2 Aug 2026, 15:28 UTC225 views6 reactionsread 6 August 2026 Photo
💫 ልጃችሁን ከሌሎች ጋር አታነፃፅሩ!
"እህትህን እይ!"፣ "ወንድምህን ተመልከት!"፣ "የእገሌ ልጅ እንዴት ጥሩ ነው!"...
እነዚህን ቃላት ብዙ ጊዜ ወላጆች ሲጠቀሙ እንሰማለን። ነገር ግን እነዚህ ቃላት ልጅን ከማበረታታት ይልቅ ልቡን ይጎዳሉ።
ራሱን በቂ እንዳልሆነ እንዲያምንና የወላጆቹንም ፍቅር ለማግኘት ሌላ ሰው መሆን እንዳለበት እንዲያስብ ያደርጉታል።
በተርቢያ ውስጥ የሚጠቅመው ልጅን ከሌሎች ጋር ማነፃፀር ሳይሆን፣ ከትናንቱ ራሱ ጋር ማወዳደር ነው።
"ዛሬ ከትናንት የተሻልክ ነህ" "በዚህ ነገር በጣም ተሻሽለሃል" "በርታ፤ አላህ ይረዳሃል"
እነዚህ ቃላት በልጅ ልብ ውስጥ ተስፋን ይዘራሉ፤ ወደ ፊትም እንዲሻሻል ያበረታቱታል።
🌿 ለተግባር: የስ…
👍6
31 Jul 2026, 14:53 UTC349 views9 reactionsread 6 August 2026 Photo
ልጅህን ስማው... ከዚያ ምክረው!
ብዙ ጊዜ ልጆቻችን ሲናገሩ እኛ መልሱን ለመስጠት እንቸኩላለን። ሳንሰማቸው እንመክራቸዋለን፤ ሳንረዳቸው እንፈርድባቸዋለን።
ነገር ግን በተርቢያ ሂደት ውስጥ ጥሩ ሙረቢ መጀመሪያ ጥሩ አድማጭ መሆን አለበት።
ልጅህ ችግሩን ሲናገር በትዕግሥት አዳምጠው። ሀሳቡን እንዲጨርስ እድል ስጠው። ከዚያ በኋላ በርኅራኄ አነጋግረው።
አንዳንድ ጊዜ ልጅ የሚፈልገው መፍትሔ ከመስጠት በፊት የሚሰማው ጆሮ ነው።
ልጆቻችን ከእኛ ጋር በነጻነት የሚነጋገሩ ከሆነ፣ ነገ ችግር ሲያጋጥማቸው ወደ እኛ ይመጣሉ፤ ይህ ደግሞ ከተሳካ ተርቢያ ትልቁ ፍሬ አንዱ ነው።
🌿 አስታውሱ ለተግባር፦ የልጅን ልብ የሚከፍተው ብዙ መናገር ሳይሆን፣ በጥሞና ማዳመጥ ነ…
👍9
29 Jul 2026, 15:04 UTC413 views15 reactionsread 6 August 2026 Photo
🌿 ለውጤት አትቸኩሉ!
ተርቢያ ውጤቱ ዛሬ ላይታይ ይችላል!
ብዙ ወላጆች፦ "ብዙ መከርኩት፣ ግን አይለወጥም!" ይላሉ
እውነታው ግን ተርቢያ እንደ ዘር ነው። ዛሬ የተዘራ ዘር ነገ ጠዋት ፍሬ አያፈራም። ውኃ ይፈልጋል፣ እንክብካቤ ይፈልጋል፣ ጊዜም ይፈልጋል።
ልጅህን ዛሬ አንድ ጊዜ መክረህ ነገ ፍጹም እንዲለወጥ አትጠብቅ። የዛሬው መልካም ቃል፣ የዛሬው ዱዓ፣ የዛሬው መልካም አርዓያነት ምናልባት ከወራት ወይም ከዓመታት በኋላ ፍሬው ሊታይ ይችላል።
ስለዚህ አትሰልቹ። ተስፋ አትቁረጡ። በጥበብ ቀጥሉ፣ በፍቅር ተጓዙ፣ በዱዓ በርቱ። አላህ መልካም ጥረትን አያጠፋም።
🌱 አስታውሱ ለተግባር፦
ስኬታማ ሙረቢና ወላጅ ውጤትን ብቻ የሚያስብ ሳይሆን፣ በየቀኑ መልካም ዘ…
👍15
27 Jul 2026, 14:32 UTC514 views13 reactionsread 6 August 2026 Photo
🌱 የተርቢያ ሁለት ክንፎች፡ ጥረት እና ዱዓ
የተርቢያ ጉዞ በማስተማር፣ በመምከር፣ በማበረታታት እና በመልካም አርአያነት ይጀምራል። እነዚህ የወላጅ ኃላፊነቶች ናቸው።
ነገር ግን የልጅን ልብ የሚመራው፣ ኢማኑን የሚያጠናክረው እና መልካምን እንዲወድ የሚያደርገው አላህ ብቻ ነው።
ስለዚህ የእኛ ተርቢያ በጥረት ብቻ አይጠናቀቅም፤ ከጥረታችን ጋር ወደ አላህ የሚያደርሰን ዱዓ ያስፈልገናል።
ብዙ ወላጆች ስለ ልጆቻቸው ብዙ ይጨነቃሉ፤ ግን ለእነሱ የሚያደርጉት ዱዓ ላይ ይዘናጋሉ። ይህ ሊታረም ይገባል።
🤲 ዘወትር አላህ ሆይ፤ ልጆቻችንን ሂዳያ ስጣቸው ምራቸው፣ ከመጥፎ ጓደኞች ጠብቃቸው፣ በመልካም ሥነ ምግባር አሳድጋቸው። ማለት ይገባል።
🌿 ለመተግበር፦ ከዛሬ ጀ…
👍13
25 Jul 2026, 16:49 UTC468 views11 reactionsread 6 August 2026 Photo
💫 ከማረም በፊት ማበረታታት!
ብዙ ወላጆች የልጆቻቸውን ስህተት በፍጥነት ያያሉ፤ ነገር ግን የሠሩትን መልካም ተግባር ለማየት ይዘገያሉ።
አንድ ልጅ አሥር መልካም ነገሮችን ሠርቶ አንድ ስህተት ቢሠራ ትኩረታችን ወደ አንዱ ስህተት ብቻ ከሄደ ልጁ "ምንም ብሠራ አይታይም" ብሎ ማሰብ ይጀምራል።
ተርቢያ ስህተትን መፈለግ ብቻ አይደለም፤ መልካም ባህሪን ማጠናከርም ነው። ልጅ እውነት ሲናገር፣ ሰላቱን በወቅቱ ሲሰግድ፣ ታላላቆቹን ሲያከብር ወይም መልካም ሥራ ሲሠራ አድንቁ። የሚገባውን ምስጋና ስጡ።
የሚበረታታ ልጅ መልካም ሥራውን ለመቀጠል ይጥራል፤ ሁልጊዜ የሚወቀስ ልጅ ግን ተስፋ የመቁረጥና በስህተቱ የመግፋት እድሉ ሰፊ ነው ።
🌱 ለመተግበር፦ ልጃችንን ስ…
👍8🤝3
23 Jul 2026, 14:17 UTC526 views13 reactionsread 6 August 2026 Photo
💫 ሁል ጊዜ ምክር መስጠት ጥበብ አይደለም!
አንዳንድ ጊዜ ወላጆች ልጃቸው ስህተት እንደሠራ ባዩ ቅጽበት ወዲያውኑ መቆጣትና መናገር ይጀምራሉ። ነገር ግን ትክክለኛ ምክር ትክክለኛ ጊዜንም እንደሚፈልግ አያስተውሉም።
ልጅ ተቆጥቶ፣ ፈርቶ ወይም እያለቀሰ የሚሰጥ ምክር ብዙ ጊዜ ወደ ልቡ አይገባም። ነገር ግን ሲረጋጋ፣ ማዳመጥ ሲችል እና ልቡ ክፍት ሲሆን የሚነገረው አንድ ቃል በአላህ ፈቃድ ሕይወቱን ሊቀይር ይችላል።
ብልህ ሙረቢ የሚናገረውን ብቻ ሳይሆን መቼ እንደሚናገርም ያውቃል።
ተርቢያ ከጩኸት ይልቅ ጥበብን፣ ትዕግሥትን እና ትክክለኛ ጊዜን ይፈልጋል።
🌱 ዛሬ እንሞክር፦ ልጃችን ስህተት ሲሠራ ወዲያውኑ ከመቆጣታችን በፊት ራሳችንን እንጠይቅ፦ "አሁን ለ…
👍10💯3
20 Jul 2026, 15:10 UTC588 views11 reactionsread 6 August 2026 Photo
🌱 ተርቢያ የሚጀምረው ከራሳችን ነው!
"ልጄ ለምን አይሰማኝም?" ብለን ከመጠየቃችን በፊት፣ "ልጄ በእኔ ምን እያየ ነው?" ብለን እንጠይቅ።
ልጆች እኛን በጥንቃቄ ይመለከታሉ። ስንናገር፣ ስንቆጣ፣ ስንታገስ፣ ስንሰግድ፣ ስናመሰግን... ሁሉንም ያስተውላሉ። ከዚያም ሳናስተውል እኛን ይኮርጃሉ።
ተርቢያ በብዙ ቃላት ሳይሆን በመልካም አርዓያነት ይጀምራል። ልጆቻችን ላይ ማየት የምንፈልገውን ስብዕና ራሳችን እንላበሰው።
ዛሬ አንድ ጥያቄ ለራሳችን እንጠይቅ፦
"ልጄ ዛሬ ከእኔ የተማረው መልካም ነገር ምንድን ነው?"
🌿 ስኬታማ ተርቢያ በቤት ውስጥ ከወላጆች ይጀምራል።
#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ሂዳያ
💫 @HidayaTe…
👍11
16 Jul 2026, 16:23 UTC763 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
ታሪክ በልጆቻችን ስብዕና ግንባታ ላይ ያለው ተጽዕኖ!
ታሪክ ልጆችን ለማስተማርና ባህሪያቸውን ለመገንባት ከሚያገለግሉ እጅግ ወሳኝ የተርቢያ መንገዶች አንዱ ነው።
ልጆች ታሪክን ከትእዛዝ ይልቅ በቀላሉ ይቀበላሉ፤ ምክንያቱም ራሳቸውን በታሪኩ ውስጥ ያያሉ፣ ከባህሪያቱም ይማራሉ።
ቁርኣን ብዙ ታሪኮችን በውስጡ የያዘው ለመዝናናት ሳይሆን ለመምራት፣ ለማስተማር እና ለመገሰፅ ነው።
ወላጆች ለልጆቻቸው የነቢያት፣ የሰሐቦች እና የደጋግ የአላህ ባሪያዎችን ታሪኮችን ዕድሜያቸውን በሚመጥን መንገድ መተረክ ይገባቸዋል።
ታሪኩን ሲነግሩ ቀላል፣ ማራኪ እና ልጁን የሚሳብ አቀራረብ መጠቀም፣ ከጨረሱም በኋላ ከታሪኩ የሚወሰዱ ትምህርቶችን ከልጁ ጋር መወያየት የግድ ይላል።
…
👍4
11 Jul 2026, 19:03 UTC745 views7 reactionsread 6 August 2026 Photo
በፉል ከለር ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል
ፈጥነው ይሸምቱ!
🏆4🤝3
Hidaya Terbiya II ሂዳያ ተርቢያ pinned a photo
11 Jul 2026, 18:49 UTC761 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
የታሪክ ማዕድ
ቁርኣን ውስጥ የተጠቀሱ ታሪኮች ለታዳጊዎች
አዲስ መጽሐፍ ከሂዳያ ተርቢያ
በፉል ከለር ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል
ፈጥነው ይሸምቱ
0921 014449
@HidayahTerbiya
👍4
5 Jul 2026, 17:47 UTC915 views10 reactionsread 6 August 2026 Photo
💫 የምስራች!
🌟 ለልጆችዎ ከሚያበረክቱት ከሁሉ የተሻለው ስጦታ ዘላቂ የዲን ዕውቀት ስጦታ ነው! 🌟
ውድ ወላጆች እና ሙረቢዎች! ልጆቻችን የእስልምናን መሠረት በሚገባ ተረድተው፣ አላህን በዕውቀት እንዲያመልኩና በመልካም ሥነ-ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ ይፈልጋሉ?
ለዚህ ትልቅ አማና (አደራ) መወጫ የሚሆን ድንቅ መፍትሔ ይዘንላችሁ ቀርበናል!
አዲስ መጽሐፍ ከሂዳያ ተርቢያ
📚 የዕውቀት ካባ
📚 የአኽላቅ ብርሃን
በቅርቡ
ለማዘዝ 💬 በቴሌግራም፦ @HidayahTerbiya ✨
👍8🏆2
Showing the 12 most recent of 17 posts we hold for @HidayaTerbiya. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.