24 May 2026, 02:56 UTC102 viewsread 31 August 2026 4. አሁን ካለንበት እንነሳ
ሁኔታዎች እንዳልነበሩ ሲሆኑ በፊት የነበርንበት እያሰብን ያንንው የሕይወት ዘይቤ ለማምጣት ከመታገል መቆጠብ አስፈለጊ ነው፡፡ በወቅቱ ለውጥ ምክንያት አሁን ካለንበት ደረጃ ለመነሳት በፍጹም አንፍራ፣ አንፈርም፡፡ አሁን ካለንበት በመነሳት የምንችለውን ብቻ ስናደርግ ሁሉም ነገር ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል፡፡
5. ከብዙ ሰው ሃሳብን ከመስማት እንቆጠብ
ነገሮች ሳናስበው ሲለዋወጡና ስሜታችን ሲናወጥ የሰዎችን ሃሳብ መስማትና ወገን ማግኘት ያምረናል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ለተለያዩ ሰዎች አሳብ አጋልጦ ሊሰጠን ይችላል፡፡ ስለሆነም፣ ስሜታችን እስሚረጋጋ ድረስ የምናማክረውን ሰው ለይተን እንወቅ፣ የምንቀበላቸውንም ሃሳቦች አመዛዝነን እንውሰድ፡…
Signed An - war (ananas) 🇲🇱
24 May 2026, 02:55 UTC96 viewsread 31 August 2026 Photo
ከዜሮ መጀመር የግድ ሲሆን!
አንዳንድ ጊዜ ለረጅም ጊዜ የገነባነው ነገር ይፈራርሳል፡፡
አንዳንድ ጊዜ የወደፊት ሕይወታችንን አብረን ለማሳለፍ ያቀድነው ሰው በድንገት ይለየናል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ለረጅም ጊዜ ያቀድነው ዓላማ እንደማይሰራ እየገባን ይመጣል፡፡
እነዚህና መሰል ሁኔታዎች ሲገጥሙን “ከዜሮ” የመጀመርን አቅምና ጥበብ ማዳበር የግድ ነው፣ ይቻላልም!
ጥቂት መመሪያዎች!
1. የሆነብንን ሁኔታ ሳንክድ እውነታውን እንቀበል
እውነታውን መቀበል ማለት ሁኔታው እንደተከሰተ ወዲያውኑ ከመፍጨርጨርና እንዳልተከሰተ ለማሰብ ከመታገል ይልቅ የሆነውን አምኖ መቀበል ማለት ነው፡፡ የሆነው ሆኗል! ያለፈው አልፏል ያጣነውን አጥተነዋል! ይህንን እውነታ ስንቀበል አእም…
Signed An - war (ananas) 🇲🇱
13 Apr 2026, 14:20 UTC118 views6 reactionsread 31 August 2026 Photo
ሳነብ ካገኘሁት
➸➸➸➸➸
የወንድ (የሰዎችን) ሕይወት በቀስታ የሚያፈርሱ 20 ነገሮች
20 THINGS THAT QUIETLY RUIN A MAN’S LIFE:/:
➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸➸
1.Laziness ➸ ስንፍና
2.Gambling ➸ ቁማር
3.Bad friends ➸መጥፎ ጓደኞች
4.Ignoring health ➸ጤናን መተው
5.Procrastination ➸ስራን ማዘግየት
6.Fear of failure ➸ውድቀትን መፍራት
7.Victim mindset ➸የተጎጂ አስተሳሰብ
8.Porn addiction ➸ የፖርኖ (ወሲብ)ሱስ
9.No clear goals ➸ ግልፅ ግብ አለመኖር
10.Lack of self respect ➸ራስን አለማክበር
11.Constant complaining ➸…
👍5❤1
Signed An - war (ananas) 🇲🇱
13 Apr 2026, 13:47 UTC100 views2 reactionsread 31 August 2026 Photo
አቡበክር እንድሪስ በአንድ ወቅት በወሎ ዩኒቨርስቲ የህግ ተማሪ የነበረ አንድ ፀሀፊ ልጅ ይነጋል (ከጨለማ ወዴ ብርሃን/softly - bright 2012 ዓ.ም)
በሚል ርዕስ በፃፈው መፃሀፋ ላይ የሚከተሉትን ቃላቶች በዚህ መንገድ ተርጎሟቸዋል። እናተስ ምን ያህል ተስማማችሁ ? እነሆ ላጋራችሁ።
➸ዋዛ ፈዘዛ : አቅም የሌላቸው ዱላ ነው
➸ሐሜት : ያለመሳሪያ ሰው መግደል ነው
➸ብስጭት : ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነው
➸ማጉረምረም : ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው
➸ቁጣ : ከስድብ የማያንስ የክፋ አድራጎት መሰረት ነው
➸ችኮላ : የትእግስት ጠላት የፀፀት አባል !! ልጁም ወኔ ነው
➸ውሸት : እውነተኛ ሰው በስውሩ የሚጎዳበት ረቂቅ ጠር ነው
➸መን…
❤1👍1
Signed An - war (ananas) 🇲🇱
28 Feb 2026, 10:56 UTC160 views1 reactionsread 31 August 2026 Photo
🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍
"የተበላሸውን እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል የሚናገሩትን ሰዎች አዳምጡ እንጂ ሰዎችን በችግሮች ላይ ቂም እንዲይዙ የሚያደርጉትን አይደለም።
ሌሎችን ብቻ የሚወቅሱትንሳይሆን ነገሮችን እንዴት መስተካከል እንዳለበት ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች ያዳምጡ።"
~ ሞሊ ኢቪንስ
🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍
👍1
Signed An - war (ananas) 🇲🇱
28 Feb 2026, 10:46 UTC133 viewsread 31 August 2026 Photo
🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍
ብዙ በአላህ እገዛ የታለፉ ከባድ ቀናት ወደፊት ለምታጣጥመዉጥዑም ጊዜ የተከፈሉ ቀብዶች ናቸዉ ።
ቀብድ የከፈልክበት ሰላምህ እስኪመጣ ዝም ብለህ ፈገግ በል !
🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍🍍
Signed An - war (ananas) 🇲🇱
24 Feb 2026, 10:30 UTC149 views3 reactionsread 31 August 2026 Photo
ወይ እንዳልታገል ከእልፍ ተጣብቄ
ከመጣ ከሄደው እንዳላልፍ ስቄ
ወይ አልሰበሰብ አልተው እንደ ዋዛ
ወይ ምኞቴ አይበርድ ወይ ልቤ አይገዛ
ወይ እንዳልዘረጋ አልያ እንዳላጥፍ
የእጣ ፋንታን ነገር እጅ መጥፎ እንዳይጥፍ
ወይ እንዳልቀመጥ ወይ እንዳልረመድ
ሆና አስቸገረችኝ ህይወት መንታ መንገድ ።
ቢሆንም ግን ! አልሃምዱሊላህ
🟡🟢🔴🍍አንዋር ይመር (አናናስ)🟡🟢🔴
❤2👏1
Signed An - war (ananas) 🇲🇱
24 Feb 2026, 10:28 UTC127 viewsread 31 August 2026 Photo
አንዬ ሆይ !
አንተ ራሴ የምወድህ
እስኪ ዛሬም ላስቸግርህ
ሰው እንደሆን :
ዝም ያልክ እንደሁ ሞኝ ይልሃል
ዝቅ ስትል ይረግጠሀል
ቢሆንም ግን አንየ ሆይ!
እንደ መሬት ሁሉን ቻለው
አንዳንደዬ መሸነፍም ማሸነፍ ነው ።
"አንዳንድ ሰው ቤት እየሰራህለት ሚስማር ይነፍግሃል ።" አይገርምም !
🟢🟡🔴✒️ አንዋር ይመር (አናናስ)🟢🟡🔴
Signed An - war (ananas) 🇲🇱
24 Feb 2026, 10:25 UTC120 viewsread 31 August 2026 Photo
👆👆👆ከምስሉ በመነሳት
አዝመራው ሲደርስ እሸቱ ሲያአፈራ
ምድሩ ሰላም ሲሆን መስከረም ሲበራ
ከብርቱካን ፍሬ ከጣዝማ ወላላ
ናፍቆቴን ላስታግስ በብዙ ልበላ
ከሙላቱ ወራት ከፀደይ ደርሼ
ሙሉአለም ሆናልኝ ተስፋዬን ለብሼ
ሲሳይ ሲሰበሰብ በረከት ሲሰፋ
ምነው በነፃነት ብላ እሚል ሰው ጠፋ ?
just for enjoyment በሚለው።
💚💛❤✒️ አንዋር ይመር (አናናስ)💚💛❤
Signed An - war (ananas) 🇲🇱
22 Feb 2026, 05:46 UTC137 views6 reactionsread 31 August 2026 Photo
አልሃምዱሊላህ ! ያረብ ዛሬን እንድኖር የፈቀድክልኝ ጌታ ሶብር :ተቅዋ : ኢስቲቃማን አንተ ወፍቀኝ። ያኢላሂ ቀኔን አንተን የማስታውስበት ከወንጀል አንተን ፈርቼ የምሸሽበት ወደ አንተ በኸይር ነገር የምቃረብበት ቀን ታደርግልኝ ዘንድ እጠይቀዋለሁ። ያ ጀባር የተሰበረውን ልቤን ትጠግንልኝ ዘንድ : አይቶ ማለፍን ሰምቶ መቻልን አንተ ወፍቀኝ ውብ በሆኑ ስሞችህ እጠይቅሃለሁ ያ ከሪሙ : ያ ሀኪሙ ያሰብኩትን ሳይሆን ያሰብክልኝን የፈለኩትን ሳይሆን የሚያስፈልገኝን ትሰጠኝ ዘንድ ያንተው ባሪያ እለምንሃለሁ። አላህዬ በቃ በለኝ ከመከራ ከጭንቀት አውጣኝ ያ ቅዱሱ ሀገሬን ሰላም አርገህ ወገኔን ደስታውን ትመልስለት ዘንድ በታላቁ ሸህ ራመዳን ተማፀንኩህ 😭😭😭😭
💚💛❤አን…
❤6
Signed An - war (ananas) 🇲🇱
16 Oct 2025, 17:52 UTC246 viewsread 31 August 2026 Photo
" ህዝብ መገዛት : ገዥዎችም መግዛት ሲያቅታቸው ያኔ አብዮት ይመጣል::"
ሌኒን
Signed An - war (ananas)
16 Jul 2025, 21:55 UTC369 views8 reactionsread 31 August 2026 Photo
እስኪ ሃሳቤን አንድ አጥር ባለች የይስማዕከ ወርቁ ግጥም ልጀምር :
"የኔማ ጓደኛ ይሄው እስከ ዛሬ ፌቴ ተጓልቶ
አትችልም ይለኛል የሱን አለመቻል እኔ ውስጥ ከቶ"
ትላለለች።
የእናንተን ባላውቅም እኔ መስታወት ፊት ስቆም በአእምሮዬ የሚመጡት ሶስቱ ጓደኞቼ ናቸው። እንደት ካለችሁኝ:
በግማሽ የተሰበረ (ከቆሸሽ) መስታወት ፊት ስቆም ያ! አትችልም:ትችላለህ ፣አቅም አለህ ፣ አቅም የለህም ታምራለህ : አታምርም እያለ ባልጠራ እይታ ተወዛግቦ የሚወዛግብ ግማሽ እኔቴን የሚነግረኝ ጓደኛዬ ትዝ ይለኛል።
ሌላው የተጋነነ የመስታወት እይታ ፊት ስቆም የሌለ ማንነቴን እየነገ አብሮ ለመዝለቅ ብቻ ጉም የሚስጨብጠኛ ወዳጄ ይታወሰኛል።
ሶስተኛው እና የመጨረሻው ደግሞ ትክ…
❤5👍2👏1
Signed An - war (ananas)
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @anelube0932. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.