18 Oct 2025, 19:07 UTC640 views3 reactionsread 26 August 2026 የሁለተኛው አጋማሽ ምልከታ || ፉልሀም 0-1 አርሰናል
👉 የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቅ ላይ በተደጋጋሚ ስናስተውለው የነበረው በተለይም ከአስገዳጅ ቅያሪዎች በኋላ የፉልሀም ከኳስ ውጪ መዋቅርን ለማስከፈት ይቻል እንደነበር ብዙዎቻችን ገምተን ነበር።
👉 ቡካዮ ሳካ ከእረፍት መልስም በአንድ ለአንድ ግንኙነቶች ፣ እድሎችን በመፍጠር ፣ የተቃራኒ ሳጥን ውስጥ በመግባት እና የቡድን አጋሮቹ እንዲገቡ ማድረግ ችሏል። እዚሁ ላይ የጨዋታ system በትንሹም ቢሆን መነካካቱ ሳካ ላይ በተለይም አዲስ አጥቂ በመምጣቱ የሲስተሙ መፍቻ የመጨረሻው ፐዝል ወይስ የስከዛሬው ቁልፍ የሚለውን በሰፊው መመልከት ይኖርብናል።
👉 ከጎሉ ደቂቃዎች በኋላ በፍጥነት የሜሪኖን ቅያሪ ማድረጉ…
❤3
18 Oct 2025, 19:07 UTC416 viewsread 26 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
18 Oct 2025, 17:36 UTC495 views3 reactionsread 26 August 2026 Photo
የእረፍት ሰዓት ምልከታ || ፉልሀም 0-0 አርሰናል
👉 በመጀመሪያ የፉልሀምን ከ ኳስ ውጪ/ Out of possession ቅርፅ የአርሰናልን መሀል ለመሀል የመፍጠር አቅም የገደቡበትን መንገድ ማድነቅ ይገባል። ሳንደር በርግ ፣ ኬርኒ ፣ ጆሽ ኪንግ እና ኢዎቢ የፉልሀም 2ኛው መስመር የአርሰናልን የፈጠራ አቅም በደንብ ቀንሰውታል።
👉 ከማርቲኔሊ ይልቅ ትሮሳርድ ቋሚ ሆኖ መጀመሩ 2V1 ሁኔታዎች ብዙ ጊዜ ከመኖራቸው አንፃር በዚህ ረገድ ትሮሳርድ ከ wide area'ዎች ቡድኑ control እንዲኖር ለማድረግ የሚመስል ሲሆን ትክክለኛ ውሳኔም ይመስላል ለጨዋታው
👉 ኤብሪቼ ኢዜ የቀኝ #8 ቦታ ላይ ራሱን ያገኘ አይመስልም ከነፃነት አንፃር ገደቡ ላልቶለት roam እያ…
👏2❤1
18 Oct 2025, 13:33 UTC348 viewsread 26 August 2026 የሁለተኛው አጋማሽ ምልከታ || ኖቲንግሀም 0-2 ቼልሲ
👉 ከእረፍት መልስ የተደረጉትን 3ቱ ቅያሬዎችን በመጀመሪያ አንስተን እንለፍ
ጊቴንስ በጋርናቾ = ሚሊንኮቪች ባለበት side የቡድኑ የማጥቃት ሂደት እንዲያድግ በአንድ ለአንድ ግንኙነቶች የተሻለ ስፔስ ለራሱ በማዘጋጀት ረገድ የተሻለ በመሆኑ
ጉዩ በሳንቶስ = ፊዚካሊ በመጀመሪያው አጋማሽ ከአሳቶ ጋር ጆ ፔድሮ በመቸገሩ እንዲሁም እድሎችን ለመፍጠር የተሻለው መንገድ ፔድሮን ወደ #10 ቦታ መመለስ በመሆኑ ፤ ከ profile አንፃር ደግሞ ፔድሮ out&out ደምበኛ አጥቂ ስላልሆነ ወርዶ እንዲጫወት
ካይሴዶ በላቪያ = ብዙ ማብራሪያ የማይጠይቅ ቅያሪ
👉 ከእነኚህ ቅያሪዎች ውጪ ግን የግራ የመሀል ተከላካይ …
18 Oct 2025, 13:33 UTC271 viewsread 26 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
18 Oct 2025, 12:31 UTC312 views3 reactionsread 26 August 2026 Photo
የእረፍት ሰዓት ምልከታ || ኖቲንግሀም 0-0 ቼልሲ
👉 የጨዋታው ዋነኛ ትኩረት የሚይዘው ጉዳይ የቼልሲ የበዛ ስህተት ነበር...የኖቲንግሀም እድሎች መፈጠር ምክኒያት ከመሆናቸው በላይ ቡድኑ settled ሆኖ ኳሱን 2ኛው የሜዳው ክፍል ላይ እንዳይቆጣጠሩት አድርጓቸዋል።
👉 የፓሲንግ ምርጫዎች ፣ ፓሱን ለማድረግ የሚወስኑበት ፔስ በተጨማሪ ደግም የኖቲንግሀም ሰው በሰው / man to man ፕረሲንግ የቸልሲን ቢውልድ አፕ የመጀመሪያ ኳሶች የሚቀበለውን ላቪያን በቀጥታ ፕረስ በማድረግ ከ 2ቱ ተከላካዮች አንዱን ብቻ ነፃ በማድረግ በረጅሙ እንዲወጡ እና ስህተት እንዲሰሩ መዳረግ ነበር የሀሳባቸው መሰረት የሚመስለው።
👉 በግራ በኩል በቻሎባህ በኩል ኳስ progress…
❤3
19 Aug 2025, 20:12 UTC721 views5 reactionsread 26 August 2026 Photo
ጨዋታው ለዩናይትድ ጥሩ ምልክቶች የነበሩት ሲሆን ይበልጥ ግን ለአመራሮቹ የትኛው ቦታ እንደቀረ ጠቁሞ ያለፈ ይመስላል። ከበጀት አንፃር እጥረት ቢኖርባቸው የአማካይ ቦታው ከግብ ጠባቂ የበለጠ አንገብጋቢ ነው የሚል የግል ምልከታ ልናስቀምጥ ወደድን።
ሌላው ከአርሰናል perspective ጨዋታው እንዴት ይመስላል የሚለውን በደንብ ለመናገር ከባድ ነው። ሌላ የግል ምልከታ እንጨምር እና ቡድኑ አዲስ ሀሳቦችን ይዞ በፕሪ ሲዝን ሲሞክሬ መቆየቱ ትንሽ ከነበሩበት የጨዋታ ቅርፅ ይዟቸው ወጥቷል።
ከሽግግሮች ባልተለመደ መልኩ አርሰናል እድሎችን ሲፈጥሩ ተመልክተናል። የማርቲን ኦዴጋርድ በትራንዚሽን ወቅት የሚወስናቸው ውሳኔዎች በመጠኑም የእድሎችን ጥራት የተገደቡ እንዲሆኑ …
👍4❤1
19 Aug 2025, 19:56 UTC471 views5 reactionsread 26 August 2026 Photo
የካሴሜሮ እና ደሊት ወደ ፔናሊቲው ጠርዝ ኳስ ለመቀበል ለተቃራኒ ቡድን ተጨዋቾች ጀርባቸውን መስጠት ኦዴጋርድ እና ራይስ build አድርገው እንዳይወጡ ለማድረግ ወደ ፊት እንዲጠጉ ያደርጋቸዋል።
ይህም ከጀርባ ብሩኖ ከባይንዲር ኳስ እንዲቀበል ያስችለዋል። ጎሉ ላይ ትልቅ ስህተት የሰራ መሆኑ እርግጥ ቢሆንም ከ ኳስ ጋር distribution'ኡ የተሻለ ነበር።
ማውንት ወደ አማካይ ክፍሉ drop ሲያደርግ ቤን ዋይት ኳስ እንዳይቀበል ይከተለዋል። ይህም ከዊሊያም ሳሊባ ጋር የሚገናኘው የግራ ዊንግባኩ ፓትሪክ ዶርጉ ይሆናል።
ከአማድ ቅያሪ በኋላ ማርቲኔሊ የሌኒ ዮሮን ነፃነትን ለመገደብ ብዙ ጊዜ ሲጠጋ አማድ ነፃ ሆኖ advance እንዲያደርግ ረድቶታል።
ይህም ከ…
❤5
19 Aug 2025, 19:06 UTC399 views4 reactionsread 26 August 2026 Photo
#የቀጠለ
አንዳንዴ ደግሞ ኳስ progress ለማድረግ ብሩኖ mark ከሚያደርገው ተጨዋች በብዙ ርቀት ቀድሞ ወደ ራሱ ጎል ተጠግቶ ከግብ ጠባቂ ኳስ ተቀብሎ በአንድ ንክኪ በቀኝ በኩል ነፃ ሆኖ ለሚጠብቀው ዮሮ ኳስ ያቀብላል።
ለዩናይትድ በቀኝ በኩል / ለአርሰናል በግራ ዮሮ ኳስ እየገፋ ለመጠጋት ጫና አይኖርበትም። ለምን ካልን ማርቲኔሊ በቅርብ ርቀት ዲዬጎ ዳሎን ስለሚከተል ነው። ስለዚህም ዮሮ ማንም እስካልተጠጋው ድረስ ኳስ ይዞ ይጠጋል ከዛም ረጅም ኳስ ይጥላል።
የደሊት situational pivot መሆን ብሩኖን ወደ ፊት እንዲጠጋ ከማስቻሉ በላይ ማውንት እና ኩኛ እየተፈራረቁ ወደ ግራው ቻናል drop ስለሚያደርጉ ዙብሜንዲን አብረው ይስቡታል።
#ይቀጥ…
🔥3❤1
19 Aug 2025, 18:53 UTC444 views3 reactionsread 26 August 2026 Photo
#የቀጠለ
ብዙ ጊዜ ያልነው እና እንዴት አሞሪም የ Central Center Back ሚናን adapt ያደርጋል ብለን ይወራንበት ሀሳብ በአርሰናሉ ጨዋታ በተለየ መንገድ ለመጠቀም ተሞክሯል።
በጨዋታው ለደሊት የተወጣው ተጨዋቹ ካለው skillset ጋር የሚጣጣም በትንሹም ቀለል ያለ ሚና ነበር። ደሊት በአሞሪም ሀሳብ ውስጥ የማይቀረውን ወደ ፊት ተጠግቶ ከካሴሜሮ ጋር double pivot ሰርቶ ብሩኖ ወደ ፊት advance እንዲያደርግ ነፃነት ሰጥቶታል።
የደሊት ወደ መሀል ከገባ በኋላ ዮሮ በቀኝ በኩል ተነጥሎ ኳስ ለመቀበል ራሱን የሚያዘጋጅ ሲሆን ደሊት ከግብ ጠባቂው ባያንዲር ኳስ ሲቀበል bounce አድርጎ ለዮሮ ኳስ ያቀብላል።
ከዛም በዮሮ በኩል ረጅም ኳሶችን…
🔥3
19 Aug 2025, 18:37 UTC393 views10 reactionsread 26 August 2026 Photo
በመጀመሪያ ዩናይትድ ካለፉት ጊዜው እድገት ያሳየውን ቢውልድ አፑን እንመልከት !
ሩበን አሞሪም ሙሉ resource ሲኖረው ሁሌም በ build up ወቅት የተቃራኒን የመጀመሪያ መስመር ፕረስ አድራጊዎችን ወደ ራሱ ሜዳ ጋብዞ ኳሱን በፍጥነት በአንድ ንክኪ የፓስ ሂደቶች ፕረሲንጉን ማለፍ ይፈልጋል።
በአርሰናሉ ጨዋታ ከሞላ ጎደልም (የተቃራኒ ቡድን ከተገኘበት የጨዋታ ቅርፅ አንፃር ሙሉ በሙሉ ማለት ስለማይችል) ይህንኑ ነው ያየነው፤
ዩናይትድ ኳስ build ሲያደርጉ 4+2 base ይኖራቸዋል። ዮሮ የተቃራኒ ቡድን ፕረሲንግ መሪን (ኦዴጋርድን) press እንዲያደርገው ይጋብዘዋል። ዮከሬሽ : ደሊትን ፣ ሳካ : ሾውን ፣ ማርቲኔሊ ደግሞ ዳሎን ኳስ ከተቀበሉ ወዲያው …
🔥7❤3
19 Aug 2025, 18:37 UTC388 views0 reactionsread 26 August 2026 Photo
✍ የአሞሪሙ ዩናይትድ ምን አሻሽሎ ቀረበ?
✍ 3 ነጥቡን ይዞ ከወጣው አርቴታስ አንፃር ጨዋታው እንዴት ይታያል?
የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ የነበረውን የኦልድትራፎርዱን ፍልሚያ በትንሹ እንቃኛለን።
t.me/Footyview
Showing the 12 most recent of 16 posts we hold for @Footyview. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.