5 Sept 2026, 04:19 UTC201 views5 reactionsread 5 September 2026 Photo
ስወድ አስቸጋሪ ነኝ! ያለኝን ሁሉ ነገር ሰጥቼ እንደሰጠሁት እንዲሰጡኝ እጠብቃለሁ።
በአጋጣሚ ህይወቴ ውስጥ የገባ ሰው የኔ ሰው ሆኖ ይመዘገባል....ያኔ ሀላፊነቱ እንዳለብኝ ይሰማኛል።
በየእለቱ ፍቅርን የምሰብ፥ በየእርምጃዬ ለመኖር ምሞክር ብሆንም በልኩ ይሁን ማለትን ከመንገዴ ተምሪያለሁ።
መኖር ቆንጆ ነገር ነው! ከሌሎች ጋር ተዋዶና ተሳስቦ መኖር ደሞ ይበልጥ ውብና ተወዳጅ ያደርገዋል።
ከምንሰጠው ብዙ ፍቅር ጋር ለምንወዳቸው ነፃነትና ለፍላጎታቸው መተውንም መስጠት ይጠበቅብናል።
ውዶቻችንን ለፍላጎታቸው መተው፥ ለውሳኔና ፍቃዳቸው አሳልፈን መስጠትም ከፍቅር ነው!
መኖር ቀለሙ ብዙ ነው፥ ልከኛ መልኩ ግን ፍቅር ነው❤
ተዛዘኑ ተዋደዱ ለብዙ ልቦች ትተርፋላ…
❤5
29 Aug 2026, 05:47 UTC877 views4 reactionsread 5 September 2026 Photo
ገጣሚ ዘውድ አክሊል አንድ ኢንተርቪው ለይ ፍቅር ማምለጫ ነው ሲል ሰማሁት.... ዋሻ ነው መሳሳት ምንችለበት ዋሻ!
ሁልጊዜ ጠባሳችንን ሸፍነን አንችልም አውልቀን የምናሳይበት ቦታ ነው ፍቅር!
ማነሳችንን፥ ሚያነክስ እጅ እግራችንን፥ ሚያነክስ ህሊና እና ልባችንን ምንገልጥበት ቦታ ነው እያለ ይቀጥላል...
አዎ በምንወዳቸው ሰወች ውስጥ ምንም መሆን ሳይጠበቅብን... ከነ ምንምነታችን ቀናትን እንሻገራለን።
መኖር ቀለሙ ብዙ አይደል በተለያዩ የህይወት መልኮች ለይ ያመላልሰናል። ታዲያ በእዚህ ምልልሶች ማንዝለው የኛ ሰወች ትከሻ አብሮን ስላለ ነው።
ለብቻ ሊሻገሩት ገደል የሆነ በጋራ ይቀላልና የእናንተን ሰወች አደራ!
እየመነዘርን ምንኖረው የተሰጠንን ፍቅር ነው…
❤4
3 Jul 2026, 09:16 UTC305 views4 reactionsread 5 September 2026 Forwarded from @efuyr
"ቡናው ነው የጠራሽ ወይስ ናፍቆቴ" አልኳት የፈላውን ጀበና እያወረድኩ
"መሄጃ ማጣቴ ነው የጠራኝ"ባኮረፈ አንደበት
"ወገኛ! ምን ሆንሽ ደግሞ?"
"ምንም" ደክሟታል
"ፊትሽ ደህና አይደለም የት ነበርሽ?"
"ደብረ ሀይል"
"ብቻሽን! ምነው ብጠሪኝ?"
"አይ! ከእሱ ጋር"
"ምነው ተጣላቹ እንዴ?"
"አገኘዋት"ቅር እያላት
"ታድያ ችግር አለው? ማለቴ እና.."ማንነቷን መጠየቅ አላስፈለገኝም
"ተያየን አስተያየቷ የመመርመር ያክል ነበር...ልብ ብላ ስታየኝ ነፍሴ ናፍቆቴን የነገራት መሰለኝ እግሬ ሳላዘው ወደርሷ ሄዶ ክንዴ ሊያቅፋት ከንፈሮቼ ሊስሞት አይኖቼ ለምን ተውሽን ብለው በእንባ ሊያወጓት ነበር (እህህህህ)...እሱ መኖሩ በጀኝ!"
"ቆይ ግን አ…
❤4
20 Jun 2026, 07:20 UTC396 views5 reactionsread 5 September 2026 Photo
የሆነ ዕለት እራሴን ሲፈግግ አገኘሁት! ያልተለመደ የኔ ያልነበረ ፈገግታ የመቻል የመቀበል ከራስም ከሌሎችም የመታረቅ የመፈወስ ፈገግታ!
ግትር ነበርኩ ማንም ምንም የማይመልሰኝ....የሌሎች ስሜት መከፋት ማያስደነግጠኝ ግትር!
ከቻሉ የሚሸሹኝ ከቀረቡም ያቃረባቸውን ሰበብ ፍፃሜ አብዝተው ሚናፍቁ፤ዳግም ሊያገኙኝ ምኞት የሌላቸው ከነዛቢያዬ እንዳሻት ብለው ሚተውኝ አይነት.........
የበደለኝም ያሻረኝም ጊዜ ነው።
ህመምን ሰተው የብቸኝነትን ስቃይ የመጉደልን ሰቀቀን አሳይተው የማጉደልን በደል የመንፈግን ህመም አስተማሩኝ። ቀናት አሳጥተው የማሳጣትን ልኩን አሳዩኝ!
ቀናት ናቸው የሰሩኝ! ደቁሰው ሸራርፈው ከኔነት አሻግረው ለእኛነት ያበጃጁኝ.......
ከተ…
❤4🥰1
20 Jun 2026, 04:16 UTC304 views4 reactionsread 5 September 2026 Photo
መሽቶ በነጋ ቁጥር ምድር መልኳን እያጣች ነው።
ሚታየው፣ ሚሰማው ሁሉ ልብ ያደክማል!
የሆነ ቀን ሰው እንዴት እንደዚ ያደርጋል... ባልን አንደበታችን እዛው ጋር ፎርሸን.... አጋጣሚ እንደሆነ ስናስረዳ አሊያም ነገሩን ልክ ልናደርገው ስንታገል እራሳችንን እናገኘዋለን።
የህይወት እሽክርክሪት ከመዳፋችን አፈትልኳል.....እርግጥ ከመሠረቱም ባለ መብት አልነበርንም።
ማንም በምን ቅፅበት የት ሊገኝ እንደሚችል ማወቅ አይችል....መኖር በራሱ እሽክርክሪት ነው ሚወስደን ምን አልባት በምንደርስበት ሁሉ የተሻለውን ለመምረጥ የሚጠጋ ዕድል እንጂ...መንገዳችንን የማበጀት ቅዋው አልተሰጠንም።
አንድ ሌት መሽቶ ሲነጋ....
አንዳንዶች ህይወታቸው ይስተካከላል....አንዳን…
🥰3🔥1
19 Jun 2026, 17:14 UTC291 views8 reactionsread 5 September 2026 Photo
እገረማለው!!!
አባት አለሜ!❤️
የምን ስሪት ነህ፣ከምን ያፈራህ
እንዴት አነፀህ፣በምኑ ሰራህ
በልብህ ያለ፣የላቀ ፍቅር
ለዓለም ይበቃል፣ለልጅህ ይቅር
እደነቃለው! ስለ ስሪቱ
አወይ ፈገግታ፣አወይ ፍካቱ
እጅ ነሳለው! ስለ ስጦታው
ከማኖር በላይ፣አቤት ውለታው
እደመማለው! ስለ ጥበቡ
ከልባሙ አንተ፣እኔን መጥረቡ
እገረማለው❤️
ግርምቴ ያልፋል፣ከአቅሜ በላይ
መቻል ስጦታህ፣ትግስትህን ሳይ
እጠይቃለው
ይህንን አቅም፣ኬት አመጣኸው
በሳቅህ ብቻ ታኖረኛለህ፣ይህን አውቃለው።
❤7🥰1
17 Jun 2026, 16:17 UTC259 views4 reactionsread 5 September 2026 Photo
ጥቀርሻ ልቤን
አዳፋ ቀልቤን
ሁሉን ታቅፌ፣
በወንጀል ክምር
ስንኮፍ በበዛው
ጎዳና አልፌ!
ሆኜ ባይተዋር
ርቄ ከራሴ
ርቄ ከመልካም
ርቄ ከደጅህ
ሁሉን ምቸረው፣
ባንተው በእጅህ!
መገን እዝነትህ🤗
❤3🔥1
13 Jun 2026, 19:03 UTC330 views9 reactionsread 5 September 2026 ማንም ሰው ሩሃችሁን እንዲያቅፍ አታስገድዱት...
ፍቅር እንደሃይማኖት ነው! በሱም ማስገደድ የለም🖤
🥰7❤1❤🔥1
12 Jun 2026, 13:27 UTC341 views1 reactionsread 5 September 2026 Forwarded from @justhoughtsss
የጨው ሀውልት መቼ እንደዚህ ይደርቃል
ጅብራ መቼ ይገተራል
ከአመታት በኋላ በቀን ጎዶሎ(እሁድም የቀን ጎዶሎ አለው?!)
ከሌላው ቀን በተለየ ጥድፊያ በሌለበት፥ በሰላም ነበረ እኮ የነቁት አረፋፍደው በተፈጥሯዊ መንገድ ማለት ነው። ፀሀይ በመስኮት ገብታ በሙቀት እና በጨረር ኮርኩራቸው ተንጠራርተንው... (ይሄ ሁሉ ዝብዘባ በስራ ቀኖች ላይ በalarm ጉትጎታ ፀሀይ ሳትነቃ ከቤት ስለሚወጡ ነው)
ከዛማ እየተንጠራሩ ተነስተው ቁርስ አብረው አብስለው እየበሉ "እሺ የዛሬ ውሏችን ምን ይመስላል" አላት አቤል ቀጥሎ የሚጎርሰውን እያስተካከለ "አልረሳሁልህም ያንን ያየሁትን sundress እገዛልሻለሁ ያልከኝን" አለች እንደህፃን እየተቁነጠነጠች
(ቁም ነገሩ እንደህፃን…
❤1
12 Jun 2026, 13:27 UTC233 views1 reactionsread 5 September 2026 Forwarded from @justhoughtsssPhoto
Photo, posted without a caption
❤1
8 Jun 2026, 09:12 UTC299 views2 reactionsread 5 September 2026 Forwarded from @justhoughtsss
እድሜ ለኮሪደር ልማት መንገዱ በመብራት ተጥበርብሮ ወደ ቤት ስገባ የተዳፈነ ጨለማ ተቀበለኝ።"ተኝታ በሆነ"እያልኩ ስገባ ቤቱ በሻማ ተንቆጥቁጧል።
የሻማው አቀማመጥ ክሬም ከለር ግድግዳውን ቀይ አድርጓታል። እንደዚህ ማድረግ የጀመረችበት ጊዜ ትዝ ብሎኝ ፈገግ አልኩ። ቀያይ ሻማዎች ልትገዛ ስትል ሲወደድባት ነው ቀያይ ብርጭቆዎች ገዝታ አሸዋ ከሰራተኞች ላይ ተውሳ ሞልታበት ያስቀመጠችው። የ'ክት' ነው ልዩ ቀን ነው ስትል ነበረ ሌላ ጊዜ የምታወጣተቸው ዛሬ ምን ተገኘ? እያልኩ ሻማውን ተከትዬ ስሄድ
የምወደው ሽቶዋ ከአሩስቶ ሽታ ጋር አብሮ አፍንጫዬን አወደው ሳላስበው ፈገግ ብዬ ሳሎን ስገባ ጠረጴዛው በምግብ ተሞልቷል አሩስቶው ጉብ ብሎ በደንብ ያስጎመጃል። ጠረጴ…
😭2
18 May 2026, 14:22 UTC421 views9 reactionsread 5 September 2026 ስወድህ......
ምርጫ እንዳልሰጠው፤
በምድር ካንተ ሌላ እንዳልተፈጠረ
ዓለምን በሙላ ዘንግቼ ነበረ።
❤8👍1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Seadiyadetamo. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.