4 Aug 2026, 15:16 UTC90 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
ተስፋዬ ገብረአብ በጣም በጣም እጅግ በጣም ይናፍቀኛል።
በአጋጣሚ የሞተ ዕለት ደሴ ነበርኩ።የጦርነት ዘገባ ላይ ነበርኩ።በዚያች አፍታ «ጃንሆይ እና ደርግ» የተሰኘውን መጽሐፉ እያነበብኩ ነበር።
የሆነ ገጽ ላይ ሥደርስ «ተስፋዬ ገብረአብ ሞተ» መባሉን ሰማሁ።
ያሳዝናል በጣም።
በቃላት ላይ የሚደንሰው የአፍሪካው ቀንድ ትጉህ ጸሐፊ እንዲህ በአጭሩ ማረፍ አልነበረበትም።
ተስፍሽ እንደተንከራተተ፣ሥሙ በጥፋቱም—ያለ ጥፋቱም እንደተበለተ ኖሮ አረፈ።
የተስፋዬ ገብረአብን መጽሐፍት ሳነብ የመጻፍ ወኔዬ ይቀሰቀሳል።የደም ዝውውሬ ይፋጠናል።የመኖር ፍላጎቴ ይጨምራል።ሀዘን ይወረኛል።በአጭሩ በሥሜት መጠጦች እሰክራለሁ።
ተስፋዬ ገብረአብ ሥሜቶችን በፊደላት እየመጠነ የ…
🤯1
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
3 Aug 2026, 16:57 UTC116 views3 reactionsread 6 August 2026 Photo
«...እኔ የምሞተው በሚወዱኝ ሰዎች ልብ ውስጥ መረሳት ስጀምር ነው!
ሥጋዬ ሞተ ብለሽ አትዘኝ!
በልብሽ ረስተሽኝ በአፀደ ሥጋ ከምንከላወስ ሞቼ ብታስታውሺኝ ለኔ ምርጫዬ ነው!"
ይህን ቃል ጋሽ ስብሃት ገብረ እግዚአብሔር በመጨረሻዎቹ ቀናት የፃፈው ነው ተብሎ tt ላይ ተጋርቶ አገኘሁት።
በፊትም አውቀዋለሁ።እና በሃዘን ይሰልበኛል።
ጋሽ ስብሃት🥰
የጋሽ ስብሃት የልብ ጓደኛ በዓሉ ግርማ'ም የራሡ ግማሽ አምሳያ አርጎ በኦሮማይ የፈጠረው ጸጋዬ ኃይለማርያም የሚባል ገጸ ባሕርይ አለው።
ጸጋዬ ለፊያሜታ ያንድ ጓደኛዬ ግጥም ብሎ፦
«የኔ ውብ ከተማ
የኔ ውብ አገር
የሰው ልጅ ልብ ነው
የሌለው ዳርቻ
የሌለው ድንበር»
የሚሉ ሥንኞች ያሉበትን ግጥም ያነበን…
🥰3
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
3 Aug 2026, 16:06 UTC104 viewsread 6 August 2026 Photo
የሰመራ ናፍቆት አለብኝ።ናፍቆቱ ከባቲ ይጀምራል።ምናቤ በማዲንጎ ድምጽ፦
«እንደ ባቲ መንገድ
እንደወዲያኛው
በዓመት አንድ ቀን ነው
የምትገኝው...»
እያለ ያለቃቅሳል።
ለእኔስ ባቲም፣ሎግያም፣ሰመራም፣ኢረብቲም፣ዱብቲም ካገኘኋቸው አራት ዓመት አለፈኝ።
ሰመራ ብዙ ያላወራንላት ኢሕአዴግ እና የአሁኑ ሕግ መንግሥት የፈጠራት ውብ ከተማ ናት።እኔ የበረሃ ከተማ ሥለምወድ አብዝቸ ሳልከየፍባት አልቀረሁም።
ግን የምርም ውብ ናት።
የሚያማምሩ የአፋር ቆነጃጅት አሁንም ቅድምም ታያላችሁ።ተጋሩ ሴቶች ፏ ብለው የሚገኙባት ከተማም ሠመራ ናት።ወሎዬዎቹ ሰመራ ላይ ረሃ ሆነው አሉ።
ሰሙዬ—ትሞቃለች በጣም።
ቢራ እንደ ጉድ ይጠጣል።ደሞ በከል የሚሉት ብስኩት የመሰለ የጢንጥዬ…
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
30 Jul 2026, 19:31 UTC171 views4 reactionsread 6 August 2026 File
«ዘላለም ናት ዛሬ
ከምወድህ ጋራ!»
የማርያም ቸርነት እዚህ ሙዚቃ ውስጥ ከኤካርት ቶሌ'ው «The Power of Now» ጋር የሚስማማ አሳብ የምታቀነቅን ይመስለኛል።
በዓሉ ግርማ'ም በ«ደራሲው»ፍቅር ማለት የሽርፍራፊ ሰኮንዶች ወይም ደቂቃዎች አልያም ዓመታት ውብ ገጠመኝ እንጂ ሁልጊዜ አለመሆኑን አትቷል።
ጥበቡም ያለው አሁንን ወይም ዛሬን በፍቅር ዘላለም ማድረግ ላይ ሆኖ ይታያል።የክርስቲያኖች መጽሐፍ 'ነገ ለራሡ ያውቃል' ይላል'ና!
ከዚሁ አሳብ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ቴዎድሮስ ካሣሁን ገርማሞ «አይዞህ ልቤ» ላይ፦
«የጊዜ ሚዛን አይላወስም
ዛሬን የሌለ ለነገ አይደርስም፤
ሳዝን አልውልም ሳላውቅ ማደሬን
የኔ ነው በቃ አልሰጥም ዛሬን!»
ብሏል።
የ'የ…
❤4
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
30 Jul 2026, 17:54 UTC153 views3 reactionsread 6 August 2026 Photo
ዘር ማንዘሬ ሁሉ የጮቄ ተፋሰስ ሰው መሆኑ ሃቅ ነው።ከዳሞት፣ከቢቡኝ፣ከእነሴ፣ከእነብሴ፣ከእናርጅ እናውጋ ሁላ እንወለዳለን።
የእኔ የትውልድ ቦታ መሐል ጮቄ ነው።አዳኝ መድኃኒዓለም...!
ከ13 ዓመት በፊት ጀምሬ በጮቄ ላይ እየተመላለስኩ የሕግ ጉዳዮች እከታተል ነበር።
የውሃው ጥራት፣የአየሩ ልዩ መዓዛ፣የሰው አስደማሚ ሥነልቡና አብሮኝ አድጓል።
ዛሬ የሆንኩትን ለመሆን በረጅሙ ሳሰላስል፣የድምጽ ልምምድ ሳደርግ፣ሳነብ ሁላ የጮቄን ጸጥ ያለ ድባብ ተጠቅሜበታለሁ።
ባይዜ ጮቄ ውስጥ «እሪ በከንቱ» የሚባል ቦታ አለ።ሰው ፈጽሞ የማይደርስበት አካባቢ ማለት ነው😀
በዚያ ቦታ እኔ የአታዬ ልዥ ብቻዬን እወዘወዝ ነበር።
አዲሳባ ስኖር ያ ሁሉ ናፈቀኝ...!
የጂጂን«…
❤3
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
30 Jul 2026, 17:22 UTC130 views2 reactionsread 6 August 2026 Photo
ይችን ልጅ ሳያት አዳማ ትዝ አለችኝ🥰
«የእኔ ውብ አዳማ»—ከተማ እና ሰው ሲሰለጥኑ ምን መምሰል እንዳለባቸው ኮርስ ለመሥጠት የተሠራች ውብ ቀዬ።
ገና በአካል ሳላያት ተማሪ ሳለሁ ከንባብ እና ዘፈን ብቻ ተነስቼ ጭሬላት ነበር።
ኋላማ መደሰቻዬ ሆና አረፈችው።
ከቆንጂዬ ልጅ ጋር(ከዚች ጋር አይደለም😀)፣ከያቡ ጋር፣ሌላ ስሟን ከማልጠራው ቆንጂዬ ልጅ ጋር፣ከራሴ ጋር፣ከሐረር ሰዎች ጋር፣ከያቡ እናት ጋር፣ከአሁኑ የሥራ አጋሬ ኧረ ከብዙ ሰው ጋር በምሥራቋ በር ፏ ፈሽ ብለናል።
አዳማ ላይ ሥጋት፣ፍርሃት፣ጭንቀት ድራሻቸው ይጠፋል።ሰውነት ከፍ ይላል።
የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ አገር የማሥፋት እና የማልማት ሕልም ከተማ ፈጥሮ የአዳማ ጌታ ሥላረገን እናመሰግን ዘንድ የ…
👍1👏1
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
28 Jul 2026, 11:53 UTC166 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
ውስጡን ለቄስ ትተን «ያልፋል አትበሉኝ» ጸዴ ክልከላ ነው።የሚያልፍ ነገር የለም።ነገሩ ከመሠረቱ ያውም በእኛው ካልተለወጠ አልያም ሥቃዩን ካልወደድነው «እለፍ እለፍ፣ያልፋል» እየተባባሉ መጽጽናት ደባሪ ነው።
አውቃለሁ'ኮ በዚች አያልፍልሽ አገር «ያልፋል» የሰው ሥም ነው።
እኔ እና አባም አንዴ የጋራ ችግር ገጥሞን ግድግዳችን ላይ«እስቲያልፍ ያለፋል» ብለን ጽፈን ነበር።
አዎ።ያለፋል።
አሁን ሳስበው ግን እሱ እንዲያልፍ መፍቀዳችን ሥተት ነበር።እኛ ማሳለፍ ነበረብን።በተግባር ያደረግነውም ያን ነበር።
ተግባራዊ እንቅስቃሴ አድርገን ነበር።
ያ እንቅስቃሴያችን አባን ለተረጋጋ ሕይወት፤እኔን ለተረጋጋ ትምህርት እና ለዛሬ አብቅቶናል።
እና ምን ለማለት ዩ?
…
👏1
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
28 Jul 2026, 07:45 UTC176 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
«ዞራ ዞራ የእኔ ናት»—በሚለው እስማማለሁ።
በአገራዊ የምክክር ሒደት እንዲታይልኝ የምፈልገው ጉዳይ «እቀበላታለሁ ወይ?» የሚለው ነው።
ባይዜ...
ተልጅነቴ ጀምሬ ሰው አፋትቸ አውቃለሁ።አንዲት ትልቅ ሴት ከባሏ እንድትለያይ ሕጋዊ እና ሞራላዊ ሒደቶችን ተከትዬ አፋታሁ።
አትፍረድ...!
'ተቃጠልኩ፣ደበረኝ፣አልተመቸኝም'—ሥላለችኝ ነው ገና በለጋ ዕድሜዬ ያንን ሁሉ ሕጋዊ ሒደት አልፌ ያፋታኋት።
ዩኒቨርሲቲ ሔጀ ሥመለስ ግን 'ዞራ ዞራ የእሱ ሆና አገኘኋት'
ይሄን ትሬንድ ቢያንስ ለ 13 ጊዜ ስትደጋግመው በሕይወት ነበርኩ።
እናም ነገሩ ሃቅ አለው እያልኩህ ነው🕺
❤1
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
27 Jul 2026, 16:45 UTC196 viewsread 6 August 2026 Photo
እዚህ ደግሞ የአንዲት ውብ ሐበሻ መልክ እና ድምጽ አለ።
ልጅነታችንን፣ጉርምስናችንን፣ተሽኮርማሚ የፍቅር ሥሜታችንን ሸክፎ የያዘ ጥበብ ከአንደበቷ ይፈልቃል።
ደርባባ ናት እሷ...!
'አገር ይያዝልኝ' አትልም።
የሠራችውን ሠርታ፣ተረጋግታ ሩቁን እና ረቂቁን ፍቅር አስዳሳን በረጅሙ ዝም ትላለች።
እነሆ የአበሻ መልክ።የሳባ ልክ።የሕንደኬ ልብ።
ሔለን በርሔ🥰
ይሄን «ፔንዱለም» ልቤ አንዲት አፍታ ላይ ማቆም ቀላል ጥበብ ይመስልሽ ይሆናል'ኮ🤗
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
27 Jul 2026, 14:06 UTC210 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
አንድ ጓደኛዬ «ምሥጢረኛ ከተማ ናት» አለኝ።በርግጥም ደርበብ ያሉ፣የማይሞቃቸው—የማይበርዳቸው ነዋሪዎች ያላት ከተማ ናት።
ልጃቸው፦
«አይሞቃቸው
አይበርዳቸው
አገሩ...
ወይና ደጋ ነው»
ያለቻቸው የባሕርዳር ነዋሪዎችን፣ያለቻትም ባሕርዳርን እንደኔ አጣጥማ ይመሥለኛል።
ባር የውበት መዲና ናት።
የጎንደር እና የጎጃም ሴት ልጆች ውበት በኩራት ይገማሸራል።
ምሥጢረኝነቷ የነገሥታት ልጆች የመሠረቷት እና ያጸኗት ንግሥት ከመሆኗ የሚመነጭ ይመሥለኛል።
የባሕርዳር ሰው የራሡን ልጆችም ሆነ እንግዶቹን በዋጋቸው ልክ አክብሮ፣ደኅንነታቸውን ጠብቆ የማስተናገድ ልዩ ክሕሎት አለው።
ባሕርዳሮች ታክሲ ውስጥ አያወሩም።ጸጥ ነው።ቲክቶክም፣መዝሙርም፣መንዙማም፣ዘፈንም መኪና…
🥰4
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
27 Jul 2026, 13:47 UTC165 viewsread 6 August 2026 Photo
«ምነው ከሳህ ጠቆርክ
ይለኛል ባላገር
የልቤን አውጥቼ
ለሥንቱ ልናገር?»
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
26 Jul 2026, 17:10 UTC197 views3 reactionsread 6 August 2026 Photo
"ልኮብኛል አሉ፣
ልኮብኛል አሉ፣
እንዳወቀው በዜ፣
የደብረታቦሩ…"
ይህ ስንኝ በፋሲል ደምወዝ "ዞብል ነው ፈረሱ" በተሰኘው ዘፈኑ ውስጥ በተደጋጋሚ ይሰማል።
ለረጅም ጊዜ ዘፈኑን ስደጋግም ካዳመጥኩት በኋላ፣ "እንዳወቀው በዜ ማን ነው?" የሚለው ጥያቄ ደጋግሞ አዕምሮዬን መደብደብ ጀምሯል።
ፋሲል ደሞዝ በግጥሙ ውስጥ "እንዳወቀው በዜ"የደብረታቦር ሰው መሆኑን ነግሮናል።
ይሄ ሰውዬ ሲበዛ እድለኛ ነው ማለት ዩ🥰
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ደብረታቦርን "የሠይፈ አርዕድ ከተማ" ብሎ ይጠራታል። ይህም የእንዳወቀው በዜ ቀዬ ወደ መካከለኛው የኢትዮጵያ ታሪክ የምትመለስ ከተማ መሆኗን ያሳያል።
ከዚህም በላይ፣ ደብረ ታቦር ከአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ ጋር በጥብ…
🤯3
Signed ታመነ መንግሥቴ ውቤ — «ጋዜጣው»
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Gazetaw. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.