1 Aug 2023, 09:29 UTC140 views2 reactionsread 9 August 2026 Forwarded from @OmnipotentmovementPhoto
Omnipotent movement presents
Omnipotent charity day 2023
⚡Hebrew 13:16
And do not forget to do good and to share with others, for with such sacrifices God is pleased.⚡
Donate trousers for men and other items
We are donating at Win souls for God, for 42 boys in the orphanage.
1 donation would mean a lot for us🙌.
Call us on 0909322576 or 0924451666 or 0974424774
Win souls for God
📍shiromeda
❤2
24 Jul 2022, 05:24 UTC221 views3 reactionsread 9 August 2026 Photo
ሁሉም ነገር እጅግ ውብ ነው!
• የዛሬዋ ቀን አንዳንድ ችግር ባያጣትም እጅግ ውብ የሆነች ቀን ነች!
• እኔም አንዳንድ ደካማ ጎኖች ቢኖሩብኝም እጅግ ውብ የሆንኩኝ ሰው ነኝ!
• ሃገራችን ብዙ ችግሮች ቢሰሙባትም እጅግ ውብ ሃገር ነች!
• የፍቅርም ሆነ የትዳር አጋሮቻችሁ የተወሰኑ የባህሪይ ጉድለት ቢኖርባቸውም እጅግ ውብ የሆኑ ሰዎች ናቸው!
• እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ አመለካከቶች እጅግ ውብ የሆኑ አመለካከቶች ናቸው፡፡
ይህንን ውብ ሃሳብ ቢያንስ ለአስር ሰው ያጋሩ!
መልካምና ውብ ቀን ይሁንላችሁ!
@Safelifeorg
👍3
19 Jul 2022, 17:34 UTC197 views1 reactionsread 9 August 2026 በዛሬው ቀን በሁለት ነገሮች የማንነታችሁ ጥራትና ክቡርነት ይመዘናል፡-
1. አደርገዋለሁ ያላችሁትን ነገር ቃል በገባችሁት ሰአትና የጥራት ደረጃ ማድረጋችሁ እና
2. ስዎቸን በቀጠራችሁበት ሰአት አክብራችሁ በመገኘታችሁና የማትገኙ ወይም የምታረፍዱ ከሆነ አስቀድማችሁ በማሳወቃችሁና ይቅርታ በመጠየቃችሁ።
@Safelifeorg
❤1
18 Jul 2022, 07:11 UTC191 views2 reactionsread 9 August 2026 Photo
"ብሞት ይሻለኛል!"
• እስከ ሕይወቴ ፍጻሜ ድረስ የምከተለው ዓላማ ሳይኖረኝ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!
• ራሴን፣ ዓላማዬንና ስራዬን በማሻሻል ላይ ከማተኮር ይልቅ ስለሰዎች ሳስብና ሳወራ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!
• ቢያንስ በአንድ ሰው ላይ መልካም ተጽእኖ ሳላሳድር ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!
• በየእለቱ ሳልለወጥ በአንድ አይነት አመለካከት፣ ስፍራና ልምምድ እየረገጥኩ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!
• መንቀሳቀስ እስከማልችል ድረስ በፍርሃት ታስሬ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!
• በሰዎች ላይ ቂም ይዤ እነሱን ካልተበቀልኩኝ በስተቀር ውስጤ አላርፍ እያለኝና እየነደደ ከምኖር "ብሞት ይሻለኛል"!
• አንድ ሰው ስለገፋኝና ትቶኝ ስለሄደ ብቻ ነገን …
❤1🔥1
3 May 2022, 07:28 UTC190 views2 reactionsread 9 August 2026 Photo
የግንባታው “ሳይት” ጉዳይ
አንድ የሕንጻ ግንባታ ስፍራ ምንም እንኳን አጥሩ ታጥሮ፣ ለግንባታ የሚሆነው ቁሳቁስ በሙሉ ተከምሮና በአካባቢው ግንባታውን ለመስራት የተዘጋጁ ሰዎች ቢተራመሱም፣ ግንባታ ተጀምሮና ተጠናቆ ስራ ላይ እስካልዋለ ድረስ ቦታው የግንባታ “ሳይት” ከመሆን ውጪ ሌላ ጥቅም የለውም፡፡
የእኔና የእናንተም ሕይወት እንደዚሁ ነው፡፡ በአእምሯችን፣ በእጃችንም ሆነ በአካባቢያችን ያሉ በርካታ አቅርቦቶች ኖረውን ሳለ እነዚህን አቅርቦቶች እንዲሁ ከማከማቸት ባለፈ ሁኔታ ከዓላማ አንጻር ካልተጠቀምንባቸው አንድ መልክ ያለውን ነገር ለመገንባት አንችልም፡፡ እነዚህን ነገሮች ስንሰበስባቸውና ከዓላማ አንጻር ስንጠቀምባቸውና ስንገነባቸው ብቻ ውጤታማ እንሆናለን፡…
❤2
21 Apr 2022, 03:30 UTC188 viewsread 9 August 2026 Photo
ተግባቦት ስንል ???!!!
አንድ ሰው እንዲህ አለ፣ “ስለ ተግባቦት ሳይገባኝ የኖርኩባቸውን አመታቶች ሳስባቸው ይቆጨኛል፡፡ ለሌሎች እድል ሳልሰጥ ብዙ ከማውራቴ የተነሳ ሰዎች ብዙ እንደማወራ ሊነግሩኝ ሲሞክሩ እንኳን ብዙ እንደማላወራ ለማሳመን ብዙ አወራ ነበር”፡፡
ሕይወት ማለት የሁለትዮሽ ንግግር (Dialogue) እና ተግባቦት ነች፡፡ ይህ ማለት ደግሞ እኛ ስናወራ እንደሚያደምጡን ሁሉ እኛም ሌሎችን ማድመጥ ማለት ነው፡፡
እንደመጥ! እናድምጥ!
@Safelifeorg
8 Apr 2022, 03:36 UTC≈1,860 views3 reactionsread 9 August 2026 Photo
ዛሬ ይጀመር!
ምናልባት ይህንን አባባል ከዚህ በፊት ሰምታችሁት ካላወቃችሁ ላሰማችሁ፣ ካወቃችሁት ደግሞ ላስታውሳችሁ፡-
“ዛፍን የመትከያው ትክክለኛውና ከሁሉም የተሻለው ጊዜ የዛሬ ሃያ አመት ነበር፤ ከዚያ ቀጥሎ የተሻለው ጊዜ ደግሞ ዛሬ ነው”፡፡
“ምነው የዛሬ ዓመት፣ አምስት ዓመት ወይም አስር ዓመት ጀምሬው ቢሆን” ኖሮ የምትሉት ነገር ካለና ያንን ባለማድረጋችሁ የምትጸጸቱ ከሆነ፣ የተጠቀሰውን አባባል ምክር በመስማት ወሳኝ እርማት ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ያን ጊዜ ብትጀምሩት የተሸለ የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የሚቀጥለው ትክክለኛ ጊዜ ዛሬ መጀመር እንደሆነ ላስታውሳችሁ፡፡
ምንም ነገር ለመጀመር ጊዜው አልረፈደምና ተነሱና ዛሬ ጀምሩ!
@Safelif…
❤3
7 Apr 2022, 03:54 UTC≈1,640 views3 reactionsread 9 August 2026 Photo
ንዴት በልኩ!
አንድ ምንጩን የማላስታውሰው አባባል እንደዚህ ይላል፡- “በአንድ ነገር ስትናደድ ምንም እርምጃ ከመውሰድህ በፊት ከሁኔታው ዘወር በማለት ከአንድ እስከ አስር በቀስታ ቆጥረህ ተመለስ፡፡
በአንድ ነገር በጣም ከተናደድክ ደግሞ ምንም እርምጃ ከመውሰድህ በፊት ከሁኔታው ዘወር በማለት ከአንድ እስከ መቶ በቀስታ ቆጥረህ ተመለስ፡፡ ይህንን ብታደርግ የንዴት ስሜቱና በዚያም ምክንያት ለመውሰድ ከተነሳሳህበት ተግባር ረገብ ብለህ ራስህን ታገኘዋለህ”፡፡
ይህችን ቀላል የምትመስል ምክርና መርህ ባለመከተልና የንዴት ስሜታቸውን እንደወረደ በመልቀቃቸው ምክንያት ብዙ ሰዎች ስራቸውን አጥተዋል፣ ትዳራቸውን አፍርሰዋል፣ ማረሚያ ቤት ተቆልፈዋል . . . ፡፡
ረገብ…
👍3
4 Apr 2022, 04:02 UTC≈1,830 views5 reactionsread 9 August 2026 Photo
አልፋችሁ ሂዱ!
ፈጣሪ በዚህች ምድር ላይ እንድትኖሩ የሰጣችሁ ይህ ሕይወት በራሱ፣ ምንም ነገር ሳይጨመርበት እጅግ ውብ ነው፡፡ ይህንን ውብ የሆነ ሕይወት ምንም ነገር እንዲያበላሽባችሁ አትፍቀዱ፡፡
• በአንድ ሰው ተግባር ብቻ ይህ ውብ የሆነ ሕይወት እንዳይበላሽ ሰዎች ከሚያደርጉባችሁ ወይም ካላደረጉላችሁ ነገር አልፋቸሁ ሂዱ!
• በአንድ ነገር አለመሳከት የተነሳ ውስጣችሁ ወድቆ ይህ ውብ የሆነ ሕይወት እንዳይበላሽ ጊዜያዊ ከሆነው የመሳካትና ያለመሳካት ገጠመኝ አልፋችሁ ሂዱ!
• ሰዎች ከሚያደርጉብን፣ ከሚያደርጉልንና ከከለከሉን ነገሮች ይልቅ በሕይወት መኖር በራሱ በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡ ከተሳካውና ካልተሳካው ሁኔታ ይልቅ በሕይወት መኖር በራሱ በብዙ …
❤4👍1
31 Mar 2022, 02:44 UTC156 views3 reactionsread 9 August 2026 Photo
አንብቡ! ተንቀሳቀሱ!
ሁለት እውነታዎች አሉ፡- 1) ማወቅ የሚገባችሁን ሁሉ አላወቃችሁም፣ 2) መድረስ የሚገባችሁ ደረጃ ላይ አልደረሳችሁም፡፡
በእነዚህ በሁለት እውነታዎች ካመናችሁና ከተስማማችሁ ሁለት ልምምዶች ሊታዩባችሁ ይገባል፡-
1. ካለማቋረጥ ማንበብ!
በዚህ ሳምንት ምን አነበባችሁ? በዚህ ሳምንት ካነበባችኋቸው ነገሮች ምን አዲስ እውቀት ገበያችሁ? ከእነዚህ ካገኛችኋቸው አዳዲስ እውቀቶች መካከል የትኞቹን ለመተግበር ሞከራችሁ?
2. ካለማቋረጥ ወደ ፊት መራመድ!
በዚህ ሳምንት በዓላማችሁ አቅጣጫ ምን አይነት እንቅስቃሴ አደረጋችሁ? በዚህ ሳምንት ምን አዲስ ነገር ጀመራችሁ? ከእነዚህ ካደረጋችኋቸው እንቅስቃሴዎችና ጅማሬዎች መካከለት የትኞቹ ውጤትን…
👍3
30 Mar 2022, 13:05 UTC134 views2 reactionsread 9 August 2026 Photo
ሁለት አይነት ሰዎች!
ሁለት አይነት ሰዎች አሉ፡- በተሟላ ቤት ውስጥ የተወለዱ እና በችግር ውስጥ የተወለዱ፡፡ የእነዚህን ሁለት ሰዎች አወላለድ ትርጉም የለሽ የሚያደርግ ደግሞ እንድ ነገር አለ፡- ጽኑ ፍላጎት!
በተመቻቸ ቤት ውስጥ፣ በተሟላ ኑሮ ውስጥና ሊደግፏችሁ በሚችሉና ፈቃደኛ በሆኑ ቤተሰቦች ውስጥ ብትወለዱና ብታድጉም፣ ያንን ይዛችሁ ወደሚቀጥለው ደረጃ የመውሰድ ፍላጎቱም ሆነ ፈቃደኝነቱ ከሌላችሁ የትም አትደርሱም፡፡
በተቃራኒው፣ በማይመች ቤት ውስጥ፣ ብዙ ነገር በጎደለበትና አቅሙ ውስን በሆነበት ቤተሰብ ውስጥ ብትወለዱና ብታድጉም ከዚያ ተነስታችሁ ወደታያችሁ ራእይና ዓላማ የመድረስ ጽኑ ፍላጎትና ፈቃደኝነቱ ካላችሁ የትም ከመድረስ አትከለከሉም፡፡
በ…
❤2
29 Mar 2022, 05:12 UTC≈1,720 views3 reactionsread 9 August 2026 Photo
ተነሱና ወደፊት!
“በሕይወት በመኖር ሂደት ውስጥ ታላቁ ክብር ያለው ባለመውደቅ ውስጥ ሳይሆን በወደቁ ቁጥር በመነሳት ውስጥ ነው” – Nelson Mandela
በሉ በዚህ ሳምንት በሆነ ነገር የወደቅን ሁሉ አብረን እንነሳና እንደገና ወደፊት!
@Safelifeorg
🔥3
Showing the 12 most recent of 19 posts we hold for @SAFELIFEorg. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.