11 Sept 2026, 05:02 UTC633 views31 reactionsread 11 September 2026 Photo
መልካም አዲስ ዓመት ! 🎉🇪🇹
አዲሱ ዓመት 2019
ውድ የገላን የወንዶች አዳሪ ት/ቤት ቤተሰቦች ፤ 2019 ዓ/ም የጤና ፣ የስኬት ፣ የበረከትና የሰላም ዓመት ይሁንላችሁ።
ፈጣሪ ሰላምን፣ ጤናና፣ በረከትን ይስጠን !
መልካም አዲስ ዓመት!
Baga bara haaraa geessan! 🎉🇪🇹
Barri Haaraa 2019
Kabajamtoota maatii Mana Barumsaa Bultii Addaa Baratoota Dhiiraa Galaan; Barri 2019 kan Fayyaa, Milkaa'ina, Eebbaa fi
Nagaa nuuf haa ta'u.
Waaqni nagaa, fayyaa fi eebba nuuf haa kennu!
Baga bara haaraa geessan!
H…
🍾18❤8😭3🎉2
10 Sept 2026, 13:15 UTC962 views18 reactionsread 11 September 2026 Photo
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት መልዕክት አስተላልፈዋል።
መልዕክታቸው ዋና ትኩረቱን በሀገራዊ ምክክር፣ በሰላምና ይቅርታ፣ በኢኮኖሚ ልማት እና በቀጣዩ የኢትዮጵያ ጉዞ ላይ አድርጓል።
መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል።
ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም
#GelanMedia
#GBBSS
🤷7💔4❤3😁3😭1
10 Sept 2026, 08:52 UTC≈1,030 views8 reactionsread 11 September 2026 Photo
የነገው ቀን
ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር
ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን እየሆነ ነው። ንግድና አገልግሎትን ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል! የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግባችን እያመራ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን አረጋግጧል። በሀገር በቀል አቅም የበለጸገው የሳይበር ሉዓላዊነታችን ደግሞ የማንቆጣጠራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጥገኝነት አላቆ በዲጂታል ኢኮኖሚ በራስ አቅሟ የምትቆም አዲሷ ኢትዮጵያ በታላቅ ምዕራፍ ላይ መሆ…
😢4😁2😭2
9 Sept 2026, 13:40 UTC≈1,170 views13 reactionsread 11 September 2026 ማስታወቂያ
ለ2019 የትምህርት ዘመን በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ለወሰዳችሁ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ፤
በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት መለያ ቁጥራችሁንና የይለፍ ቃል በማስገባት ማለፍ ወይም አለማለፋችሁን ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ያለፋችሁ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ትምህርት ቤትም እዛው ላይ ማየት የምትችሉ ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው በሁሉም የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች መስከረም 5/2019 መሆኑ ለማሳወቅ እንወዳለን።
ማሳሰቢያ ፦ ተማሪዎች የተመረጡት ባመጡት ውጤት መሰረት በጥንቃቄ የተሰራ በመሆኑ ከውጤት እንዲሁም ከተመደባችሁበት ትምህርት ቤት ጋር በተያያዘ ምንም ዓይ…
❤10😭3
9 Sept 2026, 05:32 UTC≈1,240 views6 reactionsread 11 September 2026 Photo
የኅብር ቀን
ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ እየቀረጸች ትገኛለች!
በትውልድ ቅብብሎሽ ያገኘናቸውን ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር ፍልስፍና በመመራት፣ ለጽኑ ኅብረብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል። ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር የመጀመር የታሪክ እጥፋት ተነስተን፣ የሁሉም ዜጎቻችንን ሕይወት ከሚለውጡ ሰው-ተኮር የኮሪደር ልማታችን፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን በተግባር እውን እስከማድረግ ድረስ፤ ሁላችንም በአንድነት ስንቆም የጋራ ትርክቶቻችን ወደ ጋራ ስኬት እንደሚያሻግሩን በተግባር አሳይተናል።
እኛ የምንገነባው አካታች የሆነች፣ በኢኮኖሚ ራሷን የ…
☃2😭2❤1😁1
8 Sept 2026, 06:45 UTC≈1,340 views17 reactionsread 11 September 2026 Photo
የጽናት ቀን
(ጷግሜ 3/2018 ዓ.ም) ኢትዮጵያን ስናስብ፣ ሌት ተቀን በጽናት በመቆም ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ ወጥተው ለሚያድሩት ብርቱ የፀጥታ ኃይሎቻችን ቅድሚያ ሳንሰጥ ስለ ሁለንተናዊ ከፍታ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው በዚህ የጽናት ቀን፣ ለሀገረ-መንግሥታችን ዘላቂነትና ሉዓላዊነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉትን የጀግኖቻችንን ታሪካዊ መስዋዕትነት በከፍተኛ ሀገራዊ ክብር የምንዘክረው፡፡
ዛሬ ላይ ሀገራችን በራሷ ዕውቀትና በልጆቿ አቅም የላቀ የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸውን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን፣ ዘመናዊ የታጠቁ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን፣ ከባድ መሣሪያዎችንና መድፎችን፣ እንዲሁም ተተኳሽ ጥይቶችን በራሷ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች ማምረት ችላለች፡፡…
❤9😭5😁2💯1
7 Sept 2026, 18:24 UTC≈1,590 views42 reactionsread 11 September 2026 ከ7ኛ -12ኛ ክፍል ያላችሁ ተማሪዎች በሙሉ
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚጀምረው መስከረም 5/2019 ዓ.ም ሲሆን
ተማሪዎች ወደ ግቢ የምትገቡበት ቀን መስከረም 3/2019 ዓ.ም ሆኖ ስትመጡ፡-
➢ የመግቢያ ሰዓት ጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-12፡00 ባለው ስዓት
➢ በመውጫ መግቢያ ስዓት ተያዥ የሆናችሁ ወላጅ/አሳዳጊ መካከል አንዱ/ዷ/ አብሮ መምጣትና ማስገባት አለበት፤
ከት/ቤቱ የሚሰጡ ቁሳቁሶች
➢ ፍራሽ
➢ ብርድልብስ
➢ አንሶላ
➢ መወልወያና መጥረጊያ
➢ ደብተር
➢ እስኪብርቶ
➢ ዩኒፎርም ሲሆን
ቀሪ ቁሳቁሶች ይዛችሁ መምጣት ያለባችሁ ቁሳቁስን በተመለከተ
➢ መቆለፊያ 🔐
➢ መቀየሪያ ልብስ
➢ የስፖርት ትጥቅና ሽፍን …
❤22🤣9🔥4👍3😴3🍾1
7 Sept 2026, 12:22 UTC≈1,620 views81 reactionsread 11 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
😱25💔24❤10👍5🙊5😢3🤝2🤣2
7 Sept 2026, 08:38 UTC≈1,710 views5 reactionsread 11 September 2026 ማስታወቂያ
ለ2019 ዓ/ም አዲስ ለተቋቋሙና ለነባር የፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመምህርነት ሙያ ተቀጥረው ለማገልገል የፅሁፍ ፈተና በመውሰድ የማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ ለቃለ መጠይቅ ለተመረጣችሁ መምህራን በሙሉ፣
ቃለ መጠይቁ የሚካሄደው ጳጉሜ 3/2018 ዓ. ም ማክሰኞ በኦንላይን የሚካሄደ ሲሆን በምዝገ…
🌚2😁2😈1
7 Sept 2026, 08:17 UTC≈1,800 views8 reactionsread 11 September 2026 Photo
የማንሠራራት ቀን
ከቃል ባለፈ በተጨባጭ ስኬት የቆመችው ኢትዮጵያ!
ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል። ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው። ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።
…
❤4😁4
6 Sept 2026, 15:27 UTC≈1,650 views17 reactionsread 11 September 2026 ማስታወቂያ
በ2019 የትምህርት ዘመን በፌዴራል አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ በተለያየ ምክንያት የመግቢያ ፈተና ላልተፈተናችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣
የትምህርት ሚኒስቴር በ2019 የትምህርት ዘመን በፌዴራል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተመዝግበው ለፈተና የተመረጡ ተማሪዎችን መፈተኑ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ለፈተና ተመርጣችሁ በተለያየ ምክንያት ፈተና ያልተፈተናችሁ ተማሪዎች ጷጉሜ 02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፈተና መስጫ ማዕከል በመገኘት መፈተን የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፤ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በድጋሜ መፈተን የማይቻል መሆን እንገልጻለን።
🗿8👾4❤3😁1😴1
6 Sept 2026, 06:45 UTC≈1,800 views28 reactionsread 11 September 2026 Photo
የእመርታ ቀን
አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው! በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል። በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት…
😁17❤4🔥3😐2🌚1😴1
Showing the 12 most recent of 14 posts we hold for @GBBSS_info. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.