26 Jun 2023, 17:22 UTC533 viewsread 6 August 2026 [ዙል-ሒጃ 9](የዉሙ ዐረፈሕ)
=============================
👉ነገ ማክሰኞ ዙል-ሂጃ 9 ነው.ይህንን ቀን የፆመ ሰው ያለፈዉንና መጪውን አመት ወንጀል ይሰርዝለታል።ስለዚህ በነገው ለት ሁሉም ይህንን ቀን በፆም፣በኢባዳ፣ ዱአ በማድረግ ማሳለፍ አለበት። ይህን ይፆሙ ዘንድ ለቤተሰብ፣ለጓደኛ ፣ለጎረቤት ያስታውሱ።
https://t.me/adlejema
Signed Abdlwehab Bahiru
26 Jun 2023, 01:56 UTC485 viewsread 6 August 2026 ☑️ በሁሉም ነገርህ ከሶሀባዎች ጋር ተመሳሰል !!
قـال شيخ الإسلام ابن تيميـة رحمــه الله تعالــﮯ
🔎 ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።
◐ ﻣﺸﺎﺑﻬﺔ ﺍﻟﺼﺤﺎﺑﺔ ﻭﺍﻟﺘﺎﺑﻌﻴﻦ ﺗﺰﻳﺪ ﺍﻟﻌﻘﻞ ﻭﺍﻟﺪﻳﻦ ﻭﺍﻟﺨﻠﻖ
▪️ ከሶሀባዎችና ተከታዮቻቸው ጋር መመሳሰል፦
▪️አቅልን
▪️ዲንና
▪️ስነምግባርን እንዲጨምር ያደርጋል።
📚 [ﺍﻗﺘﻀﺎﺀ ﺍﻟﺼﺮﺍﻁ ﺍﻟﻤﺴﺘﻘﻴﻢ (527/1)]
➙ለዚህም ነው ጠዋትና ማታ ሁሌም የሰለፎች (የሶሀባዎችና እነሱን በመልካም የተከተሉት አኢማዎች) መንገድ አጥብቀን እንያዝ የምንለው።
https://t.me/adlejema
Signed Abdlwehab Bahiru
16 Jun 2023, 16:35 UTC351 viewsread 6 August 2026 ቁርአንን ቢያስተነትኑት
#أفلا يتدبرون القرءان
وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ ۚ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا
በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል፡፡
(ቁርአን 65:3)
https://t.me/adlejema
Signed Abdlwehab Bahiru
16 Jun 2023, 08:12 UTC294 viewsread 6 August 2026 ጀነት ለመግባት ሰበቦቹ!
=================
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿يا أيُّها الناسُ ! أفْشُوا السلامَ، و أطْعِمُوا الطعامَ، وصِلُوا الأرحامَ، وصَلُّوا بالليلِ والناسُ نِيامٌ، تَدْخُلوا الجنةَ بسَلامٍ.﴾
“እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አብዙ፣ የተራበን አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች ሲተኙ በሌሊት ስገዱ፣ ጀነትን በሰላም ትገባላችሁ፡፡”
📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 2648
https://t.me/adlejema
Signed Abdlwehab Bahiru
11 Jun 2023, 16:58 UTC269 viewsread 6 August 2026 ሊያወሩላቸው የሚደክሙ፣ ሊገልጿቸው የማይቻሉ ንፁህ ልቦች
ስላኸው ነገር ሁሉ ማዉራት መጠቋቆም አይጠበቅብህም
በዩንቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የህክምና አስተማሪ ነው። ከእጁ የማትለይ፣ ሲበዛ የሚወዳት ሰዓት አለችው። መልኳም ሆነ ይዘቷ የሴት ነው። ሊያስተምር እጁን ሲያወራጭ ተማሪዎች ይጠቋቆሙበታል። ከዕለታት በአንዱ ቀን ታዲያ በአደጋ ምክንያት የተለየችው የልጁ ሰዓት መሆኑን ከጓደኛው አንደበት ሰሙ። ለእሷ ካለው የገዘፈ ውዴታ የተነሳ ሰዓቷን ከእጁ ሊያወልቃት አልተቻለውም።
https://t.me/adlejema
Signed Abdlwehab Bahiru
9 Jun 2023, 15:38 UTC273 viewsread 6 August 2026 🌹የመልካም ሴት ፀባይ መገለጫ🌹
قَالَ رَسُول الله ﷺ
(( أَلَا أُخْبِرُكُمْ بنسائِكم مِنْ أهلِ الجنةِ ؟
الودودُ الولودُ ، العؤودُ ؛ التي إذا ظُلِمَتْ قالت : هذه يدي في يدِكَ ، لا أذوقُ غُمْضًا حتى تَرْضَى ))
➧ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ አሉ፦
➧ከሴቶቻችሁ መካከል ጀነት ገቢዋን ልንገራችሁ?
➧ባሏን የምትወድ፣የምትወልድና ባሏ ሲቀየማት ከማኩረፍና ጀርባ ከመስጠት ይልቅ ወደ ባሏ የምትቀርብና ቅያሜያቸው እስካልተወገደና በመሀከላቸው ፍቅር እስካልነገሰ ድረስ አንዲት ጉርሻ እንኳን ብትሆን ምግብ ሚባል አልመገብም ብላ የቅያሜን ድባብ ወደ ፍቅር የምት…
9 Jun 2023, 15:28 UTC247 viewsread 6 August 2026 ማስታወሻዎች
•ደጋግ ቀደምቶቻችን« በአንድ ነገር ላይ አብዝቶ የተጣበቀ ያ ነገር መቀጫው ይሆናል» ይሉ ነበር ....ከሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት መኋከለኛ ሁን ብዙም አትቅረብ ብዙም አትራቅ ርቀህ እንዳትረሳ ቀርበህ ደግሞ እንዳትጣል ..ከብደህ እንዳይሸሹህ ቀለህ ደግሞ እንዳይንቁህ መኋከለኛ ሁን....
•ነቢ ሙሳ የተውራትን መልእክት አስወርውሮ ያበገነ ንዴትን አስተናግደዋል. ...ነቢዩላህ ያዕቁብ ዓይናቸውን በእንባ አጥፍቶ የብቸኝነት ቤትን ያስገነባ ሃያል ናፍቆትን አስተናግደዋል ..የኛው ወድ ነብይ (ሰ ዐ ወ) ልጃቸው ኢብራሂም ሲሞት ስቅስቅ ብለው አልቅሰዋል ...ባለቤታቸው/በዙሪያቸው ያሉ ውድ ወዳጆቻቸውን ያጡበት አመት "የሀዘን አመት " ተብሎ ነው የ…
12 Nov 2022, 07:01 UTC380 viewsread 6 August 2026 🚫:::::::::::አስተውል::::::::::🚫
📌ቆንጆ ሴት ብታገባ ቆንጆ ልጆችን ታገኝ ይሆናል ውበት ጀነት አያስገባም እወቅ በተርቢያ በዲን ግንዛቤ የተገነቡ ልጆች ግን አደብ ባላትና #ዲን ባላት ሴት እንጅ ላታገኝ ትችላለህ ሞዴል አግብተህ ሞዴል እንዳትወልድልህ !!
💍=====የትዳር ትልቁ አላማ ራስህን ወደ አላህ የሚያቃርብ አጋዥ ማግኘት ነው።
ዐልይ ረ ዐ እና ፋጢማ ረ ዐ _በተጋቡ ማግስት የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلم ወደ ቤታቸው በመሄድ ዐልይን ባለቤትህን እንደት አገኘሀት ?
ሲሉ ጠየቁት እርሱም አላህን_ ለመገዛት ጥሩ ረዳት ሆና አገ…
10 Nov 2022, 08:14 UTC327 viewsread 6 August 2026 Photo
ሪዝቅህን በምትፈልግበት ሀላል ስራ ላይ ልብሴ ይቆሽሻል ብለህ አትጨነቅ፤ እፍረትም አይሰማህ ፤ ዝንጥ ያሉ ልብሶችን ለብሰህ የሰዎችን እጅ ከማየት እጅግ በብዙ እጥፍ የተሻለ ነውና!
የሙስጠፋን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ምክር አንብብ👇
أَنَّ النَّبِيَّ ﷺ سُئِلَ: أَيُّ الْكَسْبِ أَطْيَبُ؟ قَالَ: عَمَلُ الرَّجُلِ بِيَدِهِ، وكُلُّ بَيْعٍ مَبْرُورٍ.
رَوَاهُ الْبَزَّارُ، وصَحَّحَهُ الْحَاكِمُ
"ከስራዎች የቱ ነው ጥሩ ስራ?" ተብለው ተጠየቁ
"ሰውየው በእጁ ሰርቶ የሚያገኘው እንዲሁም ንፁህ(ሀራም ያልሆነ ግብይት"
ብለው መለሱ÷ሰለዋቱላሂ ወሰላሙሁ አለይሂ ወሰለም
https…
7 Nov 2022, 15:48 UTC297 viewsread 6 August 2026 Photo
ጥበቡ በፍጥረተ-ዓለሙ ውስጥ እንዲህ ይገለጣል። ውበታቸው ልብን ማርኮ በሚያንበረክክ ፍጹም ድንቅ ፍጥረታት ተከበን እንዴት አላህን እንረሳለን?!
"هَٰذَا خَلْقُ اللَّهِ فَأَرُونِي مَاذَا خَلَقَ الَّذِينَ مِن دُونِهِ ۚ بَلِ الظَّالِمُونَ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ" لقمان
"ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ፡፡ በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው" (ሉቅማን፡ 11)
https://t.me/adlejema
31 Oct 2022, 06:46 UTC358 viewsread 6 August 2026 ❝ በአሁኑ ወቅት በጂንን መለከፍ የበዛበት ዋነኛ ምክንያቱ ዚክር በሚያስፈልግባቸው ቦታዎች ሁሉ ዚክር ከማድረግ የመዘናጋት ውጤት ነው ❞
~ኢብኑ ኡሰይሚን~
[የሰሂህ ሙስሊም የግርጌ ማስታወሻ:2/296]
❝ ዝንጉና ረሺ ሰዎችን ሸይጣን እንደ ሚዘርረው ሁሉ በአንፃሩ አንድ ሰው ሸይጣንን በዚክር መዘረር ይችላል❞
~ኢብኑል ቀይም~
[መዳሪጅ አስሳሊኪን:2/396]
#ዚክር #የሙስሊም_ጋሻ
https://t.me/adlejema
💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁
5 Aug 2022, 03:44 UTC530 viewsread 6 August 2026 አንድ ጎረምሳ ባለትዳር እንዲህ አለ
"ሴት ልጅ እንደ ጫማ ናት ሰውየው ለርሱ የምትሆነውን ባገኘ ቁጥር ሊቀያይራት ይችላል።"
ይህንን የታዘቡ ሰዎች በአቅራቢያቸው ወደ ነበር ጥበበኛ ሰው ሄዱና ስለዚህ ሰው ምን ትላለህ? ሲሉ ጠየቁት።
ጥበበኛውም ሰው ይህ ሰው የተናገረው ትክክል ነው።
ሴት ልጅ እራሱን እንደ እግር ለሚያይ ወንድ ጫማ ናት። እራሱን እንደ ንጉስ ለሚመለከት ሰው ግን (የንግስና) ዘውዱ ናት።
ሰውየውን አትውቀሱ እራሱን የት ቦታ ላይ እንዳስቀመጠ ግን ታዘቡ አሉ።
ይሄው ነው!
https://t.me/adlejema
Showing the 12 most recent of 16 posts we hold for @adlejema. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.