13 Apr 2026, 20:58 UTC99 views2 reactionsread 8 August 2026 👉 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ
⚡⚡⚡ሰኞ⚡⚡⚡
ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
⚡⚡⚡ማክሰኞ⚡⚡⚡
ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
⚡⚡⚡ረቡዕ⚡⚡⚡
አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም …
❤2
Signed ፲፪
11 Apr 2026, 21:22 UTC87 viewsread 8 August 2026 Photo
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''
''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''
ውድ የዝማሬ ዳዊት ቻናል ቤተሰቦች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።
ዝማሬ ዳዊት
ሚያዚያ 4|2018 ዓ.ም
@Zimare_dawit_Eotc
Signed ፲፪
11 Apr 2026, 21:22 UTC69 viewsread 8 August 2026 File
3/08/18 ዓ.ም
ዕለተ ትንሣኤሁ ለክርስቶስ
በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበ
መልዕክታት ወንጌልና ምስባክ፡፡
ዲ/ን - ቆሮ15÷20-41
ን/ዲ - 1ጴጥ 1÷1-13
ን/ካ - ግብ፡ሐዋ 2÷22-37
የዕለቱ ምስባክ:- መዝ 117÷24
ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ።
ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ።
ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።
ትርጒም፦
እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት።
ሐሴትን እናድርግ በእርሷም ደስ ይበለን።
አቤቱ እባክህ አሁን አድን።
የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ፥20 ÷1- 19
ቅዳሴ፦ ዘዲዮስቆሮስ
@Zimare_dawit_Eotc
@Zimare_dawit_Eotc
@Zimare_dawit_Eotc
Signed ፲፪
9 Apr 2026, 13:11 UTC82 views3 reactionsread 8 August 2026 ጉልባን
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡
በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡
ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ…
🙏3
Signed ፲፪
9 Apr 2026, 12:50 UTC65 views4 reactionsread 8 August 2026 File
አልፋና ኦሜጋ
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በከሃዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ
አዝ
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡህ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሠራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
አዝ
ቅዱሳት እጆችህ የፊጥኝ ታስረው
እንደ በግ ተጎተትክ ልትምራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመጻደቅ
አዝ
በአውደ ምኩናን ከጲላጦስ ፊት
አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከመሳፍንቱደዠ ደጅ
ከነ ሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአዋጅ
አዝ
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ
@Zimare_dawit_…
🙏3❤1
Signed ፲፪
9 Apr 2026, 09:39 UTC51 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
"ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን።"
ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ
👉 @ortodoxmezmur
🙏3
Signed ፲፪
9 Apr 2026, 09:38 UTC58 views2 reactionsread 8 August 2026 አክፍሎት
በሰሙነ ሕማማት ዕለተ አርብ ከስግደት በሗላ ምዕመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡
ከአርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው። አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውሃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡
ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፣ ሐዋሪያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡
ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት …
🥰2
Signed ፲፪
8 Apr 2026, 02:12 UTC75 views4 reactionsread 8 August 2026 በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው ፡-
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግዕዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
ኪርያላይሶን፦
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡
ናይናን፦
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉ…
❤4
Signed ፲፪
7 Apr 2026, 06:12 UTC70 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
የሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ
የጥያቄ ቀን ይባላል፦
ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡
ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተዓምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ /ማቴ. 21፥23-27፣ ማር. 11፥ 7-35፣ ሉቃ.21፥23-27፣ ማር.11፥27-33፣ ሉቃ. 20፥1-8/፤ እርሱም ሲመልስ፤ «እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት…
🥰3
Signed ፲፪
7 Apr 2026, 04:47 UTC75 views3 reactionsread 8 August 2026 "ሰሙነ ሕማማት"
ክፍል ሁለት
በሊቀ ብርሃናት
ኢሳይያስ ወንድምአገኘሁ
ማክሰኞ፡-
ሰኞ የረገማት በለስ ማክሰኞ ደርቃ ተገኝታለች፡፡ የበለሲቱ መረገምና መድረቅ ቀድሞ በአዳም በኩል የመጣውና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረው ኃጢአትና መርገም በክርስቶስ ሞት መወገዱን ያመለክታል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚሁ በማክሰኞ ቀን ስለግብር አከፋፈል፣ ስለትንሣኤ ሙታንና የዳዊት ልጅ የሚባል ማን እንደሆነ በመግለጥ መጻሕፍትን እየጠቀሰ ከፈሪሳውያን ጋር ይከራከር የነበረው በዚሁ ማክሰኞ በሚባለው ዕለተ ሠሉስ ነው፡፡ እንዲያውም ጸሐፍትና ፈሪሳውያንን በታላቅ ተግሣጽ ገሥጾአቸዋል
ማቴ ፳፫÷፩-፴…
🙏3
Signed ፲፪
6 Apr 2026, 14:25 UTC52 views3 reactionsread 8 August 2026 በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸ ሥርዓቶች
1, ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።
2, ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።
በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።
3, ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸው…
🕊3
Signed ፲፪
6 Apr 2026, 14:22 UTC42 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
በሰሙነ ሕማማት ቀን ሕማማት መጽሐፍ እንደጉድ እየተነበበ ነው።ካላነበባችሁት ጊዜው አሁን ነው።በከፍተኛ ጥራት ተዘጋጅቷል
ለማንበብ👇
@Bemnet_Library
@Bemnet_Library
🕊3
Signed ፲፪
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Zimare_dawit_Eotc. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.