29 Jul 2026, 11:06 UTC31 viewsread 8 August 2026 የልጆች ጉዳይ
~
* ልጆችዎ ክረምቱን በምን እያሳለፉ ነው? ሙሉ ቀን ከሳምንት ሳምንት በዋል ፈሰስ እንዳይባክኑ ቁርአን በመቅራት፣ ኪታብ በመማር፣ ሌሎች ተጠቃሚ ነገሮችን በመማር እንዲጠቀሙ ትኩረት እንስጣቸው።
* ትምህርት እናስመዝገብ። በዚህ ዘመን አለመማር ተራ ነገር አይደለም። ከተማ ውስጥ እየኖሩ ሳይማሩ ማደጋቸው ተፅእኖው ከባድ ስለሆነ ኋላ በጣም ይጎዱባችኋል፣ ያዝኑባችኋልም ጭምር። ያለንበትን ሀገር፣ እንዲሁም የዘመኑንም ተጨባጭ በጥልቀት በማሰብ መወሰን ይሻላል። በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ተፅእኖ ይሉኝታ አያስይዛችሁ። ደጋግማችሁ አስቡበት
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
28 Jul 2026, 02:58 UTC38 viewsread 8 August 2026 Photo
በነገራችን ላይ...ትዳር የሁለት ሰዎች ብቻ ሳይሆን የሁለት ባህልና ልማድ ስብስብ ነው። አንድ ሰው የራሱ አካባቢ ወይም የባህሉን ልጅ ቢመርጥ ይበልጣል። ይህ ማለት ከሌላ አካባቢ ማግባት ክልክል ነው ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ተመሳሳይ ባህል ያለው ሰው ሲሆን ትዳሩ የበለጠ ቀሊልና የተረጋጋ ይሆናል።
ምክኒያቱም የአንድ አካባቢ ልጆች አስተዳደጋቸው፣ አነጋገራቸው፣ በንግግራቸው መሃል የሚወረወሩ ዘይቤዎችን፣ የደስታና የሐዘን መግለጫዎች፣የዕለት ተዕለት የቤት ውስጥ ስርአቶችን ለመረዳት ተጨማሪ ተርጓሚ አያስፈልጋቸውም። አንዱ በዓይነ-እርግብ የሚሰጠውን መልዕክት ሌላኛው በልብ ብርሃን ይረዳዋል።ብዙ ጊዜ አባቶቻችንና እናቶቻችን የልጆቻቸውን ትዳር ሲያዩ «ሀገሩ እሩ…
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
7 Jul 2026, 03:15 UTC70 viewsread 8 August 2026 Photo
በነገራችን ላይ...ትዳር ማለት የዕድሜ መሸሻ ወይም የሰዎች ወሬ መዝጊያ ሳይሆን፣ ሁለት ነፍሶች በፍቅር የሚዋሃዱበት ጥምረት ነው።
ልቤ ሙሉ በሙሉ ያላረፈበትን፣ ፍቅሩን ያላገኘሁትንና ልቤን በሐሴት የማይሞላውን ሰው እንዴት የትዳር አጋሬ አደርገዋለሁ? ሳላገኘው ስቀር ናፍቆቱ የማይወዘውዘኝን፣ መውደዱ መውደዴን ቀስቅሶ ያልተጋባብኝን፣ ሲጠፋ እንኳ «የት ደረሰ?»ብሎ ልቤ የማይጨነቅለትንና ቅር የማይለኝን ሰው... ለምን ብዬ አገባዋለሁ?! «ቁማ ቀረች» ላለመባል ብቻ ዘው ብላችሁ ልባችሁ ያላመነበትን አታግቡ!
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
17 Jun 2026, 11:03 UTC97 views1 reactionsread 8 August 2026 ድንግልና እና ተውበት!
~
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ደካማ ነው። ስህተት የሰው ልጅ መገለጫ፣ ተውበት ደግሞ የልባም አማኞች ጌጥ ነው። ወንጀል ሰርቶ የማይሳሳት የለም፤ ነገር ግን ከስህተቱ ተምሮ፣ ተፀፅቶ እና አልቅሶ ወደ ጌታው የሚመለስ እርሱ እውነተኛ ጀግና ነው።
በተለይም በወጣትነት ዘመን በስሜት ተሸንፎ ወደ ሃራም ግንኙነት መውደቅና ከዛም ባስ ሲል ክብረ-ንፅህናን (ቢክራን) ማጣት ለሴት ልጅ እጅግ የከበደ ስነ-ልቦናዊ ጫና ይፈጥራል። ነገር ግን ዋናው ቁምነገር መውደቁ ሳይሆን፣ ከወደቁ በኋላ አቧራን አራግፎ፣ «ጌታዬ ሆይ ማረኝ» ብሎ በውነት መመለሱ ላይ ነው።
ጌታችን አላህ ወንጀልን ምሮ ተውበትን እንደሚቀበል ቃል ገብቷል። «ከወንጀሉ የተመለሰ ሰው እንደ…
❤1
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
9 May 2026, 03:27 UTC125 viewsread 8 August 2026 ╭─••──═••═─••─╮
✒️ ኡሚዬ ይቅርታ!
╰─••──═••═─••─╯
ላሳመምኩሽ ህመም ስትወልጂ ላማጥሽው
እኔን በማሳደግ ብዙ ለደከምሽው
ያኔ ላስቸገርኩሽ ልጅነት ሸውዶኝ
ድካም ልፋትሽን እንዳላየው ጋርዶኝ
ይቅርታ እልሻለሁ ደግሜ ደግሜ
እኔን በማሳደግ ለጨረሽው እድሜ
ይቅርታ ጠይቄሽ ጠብቃለሁ ምላሽ
እኔን በማሳደግ ለጠቆረው ገላሽ
ያኔ ያሳዘንኩሽ የነጠኩሽ ደስታ
አሁን ነው የገባኝ ኡሚዬ ይቅርታ
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
19 Mar 2026, 17:21 UTC172 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👍1
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
19 Mar 2026, 17:16 UTC138 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👍1
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
18 Mar 2026, 17:10 UTC68 viewsread 8 August 2026 Forwarded from @nuredinal_arebi
عاجل:
غدًا الخميس المكمّل لشهر رمضان.. والجمعة أول أيام عيد الفطر .
(المحكمة العليا)
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
27 Feb 2026, 12:22 UTC173 viewsread 8 August 2026 የመግሪብ በዕዲያ
~
ተምርና ውሃ አግኝተህ ካፈጠርክ "ጫማ ተራ" ያለው ግርግር እስከሚቀንስ ሁለት ረከዐ ቀለል ያለች ሱና ስገድ፣ የመግሪብ በዕዲያ። በር ላይ ያለውን ግርግር ካስተዋልከው በመቸኮልህና በመረጋጋትህ መካከል ያለው የቆይታ ርዝማኔ ኢምንት ነው። ጊዜው ረመዳን ነው፣ እያንዳንዱ ዒባዳ በተለየ የሚታሰብበት የተከበረ ወቅት። እያንዳንዱ ቀን ዳግም ላይገኝ እያለፈ ነው። ተጠቀምበት።
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
17 Feb 2026, 15:18 UTC189 views2 reactionsread 8 August 2026 ሰበር‼
======
የረመዷን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ሮብ የካቲት 11, 2017 E.C. የረመዷን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል። ተረዊህ ዛሬ ማታ ይጀምራል !!!
አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን!
ረመዿን ሙባረክ !!
❤1🎉1
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
16 Feb 2026, 03:39 UTC165 viewsread 8 August 2026 [ክፍል ሁለት]
☞ የሸእባን ወር ስራዎች ወደ አላህ የሚወጡበት ወር ነው።
ኡሳማ ኢብኑ ዘይድ ለነብዩ ﷺ" ሻእባንን እንደምትፆመው ሌላ ጊዜ ስትፆም አላይህም አልኳቸው" እንዲህ ሲሉ መለሱልኝ "ይህ ወር በረጀብና በረመዷን መሃከል ሰዎች የሚዘናጉበት ወር ነው። ይህ ወር ስራዎች ወደ አላህ የሚነሱበት ወር ነው። እኔ ደግሞ ፆመኛ ሆኜ ስራዬ ወደ አላህ እንዲነሱልኝ እፈልጋለሁ"።
🍊ጥቅል ስራዎች በሻእባን ወደ አላህ ይነሳሉ ፣የሳምንቱ ስራዎች ሰኞና ሀሙስ ላይ እንደሚነሱት ።
ነብዩ ﷺ
"የባሪያዎች ስራ በሳምንት ሁለት ቀን ሰኞና ሀሙስ ወደ አላህ ይቀርባሉ ፣ ለሁሉም አማኝ ምህረት ይደረግለታል ፣ በሱና በወንድሙ መሃከል ኩርፊያ/ጥል ያለበት ሰው ሲቀር ፣ የ…
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
16 Feb 2026, 03:39 UTC95 viewsread 8 August 2026 ሸህረ ረመዳን
{ክፍል አንድ}
🥕 ከአላህ ጥበቦች ውስጥ ወራቶች እና ወቅቶችን በደረጃ እንዲበላለጡ አደረገ። አሁን ያለንበት የሻዕባን ወር ለትሩፋር እንበረታ ዘንድ ደረጃውን ልናውቅ ይገባል።
★ የወራቶች ትሩፋት የሚገኙ በነሱ በመሠራት ነው ። ካልሆነማ እንደ ሌሎችንም ወራቶች ነው ሚሆነው።
🍎 ነብዩﷺ በሻዕባን መፆምን ያበዙ ነበር። ይህም የዚህ ወር ደረጃ ይጠቁማል
አኢሻ እንዲህ ትላለች" ነብዩﷺ አያፈጥሩም እስከምንል ድረስ ይጾሙ ነበር እንዲሁም መልሰው አይፆሙም እስከምንል ድረስ ያፈጥሩ ነበር ፣ ነብዩﷺ ወር ሙሉ ሲፆሙ አላየሁም ረመዳን እንጂ፣ አብዛኛው ሲፆሙ አላየሁም ሻዕባንን እንጂ " ትላለች
☞ እዚህ ጋር ሌላ ሐዲስ አለ ነቢዩﷺ"አንዳችሁ …
Signed 𝐉𝐥𝐚𝐥𝐮 𝐍𝐞𝐬𝐫𝐞
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @JlaluNesre17. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.