5 Jul 2026, 06:05 UTC69 viewsread 8 August 2026 (በእውቀቱ ስዩም)
ግድየለሽምና ፥ ከልብ ላፈቀረሽ
ሶስቴ ተቀጣጥረን፥ አራት ጊዜ ቀረሽ።
ዛሬም እንደ ወትሮው፥ ትቀርያለሽ ብየ .....
እድል የላከውን፥ እጣ የሚመስል፤ እጦት ተቀብየ፥
አበባ ሳልቀጥፍ
አልጋ ሳላነጥፍ
ሙታንታየን ሳልጥፍ
በትራስጌየ ላይ
ፎቶሽን ሳለጥፍ፥
ትቀርያለሽ ብየ........
በመስታውቴ ፊት
ከልብ አስቀይሜ
አንድ እፍኝ ነጭ ሽንኩርት
እንደ ተልባ ቅሜ
አየሩን መርዤ፥ ህዋሴን አክሜ፤
ትቀርያለሽ ብየ.......
ጥፍሬን ሳልከረክም
በመቀስ ሳልንደው፥
የጉያየን ሸክም
ትቀርያለሽ ብየ.....
ጀንበርን ቀድሜ፤ ቤ…
Signed መንገደኛው ተጓዥ
19 Jun 2026, 04:32 UTC250 views1 reactionsread 8 August 2026 ።።።። አልብሰን የፍቅርን ሸማ።።።።
በክፉት፣ ንጉስ ታውሮ
በባህር ወስዶ ቢያሰምጠኝ፣
የሞቴን ደብዳቤ ፅፎ
ጨካኝ ሰው ለሞት ቢሰጠኝ፣
አፋን፣ ቢዘረጋጋ
ዘሎ፣ ዘንዶው ሊውጠኝ፣
ጉድጓድ፤ ቢቆፈርልኝ
አናብስት ይዞ እንዲግጠኝ፣
አንተ ግን፣ ፈጥነህ ተልከህ
ችግሬን ደረማመስከው፣
የሀዘን፣ የጭንቄ ዘመን
ሚካኤል ከኔ አተነንከው፣
በሞቴ፣ ህይወት ቀይረህ
የሰርጌን፣ ድግስ ደገስከው።
:
ሰይፍህ የእሳት ነበልባል፣
ክንፍህ የመብረቅ ግርማ፣
ምህረትህ የባህር አድማስ
ዙፋንህ ኢረ…
🙏1
Signed Misge Ye አደራ ልጅ (21)
14 Jun 2026, 07:54 UTC117 viewsread 8 August 2026 ትመጫለሽ አይደል❓
በጥላቻ ገደል
ፍቅራችን ሲገደል
ትመጫለሽ አይደል?❓
ከወፎቹ ህብረት
ዝማሬ ሲታደል
ትመጫለሽ አይደል?❓
ከዱሮ ቤታችን
ሲጨስ እጣን ሰንደል
ትመጫለሽ አይደል?❓
በትዝታ ፊደል
ልባችን ሲነደል
ትመጫለሽ አይደል?❓
✍️misge
@Mis2081
Signed Misge Ye አደራ ልጅ (21)
9 Jun 2026, 18:33 UTC153 views2 reactionsread 8 August 2026 የዳዊት ልጅ ማረን🙏🙏
( ኬቢሻ)
እኛ አልሆነልንም....
የሌት ጅብ ነው ያልነው ሊበላን ነው በቀን፣
ኢትዮጵያም እጆቿን.....
አጥፋው ነው መሰለኝ በረከት የራቀን??
እርያ ስጋችን .....
ያገኘውን ሁሉ እያግበሰበሰ፣
ጥንት ከነበሩት....
ከባቢሎን ሰዎች ጥጋባችን ባሰ።
ድፍረታችን በዛ....
ከሞተልን ሳንሆን እኛስ ሜዳ ቀረን፣
አስር ፃዲቅ ካለ ....
ስለአስሩ ብለህ የዳዊት ልጅ ማረን!!🙏🙏
@Mis2081
@Mis2081
😢2
Signed መንገደኛው ተጓዥ
9 Jun 2026, 03:27 UTC345 views0 reactionsread 8 August 2026 😭...😭...😭
❗️
ገነደሱት አሉኝ
ያንን ዛፍ በመጋዝ፣
በእሳት ሊያነዱት
አርከፍክፈው በጋዝ።
ሰነጠቁት አሉኝ
ያንን ዛፍ በቁሙ፣
ክንፍ እየቆረጡ
ፍሬ እየለቀሙ።
ገነጠሉት አሉኝ
ያን የገደል እሬት፣
እንግዲህ ምን ይባል
ተቀበይው መሬት😭😭😭
(✋✋✋ ጌታ ሆይ ምህረቱን አምጣልን🙏🙏🙏)
✍️misgan
@Mis2081
Signed Misge Ye አደራ ልጅ (21)
2 Jun 2026, 17:13 UTC151 views4 reactionsread 8 August 2026 😭😭❗️❗️❗️
ምድር ቀይ አበራች
መኖር ስለፈራች
አምሏኳን ተጣራች!!
ሁሉም ስለሚያውቃት
አድብተው ላይሞቋት
ብርሀን ሲጠይቋት
ፀሀይም ጨነቃት!!
ዛፎች ኮበለሉ
መቆረጥ መፈለጥ
መረረን እያሉ!!
ወንዞች ገነፈሉ
ሳይሞቁ እየፈሉ!!
ሰዎች ቤት እያሉ
በቀን ጅብ ተበሉ!!
ፍጥረታት በሙሉ
እረ እግዚኦ በሉ!!🙆♀️🙆♂️
✍️misge
( 25/09/2018)
(ስለ ሀብተማርያም
ብለህ ይቅር በለን
…
👏4
Signed Misge Ye አደራ ልጅ (21)
1 Jun 2026, 05:04 UTC213 views5 reactionsread 8 August 2026 ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
"መቼም ጉድ ሳይወቅጡ
መስከረም አይወጡ"!!
አሉ!!🤔🤔
እንደባዘነ በግ እንደሆነ ደባል፣
ደዌ እንጎዳት ሴት እንዴሌላትም ባል፣
"እንክርዳድ" አቅርበው .....
"ስንዴ"🌾🌾 ብላ ስባል፣
እንዴት ብዬ ልጉረስ
እንዴትስ ልዋጠው፣
የቀረበው ማዕድ
ልቤን እየናጠው፣
እንዴት ብዬ ልቁረስ
እጄስ እንዴት ይድፈር፣
እንዴት ብሎ ይውረድ
ወደ ሆዴ ሰፈር፣
(አወይ አለማፈር🤭🤭!!!)
ስንቱን ጉድ ቻለችው
ይቺ የመሬት አፈር ???
✍️ ✍️misge
…
🔥5
Signed Misge Ye አደራ ልጅ (21)
30 May 2026, 05:59 UTC248 views1 reactionsread 8 August 2026 ።።። መግጠም አቆምኩልሽ ።።።
አንድ ስገነባ አንድ እየጎደለ፣
አንድ ስኮተኩት አንድ እየገደለ፣
ሽንቁር እንደበዛው እንደውሀ ማሰሮ....
ባንዱጋ ስጠግን ባንዱ እየነደለ፣
(ካንቺ ዘንድ ሲደርሱ....!)
የግጥሜ ጋጋታ ቤት እየናደብኝ፣
የቃላት ሁካታ አድሮ እየራደብኝ፣
የስንኛች ጩኸት አንጓ እየቀደደ፣
የሀረጋት ልቅሶ መርዶ እየወለደ፣
አንቺን ደስ ካለሽ.....!
ጥገቢው ያውልሽ.....!
ብዕሬን ጣልኩልሽ .... !
(ስ'ለት ተስያለሁ ዳግም ላልመኘው...)
ብዕር ማንከርፈፉን፣
ፊደል ማጣደፉን
ላንቺ መለ…
❤1
Signed Misge Ye አደራ ልጅ (21)
29 May 2026, 03:33 UTC140 views3 reactionsread 8 August 2026 ከሰይጣን ~ ከሰው ተንኮል፣
ካሰከረኝ ~ ካ'ሜት አልኮል፣
ከጎልያድ ~ ሰራዊቶች፣
በባቢሎን ~ ካሉ ከብቶች ፣
ካ'ለም በቀል ~ ካ'ለም ፍርጃ፣
ካላዳነኝ ~ ያንቺ ምልጃ፣
መሰንበቴን ~ አላውቅ እንጃ!!?
:
ድንግል ሆይ........??
:
ገመናዬን ለ"አክአብ" አትግለጪኝ፣
( ለአትክልተኛው ለ"ናቡቴ")
እናቴ ሆይ አንቺው ስጪኝ??🙏
( እርሷ በምልጃዋ ትጠብቀን!🙏)
✍️misgan
@Mis2081
🙏3
Signed Misge Ye አደራ ልጅ (21)
28 May 2026, 16:57 UTC142 views1 reactionsread 8 August 2026 ልክ ነው አይደለ.......???
አንድ ያፈቀረ ሰው........
እንደ እንደ በጋ መስኖ
ሰውነቱን ቢያርሰው፣
እንደ ጨረቃ ቤት
ገላውን ቢያፈርሰው፣
እንደ ጣና ባህር
እንቦጩን ቢጎርሰው፣
ልክ ነው አይደለ .....??
አንድ ያፈቀረ ሰው.....
ዱቤ ተበድሮ ውስኪ ቢገለብጥ፣
ላፈሰሰች ቤቱ ጋዜጣ ቢለብጥ፣
በነጣ መዳፉ እሳት ፍም ቢጨብጥ፣
አገር ስጡኝ ብሎ አገር ቢበጠብጥ፣
ልክ ነው አይደለ.....???
አንድ ያፈቀረ ሰው......
ቤተ መንግስት ገብቶ
ቁራጭ ሶፍት ቢዘርፍ፣
ቤተ ወንጌል ገብቶ
ፓስተሮቹን ቢገርፍ፣
ቢያሳድዳቸው በ'…
💯1
Signed Misge Ye አደራ ልጅ (21)
24 May 2026, 10:10 UTC154 views6 reactionsread 8 August 2026 ።።።።።።።።።።።።።
መረረብኝ ህይወቴ፣
ተዳከመች እምነቴ፣
መነመነ ጉልበቴ፣
ቅጡን አጣ ፀሎቴ፣
ሰላም ጠፉ ከቤቴ፣
ኑሮ ደፋኝ ባናቴ፣
አለም ገፋኝ ሰባቴ፣
የኔ ነገር ይሄው ነው...
አንቺው እርጂኝ እናቴ።
(ኪዳነምህረት ትርዳን!!🙏🙏)
✍️misgan
@Mis2081
❤4👍2
Signed Misge Ye አደራ ልጅ (21)
23 May 2026, 06:43 UTC227 views2 reactionsread 8 August 2026 ።።።።።።።።።።።።
እንደ መርገመ ፅድቅ
ተስፉችን የራቀው፣
እንደ ሰኔል ቅጠል
ፍቅር የደረቀው፣
እንደ በለስ ፍሬ
ደግነት የጠፋው፣
እንደ "ባሳን" ንጉስ
ልባችን የከፋው
⬇️
ያነፈርነው ንፍሮ፣
የከተፍነው ጎመን፣
ያሳረርነው ስንዴ፣
(የዚህ ሁሉ ልቅሶ)
ወደ እግዜር ቤት ጓዳ
ደርሶ ይሆን እንዴ ⁉️🤔
✍️misge
@Mis2081
( በቸርነትህ ይቅር በለን🙏🙏🙏)
❤1👍1
Signed Misge Ye አደራ ልጅ (21)
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Mis2081. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.