24 May 2026, 04:19 UTC292 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @AndkelemPhoto
ያኔ፤
የድሮ ድሮ ጥንት፤
ከአዱኛ ዝክንትል በፊት፤
አዳራሽ ሳይዘረጋ ፤ ገጸ መድረክ ሳይገለጥ፤
ኦርኬስትራ ሳይደመጥ፤
ላዕለ በገና ወክራር፤
ክሯ ሳይወጣጠር ፤ ቫዮሊን አንገት ላይ ወጥታ፤
ሕፃን ፒያኖ ተወልዶ አፍና ቁልፉን ሳይፈታ፤
ድራም ስሑት ሳይመነፍቅ፤
ከከበሮ ተገንጥሎ አስረሽ ምቺውን ሳይደልቅ፤
ሐሳውያነ መለከት፤
ሳይነሡ ሳክስ ፣ ትራምፔት፤
ሰብአ “Opera” ሳይንጫጩ፤
እም ኀበ አልቦ ሳይመጡ “Conducter” ከነልምጩ፤
ያሬድ ንዋያቱ ቅዱስ ፤ ያሬድ የዜማ ነቅዕ ምንጩ፤
በማኅሌታይ ዜማው ነበር።
በመቋሚያ እየዘመመ፤
በከበሮ በጸናጽል ፤ ምስለ ካህናት በአኮቴት ፤ አጥንት እያለመለመ።
አቦይ ሊቀ መኳስ “ሞዛርት”፤
የሙዚቃን ቀለም ይዟት፤
ለነገሥታተ አ…
❤1
Signed Kesatebirhan
2 May 2026, 10:38 UTC398 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @AndkelemPhoto
AND KELEM GE'EZ ACADEMY
*Registration Opened
In person (only 25 persons
for 1st round)
Online (Night time/Zoom)
*3 Days/ week for 1 hour.
*Secular Ge'ez that every one from from every religion and ethnicity can learn
*Registration stays through Gnbot and the class will start on sene segno.
*Integrate Classical way of teaching with modern.
DURATION - 6 month
CONT…
Signed Kesatebirhan
30 Apr 2026, 12:45 UTC279 views2 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @AndkelemPhoto
ከዛሬ ስድስት ፋሲካ በፊት ፣ በ2012 ዓ.ም ፣ ሰሙነ ኮሮና ፣ ምሳ ሰዓት ግድም ይመስለኛል። በቅርቡ የምሥራቅ አፍሪቃ አርታዕያን ማኅበር (EAES) ሆኖ የተመረጠው ዐዋቂውና ታዋቂው ጋዜጠኛ ፍትሕ ዐወቅ የወንድ ወሰንና የምወደው መምህሬ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ በ”አሐዱ ቲቪ” ዶክመንተሪ ቀመስ ቃለ መጠይቅ እያደረጉ ነው ቲቪውን ስከፍት የደረስኩት። መምህር “HOLY FIRE” የሚል ፣ ርእሱ በግልጥ የሚታይ የውጭ መጽሐፍ በእጁ ይዟል። የመጽሐፉ ጸሐፊ ሐሪስ ስካርላኪዲስ የተባለ ኦርቶዶክሳዊ ሲሆን በመጽሐፉም ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣባት ሌሊት ጀምሮ እስከ ዘንድሮ 2018 ዓ.ም ትንሣኤ ድረስ በየዓመቱ ሳይቋረጥ በተከታታይ በቅዱሱ መቃብር / Holy…
👍2
Signed Kesatebirhan
30 Apr 2026, 12:45 UTC293 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @Andkelem
የትርጉም ሥራውም ፣ አሰላ ሩፋኤል ሰፈር ዘማሪ ዳንኤል ጥበበ ሥላሴ ቤት ሳለሁ በሞራል ተጀመረ። አግብቼ ቱሉ ዲምቱ ስከ’ትም ተጠናከረ። አባ ወራነት ሲጫነኝ ግን ተዘንግቶ ቀረ። “ጊዜው ሲደርስ እምባ ይፈርስ” እንዲሉ አበው የትንሣኤው ጌታ በፈቀደለት ጊዜም ይኽውና የኅትመት ብርሃንን አየ። ለዚህ ውለታቸው ሊቁንም ፣ ፍትሕ ዐወቁንም አመሰግናቸዋለሁ በእናንተ በአንባቢዎች ስም።
እነሆ መጽሐፉን www.andkelempress.com ላይ ገዝተው Andkelem press mobile appን ከAppstore/playsore በማውረድ ያንብቡ።
___
www.andkelempress.com
www.andkelempress.com
Signed Kesatebirhan
27 Apr 2026, 03:24 UTC351 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @AndkelemPhoto
የቅዱሱ እሳት ለኢትዮጵያዊው ተጓዥ መውረድ/ገጽ 47
(ሙሉ መጽሐፉን ገዝቶ ለማንበብ)
👇👇👇👇👇👇👇
www.andkelempress.com
በ1470 ዓ.ም አካባቢ የተጠናቀቀው “ተአምረ ማርያም” 290 የተሰኘው ኢትዮጵያዊ መጽሐፍ “በእንተ ርደተ ብርሃነ ትንሣኤ” በሚል ርእስ አጭር ታሪክ የያዘ ሲሆን ማንነቱ ባልተገለጠ ፣ ኢየሩሳሌም በሚኖር ኢትዮጵያዊ ተጽፏል። ይህ ትረካ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የሆነ ዓመት ላይ በሽፍቶች ተደጋጋሚ ጥቃት ምክንያት ወደ ኢየሩሳሌም የሚደረግ የተሳላሚዋች ጉዞ እንደተቋረጠ ይነግረናል። በዚህም ምክንያት በዚያ ዓመት በቅዱሱ እሳት ሥነ ሥርዓት ላይ ጥቂት ተሳታፊዎች ነበሩ። ከእነሱ መካከል አንድ ኢትዮጵያዊ ተሳላሚ ነበር። …
❤1
Signed Kesatebirhan
25 Apr 2026, 11:34 UTC314 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @AndkelemPhoto
Photo, posted without a caption
Signed Kesatebirhan
13 Apr 2026, 16:29 UTC417 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @AndkelemPhoto
“ይህችውም ብርህትና ነጸብራቃዊት የቅድስቲቱ እሑድ ቀን መለኮታዊው ብርሃን ከመቃብር ውስጥ ግልጥ ሆኖ የታየባት ፣ በትንሣኤ ሠርግ ላይ እንደ ውብ ሙሽራ ናት።”
ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ
“እግዚአብሔር ዓመታዊውን ተአምር ማድረግ ፈቃዱ ባይሆን የሚናፈቀው ፣ ወደር የሌለው የጌታ የመቃብር ቦታ ምን ያህል ውድ ይሆን ነበር? . . . ወንድሞቼ ሆይ ይህን የሚያህል ድንቅ ተአምር ልቡን ያልነካው ማን ነው? እመኑኝ! እንደዚህ ዓይነት መለኮታዊ ጸጋ ተገልጦለት ወደ እምነት የማይሸጋገር ያ ሰው ጨካኝና ልበ ደንዳና ነው።”
የፖፕ ኡርባን ዳግማዊ
“አንድ ሡልጣን እንዳይበራ የመዳብ ሽቦ በፈትሉ ቦታ ላይ እንዳስገባ ታሪኩን የተረከልን ሰው ጨምሮ ነግሮኛል። ይሁን …
Signed Kesatebirhan
11 Apr 2026, 13:41 UTC392 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @AndkelemPhoto
በቅርብ ቀናት ይጠብቁ! በቅድመ ትእዛዝ ብቻ የሚሸጥ በመሆኑ መጽሐፉን መግዛት የምትፈልጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጠቅመው ወደ "የትንሣኤው ብርሃን ገዢዎች" group ይቀላቀሉ
https://t.me/+p8xAXG85vYtjMTRk
https://t.me/+p8xAXG85vYtjMTRk
Signed Kesatebirhan
10 Apr 2026, 08:49 UTC381 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @AndkelemPhoto
ጌታን ለሞት ያበቃው ሕማማተ መስቀል የቱ ነው?
(ከመጽሐፈ መሠረት ለጥያቄዎች መልስ ከተሰጠበት ምእራፍ የተወሰደ)
የጌታ ሕማማት ሁሉም አስጨናቂዎች ናቸው። ጌታ ከተቀበላቸው ጽዋትወ መከራ አንዱን ከሌላው ለይቶ “ይህ ያንሳል ፣ ይህ ይበልጣል” ለማለት አይቻልም። እነዚህን ሕማማት ባሰብናቸው ቁጥር ሕዋሳተ አፍኣና ሕዋሳተ ውስጥ ይንቀጠቀጣል። ስለዚህ የሊቁን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ይመለከቷል። ነገር ግን አንዱን የጌታ ሕማመ መስቀል ከሌሎቹ ሕማማተ መስቀል ለይቶ ለሞት ያበቃው የመጨረሻው ይህ ነው ብሎ ለመናገር ያዳግታል። ምሳሌ እንውሰድ።
አንድ ሌሊት በረዶና ዝናም(ውኃ) ቀላቅሎ ዘነመ እንበል። በዚህም ወጀብ ውስጥ ሰው ሞተ እንበል። “የገደለው የትኛው…
❤1
Signed Kesatebirhan
6 Apr 2026, 09:34 UTC390 views3 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @AndkelemPhoto
እዩት የምትወዱት አልቅሱለት ልቅሶን፥
"ለከ ኃይል ወስብሐት" በሉ "ኪርያላይሶን"፥
እንደ ቍጹረ ገጽ በዕንባ ሰባ ዘመን፥
ቢቻለን እንዘን፥
ቢሳነን እንመን።
(ዲ/ን ዘለዓለም ታከለ ከዘመረው "እዩት" የተሰኘ ግጥም ሥንኝ የተወሰደ)
ሌሎት 81 የጌታ ብቻ የሆኑ የዲ/ን ከሣቴ ብርሃን የመዝሙር ግጥሞች በAndkelem press በዲጂታል ኅትመት ወደ እናንተ ቀርቧል። በplay store እና በapp store "Andkelem press" mobile pressn አውርዳችሁ ሕማሙን በቅኔ ያድንቁ!
ለበለጠ መረጃ ይህን ድረ ገጽ ይጎብኙ!
www.andkelempress.com
____
t.me/andkelem
t.me/andkelem
❤3
Signed Kesatebirhan
29 Mar 2026, 05:48 UTC441 views1 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @Andkelem
https://youtu.be/AzAj_M1hG30?si=bnUNEktCRUJhzu3I
👍1
Signed Kesatebirhan
29 Mar 2026, 05:44 UTC421 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @daregotmediaPhoto
የኒቆዲሞስ ታላቅነት
በዚያ “አልቦ ዘመድ በጊዜ ተዋርዶ” በተባለበት ፣ ሐዋርያቱ እንኳ ጥለው በሸሹበት ዕለተ ዓርብ የልጇን መለኮት የተዋሐደው ሥጋ ከአርማትያሱ ሰው ከዮሴፍ ጋር ከመስቀል አውርዶ በቀበረ ጊዜ እመቤታችን ለኒቆዲሞስ የመረቀችው ምርቃት “ታላቅ ያድርግህ!”(1) የሚል ነበር።
ይኸውም ሲደርስ ሲፈጸም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የታላቁ አቢይ ጾም ፯ተኛ ሳምንት መጠሪያ አድርጎት ፤ በጾመ ድጓውም “ወሀሎ አሐዱ ብእሲ እምፈሪሳውያን ዘስሙ ኒቆዲሞስ ፣ዘሖረ ኀቤሁ ቀዲሙ ሌሊተ ፣ ወይቤሎ ለኢየሱስ እጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ ፣ አንሥአኒ በትንሣኤከ” (2) እያለ ዘምሮለት በዓመቱ ታሪኩ ሲነገር ታላቅነቱ ሲወሳ ይኖራል።
ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ https://tele…
Signed Kesatebirhan
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @KesatebirhanZeTewahdo. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.