8 Aug 2024, 10:41 UTC493 views2 reactionsread 8 August 2026 ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ሐምሌ 30, 2016)
የአማራ ክልል የጸጥታ ችግር እየጨመረ በመጣበት ወቅት የጸጥታ እርምጃዎችን አጠናከረ
የአማራ ክልል መንግስት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በቅርቡ የተከሰተውን ውጊያ ተከትሎ ጥብቅ የጸጥታ እርምጃዎችን ውስዷል። ሐምሌ 21 ቀን ባህር ዳር ከተማ የሰዓት እላፊ አዋጅ ያወጣ ሲሆን በከተማው ውስጥ የጦር መሳሪያ መያዝም ተከልክሏል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተማዋና አካባቢዋ ብዙ መሳሪያዎችን የያዘ ሲሆን በደቡብ ጎንደር ዞን ምስራቅ እስቴ ወረዳ በፋኖ ታጣቂዎች ላይ ዘመቻ አድርጏል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰኔ 2016 ቢያበቃል የፀጥታ ችግር በክልሉ ቀጥሏል። ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ …
❤2
1 Aug 2024, 16:03 UTC393 views2 reactionsread 8 August 2026 ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ሐምሌ 23, 2016): የፋኖ ታጣቂዎች በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን ፈፅመዋል የተባለ ሲሆን በእነዚህ ጥቃቶች ቢያንስ የሰባት ሰላማዊ ሰዎች ሞተዋል። በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በጥቃቱ ምክንያት በታጣቂው ቡድን እና የፀጥታ ኃይሎች መካከል ውጊያ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል። በቅርብ ጊዜ የወታው ዘገባችን ስለእነዚህ ክስተቶች እና ስላላቸው አንድምታ ሰፋ ያለ ዳሰሳ ያቀርባል።
ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ፡- https://bit.ly/3SwJitl
👍2
25 Jul 2024, 17:21 UTC335 viewsread 8 August 2026 #ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ሐምሌ 6-12, 2016): ተቃውሞ እየተደረገ ቢሆንም ተፈናቃዮች የይገባኛል ጥያቄ ወደ ሚነሳባቸው የትግራይ ደቡባዊ ዞን አካባቢዎች መመለሳቸውን ቀጥለዋል። ዘገባው በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የተከሰቱ ውጊያዎች እና ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችንም ይሸፍናል።
ሙሉ ዘገባውን እዚህ ያገኛሉ፡ https://bit.ly/3zXPEeO
19 Jul 2024, 12:56 UTC308 viewsread 8 August 2026 ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ሰኔ 29-ሐምሌ 5, 2016)
- በኦሮሚያ ክልል ከ100 በላይ ተማሪዎች ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ በቀጠለው የጸጥታ ችግር በሰላማዊ ሰዎች መጎዳታቸውን ቀጥለዋል። የኦሮሚያ መንግስት 160 ተማሪዎችን ማስፈታቱን ቢናገርም የታጋቾች ቤተሰቦች ግን አብዛኞቹ አሁንም በአፋኞች እጅ ውስጥ እንዳሉ ይናገራሉ።
- በአማራ ክልል የተመሠረተው የሰላም ኮሚቴ ጥረቱን ቢቀጥልም በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚደረግ ውጊያ ሳይቋረጥ ቀጥሏል። በተመሳሳይ በሱዳን ስደተኞች ላይ በታጣቂዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች የቀተሉ ሲሆን ሰኔ 29 ቀን የሱዳን ስደተኞች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች አንድ ቀን ቀደም ብሎ የታገተ የሀገራቸው ስደተ…
12 Jul 2024, 11:58 UTC287 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
ኢትዮጵያ ሳምንታዊ ዘገባ (ሐምሌ 2, 2016): በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች አፈና እና ውጊያ መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን በአማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ተገድለዋል። ይህ ዘገባ በትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች የይገባኛል ጥያቄ ወደሚነሳባቸው አካባቢዎች መመለስ መቀጠላቸውን እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት መቀጠሉን ያካትታል።
ለተጨማሪ መረጃ ሙሉ ሪፖርቱን ያንብቡ፡ https://bit.ly/3xTExmm
❤1
24 May 2024, 13:53 UTC338 views2 reactionsread 8 August 2026 በአማራ ክልል የፋኖ ታጣቂዎችን ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት የሰላማዊ ሰዎችን ሞት አስከትሏል። ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች እና በጋምቤላ ክልል እንደገና ግጭት ተቀስቅሷል።
ለተጨማሪ መረጃ በቅርብ የወጣውን የ #ኢፒኦ ሳምንታዊ ዘገባ ይመልከቱ፡ https://bit.ly/3R0aEqW
Read the full report in English here: https://bit.ly/3VfioIe
👍2
3 May 2024, 16:08 UTC304 views2 reactionsread 8 August 2026 #የኢፒኦ ሳምንታዊ መረጃ - ከሚያዚያ 12 እሰከ 18, 2016፡ በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ ለአንድ አመት የቀጠለ ሲሆን በተለይም በቅርቡ በነበረ ውጊያ 20 ታጣቂዎች መሞታቸው ተነግሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያም ግጭት የቀጠለ ሲሆን በምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ውጊያ ነበረ። ምንም እንኳን ሚያዝያ 10 የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም በአፋር እና ሶማሊ ድንበር አካባቢ ሚያዚያ 4 እና 5 እንደገና ያገረሸው ውጊያ የሰላም ጥረቶችን አውኳል። በእነዚህ ተግዳሮቶች መካከል ኢትዮጵያ በ2013 ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ባልተካሄደባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ሰኔ 9 ቀን ምርጫ ለማድረግ እየተዘጋጀች ነው።
ስለእነዚ…
❤2
25 Apr 2024, 12:55 UTC282 views2 reactionsread 8 August 2026 ባለፈው ሳምንት በ#ኢትዮጵያ ደቡባዊ ትግራይ ዞን ውጥረት ጨምሯል።። የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ውጊያ ከ50,000 በላይ የሚሆኑ ስዎች የተፈናቀሉ ሲሆን የፕሪቶሪያ ስምምነት ተከትሎ የነበረውን መረጋጋት አደጋ ላይ ይጥላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ክልል በነበረ ጦርበት 64 የፋኖ ታጣቂዎች እና በከባድ መሳሪያ ተኩስ የተገደሉ ቢያንስ አምስት ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ በርካቶች ላይ ጉዳት ደርሷል። በኦሮሚያ በኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ በትራንስፖርት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን መፈጸሙን ተከትሎ በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ በማሳደሩ በክልሉ ያለው አለመረጋጋት ቀጥሏል።
ስለነዚህ ሁኔታዎች ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ለማግኘት የእኛን ዝርዝር…
👍2
12 Apr 2024, 06:18 UTC282 viewsread 8 August 2026 #ኢፒኦ ሳምንታዊ መረጃ (ከ21-27መጋቢት)፡ በአማራ፣ ትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተከሰቱ ግጭቶች በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ጋር ተደምሮ ስንብቷል። የአማራ ክልል ከእጅ ቦምብ ጥቃቶች ጎን ለጎን በመንግስት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መቀጠሉ ተዘግቧል። በትግራይ ክልል የዩንቨርስቲ ተማሪዎች እና የአማራ ተወላጆች ተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በኦሮሚያ ከኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ ጋር የተያያዘ ውጊያ እና በዚህ ታጣቂ ቡድን እና በመንግስት ኃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነግሯል። በተመሳሳይ በቅርቡ ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ እና ፑንትላንድ ጋር ባደረገችው ግንኙነት ምክንያት ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር በማባረር የራሷ…
5 Apr 2024, 07:35 UTC262 viewsread 8 August 2026 በቅርብ የወጣው #ኢፒኦ ሳምንታዊ በትግራይ ክልል በደቡብ ትግራይ ዞን አወዛጋቢ አካባቢዎች ስለተከሰተው ውጊያ፣ በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለደረሱ ጥቃቶች እና በጋምቤላ ክልል ስለቀጠለው ግጭት ይሸፍናል።
ሙሉ ዘገባውን እዚህ ያንብቡ፡ https://bit.ly/3PMcScT
22 Mar 2024, 13:59 UTC285 viewsread 8 August 2026 በቅርብ የወጣው የ #ኢፒኦ ሳምንታዊ ዘገባ በአማራ ክልል በመጠኑም የቀነሰ ቢሆንም በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ኃይሎች መካከል ስለቀጠለው ውጊያ እና በኦሮሞ እና በአማራ ብሔር ታጣቂዎች መካከል ስለተቀሰቀሰው ውጊያ ያጠቃልላል። በኦሮሚያ ክልል በመንግስት ኃይሎች እና በኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ መካከል ስለተካሄደው ጦርነትም ይዘረዝራል።
ሙሉ ዘገባውን እዚህ ያንብቡ።
4 Mar 2024, 09:02 UTC292 viewsread 8 August 2026 የካቲት 13 ቀን በትግራይ ክልል በደቡባዊ ትግራይ ዛታ ወረዳ የትግራይ ብሔር ታጣቂዎች ከአማራ ብሔር ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል። ይህም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጣልቃ እንዲገባ አርድጎታል። ይህ ውጊያ ባለፈው ሁለት ሳምንት በኮረም ከተማ አቅራቢያ እና በጨርጨር፣ በራያ አላማጣ እና በራያ ባላ ወረዳዎች የካቲት 6 እና 7 በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረጉ ውጊያዎች ቀጣይ ነው። እንደ ቀደመው ሳምንት ሁሉ የባለፈው ሳምንት ውጊያ ለአጭር ጊዜ ብቻ የቆየ ሲሆኑ ይተዘገበ ሞት አልነበረም።
ለተጨማሪ መረጃ በቅርብ የወጣውን የ #ኢፒኦ ሳምንታዊ ይመልከቱ፡ https://bit.ly/49BjLW7
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @EthiopiaPeaceObservatory. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.