9 Mar 2026, 13:12 UTC67 viewsread 7 August 2026 💫💫
ለ አሽረል አዋኺር መረሳት የሌለባቸው 3 ነገሮች
💞💞
-ለመስራት ቀላል
-ቦታ የማይመርጡ
-ጊዜ የማይወስዱ
-ትልቅ አጅር የሚያስገኙ
💞💞
💌በየቀኑ ከኢሻዕ ቡሃላ ቢያንስ 1ብር ሰደቃ ላገኘነው ድሀ መስጠት
💮1ዱ ለሊት ለይለቱል ቀድር ላይ ስለምንሰጥ 84 ዓመት ሙሉ ሰደቃ የሰጠን ያህል ይፃፍልናል
💌ሁለት ረከዐ በየለሊቱ መስገድ
💮ለይለቱል ቀድር ላይ 84 ዓመት ሙሉ ለይል እንደቆምን ይፃፍልናል
💌ሱረቱል ኢኽሏስ 3 ጊዜ መቅራት
💮ሱረቱል ኢኽላስ 3 ጊዜ የቀራ ሰው ቁርአን ሙሉ እንደቀራ ይቆጠራል፡ ለይለቱል ቀድር ላይ ስንቀራ 84 ዓመት ቁርዓን እንዳከተምን ይፃፍልናል
💥ሱብሀነላህ!!
ይሄን መልዕክት ቢያንስ ለ30 በመላክ ተጠቃ…
Signed يسرى
27 Jan 2026, 18:39 UTC84 viewsread 7 August 2026 ✍"ኢንሻ አላህ ይህን ወንጀል ነገ እተወዋለሁ..."
🩸ይቺ ቃል የብዙዎቻችን ማደንዘዣ ሆናለች። መጀመሪያ "ስህተት" ብቻ ነበር፤ ቀጥሎ "ልምድ" ሆነ፤ ዛሬ ነገ ስንል ግን ተዋህዶን "ሱስ" ሆኗል።
♻️ወዳጄ ሆይ! የሞት መልአክ "ነገ እመጣለሁ" ብሎ ቀጠሮ አይሰጥም። ዛሬ ነገ እያልን የቀጠሮ ሰንሰለት ስንሰራ፥ ልባችን በወንጀል እንዳይዝግና የመመለስን በር እንዳንረሳው እፈራለሁ።
🍁 ተመለስ! አላህ አሁንም በራህመቱ እጁን ዘርግቶ ይጠብቅሃል። መመለሻህ "ነገ" ሳይሆን "አሁን" ይሁን።
☝️አላህ ካለበት መጥፎ ልምድ ተላቆ፣ ወደርሱ ከሚመለሱት ያድርገን!🤲
Signed يسرى
19 Jan 2026, 10:46 UTC89 viewsread 7 August 2026 ዓለም በተኛችበት፣ ጸጥታ በነገሰበት እና የሌሊቱ ጨለማ ምድሪቱን በውጠበት ሰዓት... አንድ ድንቅ "ቀጠሮ" አለ። የፍጡርና የፈጣሪ ልዩ ግንኙነት!
ሞቅ ያለውን ፍራሽ፣ ጣፋጩን እንቅልፍ ትቶ ለጌታው የሚቆም ሰው እንዴት የታደለ ነው? አካልህ በውሃ ሲነካ የልብህ ዝገት ይራገፋል። ግንባርህ መሬት ላይ ሲያርፍ፣ ነፍስህ ወደ ሰማይ ትመጠቃለች።የለይል ሶላት ማለት የቀን ውጣ ውረድ ያጎበጠውን ጀርባህን የምታቃናበት፣ በሰዎች ፊት ያጣኸውን ክብር በፈጣሪህ ፊት የምታገኝበት ልዩ መድረክ ነው። ማንም ሳይሰማህ፣ ማንም ሳያይህ... አንተ ታወራለህ፤ እሱ ይሰማሃል። ችግርህን በሹክሹክታ ስትናገር፣ መፍትሄው በገሃድ ይወርዳል።
እመነኝ! በለይል ሶላት ላይ ሆኖ ያለቀሰ ዓይን…
Signed يسرى
20 Dec 2025, 18:20 UTC86 viewsread 7 August 2026 #ኸይር_ኹሉ_የሚፈስበት_ረጀብ
«የተባረከውን የረጀብን ወር ሀቅ (ክብር) በብዛት እስቲግፋር በማድረግ (ምሕረት በመለመን) ተጠቀሙበት፤ ጌታችሁ በዚህ ወር ውስጥ ከእሳት ነጻ የሚያወጣቸው ባሮች አሉትና።»
ሙረቢ ሐቢብ አቡበክር መሽሁር (ቀደሰላሁ ሲረሁ)
ምሕረት መለመንን በማብዛት ብቻ ኸይን የምንከጅልበት ታላቁ ወር ዛሬ ለይል ይገባል። ይህን ለሊት ምህረት በመለመን መጀመሩ ይወደዳል። በዚህ ለሊት ጸሎት (ዱዓ) በይበልጥ ለተቀባይነት የቀረበ እንደኾነም በአንዳንድ ዘገባዎች ተገኝቷል።
በዱአቹ አትርሱኝ!🖤
Signed يسرى
19 Oct 2025, 17:58 UTC105 viewsread 7 August 2026 ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
ታላቁ አባት ሐጂ ኡመር ኢድሪስ አረፉ።
ይሄ ውብ ፈገግታ ፤ ይሄ ጣፋጭ አንደበት ፤ ይሄ በሁሉ ሰው የሚወደድ ተግሳፅና ንግግር ከእንግድህ በሀያት ላንሰማው አላህ ወሰነ።
ከነግርማቸው ሁሉ እንደወደዳቸው ፤ እምነት ሳይለይ ሁሉ እንደሳሳላቸው ፤ ምሁሩ ተራው ህዝብ ሳይቀር እንተማረከባቸው ተከብረው ከነ ለዛቸው ይህችን ጠፊ ዱኒያ ተሰናበቷት።
ዒልምን ለማድረስ የሚተጉ! ኡማውን ለማስተማር እንቅልፍ ያጡ የሕይወት አቅጣጫን አመላካች
ስንቱ በዱአ ቢጨነቅላቸውም አላህ ለእርሳቸው የተሻለውን መረጠላቸው።
አላህ ከሚወዷቸው ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ጎረቤት ያድርጋቸው።
የዚህ ሁሉ ኸልቅ ውዴታ ከአላህ ዘንድ ትልቅ ምስክር ነው…
Signed يسرى
7 Sept 2025, 18:26 UTC98 viewsread 7 August 2026 للهم ارحمنا إذا برق البصر وخسف
القمر وجمع الشمس والقمر، اللهم
اجعل خسوف القمر هذا رحمة لنا ولا
تؤاخذنا بذنوبنا ولا تنزل غضبك علينا
واغفرلنا وارحمنا يا ارحم الراحمين🤲
Signed Feruz S
23 Aug 2025, 16:47 UTC109 viewsread 7 August 2026 Assalamualikum, I want to ask you a small request if you can, and I know that you will be able to. We want to do a campaign for Gaza, so I want you to send this sentence (Glory be to Allah and praise be to Him, O Allah protect Gaza and its people, O Allah, may peace and blessings be upon Gaza and its people) to 20 friends. This is a trust and request to Allah for His intervention. Salam, can you share with your group…
Signed Feruz S
4 Jun 2025, 19:06 UTC126 viewsread 7 August 2026 ሰዎች "ዱዓ አድርጉልኝ" የሚሉት ገንዘብ ስለቸገራቸው ብቻ አይደለም። የሚጠቃቀሙበት ወጪ መሸፈን ስላቃታቸው ብቻም አይደለም። በርግጥ ዱንያ ልጋጋም ነች አስቀይማቸው ሊሆን ይችላል።
ሰዎች ሰውን ፈልገው "ዱዓ አያድርጉልኝ" ሊሉ ይችላሉ።
ከአላህ ጋር ያላቸውን ቅርርብ ለማስተካከል "ዱዓ አድርጉልኝ" ሊሉ ይችላሉ። አብሽሩ፤ አይዟችሁ የሚላቸውን ፈልገው "ዱዓ አድርጉልኝ" ሊሉ ይችላሉ። ፈተናዎቻቸው በዝተው መቋቋም ተስኗቸው ዱዓ አድርጉልኝ" ሊሉ ይችላሉ።
አኼራቸው አስጨንቋቸው ወንጀላቸው አሳስቧቸው "ዱዓ አድርጉልኝ" ሊሉ ይችላሉ። እራስን ስለ ማጥፋት እያሰቡ ከዚህ ሀሳብ እንዲላቀቁ ዱዓ አድርጉልኝ ሊሉ ይችላሉ። ተስፋ እንዲቆርጡ የሚያስገድዳቸው ነገር ዙርያቸውን ከ…
Signed Feruz S
27 May 2025, 18:41 UTC121 viewsread 7 August 2026 🌟የተከበረው የዙል ሂጃ ወር ነገ ይጀመራል
ከጃቢር እንደተዘገበው ረሱል እንዲህ ብለዋል
" ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው 10ቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው"አልበዛር ዘግቦታል
በሌላ ሐዲስ
"በነዚህ10ቀናቶች ውስጥ ከሚፈፀም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆንባቸው ቀናት የሉም.."ቡኻሪ
በነዚህ ውድ ቀናት ፆም ፣ሰላት ፣ሰደቃ፣ዚክር ፣ለይል መስገድ፣ቁርዓን መቅራት ፣ዱዓ፣ ተክቢራ ማለት፣ወላጆችን መታዘዝ፣የታመመን መዘየር፣የተቸገረን መርዳት...በሌሎችም መልካም ስራዎች ልንበረታ ይገባል ከሁሉም ወንጀሎች ልንርቅም ይገባል
አላህ ጊዜያቸውን በኢባዳ አሳልፈው መልካም ስራቸውን ከሚቀበላቸው ባሮቹ ያድርገን🤲🤲
Signed يسرى
23 May 2025, 06:10 UTC118 viewsread 7 August 2026 ዱአ አዘጋጁ
እነዛ ታላላቅ የአረፋ /የዙል-ሂጃ ቀናቶች እየመጡ ነዉ
Signed Feruz S
31 Dec 2024, 18:07 UTC183 viewsread 7 August 2026 File
I am sharing 'جوامع الادعية' with you
Signed يسرى
31 Dec 2024, 18:06 UTC197 viewsread 7 August 2026 ነገ ረጀብ አንድ ብሎ ይጀምራል። ዛሬ ምሽት ከመግሪብ ጀምሮ እስከ ፈጅር ድረስ ዱዓ መቅቡል ከተደረገባቸው አምስት ለሊቶች መካከል አንዱ ነው።
እንደተፋዑል ጃንዋሪ 01/2025 ነገ ነው። ረጀብ አንድም ነገ ይጀምራል። በነጮቹ የአመቱ መጀመሪያ ዕለት የሻዕባንና የረመዳን ዋዜማ ወር የኾነውን ረጀብን እንጀምራለን። ወሩን በተለዩ አምልኮዎች ለማጌጥ ኒያችንን ከፍ በማድረግ እንጀምር።
መልካም አዳር😍
Signed يسرى
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Islamicknowledgechanal. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.