘዋወርኩ ሳለው
ድንገት ከቅጥሬ ውጭ ብዙ ጩኸት ሰማው
የሀይማኖት አባቶች ና የጦር መኮንኖች
በአንድነት ተያይዘው መስለው ወዳጆች
በአንድነት ቆሙ ክሳቸውን ሊያስማሙ
ተከሳሹን ያለ ጠበቃ በፊቴ እያቆሙ
ተከሳሹን እንደ…
Signed እግዛአብሔር ዛሬም ይወደኛል
20 Jun 2024, 02:04 UTC115 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @akiyaneh
የሻማ ና የአምፖል ወዳጅነት
ማብራት መጣ ብለህ ሻማህን አታጥፋው
የችግር መውጫህን አለውጥ በማይቆየው
የአምፖል ብርሀን ቀድሞ በሄደበት አሁንም ይሄዳል
የሻማ ብርሀን ግን እስከ መስዋዕት ድረስ ይሰነብታል
የአምፖል ወዳጅነት ችግርን ይሸሻል
ነጎድጓድ በመፍራት እራሱን ይሰውራል
ሲፈልግ ና ሲሞላለት ብቻ በመብራት
ምንም ያህል እንክብካቤ ብናበዛለት
እኛ ዘንድ መቆየት ሚፈልገው
እርሱ ሲፈልግ ሲመጣ ብቻ ነው
ምንም ያህል በብዙ ቢጠቅመንም
መተማመንን ግን አይፈጥርልንም
እንደ ጥቅሙም ጉዳቱም የከፋ ነው
ከእርሱ ጋር የሚኖረው በዓይነ ቁራኛ ነው
ካልገፋነው የማይሄደው
ካላጠፋነው የማይጠፋው
እስከ መስዋዕትነት እኛ ዘንድ የሚቆየው
ሻማ ብቻ ነው በጨለመን ሰዓት ምናገ…
Signed እግዛአብሔር ዛሬም ይወደኛል
1 Jan 2024, 16:19 UTC629 viewsread 10 August 2026 ልብ እየጠበበ ጨጓራ ሲሰፋ
ታዋቂ ሰው በዝቶ አዋቂ ሰው ጠፋ
መቆሙን ሳያውቅ ለመጣል ሚጋፋ
ነግ በእኔም እረስቶ ይጠብቃል ወረፋ
የዘራነው እንደማይበቅል መስሎን ስንከፋ
እርሻችን በአረም ተይዞ በሙላት ተስፋፋ
አወይ አለማስተዋል አጭር ብቻ ማየት
በፈገግታ ተሸውዶ በሀዘን መሰቃየት
በል በል ያለ ሁሉ ከአጠገብ እንደማይገኝ
በሽንገላ ከንፈር ተታለን ዛሬም የምንሞኝ
የዛሬን ደስታ ብቻ ተመልክተን ነገን በጭለማ
በድንግዝግዝ እየዘራን እንክርዳድ ምናለማ
አወይ ሰው አርሶ ዘርቶ ፆም ማሳደር
የላሟ እርግዝና ሲጠበቅባት ጊደር
በእንጭጩ ቀጭተው አስቀሩባት
ወተቷን እየወሰዱ ጥጃዋን ነፈጓት
የማይሞላ ጎተራ በአደባባይ ተሸክመው
ማስገባት እንጂ ማስወጣት የማያውቀው
ብል እና ነቀ…
Signed ይወደኛል ጌታ ይወደኛል
26 Dec 2023, 14:43 UTC416 viewsread 10 August 2026 😱😱😱ዛሬም ያው ነው😱😱😱
ሰው ትንሽ ቆይቶ ሲመለስ
ስለሄደበት ጆሮ ለመዳበስ
ዛሬም ያው ነው አልተለወጠም ይላል
የርሱ ለውጥ ለራሱ ታይቶት ይገረማል
እራሱን ልዩ አድርጎ ሌላው እንደነበረ
ስለ ትላንት ያወራል ዛሬን እያመሳከረ
በራሱ ዕውቀት በራሱ ዕይታ
ታውሮ ሲንቀሳቀስ በድንፋታ
ዛሬም ያው ነው እያለ ዘመኑን ይፈጃል
በራሱ ዓለም እየናኘ ዛሬን ይሸውዳል
አድማጭ ለሌለው ራሱን ያደክማል
ግን አንድ አለ ዛሬም ያው የሆነ
ሁሌ ጊዜ አዲስ ግን ያው የሆነ
ሁሉን እየለወጠ እርሱ ግን ያልተለወጠ
ዘመን የማያስረጀው ስንፍና የማያውቀው
ለወዳጁም ለጠላቱም እኩል ፍቅር ያለው
እርሱ የሚወደኝ እግዚአብሔር ነው
ትላንትናም ዛሬም ዘላለም ያው የሚሆነው
እርሱ የኔ ውድ ነው ሁኔ…
Signed ይወደኛል ጌታ ይወደኛል
20 Dec 2023, 07:22 UTC396 viewsread 10 August 2026 😱😱😱እኮ እኔ ማነኝ😱😱😱
እርሱ እኔን ብሎ ከሰማይ መጣልኝ
እኔ ለእኔ ብዬ እርሱን ተጠጋሁኝ
አሁን እኔ እራስ ወዳድ ነው ምባለው?
ወይስ ከጠቢባን ተርታ ነው የምሰለፈው?
ሰው ሰውን ለጥቅሙ ሲጠጋው
ጥቅመኛ ይሉታል
ሰው አምላኩን ለጥቅሙ ሲጠጋውስ
ምን ይሉታል?
ግን ምንም ይበሉኝ ምንም
እኔ ግን ከርሱ ፊት አልሸሽም
እርሱ ወድኃለው ብሎ ከቀረበኝ
እኔ ተወደድኩ ብዬ የምል አሻፈረኝ
እኮ እኔ ማነኝ?
እኮ እኔ ማነኝ እና የማን ብቃይ
እንዳልተቀበ ሰው ራሴን ማሳይ
ለሰው ይሉኝታ ስጦታዬን ምደብቅ
ሰጪውን ገፍቼ ተቀባዩን የማደምቅ
እኮ እኔ ማን ነኝ?
እኮ እኔ ማን ነኝና ነው ሚ…
Signed ይወደኛል ጌታ ይወደኛል
28 Nov 2023, 08:43 UTC402 viewsread 10 August 2026 ❤️❤️የሻገተ ነገር❤️❤️
መሰንበት ጥሩ መጥፎም ጎን አለው
አስተውሎ ማድረግ ግን ብልሀት ነው
አንዳንድ ነገሮች የማይመለሱ አሉ
ጊዜ እና ዕድልን ይዘው የሚዋልሉ
ማረፊያ ፈልገው ማረፊያ ካልሰጠናቸው
መውጣት ፈልገው እኛ ጋር ካቆየናቸው
እመኑኝ ነጋችን መራር እና ብኩን ይሆናል
የሻገተ ነገር መች በጤና ያስቀምጣል
በልባችን የሰነቅነው ምንድን ነው?
ተበላሽቶ እኛን የሚያበላሽ ነው?
ወይስ ቆይቶ እኛን የሚያራምድ ነው?
በልቤ ውስጥ ብዙ ብዙ ነገር አለ
ነገሮች እንዳላከናውን እኔን የከለለ
እንዳላወጣው ፍርሀት እና ውጤቱ አስፈርቶኝ
እንዳላቆየው ውስጤን ቦጥብጦ ቀፎ እያደረገኝ
አማራጭ እንደሌለው ሰው በዝምታ እጓዛለው
የመጣ ሁሉ ቁስሌን አያደማው ሲሄድ እያየው
…
Signed ይወደኛል ጌታ ይወደኛል
24 Nov 2023, 20:53 UTC394 viewsread 10 August 2026 🤫🤫ሊነጋ ነው መሰለኝ🙀🙀
ነገሮች ተደራርበው ~ ደረጃ ሰርተዋል
ሊጥሉኝ ይሁን ሊያነሱኝ ~ ተሰልፈዋል
እኔም በግርምት ~ እያየዋቸው ነው
የውስጤን ተስፋ ~ ሰውሬ ከፊታቸው
ልቤ እንደ ምላሴ አይደለም ~ ሞኝ ነው
በቤቱ እንደ እንግዳ ነው ~ የሚሆነው
ለዚህ ነው እንደ ዕንቁ ~ የሰወርኩት
እራሴን በእራሴ ውስጥ ~ የረሳሁት
አሁን ግን ~ ሊነጋ ነው መሰለኝ
ጭለማው በርትቷል ~ እየታገለኝ
የዶሮዎቹ ጩኸት ~ የወፎቹ ዜማ
በአንድነት ተቀናብሮ ~ ልቤን ሊያደማ
ምን ይሻልሃል ሲለኝ ~ ጩኸቱን እያሰማ
ተስፋ እንደሌላቸው ~ ተስፋዬን ሊቀማ
ሞኝ ነው ሞኝ ነው ~ እኔን ተስፋ ማድረጉ
እኔ እንደሆነ ~ አንዴ ተጠርቻለው ለሰርጉ
ሞኝ ነው ~ ሞኞችን ወደ እኔ መላኩ
የጥ…
Signed ይወደኛል ጌታ ይወደኛል
7 Nov 2023, 08:49 UTC362 viewsread 10 August 2026 ቆይ ምን መሆንህ ነው~ ሰው ይለኛል
ምን እንደሆንኩ~ እኔም ግራ ይገባኛል
ነገር ግን እኔ እኔ ማለት~ ብዙ ባልወድም
ተወዛግቤ ማወዛገቤን ግን~ አልክድም
መወዛገብ የፈለገ~ ካለ ማለቴ ነው
ያለ ክፍያ ነው~ በነፃ የምሰጠው
ግን እኔ ምን ሆኛለው
እስቲ ራሴን ልገምግመው
ሀሳብ አስተያየት መስጠት~ አይቻልም
ውጦ ማስቀረትም ደሞ~ አይፈቀድም
ምን እንደምታደርጉት~ እኔም ባላውቅም
ከክፋት ደግነትማ~ ሳይሻል አይቀርም
ብቻ ከንፈራችሁን~ መምጠጥ ባይፈቅድም
ባህል ስላደረግነው~ ማፍረስን ግን አልሻም
ወደ ትወናዬ ዓለም~ ልግባና
ምፀቴን ላስቀምጥ~ እንደገና
ከፊት ስሆን~ ስረዓት ይጎትተኛል
ከኋላ ስሆን~ ለዘብተኛ ይጋርደኛል
ከመሀል እንዳልሆን~ አመነታለው
መሀል ሰፋሪ…
Signed ይወደኛል ጌታ ይወደኛል
26 Jul 2023, 14:54 UTC356 viewsread 10 August 2026 Akiya
ከአምናው የዘንድሮው
ይለይብኛል የእኔ ኑሮው
ውጫዊ ባልሆነ እርካታ
መረበሽ በሌለበት ፀጥታ
በኢየሱስ ያገኘሁት ሰላም
አይወዳደርም ከዚህ ከዓለም
👇👇
ሰላሜ
Azuza
እኮ ሰላምህ
Akiya
ከውስጥ ወደ ውጭ ፈሶ የሚታየው
በሁኔታዎች መለዋወጥ የማይቀያየረው
በእኔ ድካም በእኔ ጥረት ከቶ ያላገኘሁት
በገንዘብ በአጀብታ የማይገኝ በስሜት
Azuza
ታድያ መገኛው የት ነው
Akiya
ቦታው አለቃው ጋር ነው
Azuza
የምን አለቃ
Akiya
የሰላሙ አለቃ
Azuza
ማነው ይሄ የሰላም አለቃ
Akiya
ኢየሱስ ነው ለሁሉም ሚበቃ
👇👇
ላመኑበት ህይወት እና ሰላም የሚሰጥ
የቀረቡትን ከጀርባ ሆኖ የማይቀጠቅጥ
ኢየሱስ እርሱ ክርስ…
Signed ይወደኛል ጌታ ይወደኛል
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @artmkc. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.