1 Sept 2026, 19:48 UTC82 views1 reactionsread 2 September 2026 Photo
አብን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ ጥቃቶችን አወገዘ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች በንጹኃን ዜጎች ላይ ተፈጸሙ ያላቸውን ጥቃቶች እና ተከሰቱ ያላቸውን ሰብዓዊ ቀውሶች አውግዟል።
ፓርቲው ይፋ ባደረገው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በምሥራቅ ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምሥራቅ አርሲ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች በንጹኃን ዜጎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች፣ የንብረት ውድመት፣ ማፈናቀል እና የእምነት ተቋማት ጉዳቶች እንዲሁም የተጓዦች እገታ በሀገሪቱ ሰላምና ማኅበራዊ አንድነት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል።
አብን የዜጎችን ሕይወትና ንብረት የመጠበቅ እንዲሁም የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታ የመንግሥት በመሆ…
😭1
1 Sept 2026, 19:11 UTC124 views1 reactionsread 2 September 2026 Photo
እንግሊዝ ከ1884 ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ የበጋ ወቅት አስተናገደች
እንግሊዝ መረጃዎችን መመዝገብ ከጀመረችበት ከከውሮፓዎያኑ 1884 ወዲህ በታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ ከባድ እና ሞቃታማ የበጋ ወቅት ማሳለፏ ተገለጸ።
የሀገሪቱ የሜትሮሎጂ ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ የዘንድሮው የ2026 የበጋ ወራት አማካይ የሙቀት መጠን 16.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ደርሷል፤ ይህም በብሪታንያ የአየር ንብረት ታሪክ ከፍተኛውና አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሆኖ ተመዝግቧል።
አገሪቱ በተከታታይ ሁለት ዓመታት ተመሳሳይ የሙቀት ማዕበል ማስመዝገቧ፣ የዓለም የሙቀት መጠን መጨመር አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳይ እንደሆነ ተጠቅሷል።
ወቅቱን ተክቶ የተከሰተው ብርቱ የሙቀት…
😢1
1 Sept 2026, 17:24 UTC151 views2 reactionsread 2 September 2026 Photo
ማኅበራዊ ሚዲያ የጥፋት መሣሪያ እየሆነ መምጣቱ ሊገታ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳሰበ
በአሁኑ ወቅት ማኅበራዊ ሚዲያ ከመረጃና ከዕውቀት ማጋሪያነቱ አልፎ፣ ጥላቻን በመዝራት እና ወንድምን በወንድሙ ላይ በማነሳት የጥፋት መሣሪያ እየሆነ መምጣቱ ከባድ ስጋት መደቀኑ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንዳመለከቱት፣ ማኅበራዊ ሚዲያ መጀመሪያውኑ ሰዎችን ለማቀራረብ የታለመ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መልካም ዓላማው ተዛብቶ የጥፋት መሣሪያ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።
በመካከላችን ብዝኃነትን ለማደብዘዝ እና እኩይ አላማቸውን ለማሳካት ሌት ተቀን የሚሠሩ አካላት መኖራቸውን የጠቆሙት ዋና…
❤1👍1
1 Sept 2026, 16:37 UTC142 viewsread 2 September 2026 Photo
እስራኤል የሐማስ ከፍተኛ አመራር መያዙንና በጋዛ የሚገኙ የድርጅቱ አባላት ላይ ጥቃት መፈጸሟን ገለጸች
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ይስራኤል ካትዝ (Yisrael Katz) በጋዛ ከተማ በተካሄደ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን አንድ የሐማስ ከፍተኛ አዛዥ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቁ።
ኦፕሬሽኑ በእስራኤል የሚደገፍ የአካባቢው ታጣቂ ቡድን በተሳተፈበትና በቀጥታ የአየር ድጋፍ በተደረገበት ሁኔታ የተከናወነ መሆኑ ተገልጻል።
ሚኒስትሩ በቁጥጥር ስር የዋለውን የሐማስ አዛዥ ማንነትም ሆነ ኦፕሬሽኑን የፈጸመውን የጦር ክፍል ከመግለፅ ቢቆጠቡም፣ እስራኤል ሊሰነዘሩ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድሞ በመምታትና የሐማስን መዋቅር በማፍረስ ላይ የተመሰረተ ወታደራዊ እርምጃዋን በቀ…
1 Sept 2026, 16:20 UTC121 viewsread 2 September 2026 Photo
በሳውዲ-የመን አቅራቢያ በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሳውዲ አረቢያ ድንበር እና አል-ሻርቃ (ወይም በረሃማ) አካባቢዎች በጥቂት የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል የተከሰተውን እርስ በእርስ ግጭት እና አሰቃቂ የነፍስ ግድያ ወንጀል ተከትሎ፣ ዋናው ተጠርጣሪ ከአምስት ግብረአበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
ኤምባሲው ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በቅርቡ በተወሰኑ ዜጎች መካከል በተከሰተ እርስ በእርስ ግጭት እና በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ባሳደረ አሰቃቂ የነፍስ ግድያ ወንጀል ዙሪያ ከሳውዲ አረቢያ የጸጥታ አካላት እና ከህብረተሰቡ የተገኙ መረጃዎችን መሰረት…
1 Sept 2026, 15:44 UTC109 viewsread 2 September 2026 Photo
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን ሊካሄድ ነው
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አስታወቀ።
ምክር ቤቱ ከጀርመን የልማት ድርጅት (GIZ) እና ከኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት (SNV) ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ይህ መድረክ፤ በሀገሪቱ የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በግል ሴክተር ውስጥ እንዲጎለብትና ተግባራዊ እንዲሆን ለማስቻል ያለመ ነው።
በዚሁ ሀገራዊ መድረክ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የንግድ ምክር ቤትና የማህበራት መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ በዘርፉ የተሰማሩ የሀገር ውስጥና…
1 Sept 2026, 13:18 UTC119 views2 reactionsread 2 September 2026 የ”የኔታ” እና የ”መድረሳ” የሃይማኖት ትምህርት ቤቶች በቂ ትኩረት እንዲሰጣቸው ተጠየቀ
ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ ለሆኑት የ”መድረሳ” እና የ”የኔታ” (የአብነት) መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች በቂ ትኩረት እንዲሰጣቸው የኪንግ ኦፍ አባይ ንቅናቄ መስራችና የሃይማኖት አባት ኡስታዝ ጀማል በሽር ጠየቁ።
ኡስታዝ ጀማል በሽር ይህን ያሉት ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ሲሆን፣ ከእስልምና የመድረሳ (የቁርዓን ቤት) እና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሚገኘው የየኔታ (የአብነት) መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ትውልዱን በመቅረጽ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ቢኖራቸውም፣ በቂ ትኩረት እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ልጆች በእነዚህ የሃይማኖት ተቋማት ግብረ-ገብነት…
❤1😁1
1 Sept 2026, 13:18 UTC104 viewsread 2 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
1 Sept 2026, 11:47 UTC113 views2 reactionsread 2 September 2026 Photo
የቻይና መንግስት በቲቤት የጎርፍ አደጋ ዙሪያ መረጃዎችን እያፈነ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች ወቀሰ
የቻይና መንግሥት በቲቤት ደርሶ በነበረው አሰቃቂ የጭቃና ጎርፍ አደጋ ዙሪያ እውነተኛ መረጃዎች እንዳይወጡ ጥብቅ እገዳ (ሴንሰርሺፕ) ማድረጉን ሂውማን ራይትስ ዎች ገለጸ።
በአደጋው ሳቢያ በርካቶች በተጎዱበት በዚህ ወቅት፣ የመንግሥት አካላት የፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግን እንቅስቃሴ እና የፖሊስ ስራዎችን ብቻ በሀገሪቱ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አጉልተው እያሳዩ ይገኛሉ ሲል ድርጅቱ ኮንኗል።
ነፃ ጋዜጠኞች ወደ አደጋው ቦታ እንዳይገቡ የተከለከሉ መሆኑንና “ሐሰተኛ ወሬ አሰራጭታችኋል” በሚል ከ10 በላይ ሰዎች የተቀጡ ሲሆን እውነተኛው የአደጋው ቪዲዮም ከሀገር ውስ…
❤1👏1
1 Sept 2026, 11:42 UTC92 views2 reactionsread 2 September 2026 Photo
በኒውዮርክ ሃይቅ የጠፋው ቀለበት ከ28 ዓመታት በኋላ ተገኘ
ኪም ራስቤክ የተባለች አሜሪካዊት በአውሮፓውያኑ 1988 ከ28 ዓመታት በፊት በኒውዮርክ ሳካንዳጋ ሐይቅ ላይ ከጓደኖቿ ጋር እየተዝናናች ባለችበት ወቅት ጠፍቶባት የነበረ ቀለበት በፈላጊዎች ተገኝቶላታል።
ማይክል ሲግል እና ዲላን ላፖርት የተባሉት በጎ ፈቃደኛ አሳሾች ብረትን በመጠቀም ፍለጋ እያደረጉ በነበሩበት ወቅት የኪም ራስቤክ የሬድ ክሪክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምረቃ ቀለበት እንዳገኙ ገልጸዋል።
ማይክል እና ዲላን ለትምህርት ቤቱ ደውለው ስለቀለበቱ በጠየቁበት ወቅትም ያናገረቻቸው ፀሐፊ የኪም የቀድሞ የቡድን ጓደኛ በመሆኗ ወዲያውኑ ቀልበቱ የወዳጇ ኪም መሆኑን መለየቷ ተገልጿል።
በዚህም…
❤1👍1
1 Sept 2026, 06:51 UTC106 views3 reactionsread 2 September 2026 Photo
የአደጋዎችን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ የመስኖና የግል ሴክተር ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል ተባለ
የተፈጥሮና የሰው ሰራሽ አደጋዎች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድሩትን ጫና ለመቀነስ የመስኖ ልማትና የግል ሴክተሩ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ተጠቆመ።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያና የፖሊሲ አማካሪ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርሄ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ድርቅና ጎርፍን ጨምሮ የተለያዩ አደጋዎች በሰው ሕይወትና በሀገር ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርሱ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
የአፈርና የተፈጥሮ ጥበቃ ሥራዎች በበቂ ሁኔታ አለመጠናከራቸውና በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች በምርትና በምርታማነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆኑንም …
❤1👍1👏1
1 Sept 2026, 06:40 UTC95 views2 reactionsread 2 September 2026 Photo
የኮሎምቢያው ፕሬዝዳንት የታጣቂ ቡድኑ መሪ በፖሊስ እርምጃ መገደሉን አስታወቁ
የኮሎምቢያው ፕሬዝዳንት አቤላርዶ ዴ ላ ባሳለፍነው እሁድ በሀገሪቱ ታዋቂ የሆነው የፋርክ ታጣቂ ቡድን መሪ መገደሉን ይፋ አደረጉ።
«ፌሊፔ» ወይም «አርካዲዮ» በሚል የሚታወቀው የዚህ አብዮታዊ ጦር መሪ ሊገደል የቻለው በምዕራብ ኮሎምቢያ በሚገኘው ቫዬ ደል ካውካ ግዛት በተካሄደ የፖሊስ ስፖንሰር የተደረገ የፀደቀ የጸጥታ እርምጃ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
የተገደለው ታጣቂ መሪ ከዚህ ቀደም ዳጓ እና ኤል ኩራማል በተባሉ አካባቢዎች በሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች፣ ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች እና ፈጣን መንገዶች ላይ ድሮኖችን በመጠቀም በርካታ ጥቃቶችን በማድረ…
👍1🔥1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Harambeeradio. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.