7 Feb 2023, 08:44 UTC88 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @Bisrateselam
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
እንኳን ለነነዌ ጾም ሁለተኛ ቀን በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ እያልኩኝ ከደጉ ቅዱስ ገብርኤል ወጣት ማህበር አባላት ጋር በስልክ እንደተነጋገርኩት እናም ሄጄ እንዳየሁት የምዕመኑ ቁጥር ያነሰ እና የጸጥታ አካላት ትኩረት የበዛ ስለሆነ የምንችል ሰዎች የዛሬዉን (30/05/2015) የሰርክ ጉባኤ በደጉ ገብርኤል ለመሄድ ስለታሰበ የምትችሉ ሁሉ ከቀኑ በ10:30 በኮዬ ንቡ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተገናኝተን በጋራ ወደ ደጉ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን እንሄዳለን።
ሼር በማድረግ ለቤተክርስቲያን ልጆች አዳርሱ🙏
Signed Amu
6 Feb 2023, 08:50 UTC78 views0 reactionsread 10 August 2026 Forwarded from @Bisrateselam
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
አሁን በደጉ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ደርሰናል፤ ጥቁር ልብስ የለበሰ አሁንም ድረስ መግባት አይችልም።ቢሆንም ግን ምዕመን ግን ብዙ የለም ሰለዚህ የማታዉ የጸሎት እና የምህላ ጉባኤ ላይ መገኘት ለሚችሉ ህዝበ ክርስቲያን ሁሉ ቅስቀሳ እንድታደርጉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እና ህዝቦቿን ከክፉ ሁሉ ይጠብቅ🙏። አሜን
ሼር በማድረግ ለሕዝቡ አድርሱ🙏
Signed Amu
6 Feb 2023, 07:11 UTC61 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @Bisrateselam
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
አስቸኳይ ጥሪ
ከአጥቢያችን በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘዉ ደጉ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ወጣቶችን እና ምዕመናንን ጥቁር ልብስ ለብሳችሁ ለምን ተገኛችሁ በሚል ሰበብ ስድስት የወጣት ማህበር አባላት በጸጥታ አካላት ተይዘዉ ፖትሮል እስኪመጣ ድረስ በመጠበቅ ላይ ናቸዉ። የምንችል ሰዎች በመገኘት እንድናግዛቸዉ እንጠይቃለን።
እንዲሁም ከጎኑ ባለዉ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያንም ጥቁር ልብስ ለብሶ መግባት አይቻልም ተብሎ በጸጥታ አካላት እየተጠበቀ ይገኛል።
መገኘት የማትችሉ ሼር በማድረግ አግዙን🙏
Signed Amu
4 Feb 2023, 13:09 UTC44 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @BisrateselamPhoto
Photo, posted without a caption
Signed Amu
4 Feb 2023, 13:09 UTC52 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @Bisrateselam
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
በመጀመርያ እንኳን ለነነዌ ጾም በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ እያልን፤ በቤተክርስቲያናችን ላይ የደረሰዉ የሰይጣን ዲያብሎስ መጠቀሚያ በሆኑ አካላት ከሁለት የመክፈል የታቀደበት ሴራ ማዘናችንን እና ምንም ቢመጣ ከቤተክርስቲያን ጎን የምንቆም መሆኑን እያሳወቅን በቤተክርስቲያናችን በቅዱስ ሲኖዶስ በታወጀዉ መሰረት የነነዌን ጾም በጾም፣ በጸሎት፣ በምህላ ለማሳለፍ ስለታሰበ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን በየአጥቢያው ባለዉ ቤተክርስቲያን በመሄድ የተቃጣዉ እኩይ ተግባር በቶሎ በአምላካችን ቸር እጅ እንዲፈታ መጸለይ ማልቀስ ይገባልና የሚዘናጋ እንዳይኖር እያሳሰብን በኮዬ ፈጬ የምትኖሩ ምዕመናን(እናቶች፣አባቶች፣ወጣ…
Signed Amu
16 Jan 2023, 17:40 UTC46 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @Bisrateselam
ለ፡ ደብራችን ሰ/ት/ቤት እና ለምዕመናን በሙሉ
በመጀመርያ እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በአለ ጥምቀት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ እያልን በነገዉ እለት ማለትም በ09/05/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የጥምቀተ ባህር ፅዳት ስለሚኖር መገኘት የምትችሉ ሁሉ ተገኝታችሁ ከበረከቱ ትሳተፉ ዘንድ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
ቦታ: ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ዝቅ ብሎ(ቦኖ ፊትለፊት)
ቃለአብ ጌታቸዉ
የሰንበት ት/ቤቱ ሰብሳቢ
Signed Amu
1 Oct 2022, 10:39 UTC59 viewsread 10 August 2026 "የሰዉ ልጅ ሁለት አይኖች እዉነትን ሳይሆን ነፀብራቃዊ ምስሉን ይመለከታሉ።አስተዋይ ልቦና ግን በንስር ዓይን ይመሰላል።ከሰማይ አናት ላይ ሆኖ ዉቅያኖስ ዉስጥ ያለን እዉነት መመልከት ይቻላልን።"
ዮቶር ገጽ 43
ዓለማየሁ ደመቀ
Signed Kaleab
1 Oct 2022, 10:39 UTC69 viewsread 10 August 2026 " የአንድ ዕቃ ወይም ጉዳይ የሚለካዉ፣ በዕቃዉ ወይም በጉዳዩ ዓይነት ሳይሆን፣ ዕቃዉ ወይም ጉዳዩ ባረፈበት ሰዉ ማንነት ነዉ"
ዮቶር ገጽ 92
Signed Kaleab
30 Sept 2022, 03:29 UTC62 viewsread 10 August 2026 " ለዚህ ነዉ ዛሬሽን እንዳትሰጪ ያልኩሽ። መልስ የማግኘት እድልሽ ጠባብ ነዉ÷መንገዱንም ነግሬሻለሁ። መመልከት፣ መጠበቅና መሸሽ - እነዚህን ተጠንቀቂ።ተመልካች አትሁኚ፤ ተሳተፊ፣ ተቀላቀይ፣ የምትታዪ ሁኚ።ዝም ብለሽ አትጠብቂ፣ ማንንም አትጠብቂ።አንቺ የምትፈልጊዉን በጊዜዉ፣ ባወቅሽዉ ልክ አድርጊ፤ ባለማወቅሽ አትስጊ።ግድ የለም ተሳሳቺ፤ መሳሳት ከመሸሽ ይጠብቅሻል።ከመሸሽ ደግሞ ደግመሽ ደጋግመሽ መሳሳት ይሻላል"
አለማወቅ ገጽ 297
ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ
Signed Kaleab
26 Sept 2022, 04:17 UTC65 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @Bisrateselam
እንኳን ለደመራ በአል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ።
በአሉ የሰላም ፣የጤና ፣የበረከት እንዲሆንልን ተመኘን።
በአሉን ለማክበር በፋንታ መስቀለኛ መንገድ ጋር ሁለቱ (ቅዱስ መድኃኔዓለም እና ቅዱስ ገብርኤል ) አድባራት በአንድነት ስለሚያከብሩ በቦታዉ ከ9.30 ጀምሮ እንድትገኙ ስንል አክብረን ጠርተኖታል።
መልካም በአል
ሰንበት ት/ቤቱ
https://t.me/Bisrateselam
Signed Kaleab
29 Mar 2022, 19:32 UTC110 viewsread 10 August 2026 አስተማሪ አጭር ታሪክ .!
አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ ። አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡
ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ ሰውየውም ከመረመረው በኋላ "አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ
እንሸጠዋለን፡፡" ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል ።
ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥአሰራር ጥበብ ተካነ …
Signed Kal
26 Mar 2022, 18:15 UTC75 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @BisrateselamPhoto
ለሁሉም እንዲዳረስ share ማድረግ እንዳይረሳ
ጉባኤዉ እዲሰፋ እና የበለጠ እንዲያምር ለማገዝ ይደዉሉ፦ 0942221391
@Bisrateselam
Signed Kal
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Thug4r. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.