11 Sept 2021, 19:26 UTC310 viewsread 11 August 2026 ....በትላንት የትዝታ ስቃይ በነገው የህልም ስቃይ በዛሬው የህይወት ስቃይ መሀከል መሆን ምነኛ ይከብዳል።...
...ግን በህይወት የሚኖር ሰው በነዚህ ሶስት ነገሮች ውስጥ ማለፉ የግድ ነው።...በመቃብር የተሞሉት የአእምሮዬ እና የልቤ ጓዳዎች ሌላ ቦታ እስከማይኖራቸው ድረስ በተቀበሩ ሀሳቦች እና በተቀበሩ ፍቅሮች 🖤 ተሞልተዋል።...ግን ደስ የሚለው ነገር በዚያው ልክ አእምሮዬም አዲስ ሀሳብ ማመንጨቱን ልቤም አዲስ ፍቅር ማለሙን አላቆመም ።...ለዛም ነው ተስፋ ያለኝ...ትላንትናዬን ከዛሬዬ ፤ ዛሬዬን ከነገዬ ለማስማማት በማደርገው ጥረት ብዙ ፈተናዎች እየገጠሙኝ ነው።...የማወራው ስለ ፍቅር ፤ የማወራው ስለ ቤተሰብ ፤ የማወራው ስለ ጎደኛ …
Signed ቋንቋዬ ነሽ ድንግል ❤
23 Aug 2021, 12:25 UTC366 viewsread 11 August 2026 <የታፈነ ጩኸት>
✍ትዝታ ለገሠ
በፅልመት አለም ላይ የዝምታ ጉዞን
የታፈነን ጩኸት የማይገልፅ ልሳን
ዝምታም በሆዱ ጩኸትን አርግዞ
የህይወት ጎዳናን በጭንብል ሸፍኖ
በፈለከው ሳይሆን በፈለገው አረጎ ያኖራል አፍኖ
በዝምታ ሚዛን ትዝታ እና ተስፋ
ያለውም ሲወቅሰኝ ለመጪው ስለፋ
በዝምታ መርከብ አጥብቦ ወስኖ
ለመኖር ስታክት ሀሳብን ገድቦ
ቆይቶ ቆይቶየተፈታ ለታ የታፈነ ጩኸት
ዘግይቶ ዘግይቶ ደግሞም ከፈነዳ
ሁሉን ይመርዛል ለማንም ሳይዳዳ
የታፈነ ጩኸት
የውስጤን የሚገልፅ ግጥም ነው ተጋበዙልኝ
#share_join
@Hiluysss.......@Hiluysss
@Hiluysss........@Hiluysss
@Hiluysss.....…
Signed ቋንቋዬ ነሽ ድንግል ❤
22 Aug 2021, 19:41 UTC295 viewsread 11 August 2026 ።።።።።።።።።።።ታማችኋል።።።።።።።።።።
በአፍላ ትጀምራላችሁ በወረት ትተዉታላችሁ ያወቃችሁትን ትረሳላችሁ፤ያላወቃችሁትን ለማወቅ ትጥራላችሁ የያዛችሁትን ትረግጣላችሁ፤የረገጣችሁትን ትይዙታላችሁ፤ምኞታችሁ ልክ የለውም፣አምሮታችሁ ብዙ ነው፣ያማራችሁን ስታገኙ ወዲያው ይሰለቻችኋል፣ ተው የተባላችሁትን ትሽራላችሁ፣የተከለከላችሁትን ትደፍራላችሁ፣የተፈቀደላችሁን ችላ ትሉታላችሁ
# ቤተ መቅደስ እንዳትገቡ ብትከለከሉ ወደፊት ቤተመቅደሱን በመስታወት ሰርታችሁ መቅደስ ባትገቡ እንኳን ሁሉን ከውጪ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ፣ ሁሉን ማወቅ ትፈልጋላችሁ በአንዱም ግን አትጠቀሙበትም... ሁሉ አላችሁ ግን ባዷችሁን ናችሁ ኃይማኖት እንጂ እምነት የላችሁም ጥበብን ሀ-ግእዝ ብዬ ላስተ…
Signed ቋንቋዬ ነሽ ድንግል ❤
21 Aug 2021, 21:45 UTC222 viewsread 11 August 2026 የሰው ልጅ ውስጡን ማየት ካልቻለ ፍቅርን ፍለጋ አለምን ቢያካልል ይንከራተታል እንጂ አያገኘውም። ሰው እንጀራ ፍለጋ በየበረሀው በረሀብ እና በድካም ሲወድቅ ፤ በየባሕሩ ሲሰምጥ እናያለን😒። ፍቅርን ፍለጋ ግን አንድ እርምጃ ወደራሱ ልብ በመመለስ ለፍቅር ሲወድቅ አላየንም😼
አንዳንድ ሰው በመጠጥ ሰክሮ ሲንገዳገድ እናያለን🙄። በፍቅር ሰክሮ ግን የወደቀ አላየንም🙆♂ ጥቂት የማይባሉ አምሺዎች ምሽታቸውን በአስረሽ ምቺው ቤት ሲያሳልፉ እናያለን። ቤታቸው ሲገቡ ግን ደስታም ሆነ ፍቅር የለም።ሰው ለደስታ እያለ ይጠጣል በጊዜያዊ ደስታው ውስጥ ግን ፍቅርን ረስቶዋል። የጠበበውን የሚያሰፋ፤ የራቀውን የሚያቀርብ ፤ የጨነቀውን ሚያረጋጋ፤ የደከመውን የሚያሳርፍ ልከኛ መድሀኒ…
Signed ቋንቋዬ ነሽ ድንግል ❤
15 Aug 2021, 18:11 UTC297 viewsread 11 August 2026 🟪አልወዳትም እንጂ አልጠላትም
#ክፍል_አራት
#ተከታታይ ልቦለድ
'ከቤቴ ውጪልኝ' የሚለውን ዘላ 'ከህይወቴ ውጪልኝ' ያልኳትን ሰምታኝ መሰለኝ....... የሞተችው......
"ኤዱዬ የኔ ከህይወትሽም ከቤትሽም መውጣት አንቺን አያስተካክልሽም!! Let us make this right!! ላግዝሽ?" አለችኝ ....
"የቱን? የቱን ነው የምናስተካክለው?" አልኳት "ያንቺ እህት አለመሆኔን? ንገሪኝ ከየት እንጀምር? ገና ሳልወለድ ቤተሰቦችሽ ከከዱኝ? ወይስ ለ13 ዓመት እማ አባ ያልኳቸው ቤተሰቦቼ ሳይሆኑ የወለደችኝ ሌላ ሴት መሆኗን እንዴት ነው የምናርመው? ከየት እንጀምር ንገሪኝ? .... ጥፋት ሳጠፋ 'ዘር ከግንዱ ይመዘዛል' እየተባልኩ .... በራሴ መንገድ ስ…
Signed Hïlüshä 💞💞
15 Aug 2021, 15:24 UTC231 viewsread 11 August 2026 ምርጥ ምርጥ የኢትዮጵያውያን አባባል እና ምሳሌዎች በእንግሊዝኛ
0. የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ
☞😂😂The wall of fast fast's house is straw😂😂
1. የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው
☞😉😉 The mother stomach is ranger😁😁
2. ከመሬት ተነስቶ አፉን ይከፍታል
😝😝☞Standing from the earth open his mouth😜😜
3. ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ
🙀🙀I have cow 🐄in the sky no🙈🙈Milk
4. ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ
👻👻Hyna go dog🐕 shout
ህልምና እንግሊዘኛ እንደ ፈቺው ነው
Dream and english like unhitch😁😁😁😁
ታዲያ ማን ይሞታል
#share_join
@Hiluys…
Signed Hïlüshä 💞💞
15 Aug 2021, 15:02 UTC200 viewsread 11 August 2026 ከሀሳቤ ጋ.......❗️
አንዳንዴ ህይወት ወዴት እንደምትወስደን ባላዉቅም… ከአንድ ጅረት ወደሌላዉ ወደ ሩቅና ጥልቅ ወደሆነ የሆነ ጅረት እያገላበጠችና እያስፈራራች አልያም እያባበለች ትገፋናለች፡፡ መገፋት ለኔ አዲስ ነገር ባይሆንም በብዙ የፍቅር ዉጣ ዉረድ ዉስጥ ማለፌና መጎዳቴን ሳየዉ እጅጉን አዝናለሁ፡፡ " መጎዳት እንዴት ያማል…..…ከባድ ነዉ…......!
አዉ በተለይ ባንተ በፍቅሬ….
የፍቅርህ ታማሚ ሆኜ ስኖር መናፈቅ ለአመታት አይንህን መራቤ በአንተ ምክንያት በፍቅርህ መሰቃየት ለኔ ብርቄ አልነበሩም…ሁሌ ከሞት ጋር ፍጥጫ ሁሌ ሲኦል ሁሌ ትግል በዚያ ጨለማ ቅዠት ዉስጥ አይቼዋለሁ…ይህ ሁሉ ሆኖ እንኳን ካንተ ጋር የነበረኝን አይረሴ ጣፋጭ ልዩ …
Signed Hïlüshä 💞💞
14 Aug 2021, 18:06 UTC172 viewsread 11 August 2026 " አልወዳትም እንጂ አልጠላትም" የተሰኘዉ ድርሰት ይቅርታ ዛሬ መልቀቅ አልቻልኩም በሱ ምትክ "ያልታጠበ እንባ " ሚሰኘዉ ድርሰቴን ለቅቄላቹሀለዉ መልካም ንባብ መልካም ምሽት🙏
Signed Hïlüshä 💞💞
14 Aug 2021, 18:00 UTC187 viewsread 11 August 2026 😘ያልታጠበ እንባ😢😢😢🤦♀
🔥ክፍል 16
✍ደራሲ ህሊና ሳህሌ
.
.
የናቲን ስልክ ሴት አነሳችዉ ?! ለዛዉም በዚ ለሊት ...ስልኩን በቁሜ መልቀቅ ነዉ የቀረኝ....! ሰማይ የተደፋብኝ ያክል ከበደኝ ጭራሽ ደጋግማ በእንቅልፍ ስሜት ላይ ባለ ሰዉ በሚመስል ድምፅ ሄለዉ ሄለዉ ትለኛለች ። በዛ ላይ የሱ እኩያ ሴት መሆኗን ለመገመት አይከብድም። ለስለስ ያለ የወጣት ሴት ድምፅ ነዉ !
ማመን አቃተኝ...!!! እኮ የኔዉ ናቲ በዚህ ለሊት ከሴት ጋር ምን ይሰራል ማናት !??? ደግሞ የሱን ስልክ እሷ ማንሳቷ ለምን አስፈለገ..? እኔን ማዉራት ቢያስጠላዉ እንኳን ቢዘጋብኝ ይሻለኝ ነበር ። እስከዛሬ ስልኩን አጥፍቶ ከጠፋዉ ነገር ዛሬ ስልኩ ጠርቶ እኔ …
Signed Hïlüshä 💞💞
14 Aug 2021, 18:00 UTC183 viewsread 11 August 2026 ቄንጥ እንዳታወጣ የምር አንድ ነገር እንዳትናገረኝ አለችዉ! " አቦ በናትሽ እስኪ ዝም በይ እኔ ያንቺን አዋዋጥ ስታይል ልሾፍ የመጣዉ መሰለሽ እንዴ ?
"ግን ቤኑ በፈጣሪ ምን ሁነሽ ነዉ ፊትሽ ሁላ ኖርማል አደለም ቆይ ምንድነዉ የተፈጠረዉ ቆይ ራስምታት ከዚ በፊት አለብሽ አለኝ "ሁስንያ ባክህ ፍቅረኛዋ ብላ ስትጀምርለት እ ፍቅረኛ አላት እንዴ ብሎ ከተቀመጠበት ብድግ አለና ላለማስነቃት ብሎ የለበሰዉን ሸሚዝ አስተካክሎ ቁጭ አለ እሺ ፍቅረኛዋ ምን ብሎ ጠየቃት " ኡኡኡፍ በቃ ከዳት " መስኪ ፈጠን ብላ አንቺ ያምሻል እስኪ ስለማታቂዉ ነገር አታዉሪ አለችና ተቆጣቻት "
ስለማታዉቂዉ ነገር አታዉሪ ማለት ምን ማለት ነዉ ከዚ በላይ ምን ልወቅ እ ስማኝ ዳኒ…
Signed Hïlüshä 💞💞
14 Aug 2021, 07:36 UTC500 viewsread 11 August 2026 Voice message
#አስተማሪ _ታሪክ_ለወንዶች
አንዲት ቆንጆ ልጅ ተዋወክ ወደድካት እሷም ወደደችህ ወራት ተቆጠሩ በፍቅርህ ከነፈች አንተ ግን የሷን ያህል ስሜት የለህም .......... @Hiluyss
@Hiluysss
Signed Hïlüshä 💞💞
13 Aug 2021, 17:33 UTC156 viewsread 11 August 2026 🟪አልወዳትም እንጂ አልጠላትም
#ተከታታይ ልቦለድ
#ክፍል_ሁለት
"ከእኔና ከርሷ ምረጥ ብትባል?"
"ደሞ ጀመረሽ .... ተይ ኤዱ እረፊ.... "
"ንገረኝ... ምን መስማት እንደምፈልግ ታውቃለህ!! ... ንገረኝ!!" እጮሃለሁ ... በጥፍሬ ቆዳውን እጫነዋለሁ .... ሚስቱ(እህቴ) ሰውነቱ ላይ ምንም ምልክት እንድታገኝበት አይፈልግምኣ ...
"አንቺ!!.. አንቺ ትበልጫታለሽ!" ይለኛል:: ከሚስቱ ንፁህ ልብ እና ከእኔ እብድ ጭን መሃል እየዋለለ ... ቃላቶቹ አፉን ለቀው ሲወጡ ይጎመዝዙታል..... ያስታውቅበታል:: .....
ፍቅር ይሁን ተንኮል አልጋው ላይ የምሰራው አይገባኝም ..... ፍቅር የያዘኝ በውጊያችን መሃል ከሚነግረኝ ቃላቶች ነው .... የ…
Signed Hïlüshä 💞💞
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Hiluysss. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.