9 Aug 2024, 08:11 UTC96 viewsread 9 August 2026 ሳቂልኝ
ሳቂ እንደ በፊቱ፣እንዳም ካቻምና፥
እንደ ከዚ ቀደም፣ እንደ ትላንትና።
ሳቂ ልመልከትሽ፣ ልክ እንደ በላቸው፤
እንደ የሳቅ ንጉስ፣ስቆ እንደሚያስቀው።
ሳቂልኝ የኔዓለም፣ ከትላንት ጨምረሽ፤
ከዓምና ከሀቻምና፣ ሺህ እጥፍ ደርበሽ፤
ሳቂልኝ እንዳሻሽ፣ እፅ እንደውሰደም፤
እንደ ሰከረ ሰው፣ እንደመረቀነም፤
በሳቅሽ ሙት ይንቃ፣ የደረቀ ይለም፤
ዘመኑ ይባረክ፣ የሕያዋን እድሜ ይርዘም፤
ይንጋ የጨለመው፣ በጥርስሽ ወገግታ፤
ይፈውስ ደዌያችን፣ እስራችን ይፈታ፤
እንሻር ጭለማውን፣ ይገፈፍ ድቅድቁ፤
ህዝቡን ሁሉ ይግረመው፣ ምዕመን ይደነቁ፤
በሳቅሽ ተረተው፣ ከዋክብት ሲወድቁ።
ሳቂልኝ ደጋመሽ፣ እንደትላንትና፤
እንደከዚህ ቀደም፣ እንዳምና ሀቻምና፤
በሳቅሽ 'ሚበራ፣ ጨለ…
Signed እኔ አባቴ አያቴ ወዘተ አዳም
Channel photo updated
23 Oct 2021, 13:17 UTC269 viewsread 9 August 2026 ሳልነግርሽ…
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አፍቅሬ እንዳጣሁሽ…
በነብያቶች አፍ፣
ፍልስፍና ሚመስል ፣ ትንቢት ተነገረ
ታምር የሚሰራ…
ጎትቶ ጎትቶ ፣
በመርፌ ቀዳዳ ፣ ግመል አሻገረ
ግመሉ ሲሻገር ፣ መርፌው ተሰበረ፡፡
በሰባራ መርፌ….
ፍቅርሽን ከፍቅሬ ፣ ባንድነት ልሰፋ
ይኸው እደክማለሁ…
ክር ሆነሽ እያጠርሽ ፣ ኖራለሁ ስለፋ፡፡
………………………………….
ሳልነግርሽ…
የኔ አለም ያላንቺ ፣እንደሆነ ራቁት
ባንቺ እንደነበር ፤ ቀንና ሌሊቴ የሚፈራረቁት፡፡
እንደተለየሽኝ …
አለም ባዶ ሆና ፣ መኖር እንዳስጠላኝ
ፍቅርሽ እከክ ሆኖ…
በልቤ ተተክሎ ፣ ነፍሴን እንደበላኝ፡፡
…………………………………
ሳልነግርሽ….
የነብያት ትንቢት ፣ በኔ መፈፀሙን
‹‹ታምሪያለሽ ›› እያልሁኝ …
Signed t------- T
6 Aug 2021, 15:10 UTC249 viewsread 9 August 2026 https://www.youtube.com/watch?v=V9ol2y85nTE&t=6s
Signed t------- T
Channel photo updated
22 Apr 2021, 20:50 UTC287 viewsread 9 August 2026 📝📝📰📰📘📗📙📚📚📖📖
የተለያዩ ምርጥ ምርጥ
መፀሀፎችን 📕📗📘📙📚
ያልተኖረ ልጅነት,ሰመመን,
ፍቅር እስከ መቃብር,በ Pdf ለማንበብና,📖📖
እመጓ,ሄክተር ፔተርሰን, ኦሮማይ,
በትረካ መልክ ለማዳመጥ 🎧🎧🎧
ከፈለጉ ቻናላችንን ይቀላቀሉ ።
🎧🎧🎤🎤🎧🎧🎤🎤🎧🎧🎤🎤
Signed t & T
29 Jan 2021, 20:08 UTC322 viewsread 9 August 2026 #ሀገር_የከፋት_ለት
፡
በቀን ግፍ ተገፍቶ ለመሄድ ሲገደድ
ሀገር ጸንታ ሳለች ሰው ነበር ሚሰደድ።
ግን እንዲህም ደሞ
ብሶት ከሰው ወርሳ
በእንባ ድጥ ርሳ
ከጫፉም ጫፍ ደርሳ
በጨካኞች ግፊ
አገርም እንደሰው ሲላት ጥፊ ጥፊ
ጨለማን አልብሼ…
ፊቷን ለመሸሸግ ቀኔን እያስመሸሁ
እንባዋን አብሼ…
የተሰበረውን ጥንድ እግሯን እያሸሁ
በጀርባዬ አዝያት ሀገሬን ባሸሸሁ።
ገጣሚ፦ ኢዛና መስፍን
Signed t------- T
28 Jan 2021, 10:39 UTC287 viewsread 9 August 2026 ሐረግ የወረረው የህንፃ ቅሪት ሳይ
(በእውቀቱ ስዩም)
ሐረግ የወረረው የህንፃ ቅሪት ሳይ
አንቺን አስባለሁ
የረገፈ ቅጠል፤ ከትልልቅ ዛፍ ላይ
አንቺን ያሳስባል
እኮ ለምን ቢባል
ምናቃለሁ እንጃ
ያለ ሰበብ ማሰብ ፤ የመለከፍ ፍርጃ
ግን ብፈልግ አጣሁ ያለ ሰበብ መርሻ
ትዝታሽ ወጌሻ
ሳይጠሩት የመጣ
ያለ ማደንዘዣ ራስ የሚበጣ
ልብን እንደ ሙዳይ ከፍቶ የሚገጥም
ብቻ
ላያስችል አይሰጥም!
ግንቡን አስረጅቶ ለሀረግ አውርሶ
ከትልቁ ዛፍ ላይ ቅጠሉን አፍልሶ
የሰጠውን ወስዶ ዘመኑ፤ ይነጉዳል
ብቻ
ባይድን ወይ ባይገድል ፤ ህመም ይለመዳል
Signed t------- T
23 Jan 2021, 06:30 UTC454 viewsread 9 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed t------- T
21 Jan 2021, 20:47 UTC446 viewsread 9 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed t------- T
20 Jan 2021, 21:15 UTC685 viewsread 9 August 2026 #ሀገር_የከፋት_ለት
፡
በቀን ግፍ ተገፍቶ ለመሄድ ሲገደድ
ሀገር ጸንታ ሳለች ሰው ነበር ሚሰደድ።
ግን እንዲህም ደሞ
ብሶት ከሰው ወርሳ
በእንባ ድጥ ርሳ
ከጫፉም ጫፍ ደርሳ
በጨካኞች ግፊ
አገርም እንደሰው ሲላት ጥፊ ጥፊ
ጨለማን አልብሼ…
ፊቷን ለመሸሸግ ቀኔን እያስመሸሁ
እንባዋን አብሼ…
የተሰበረውን ጥንድ እግሯን እያሸሁ
በጀርባዬ አዝያት ሀገሬን ባሸሸሁ።
ገጣሚ፦ ኢዛና መስፍን
Signed t------- T
20 Jan 2021, 21:11 UTC643 viewsread 9 August 2026 በስንት ምህላ
በፆም በሱባኤ...
ፅደቅብኝ ያልኩት ፥ ካልሳበሽ መድኔ
ሰይጣንሽን ጥሪው ፥ ይነጥልሽ ከኔ ።
#አብርሃም_ተክሉ
Signed t------- T
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @JoinAsSenatTSehufe. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.