12 Apr 2025, 07:01 UTC104 viewsread 7 August 2026 The Warning of an Unknown Voice
I am blind; I cannot see anything.
I don't have ears to hear while birds sing.
I don't know whether I was a slave or a king,
Because I'm nothing.
I am forgotten; no one knows me.
I have neither friends nor enemies.
I was like you before I became nothing.
Now you'd be like me unless you do something.
ABENEZER ABERA✍
Signed 'ABENI
4 Apr 2022, 14:39 UTC≈1,050 viewsread 7 August 2026 #ቢያርስ
ለመሮጥ ደክሞ የማያውቅ
ሁልጊዜ ጡንቻው ፈርጣማ
ሲመጣ ሰው የሚያሳቅቅ
እግሮቹ ትላልቅ ጎማ
ሁልጊዜ ዛፎች ሚነቅል
ቤቶችን የሚያተራምስ
ምን ነበር ቆሻሻን ጠርጎ
ለድሀው መንገድን ቢያ'ርስ
ABENEZER✍
@yebermerkoga
@yebermerkoga
Signed ABENI the 2nd
5 Oct 2021, 08:25 UTC≈1,130 viewsread 7 August 2026 #አጀብ_ነው_ዘንድሮሰ_ወገን!
ጦቢያ ላይ መውደድ ቢጠፋ
ባገሩ ፍቅር ቢነጥፍ...
ሰው ሁሉ 'ኻክ እንትፍ' ይላል
ምራቁን ሰው ፊት ሊለጥፍ!
ትፋቱን ሰው ላይ ሊለጉድ
አጀብ ነው የዘንድሮስ ጉድ።
አጀብ ነው ዘንድሮስ ወገን!
ዛሬ ላይ ፍቅር ተነፍገን
በፍትሕ ጥማት ጠውልገን
የጥንቱን ፍቅር የረሳ....
ጥላቻ ዘግኖ ሲምገን......
የሰው ጅብ ቢፈላ እንዳሸን
ሰው ፈርተን ወደዱር ሸሸን
ጉድጓድ ስር ውለን አመሸን።
አቤንኤዘር አበራ✍
@yebermerkoga
@yebermerkoga
Signed ABENI the 2nd
25 Mar 2021, 07:46 UTC≈1,260 viewsread 7 August 2026 #አጀብ_ነው_ምታሰኝ_ዓለም
ያዳም ዘር ሽብር ካማረው
ከኔ ውጭ ለአሳር ካለ
ለክፋት ጥርሱን ካሾለ
ሰው ካውሬ በምን ተሻለ?
መቼም.................
አጀብ ነው ምታሰኝ ዓለም
ዘንድሮስ አንሰማው የለም!።
አቤንኤዘር አበራ✍
@yebermerkoga
@yebermerkoga
Signed QRISTO
4 Nov 2020, 17:20 UTC≈1,460 viewsread 7 August 2026 የ እ ና ን ተ ን ሚ መ ስ ል
እ ኛ ም አ ለ ን ቁ ስ ል!!
😢😥😥😢😥😢😥😥😥
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አቤኔዘር✍
@yebermerkoga
@yebermerkoga
Signed ፈላስማው ደራሲ✍
29 Aug 2020, 09:59 UTC≈4,290 viewsread 7 August 2026 #yanshal !!
የሰራነው ሐጥያት
ለገሀነም ካጨን
በምድር ብንሰቃይ
ለምንድን ሚቆጨን?
Abenzer✍
@yebermerkoga
@yebermerkoga
Signed ፈላስፋው ደራሲ✍
23 Apr 2020, 12:19 UTC≈4,220 viewsread 7 August 2026 #ገደል_ይዞን_ገባ!
ህዝቡን በጭካኔ....
አውላላ ሚዳ ላይ ያስዘራነው እንባ
ሞትና በሽታ..........
ጎርፍ ሁኖብን ዛሬ አዘቅት ይዞን ገባ!
አቤኔዘር✍
@yebermerkoga
@yebermerkoga
Signed ፈላስፋው ደራሲ✍
10 Apr 2020, 12:40 UTC≈6,860 viewsread 7 August 2026 #ማን_አለ?
እንደው፥በእግዜር፥ምህረት
ከኮሮና ተርፎ፤መኖር ከተቻለ
እስኪ፥መልስ፥ወገን!
በግንባሩ ቆሞ፥ምስጋና ለማቅረብ
ሚቀድመኝ፥ማን አለ?
አቤኔዘር✍
@yebermerkoga
@yebermerkoga
Signed ፈላስፋው ደራሲ✍
4 Apr 2020, 07:33 UTC≈10,200 viewsread 7 August 2026 #የምናብ_ላይ_ስዕል
የሳልኩት ስዕል ላይ ፤ የሚታየው ቀለም
ዝብርቅርቅ አይደለም ፤ ውስብስብ አይደለም
ህይወት ነው ፍቅር ነው ፤ የኔና ያንች አለም።
መቼ ለታ ጠዋት ፤ ቆሜ በማለዳ
የሌቷ ጨረቃ፥ማርገዟን ሳትነግረኝ፥ ድንገት ፀሐይ ወልዳ
በርዶ የነበረውን ፤ ልቤን ስታሞቀው
አጉል ውስጤ ሰርጋ ፤ ስታኮሰምነው ስታሞቀሙቀው
"ተይ ጥለቂ ብላት"
ብትስቅብኝ እንጂ፥ የልቤን ወላፈን፥ እሷ መቼ ታውቀው?።
ታድያ ያን ለት ጠዋት ፤ እዛው በማለዳ
ስዕል ምስልበት፥ሸራ ስወጣጥር፥ቀለም ሳሰናዳ
ኤርፎኔን ሰክቼ ፤ ሙዚቃ ከፍቼ
የታምራት ደስታ ፥አስራሁለተኛውን፥ትራክ አጫውቼ
ሱሪዬን ታጥቄ ፤ ሽርጤን አጥብቄ
ከወዳደቀበት፥ ብሩሽ ለቃቅሜ ፥ቀለም ደባልቄ…
Signed ፈላስፋው ደራሲ✍
3 Apr 2020, 08:27 UTC≈12,500 viewsread 7 August 2026 t.me/yebermerkoga
አጅሬው ኮሮና 😷😷😷😷
ህፃን ይሁን ወጣት ወይም ሽማግሌ
መለየት አያውቅም እገሌ ከገሌ
ነጭ ጥቁር አይል ሀበሻና ፈረንጅ
አንዴ ከፈነዳ ይፈጃል እንደፈንጅ
መምጣቱስ ካልቀረ እንዲህ ከምትፈሩ እንዲህ ከምትባቡ
መኖር አይሻልም ከፈጣሪ ታርቆ ንስሀ እየገቡ?
አቤኔዘር✍
@yebermerkoga
@yebermerkoga
Signed ፈላስፋው ደራሲ✍
25 Jan 2020, 05:40 UTC≈8,450 viewsread 7 August 2026 #ሙስና
እንደው ኢትዮጵያዬ
ምስኪኗ እማማዬ
አንዳች እንኳ የለሽ የሚያጎድልሽ በዝቶ
ያለሽን ሲነጥቁሽ በሙስና ሰርቶ
ሀብትሽን አሟጠው ምንጭሽን
አድርቀው
ልንገድብ ነው ብለው የህዝቡን ብር በልተው
በሙስና ሰርተው በሙስና አድገው
ደሞ ተኮፍሰው ምን ቢሉን ጥሩነው
ሀገር ያደኸያል ሙስና ወንጀል ነው
😏😏😏😏😏😏😏😒😒😏
አቤኔዘር✍
@yebermerkoga
@yebermerkoga
Signed አወዛጋቢው ገጣሚ✍
1 Jan 2020, 07:45 UTC≈4,570 viewsread 7 August 2026 ( #ናፍቆኛል )
#እና_እንደነገርኩሽ!
ህፃን ከሚጠባው ከእናቱ ጡት ላይ
ከወተቱ ውጪ ሌላ እንደማያይ
እናቱ ስትርቀው አይቶ እንደሚያለቅስ
እጆቹን ዘርግቶ ጮሆ እንድትመለስ
እንቅልፉን ተኝቶም ከእናቱ ሲርቅ
ብንን ብሎ ነቅቶ ደግሞ እንደሚናፍቅ
ደስታ ከሞላበት የልጅነት አለም
ከዛ የበለጠ ምንም ናፎቆት የለም።
#ነገርግን_ዛሬ_ናፍቀሺኛል!!
ከእናቴ በልጦ ትውስ ብሎኛል
አብረን የዞርንበት የመንገዱ አፈር
በጥቁር መሬት ላይ ያሰመርነው መስመር
በእንስራ ስትቀጂ ውሀሽን ማግዘው
ከቤት ቂጣ ሰርቀን ምንጎራረሰው
በሚያምሩ አይኖችሽ ምታዪኝ ቀን ሙሉ
የምንዘልበት ገመድ ቅጥልጥሉ ተራራው ገደሉ
ምን ብዬ ልንገርሽ ናፍቆኛል ያ.. ሁሉ።
#እና_እንደነገርኩሽ…
Signed ብዕር ነች አመሌ✍
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Yebermerkoga. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.