16 Sept 2021, 08:11 UTC913 viewsread 10 August 2026 " መቅደላዊት "
ክፍል ፳፪
በአምባዬ ጌታነህ
በዚህ ሁሉ መሀል ሜላት እያለቀሰች በስስት ትመለከተው ነበር። ልቧ ያለማቋረጥ ይመታል። የሚመታውን ልቧን ለማዳመጥ እጇን በሰደደች ጊዜ እንደ ጦር ይወጋታል። ለሷ ከደማሚት ልቆ የሚሰማትን የልብ ምቷን አጠገቧ ያሉት ሰወች የሚሰሙት መስሏት በሀፍረት ተሸማቀቀች። " ግን እኮ እሱ አይወደኝም ፣ በመጀመሪያ ቀን የራሱ እንዳደረገኝ አልተረዳም። ነፍሴን እንደሚያስጨንቃት አያውቅም። ለእኔ ግድ አይሰጠውም የሱ ግድ እራሱ ና አባቱ ነው።ምን ላደርግ እችላለሁ ? እንዴት ብየ የኔ አደርገዋለሁ እንዴት እንዲወደኝ ማድረግ ይቻለኛል? ሁሌም ቢሆን ይህ ነገር እኔ ላይ እንዳይደርስ እጨነቅ ነበር እሱን ላለማስከፋት ነው የ…
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
16 Sept 2021, 08:10 UTC758 viewsread 10 August 2026 " መቅደላዊት "
ክፍል ፳፩
በአምባዬ ጌታነህ
ሁሉም ታዳሚያን ዝግጅቱ ከመጀመሩ 30' በፊት ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል። ዝግጅቱ እስኪጀመር ደጄው አዳራሽ ያለውን ታዳሚ በሙዚቃ ፣ በግጥም እንዲሁም በአጫጭር ስላቅ ወጎች እየከፈተ ማዝናናቱን ይዟል። አስር ደቂቃ ሲቀረው ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዦች የተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ ተቀመጡ። መድረክ መሪው ማይኩን ጨበጠ " ክቡራትና ክቡራን የተወደዳችሁ የአንጋፋው እና የታሪካዊው አድዋ ዩኒቨርስቲ የስራ አመራሮች ፣ ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች እንኳን በደህና መጣችሁ" ጨብ ጨብ ጨብ ጨብ ጨብ ፣ አዳራሹ አስተጋባ መድረክ መሪው ከጭብጨባው በኋላ ማውራቱን ጀመረ። " እንግዲህ የዛሬው ምሽታችን በተወዳጅ እና በአዳዲስ ገጣሚያ…
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
15 Sept 2021, 05:06 UTC594 viewsread 10 August 2026 " መቅደላዊት "
ክፍል ፳
በአምባዬ ጌታነህ
የአድዋ መንገድ ዳሮች በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ወረቀቶች ተንቆጥቁጠው አሸብርቀዋል። የምሽቱ የስነፅሁፍ ዝግጅት ባመረ ማስታወቂያ እየተካሄደ ነው። " ታላቅ የጥበብ ድግስ! በአድዋ ዩኒቨርስቲ ሁለገብ አዳራሽ ! ታዋቂ እና ጀማሪ ገጣሚያን የሚሳተፉበት ድንቅ ምሽት ሳያወጡ የሚያተርፉበት ውብ ማታ በእለቱ ፣ ወጎች ፣ መነባንብ ፣ ዲስኩር፣ ሙዚቃዊ ተውነት፣ እንዲሁም ስላቅ እና ሌሎቹም የመድረኩ ክዋኔወች የተካተቱበት በአይነቱ ለየት ያለ ምሽት ነው ።እንዳይቀሩ ተጋብዘዋል" ማስታወቂያው በየ አምስት ደቂቃ ልዩነት ይቀርባል። ሁሉም ሰው ጆሮወቹ እና ቀልቡ ማታ በሚዘጋጀው የስነፅሁፍ ምሽት ነው። እንደገና ማስታወቂያው በመሀል…
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
15 Sept 2021, 05:05 UTC496 viewsread 10 August 2026 " መቅደላዊት "
ክፍል ፲፱
በአምባዬ ጌታነህ
ምን ያልገባሽ ነገር አለ ? ከጣፍኩልሽ ውስጥ? " ዝምታውን ለመስበር እና የውይይት መጀመሪያ እንዲሆን አስቦ ባሩክ የጠየቀው ጥያቄ ነበር። " ሀሳብህ በጣም ከባድ ነው እኔ ያን ማድረግ አልችልም እዚህ እኔን የሚያውቁኝ ብዙ ናቸው ። ቤተሰቦቸንም የሚያውቋቸው ተማሪዎች አሉ። አንተ ያልከውን ባደርግ እና ብል ያለ ጥርጥር ቤተሰቦቼ ጋር እቀያየማለሁ በስስት የሚያየኝን እና የሚወደኝን አባቴን እስከመጨረሻው አጣዋለሁ። እናም በጭራሽ አልችልም። ወይ ለዚህ ሀሳብህ ሌላ ሴት መፈለግ ሳይኖርብህ አይቀርም ።" አለች " የሀሳቡ አመንጪ እኮ እኔ አይደለሁም ይሄን የስነልቦና ህክምና የጀመራችሁት አንቺ እና ናታኔም ናችሁ…
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
14 Sept 2021, 20:32 UTC436 viewsread 10 August 2026 " መቅደላዊት "
ክፍል ፲፰
በአምባዬ ጌታነህ
ማን ነው ስራህን ያቀለለልህ? ምን አይነት ስራ ነበር የነበረህ? " ናሆም ጥያቄወቹን አከታተለበት ። " አሳይመንት ነበረኝ እሱን ሰርቶልኝ ነው " አለ ናታኔም በድንጋጤ " ታዲያ ምነው ደነገጥክ? " " በድንገት ስለገባህብኝ ነዋ " " እንደዛ ከሆነ ጥሩ ግን..... ምን አሳይመንት ነበር? እንዴት ስታወራ አልሰማህም?" አለ ናሆም " አየ ወንድሜ ለዚህ እኮ ነው እኔ እና አንተ ተጠፋፍተናል የምልህ ።ግን የስነፅሁፍ ዝግጅት አለብኝ ምናምን ብለኸኝ ነበር እኮ እንዴት ታዲያ ተመለስክ?" " ባክህ ያቺ መቅደላዊትን ከሩቅ አይቻት የሁሉም ነገር ፍላጎቴ ጠፋ " " ቆይ ግን ይቺ ልጅ ምን አድርጋህ ነው እንዲህ ጠ…
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
14 Sept 2021, 20:30 UTC377 viewsread 10 August 2026 " መቅደላዊት "
ክፍል ፲፯
በአምባዬ ጌታነህ
ናሆም ዶርም ሲገባ ናታኔም አልሰማውም ። ምክንያቱም ናታኔም በረንዳ ላይ ጀርባውን ለዶርሙ በር ሰጥቶ እያነበበ ነበር። ናሆም የሚቀይረውን ልብስ ቀይሮ ሊወጣ ሲል ናታኔም ደግሞ ቀና ሲል አይን ለአይን ይገጣጠማሉ ። ናታኔም ብድግ ብሎ "እንዴ ናሆም ደህና ነህ አሁንማ ተጠፋፋን እኮ ወንድሜ " አለ " በጣም ደህና ነኝ ወንድሜ ልክ ነህ በጣም ነው የተጠፋፋነው ግን ደግሞ ያው አንተም ስታነብ ነው የምትውለው እኔም ማንበብ ስለጀመርኩ ነው ።በል አሁን ቶሎ መውጣት አለብኝ " " ናሆም ወደየት ነው እንዲህ የምትቻኮለው? ቀስ በል እንጅ" አለ ናታኔም ወደ ናሆም እየተጠጋ " እየውልህ ወንድሜ ቶሎ መሄድ አ…
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
14 Sept 2021, 20:29 UTC345 viewsread 10 August 2026 " መቅደላዊት "
ክፍል ፲፮
በአምባዬ ጌታነህ
ነፋሱ ያለ ማቋረጥ ዝቅዝቅ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ይነፍሳል በዛፎች ዳር እና ዳር የታጀበው አስፓልት በወጀቡ ነፋስ በረገፉ አበባወች ተንቆጥቁጦ አንድ ሀፍታም ለአንዲት ሚስቱ ስጦታ ያነጠፈው መስሎ ሊረግጡት ያሳሳል። ከትንሽ ወጀብ ነፋስ በኋላ ያለ ምንም ግምግምታ ዝናቡ ጣለ ።መቅደላዊት ፀጉሯን በእጇ ሸፍና ወደ ራስ ተፈሪ ህንፃ ስትገባ ናሆም ያያት እና እሱም ወደ ህንፃው ተከታትሏት ገባ። መቅደላዊት ከመግባቷ እዛ የተጠለሉት ተማሪወች አይናቸውን ይጥሉባታል። አንደኛው " ይቺን ልጅ ላወራት ነው!" አለ ሌላኛው ቀበል አድርጎ" ሰው ይዘህ ነው ወይስ ራስህን ችለህ?" ሲለው "ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ራሴን ችየ ነ…
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
13 Sept 2021, 14:34 UTC332 viewsread 10 August 2026 " መቅደላዊት "
ክፍል ፲፭
በአምባዬ ጌታነህ
ዲዮጋን እና ናታኔም የአንድ ሰፈር ልጆች ናቸው ዲዮጋን የአራተኛ አመት የ electrical engineering ተማሪ ነው። ዲዮጋን የአራተኛ አመት electrical engineering department ሁለተኛ ሰቃይ ነው። "ህይወት እና ጥበብ ያበሰለችው፤ ልቦለዱን ከገሀዱ መንዝሮ በብልሀት የሚኖር ፤ የፍልስፍናው ቀበኛ ፣ ሰው ቢኖር እሱ ዲዮጋን ብቻ ነው "ይላል ናታኔም ሁልጊዜም ስለ ዲዮጋን ( ባሩክ ስስጢፋኖስ ) ሲናገር።
" ባሩክ ዛሬ አንድ የምነግርህ ትልቅ ነገር አለ እና በረቀቀ ሀሳብ ልትደግፈኝ ይገባል " አለ ናታኔም " እሽ አለ ባሩክ ( ዲዮጋን ) ከንፈሩን እያሸራመጠ
እየውልህ ባሩክ ናሆም ከእና…
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
13 Sept 2021, 14:34 UTC316 viewsread 10 August 2026 " መቅደላዊት "
ክፍል ፲፬
በአምባዬ ጌታነህ
የጠዋቷ ፀሀይ ገና ከመውጣቷ በጉም ተሸፍና ልውጣ አልውጣ ትላለች ከአድማስ ማዶ የሚታየው የፅሀይ ብርሀን ዶርሙን በፈገግታ ሞልቶታል አይኖቹን እያሻሸ ከእንቅልፉ ተነሳ እና እራሱን ከአልጋው ሳይወርድ ማነቃቃት ጀመረ።ናታኔም በተደጋጋሚ በቀኝ እጁ መዳፍ የቀኝ አይኑን ያሻል። አጭር ቁምጣ በቲሸርት በነጠላ ጫማ ተጫምቶ ከዶርሙ ወጣ ።ታች ሲደርስ ተማሪዎች ስለ ናሆም እያወሩ ይሰማ እና ጆሮውን በደምብ ሰጥቶ ያዳምጣል ።እንደው ይሄ ልጅ ምን አድርጎ ይሆን " አለ ። አንደኛው ተማሪ ደግ አድርጎታል ይሄ ቆሻሻ መምህር እሱን ቢሉ አዋቂ ጭራሽ ከእሱ በላይ ሰው ያለ አይመስለውም እንደው ገና ሳንጀምረው ምን አይነት ጠማማ …
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
12 Sept 2021, 21:00 UTC302 viewsread 10 August 2026 " መቅደላዊት "
ክፍል ፲፫
ንጋት የአህያ ሆድ መስሏል። ጨለማው በፅሀይ ፈገግታ ሳይሸነፍ አይቀረም ቀዝቃዛዋ ፀሀይ የምስራቅን አቅጣጫ ተንተርሳ ከእንቅልፏ የነቃች ትመስላለች ።የወፎቹ ጫጫታ ተግ ብሏል። ገሚሱ በየ ዶርሙ አንቀላፍቶ ሞቱን በእንቅልፉ ይሰልላል ።እንደ ናሆም አይነቱ ደግሞ በሌሊት ወፍ ጭጭ ሳይል ይነሳና በዶርሙ በረንዳ ሆኖ የተፈጥሮን ዑደት እያነሳ እየጣለ ስለ ሰማይ እና ምድር ፈጣሪ አልፋ እና ኦሜጋ ጥበብ እየተደመመ የመጀመሪያዋን የፅሀይ ጨረር በአይኑ ይቀበላል ። ናሆም በጧቱ ተነስቶ በረንዳው ላይ ተቀምጦ አንድ ሀንድ አውት ያገላብጣል ነገር ግን ሊነበበው አልቻለም ። በተመሳሳይ ስለ አንድ ነገር ያስባል ስለ መቅደላዊት ።የመቅደላዊት ነ…
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
12 Sept 2021, 20:58 UTC305 viewsread 10 August 2026 መቅደላዊት
ክፍል ፲፪
***
መቅደላዊት ስልክ እያወራች ናታኔም በመሀል ሲገባባት የመጀመሪያውን ስልክ " ቆይ አንድ ጊዜ መልሼ እደውላለሁ ስልክ ልቀበል አለችና የመጀመሪያውን ስልክ ዘግታ " መጣህ ናታን? "" አወ መጥቻለሁ የክበባት መንደር ከሚገኘው ካፌ ውስጥ ነኝ መምጣት ትችያለሽ " እሽ አሁኑኑ መጣሁ " አለችና ስልኩን ዘግታ ልብሷን መልበስ ጀመረች ።መቅደላዊት ለመልበስ አፍታ አልፈጀበታም ሜካፗን ብዙም ሳይበዛ ከተጠቀመች በኋላ ወደ ክበባት መንደር ገሰገሰች እንደገባች ወደ ውስጥ ገባ ያለች ቦታ ይዞ ስለነበር እዛ እንደሆነ በመገመት ገባች እና ከናታኔም ጋ ሰላምታ ተለዋውጠው ተቀመጡ። አስተናጋጇ መጣችና መቅደላዊትን እያየች " ምን ልታዘዝ ? " አለች "…
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
12 Sept 2021, 13:13 UTC275 viewsread 10 August 2026 እስኪ ቀለል ያለ ባል ፍልግልኝ ስናደድ እያነሳው የማፍርጠው አለችኝ😳😝😝
Signed ㄖㄩ丂爪乇 几乇Ꮆ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @MUBA_INFORMATION. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.