2 Jun 2025, 09:25 UTC117 views5 reactionsread 10 August 2026 Photo
አማራ ክልል ከጌጣጌጥ ማዕድን ሽያጭ 9 ሚሊዮን ዶላር አገኘ
| የአማራ ክልል ከጌጣጌጥ ማዕድን ምርት ወደ ውጪ በመላክ የ9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። ይህ ገቢ የተገኘው በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አስር ወራት ውስጥ ነው።
ክልሉ በዚሁ ወቅት 23,558 ኪሎ ግራም የጌጣጌጥ ማዕድናትን ያመረተ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 8,768 ኪሎ ግራም የሚሆነውን ወደ ውጭ በመላክ የተጠቀሰውን ገቢ አስገኝቷል። ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ44.5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
በተጨማሪም ክልሉ በዚሁ የአስር ወራት ጊዜ ውስጥ 75.9 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ በማስገባት፣ ካለፈው ዓመት ተመሳ…
❤5
1 Jun 2025, 11:41 UTC91 views1 reactionsread 10 August 2026 Photo
የፒኤስጂ ደጋፊዎች በፓሪስ ደስታቸውን ሲገልፁ 2 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ ከ500 በላይ ሰዎች ታስረዋል
**********
ፒኤስጂ ትናንት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ማሸነፉን ተከትሎ የክለቡ ደጋፊዎች በፈረንሳይ ዋና ከተማ በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ ደስታቸውን ሲገልጹ አምሽተዋል።
በዚሁ ወቅት በተነሳ ግርግር 2 ሰዎች ሞተው 192 ደግሞ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ ከ500 በላይ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
ይህ እንዳይመጣ ተፈርቶ ከ5 ሺህ 400 በላይ ፖሊሶች በደንብ ማስከበር ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበረ ቢሆንም፤ ደስታቸው ከቁጥጥር ውጪ የሆነባቸው ድጋፊዎች ግን በተለያዩ ቦታዎች እሳት አስነስተዋል።
በዚህም 200 ያህል መኪኖች እንደተቃጠሉ እንዲሁም የ…
❤1
1 Jun 2025, 11:14 UTC46 viewsread 10 August 2026 Photo
ቻይና በታይዋን እና በዩክሬን መካከል የሚደረገውን ንፅፅር እንደማትቀበለው አስታወቀች
**
ቻይና የታይዋንን ጉዳይ ከዩክሬን ጋር በማነጻጸር "ደብል ስታንዳርድ" በሚል የሚሰነዘሩ ትችቶችን አውግዛለች።
ይህ የሆነው የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑዌል ማክሮን ሩስያ "የዩክሬንን ግዛት እንድትወስድ መፍቀድ ቻይና በታይዋን ላይ የምታደርገውን ማበረታታት ነው" ካሉ በኋላ ነው።
በሲንጋፖር የሚገኘው የቻይና ኢምባሲ በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ፥ የታይዋንን ጉዳይ ከዩክሬን ጋር ማነጻጸር ተቀባይነት የለውም ብሏል።
የታይዋንን ጉዳይ ከዩክሬን ጋር አንድ ዓይነት አደለም፤ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ነው ብሏል ኤምባሲው ስማቸውን ሳይጠቅስ ከማክሮን ፎቶ ጋር አያይዞ ባሰፈረው ጽሑ…
1 Jun 2025, 11:12 UTC41 views1 reactionsread 10 August 2026 Photo
ኢትዮጵያ ቡና የ100 ሺህ ብር ቅጣት ተጣለበት
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጰያ ፕሪሚየር ሊግ 32ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ባጠፉት ጥፋት ክለቡ የ100 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበታል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ያደረገውን የ32ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ያለምንም ግብ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
በጨዋታው ወቅት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትን፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበርን እና የኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝን በስም በመጥራት አፀያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦ…
❤1
1 Jun 2025, 11:05 UTC27 views1 reactionsread 10 August 2026 Photo
በካናዳ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት
| በካናዳ ማኒቶባ ክፍለ ሃገር የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በፍጥነት በመዛመት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
የህይወት አድን ሰራተኞች የጦር አውሮፕላኖችን እና ሄሊኮፕተሮች በመጠቀም ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማሸሽ ላይ ይገኛሉ።
በምዕራብ ካናዳ ሳስካችዋን እና ማኒቶባ አካባቢዎች እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መኖሪያቸውን ለቅቀው እንዲወጡ መደረጉም ታውቋል።
በአካባቢዎቹ ለአንድ ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን የአካባቢው ባለስልጣናትም ተጨማሪ የእሳት አጥፊ ባለሙያዎች ላኩልን ጥሪ ለዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ ማስተላለፉቸው ተነግሯል።
በአካባቢዎቹ በቀጣይ ቀናት ደረቅ እና ሞቃታማ የዓየር ንብረት እንደሚኖር መተንበዩን…
❤1
1 Jun 2025, 11:01 UTC24 viewsread 10 August 2026 Photo
ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ሁለት ወራት 74 ዓለም አቀፍ ጉባዔዎችን ታስተናግዳለች
| በኢትዮጵያ በመጪዎቹ ሰኔና ሐምሌ ሁለት ወራት ብቻ 74 ዓለም አቀፍ ጉባኤ እንደሚካሄድ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ይግዛው ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ በኢትዮጵያ በመጪዎቹ ሰኔ እና ሐምሌ ወራት 74 ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች እና ሁነቶች እንደሚካሄዱ ይጠበቃል።
በሰኔ ወር 31 በሐምሌ ወር ደግም 43 ዓለም አቀፍ ጉባዔ እና ሁነቶች ይካሄዳሉ ብለው፤ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ በአምቦ፣ በደሴ እና በደብረ ታቦር የሚካሄዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከዓለም አቀፍ ጉባዔዎችና ሁነቶቹ መካከል…
1 Jun 2025, 10:59 UTC21 viewsread 10 August 2026 Photo
ድርቤ ወልተጂ አሸነፈች
በግራንድ ስላም ትራክ ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ አሸንፋለች።
በአሜሪካ ፊላደልፊያ በተደረገው የ1500 ሜትር አጭር ርቀት አትሌቷ በበላይነት አጠናቃለች።
3 ደቂቃ 58.04 ሰከንድ አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰአት ነው።
የኪንግስተን ሻምፒዮኗ ድርቤ ወልተጂ በ12 ነጥብ እየመራችም ትገኛለች።
በዚህ አመት የተጀመረው አዲስ ውድድር ቀደም ብሎ በኪንግስተን እና ማያሚ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ሌሊት ላይ በ3ኛዋ ከተማ ፊላደልፊያ ተደርጏል።
በ3 ሺህ ሜትር ረጅም ርቀት ደግሞ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 2ኛ ወጥታለች።
መዲና ኢሳ 6ኛ ስትወጣ ጽጌ ገብረሰላማ 8ኛ ደረጃን በማግኝት አጠናቃለች።
በአንተነህ ሲሳይ
ወቅታዊና ትክ…
1 Jun 2025, 10:51 UTC21 viewsread 10 August 2026 Photo
ሶማልያ ሆይ ራስሽን ቻይ
| የአሜሪካው ጄኔራል ሱማሊያ የራሷን ፀጥታ ለማስከበር ሀላፊነቱን እንድትወስድ አሳሰቡ፡፡ የአሜሪካ የአፍሪካ እዝ(አፍሪኮም) ዋና አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ማይክል ላንግሊ እንደገለፁት አሜሪካ ከዚህ ቀደም ቀጠናውን ለማረጋጋት ትሰጠው የነበረውን እርዳታ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሳለች፡፡
በመሆኑም ሱማሊያን ጨምሮ በቀጠናው ያሉት አገራት ሰላምና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ሀላፊነቱን መውሰድ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ጄኔራሉ በናይሮቢ በሰጡት መግለጫ ሲናገሩ ‹‹እኛ ከዚህ ቀደም እናቀርበው የነበረው ድጋፍ ከዚህ በኋላ ላይኖር ይችላል፡፡ በመሆኑም የአፍሪካ ቀንድ አገራት ራሳቸውን በማጠናከር ሀላፊነቱን ለመውሰድ እንዲዘጋጁ እንጠይቃለን›› ብለዋል፡፡…
1 Jun 2025, 10:48 UTC20 viewsread 10 August 2026 Photo
በላይነህ ክንዴ ግሩ (BKG)
| በላይነህ ክንዴ ፊበላ ኢንዱስትሪያል የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት አገልግሎት እድገትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፉ ላይ ጉልህ ሚና እየተወጣ ይገኛል። ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል።
በደብረ ብርሃን ከተማና ገላን ከተሞች በሚገኙ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መካከለኛና ከፍተኛ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ለገበያ አቅርቧል። እያቀረበም ይገኛል።
ቢኬጂ የኢትዮጵያን ትራንስፖርት ችግር ማቃለል ባሻገር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ እሴት እየጨመረ ያለ ግሩፕ ነው።
በተለይም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማምረት የአካባቢ አየር ብክለትን ከመከላከል በተጨማሪ በከፍተኛ የውጭ…
1 Jun 2025, 06:29 UTC≈1,180 viewsread 10 August 2026 Photo
ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ14 ሀገራት ላይ የቪዛ እገዳ ጣለች
| ሳውዲ አረቢያ በድምሩ በ14 ሀገራት ዜጎች ላይ የብሎክ ቪዛ ማውጣትን በጊዜያዊነት ማገዷን አስታውቃለች። ከነዚህ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰባት የአፍሪካ ሀገራት ይገኙበታል።
ይህ የቪዛ እገዳ አዲስ የጊዜያዊ የሥራ ቪዛ ማመልከቻዎችን እና በመጠባበቅ ላይ ያሉትንም የሚመለከት ነው የተባለ ሲሆን በውጭ ዜጎች የሥራ ኃይል ላይ የተመሰረቱ የሳውዲ አረቢያ ዘርፎችን እንደሚጎዳ ተገልጿል።
በእገዳው ሰለባ ሆነዋል ከተባሉት የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ አልጄሪያ፣ ሱዳን፣ ቱኒዚያ እና ሞሮኮ ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪ ኢንዶኔዥያ፣ ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ፣ የመን፣ …
1 Jun 2025, 06:22 UTC57 viewsread 10 August 2026 Photo
🇳🇬 የሟቾች ቁጥር 151 ደርሷል
| በናይጄሪያ የደረሰው የጎርፍ አደጋ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን የሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር (SEMA) አስታውቋል።
ጎርፉ 380 ኪሎሜትር መሸፋኑን የገለፀው አስተዳደሩ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የማፈላለግ ስራው ቀጥሏል ብሏል።
በዚህ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ከ3000 የሚበልጡ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገልጿል።
በተመሳሳይ መልኩ 500 የሚደርሱ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተወስደዋል ተብሏል።
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት
👇👇SUBSCRIBE SHARE👇👇
https://t.me/ahadunewsmereja
https://www.facebook.com/share/1BpPiwbJUH/?mibextid=wwXIfr
1 Jun 2025, 06:09 UTC18 viewsread 10 August 2026 Photo
የፍየል ወተት : የመቀንጨር ችግርን ለመቀነስ
| በኢትዮጵያ የህጻናት መቀንጨርን ለመቀነስ እና ለመከላከል የፍየል ወተት ጠቃሚ ቢሆንም በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ካለመኖራቸውም በተጨማሪ በመቀንጨር ለተጠቁ አከባቢዎች የፍየል ድጋፍ ከማድረግ ውጪ ዘርፉን ለማሳደግ ክፍተት እንዳለበት የግብርና ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
የሰቆጣ ዴክላሬሽን ላይ በመቀንጨር የተጠቁ አካባቢዎች ለፍየል ተስማሚ በመሆኑ ብሎም የፍየል ወተት የመቀንጨር ችግር እንዲቀንስ ማድረጉ በጥናት በመለየቱ የፍየል ድጋፍ ለተጠቂዎች መደረጉን በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ፣አሳ እና የወተት ሃብት ክትትል ባለሙያ አቶ ሰኚ በዳሳ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የፍየል ወተት ለጤና ጠቃሚ የሆኑ …
Showing the 12 most recent of 13 posts we hold for @ahadunewsmereja. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.