17 Oct 2023, 20:31 UTC581 viewsread 9 August 2026 Forwarded from @EthioStudentsPhoto
የወጣቶች ራስን ማጥፋት ምክንያቱ ምን ይሆን?
ብንሄድ ይሻለናል የሚልዕክት በፌስቡክ ገጿ ላይ ያሰፈረችው ወጣት ራሷ. አጠፋች!
ናዝራዊት ተስፋዬ ትባላለች። ከሁለት ቀን በፊት ስንብት የሚመስሉ ልጥፎችን አጋርታ ዛሬ ራሷን ማጥፋቷ ተሰምቷል። ይሄ ድርጊት እየተለመደ መጥቷል። ይህቺ ነፍስ ብዙ መከራ ብቻዋን እንደታገለች፣እምባ ዘመዷ እንደሆነ፣የምታዋየው፣ልቧ የሚያርፍበት ሰው ማጣቷን ያሳብቃሉ ልጥፎቿ። ምንም ማድረግ ባንችል አጠገባችን ያሉ ሰዎችን እናስተውል፣የአንዳንዱ ችግር ''አይዞን'' በሚል ነጠላ ቃል ይቀረፋል። በሰው ረሃብ ቸነፈር የተገረፈ ስንቱ አለ? ብዙ የነገ ተስፋዎቻችንን አይነጠቁብን፤የአንዳችን መኖር ለሌላኛችን ነው!! የነፍሳችን ባለቤት ፈጣሪ ነ…
Signed Bèsí
1 Oct 2023, 20:54 UTC457 views0 reactionsread 9 August 2026 ሰው ለራሱ ጥቅም
እኔን የማይመጥን ውሸት ቢለቃቅም
ተይው ፊት አትስጪው
እኔን የመሰለ ሸጋ ነው ምታጭው
ይልቅ ብለሽ ጠንቀቅ
እኔን ብቻ ማድነቅ
ልማድሽ አድርጊ
ነገረኛን አምነሽ ነገር አትፈልጊ
ይልቅ አስቢበት
አዋቂ ያስመሰለኝ ጺሜ መከረኛው
ሸሚዝ ማይጣላው አቋሜ ጉደኛው
ሚስት ሳያሳጣኝ ይሉኛል ብቸኛው
መለስ ካላልሽ አንዴ
ሊቀሙሽ ነው ውዴ
ለራስሽ ብዬ ነው
ማኩረፍ ላያዋጣሽ
መፀፀት አይቅጣሽ
ብቻ ፈራሁልሽ
እንዳይቆጭሽ ሲያታልሉሽ
ፈዝዘሽ ቁመሽ እንዳይቀሙሽ
በኋለ አጥተሽኝ ደጅ ከምትጠኚ
እድል አያምልጥሽ በይማ ፊጠኚ
Signed Bèsí
1 Oct 2023, 20:53 UTC417 views0 reactionsread 9 August 2026 ይቀጥላል...
👨🦼አካልህ በድኖ አንደበትህ ታስሮ
መከራህ ቢበዛ ችግር ተደማምሮ
መሸከም ቢያቅትህ ጫንቃህ አቅም ቢያጣ😔😔😔😔😔😔😔
መኖር ቢሰለችህ ምን ሀዘን ቢመጣ
መኖር ይቀጥላል የመጣው ቢመጣ።
ገንዘብ ቢበዛለት በምቾት ቢደለቅ
በደስታ ቢጨፍር በሳቅ ቢፍለቀለቅ
በሰዎች ቢከበር ስልጣን ላይ ቢወጣ
ፈላጭ ቆራጭ ቢሆን ምን ነገር ቢያመጣ
ሀገር ቢያስተዳድር አለምን ቢገዛ
መሞት ይቀጥላል መኖርም እንደዛ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ከአዒሻ
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
Signed Bèsí
29 Sept 2023, 17:57 UTC383 views1 reactionsread 9 August 2026 ፨፨፨ የልብ_ቋንቋ ፨፨፨
==========================
💜 የህይወት ጥዕሙ የጠፋባቸው ሰዎች አሉ ። በየእለቱ ተመሳሳይ ህይወት የሚኖሩ እና በህይወታቸው ውስጥ አዲስ ክስተት አጥተው ስልቹ የሆኑ ሰዎች ። ዘውትር ተመሳሳይ ህይወት ፣ መግባትና መውጣት ፣ መብላትና መጠጣት ብቻ አዲስ ህይወት የሌለበት ስልቹ አለም ።
💜 እነዚህ ሰዎች ህይወትን በማሰብ ( አይምሮ ) ብቻ የሚኖሯት ሰዎች ናቸው ። ምክንያቱም የሰው ልጅ የልብ ቋንቋ ካልገባው በአይምሮው ብቻ ከኖረ ህይወት ትርጉም የሌላት ባዶ ስለምትሆን ህይወትህን በአይምሮህ ብቻ ሳይሆን በልብህ ኑራት ፣ ህይወትህን በልብ ቋንቋ ስትመራት አይምሮህ ታላቅ ተፈጥሮን ያሳይሀል ። በአይምሮህ…
❤1
Signed Bèsí
3 Sept 2023, 20:11 UTC481 viewsread 9 August 2026 ቃል ይስጠን 🙏
መራቀቅ ባልችልም
ሚስጥር ማወጣጣት
ግን አለሜ እወቂ
ፍቅር አይፈልግም ተራ ባዶ ቃላት
አይን አፋሮች ሆነን
መናገር ብንፈራ
እንባች ይወርዳል
በተራ በተራ
ቃሌን በመጠበቅ
አንቺም ሳታወሪ
ተለያይተን ሳንቀር
ቃል ይሰጠን ፈጣሪ 🙏
Signed Bèsí
Channel name was changed to «ገምሀልያ አንሆንም»
8 Aug 2023, 20:57 UTC433 views1 reactionsread 9 August 2026 #አልገባሽም
:
:
:
ስንለያይ ጊዜ
የየብቻው ጉዞ ገና ሲጠነሰስ፤
አብረን የገራነው የጋራችን ፈረስ፤
ትዝታን ሸክፎ ቤትሽ እንደመጣ፤
ከዛም ከደጃፍሽ አራግፎ እንደወጣ፤
የኋሊት ጎትቶ ሆዴን ሊያላውሰው፤
በሰመመን ስትሄጅ ነግሮኛል ያየሽ ሰው።
:
:
ስንለያይ ጊዜ
ህይወት በኛ ስትከር፤
እንዲው እንደ ዘበት ፍቅራችን ሲሰበር፤
የሀዘን ድንኳን ጥለሽ፤
እንዴት ሆነ ብለሽ፤
እንባሽን ስትዘሪ፤
ደግሞም ከራስሽ ጋር ስትከራከሪ፤
ባላይ እንኳን ባይኔ፤
ያየሽ አርድቶኛል ሁሉን ክንዋኔ።
:
:
ስንለያይ ጊዜ
ያቆራኘን ገመድ እንደተበጠሰ፤
የትካዜው ሾተል ስለቱን አስሎ ካንቺ እንደደረሰ፤
ከዚያም አልፎ ተርፎ እንዶነብሽ እዳ፤
ሁሉን ሰምቻለው ያንቺን ሳሎን ጓዳ።
:
:
ስንለያይ …
❤1
Signed Bèsí
6 Aug 2023, 22:13 UTC358 viewsread 9 August 2026 #ለፈገግታ😁
🙅♀እሺ አትበይ አሁን🙅♀
አፈቀርኩሽ ብልሽ
ሁሌ ብከተልሽ
እያልኩኝ ብነግርሽ
ካላንቺ አልኖርም
ሳላይሽ ከዋልኩኝ እህል ባፌ አይዞርም
የተጎዳው መስሎሽ እየተሰማሽ ሀዘን
እባክሽ ቸኩለሽ እሺ አትበይ አሁን::
:
:
እንዴት ካልሽኝ ለምን?
ግራ እንዳትጋቢ ልንገርሽ ምክኒያቴን::
:
:
በዚ እሳት ዘመን በዚ ከባድ ኑሮ
ምግብ ስለዘጋኝ ብር ቆጠብኩ ዛሬ
ታሪክ ተቀይሮ
:
:
እና እሺ ብለሽ ሆዴ ከሚከፈት
መልስሸ ይቆይና ለትንሽ ጊዜያት
ዘግቶኝ ልኑርበት::🙏
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @Gemhalya
Signed Bèsí
6 Aug 2023, 22:13 UTC322 viewsread 9 August 2026 ❤️❤️ሰበበኛው ልቤ❤️❤️
ለስንት አመት ኖሮ ሆኖ ኩሩ ላጤ
ዛሬ ቢነካካው ትንሽ ፍቅር ቢጤ
ያ ልቤ ከውስጤ ሳይወጣ አምልጦ
ያስጨንቀኝ ጀመር ካምሮዬ በልጦ::
:
:
ባፅኖት ነግሬው ሰላም እንዲሰጠኝ
በስድብ በቁጣ
ጭራሹን ባሰበት እሷ ስትመጣ::
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
✍️ @Gemhalya
Signed Bèsí
14 Jul 2023, 06:51 UTC356 views3 reactionsread 9 August 2026 [ማ መ ን ታ ት]
.
አየሽ ልቤ...
ትታህ ሄዳለች| ይለኝና
(መራቅሽን ያስብና)
ሌላ ሴት| ገላ ለመልመድ፤
(ይጀምርና፥ መራመድ...)
ድንገት ያስባል| መንገድ ላይ ቆሞ፣
ማን ያዉቃል| ብትመጪስ ደግሞ!?
(ልጠብቅሽ መሰል...)
.
ይሄዉ|ይሄዉ
አሁን
አሁን
ዛሬ
ዛሬ
(እንደ ትላንት፥እንደ ነገ)
ፀሀይ ወጣች|ፀሀይ ገባች፣
ነፍሴ ሳቀች| ደግሞ ባባች።
ደግሞ መሸ| ደግሞ ነጋ።
ደግሞ አንዲት ሴት|መልከ ሸጋ፤
ሀር ፀጉር|ጠይም ሎጋ፣
(ለነፍሷ ነፍሴን ፈልጋ)
ባይኖቿ እየጠራችኝ፣
(በቅንድቧ በብሌኗ)
አነጋግረኝ?| እያለችኝ።
ለጥቂት ቅፅበት (ለሰከንዶች)
ልቤ ሄደሻል ብሎ፣
ቀልቡን ከ`ሷ ላይ ጥሎ።
ለመሄድ ይሽተዉና፣
ይጨነቃል እንደገና።
.
.
.
.
(እንደገና ይ…
👍3
Signed Bèsí
28 Jun 2023, 11:37 UTC336 views1 reactionsread 9 August 2026 ✨ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444'ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!❤️
@Gemhalya
@Gemhalya
❤1
Signed Bèsí
Channel photo updated
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Gemhalya. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.