4 Apr 2022, 20:01 UTC≈1,030 views15 reactionsread 9 August 2026 የመጠቁ ሀሳቦች
፨፨፨
"ጎበዝ ሰው ለጥያቄዎች በሚሰጠው መልስ ይታወቃል። ብልህ ሰው ግን በሚጠይቀው ጥያቄ ይመዘናል።"
"ድርቅ የተፈጥሮ ምክንያት አለው። ርሀብ ግን ሁሌም የተዛባ ፖለቲካዊ መስመርና ፖሊሲ ውጤት ነው። "
"...ሞኝ አትሁን! ፍቅር፣ ወሲብ፣ ምናምን ቀድሞ የተዘጋጀ ቀመር የለውም። የምክንያትና የሎጂክ ጣጣም አያውቅ። ድንገት ብቅ ይላል፣ ሀሴት አዝንቦልህ መልሶ ይሰወራል። እንደገና ትናፍቀዋለህ። ይሄንን የተፈጥሮ ሕግ እንኳንስ አንተ የፍቅር አማልክት ሊለውጡት አይችሉም ።..."
"ምሥጢር በትክክል ምሥጢር የሚሆነው የአንተ እስረኛ ሲሆን ነው። ሌላ ሰው ጆሮ ከደረሰ ግን አንተ የምሥጢርህ እስረኛ ትሆናለህ!..."
"የሚኖሩለት ዓላማ አ…
👍15
4 Apr 2022, 19:52 UTC874 viewsread 9 August 2026 🌺🌺🌿#የፍቅርሽ_ትንታ🌿🌺🌺
በረቀቀ ጥበብ በረቀቀ ሚስጥር
ያለምንም ስስት ያጎረሺኝ ፍቅር
ጨጓራዬን ትቶ ልቤ ላይ በማረፍ
በፍቅር ትንታ ዘውትር ስንደፋደፍ
ይሻለኛል ብዬ ከዛሬ ከነገ
ጀርባዬን ባስመታም ይባስ እያደገ
ሊለቀኝ አልቻለም የፍቅርሽ ትንታ
ውሀም ብጠጣበት ጠዋትና ማታ።
4 Apr 2022, 18:59 UTC849 viewsread 9 August 2026 " አንድን መርከብ የሚያሰጥመው በዙርያው ያለው ውሃ ሳይሆን ወደ ውስጡ የሚገባው ውሃ ነው ። አንተም በዙርያህ በሚከቡ መጥፎ ድርጊቶች ሳይሆን ውስጥህ እንዲገቡ በፈቀድክላቸው ማንነቶች በማይረባ አመለካከት መስጠምህም ሆነ በመልካምነት ወንዝ ላይ መንሳፈፍህ ሁሉቱም ባንተ ይወሰናል ። የከበበህ ሁሉ ሳይሆን ውስጥህ እንዲገባ የፈቀድክለት ነው ጥፋትህንም ኑረትህንም የሚወስነው "
2 Apr 2022, 20:48 UTC782 viewsread 9 August 2026 ወዳጆቼ ፍቅር ማለት እንዲህ ነው…እጅ መስጠት፣ ወዶ መግባት፣ ከራስ መነጠል፣ መጥፋትና በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ነው በቃ ፍቅር እንዲህ ሲሆን ነው ትክክለኛ ስሜቱ የሚታወቀው😍
2 Apr 2022, 18:41 UTC723 viewsread 9 August 2026 . 人 ★* 。 • ˚* ˚ 🌙
. (_ _) * RAMADAN * ★
. ┃口┃ * KAREEM *
. ┃口┃★ * ***. . *˛•
. ┃口┃★ * •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ *
. ┃口┃ .-:'''"''''"''.-.
. ┃口┃ (_(_(_()_)_)_)
┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ┃. ┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. 三_三三三三三
𝚓𝚘𝚒𝚗 & 𝚜𝚑𝚊𝚛𝚎
29 Mar 2022, 22:16 UTC753 viewsread 9 August 2026 የተግባር ሰው ሁን!
"ስፖርት መስራት እጀምራለሁ፣ አንድ መፅሀፍ በሳምንት አነባለው፣ በጠዋት እነሳለው፣ ራሴን አሻሽላለው" ብለህ ካሰብክ ቆየህ ፤ ግን መቼ ነው ወደ ተግባር የምትገባው? ሁልጊዜ ሰኞ ሲመጣ ወይ ወሩ ሲያልቅ፣ ወይ አመቱ ሲፈፀም ማቀድ አልሰለቸህም?
ወዳጄ ምግብ የበላ እንጂ ለመብላት ያሰበ አይጠግብም እኮ! መድሀኒቱን የዋጠ እንጂ ስለ መድሀኒቱ አብዝቶ ያወቀ አይድንም እኮ! ማወቅ ማሰብ ማቀድ አሪፍ ቢሆንም ተግባር ከሌለው ግን በዜሮ ነው ሚባዛው! ስለዚህ አንዱን ዕቅድ አሁኑኑ ጀምረው! ዳይ ወደ ተግባር!
የተግባር ህይወት ተመኘንላችሁ🙏
@Yemuu
29 Mar 2022, 21:17 UTC636 views1 reactionsread 9 August 2026 አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል!!
ገበሬው በአቅራቢያው ያለ ጃምቦ ቤት በቀን አረቄ በጃንቦ ይጨልጣል።
አንድ ሌላ የሚያውቀው ሰው ይመጣና ይጠይቀዋል
" በዚ የስራ እና የምርት ሰዓት ግን እዚ መጠጥ ቤት ምን ታደርጋለህ?"
ገበሬው ጭንቅላቱን እያወዛወዘ
"አንዳንድ ነገሮችን ማብራራት ይከብዳል።" ይላል።
ሰውዬው ወንበር ስቦ እየተቀመጠ ገበሬውን ይጠይቀዋል
"ወዳጄ ምን ሆነህ ነው ንገረኝ፣ሲያወሩት ይቀላል"
"እሺ ካልክ...!" ብሎ ገበሬው ይጀምራል
"እሄውልህ ዛሬ ጠዋት ተነስቼ ግብርና በብድር የሰጠንን ነጯን ላም እያለብኩ
ነበር። አንድ እቃ እንደሞላው ግራ እግሯን አንስታ የታለበውን በሙሉ ደፋችው"
"እሺ ግን ይሄ እኮ ታድያ ብዙ አያስከፋም ለዚህ ሁኔታም…
👍1
29 Mar 2022, 20:12 UTC539 viewsread 9 August 2026 ተቃራኒ ኑሮ .....😊 / 😞
ሁለት ሰዎች አሉ ተቃራኒ የሆኑ
ካንዱ ደስታ ሲሆን አንዱ የበዛ ሀዘኑ
አንደኛው ሞልቶለት ፍላጎቱ ብዙ
ሁሉም ተትረፍርፎ የበዛ መዘዙ
ቄንጠኛ መኪና ቄንጠኛ አለባበስ
ዉድ ዉድ እቃዎች ሁሉንም ሲያዳርስ
መስጠት ያላወቀ መቀበልን ብቻ
ዉስጡ ሰላም ያጣ ያነፀዉ ጥላቻ 😡
ሁልጊዜ የሚኖር ለገንዘቡ ብቻ🤑
በዛዉ ልክ ደግሞ ይሄኛው ድሀ አለ
የቀን ገቢ ዉሎዉ ለምግብ ያልዋለ
ቀኑን የሚጀምር ጌታን አመስግኖ
ህይወቱን የሚኖር በስራ መንኖ
የእሱ ሀብት ድሎታዉ ፈጣሪ የቸረዉ
የጤና ሀብተኛ ሁን ብሎ የመረቀዉ
ታዲያ ያኛው ለምን ጤና የጎደለው???
ሁሉንም አግኝቶ የበዛለት ተድላዉ
ያሻውን አድርጎ ያማረውን በልቶ
ትንሽ ደበር ሲለው ራሱን አዝናንቶ💆♂…
29 Mar 2022, 19:42 UTC507 viewsread 9 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
29 Mar 2022, 19:39 UTC496 viewsread 9 August 2026 እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣
ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡››
[ በፍልስፍና መደመም - ገፅ 40 ]
29 Mar 2022, 19:19 UTC487 viewsread 9 August 2026 ጨዋታ.....🤡
አንዳንዴ የሰጠነዉ ለፍቅራችን ቦታ
ሆኖ ስናገኘው ለየቅል ለአንዳፍታ
ብዙ አጋነነዉ ለሰው እስኪሰለች
እርግጠኛ ሆነን አዉርተን ለሰዎች
ሁሉም እስኪገረም ጭኖ እጁን በአፉ ላይ
ለፍቅራችን ቦታ ሰጥተን ከሞት በላይ
ጥርጥር ሳይገባን ለነሱ ያለን እምነት
ሰዉ ሁሉ ቢያማልን ስንላቸው ዉሸት
ከአልማዝ ከእንቁ በላይ ስንሳሳላቸዉ
ልፋታችን እነሱ በመዳብ ቀይረው
ምንም ሳንጠረጥር ሳይገባን ቅሬታ
አደረጉት እኮ ፍቅርን ጨዋታ።
✍ ፅጌሬዳ አስናቀዉ
29 Mar 2022, 09:41 UTC471 views3 reactionsread 9 August 2026 "ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"
# በህይወት እስካለህ:-
:
ልትሳሳት ፣ልትወድቅ ትቸላለህ ፣
:
ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣
:
ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ፣ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣
:
በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣
:
ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።:"
:
☞በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው።
:
መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል።
:
አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል።
:
ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል።
:
ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞ…
👍3
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Human_intellegence. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.