14 Jan 2025, 18:35 UTC132 views0 reactionsread 8 August 2026 ሌላ ሴት ልታገባ ያልክ ቀን እንኳ ብደውልልህ እሷን ትተህ እኔ ጋር ነው አይደል የምትመጣው? እለዋለሁ ሁሌ …. ፈገግ ብሎ ያየኝና “ደፋር ኮ ነሽ….ይለኛል።
ካለሁ ነገር ሁሉ እኔን አስበልጦ እንደሚወደኝ አውቃለሁ ሲሳሳልኝ ከራሱ ሲያስቀድመኝ ሲጨነቅልኝ ለኔ ሲኖር አይቻለሁ በእርግጥ እንዲ ማለት ከባድ ይመስላል።
እኔ ግን አይኑን ሳያርገበግብ ይሄን ልጅ ግን ምን አስነክታው ነው እስኪባል የሚያውቁን ሁሉ እስኪገረሙ ድረስ ….ሳናድደዉ ሳበሳጨው ችሎ በክፉ ቀናቶቼ ላይ ለደስታዬ ሲፈጋ አብሮነታችንን ለማቆም ብዙ ሲለፋ አውቅ ነበር።
ይመስለኛል የበዛ መውደዱ የትም አይሄድም ብዬ እንዳስብ ለኛ እንዳልጨነቅና በተወዳጅነት ተኮፍሼ ለሚሰጠኝ መውደድና ክብር ትንሽ…
Signed Melat
4 Nov 2024, 12:23 UTC133 viewsread 8 August 2026 የጠገበ ልቤን የሚወጥር ሙገሳ ጆሮዬ ገባ። ኪዳን ከልጆች ጋር ተጣልቶ ሲያለቅስ የሰፈር ማቴ ለእኔ ሊያሳብቅ ሲሮጥ አንድ አልፎ ሂያጅ«አሁን አንተ የአባትህ ልጅ ነህ? ያ አባትህ ቢያይህ እንዴት ይክፉው? ወንድ አይደለህ እንዴ ምን ያነፋርቅሃል? ልጅማ ወልዷል የሴት ወንድ፣ የአባቷ ልጅስ እሷ ናት።» ያለውን ኪዳን ሲነግረኝ ጥጋቤ አናቴ ላይ ወጥቶ አጎቴን አሳር አሳየሁት። እየሰነባበተ የሆነ ቀን አንድ የኛ መንደር ልጅ እና የአባቴ ገዳዮች ወገን ልጅ ገበያ መሃል በተነሳ የግል ፀብ ሲያያዙ መሃል ጥልቅ ብዬ <እጇ ላይ መሞቱ ነው> ብሎ ሰው ጠልቃ እስኪገባ ድረስ በጥላቻዬ ልክ ቀጠቀጥኩት። ከአጎቴ ውጪ ማንም የከፋው አልነበረም። ይባሱኑ መንደርተኛው «ቁርጥ አባቷ…
Signed Melat
4 Nov 2024, 12:23 UTC75 viewsread 8 August 2026 #የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ሶስት)
(ሜሪ ፈለቀ)
«አባቴም እንደእነሱ መጥፎ ሰው የነበረ ቢሆንስ? የሆነችን ልጅ አባት የገደለ ቢሆንስ? የሆነኛው ሰው ሚስት ስትደፈር ቆሞ አይቶ ቢሆንስ? መቼም ከተማቸውን በእሳት ሊለኩስ ሲሄድ <የእግዜር እንግዳ> ብለው አልተቀበሉትም! ተታኩሰዋል አይደል? በተኩሱ መሃል የገደላቸው ሰዎች እነሱም የሆነች ህፃን አባት ፣ የፀቡ ግብም አላማም ያልገባት የሆነች ምስኪን ሴት ባል ይሆናሉ።» አልኳት እናቴን ከቀናት ድንዝዝና እና ማሰላሰል በኋላ የሆነ ቀን። ከአሁን አሁን ትጎፈላለች ብሎ በዓነቁረኛ የሚከታተለኝ አጎቴ ዝግንን እያለው
«ውይ በስመአብ!!! እውነትም አባትሽን ዘን…
Signed Melat
4 Nov 2024, 12:19 UTC67 viewsread 8 August 2026 *ፀጉረ ልውጡ*
ክፍል ሀያ
የመጨረሻ ክፍል
...ዘንዶው ወደኔ ሲመጣ አይኖቼ ተስፋ ቆርጠው እየተስለመለሙ ተከደኑ የሞቴ ቀን ከዛሬ ውጪ መቼም ሌላ እንደማይሆን ለራሴ ነገርኩት ግን በድንገት ነጭ ልብስ የለበሱ መዘምራን ህዝብ በሞላው አዳራሽ ውስጥ ሲዘምሩ አየሁ እንዲ ይል ነበር መዝሙሩ
*አልሞትም በህይወት ኖራለሁ፣
*ያምላኬን ስራ አወራለሁ፣
*የሞቴን መርዶ የሰማችሁ፣
*አለሁኝ ደስ ይበላችሁ፣
ይሄን ዝማሬ ከሰማሁ በሗላ አቅሜ በረታ አይኖቼ ከቀድሞ ይልቅ በድፍረት እና በምሬት ተገለፁ በውል የማላስተውለው የሰጣ ገባ ድምፅ ጆሮዬ ገባ ክንዴን መሬት አስደግፌ እጄን ተመርኩዤ ቀና አልኩኝ ዘንዶው ወደ ቀድሞው ፈረስነቱ ተቀይሯል የዋሻው ሰው በፀጥታና በድንጋጤ መሀል…
Signed Melat
28 Oct 2024, 16:13 UTC66 viewsread 8 August 2026 እናቴ ያቆመችውን ልመና በለቅሶ ታጅባ ቀጠለች። የሰማት አይመስልም። ቢሰማትም ግድ አልሰጠውም። ይልቅ እንደመቆጣት እያለ
« ስንት ነገር እያለብን አንተ እዚህ ወገብህን ታላቅቃለህ? ተነስ ወደዚያ!» ብሎ አምባረቀ። አለቃቸው ነገር ይመስላል።
መሳሪያውን ይዞ የቆመው ሰውዬ «መሬቱን ወስደንበታል። ሚስቱንም እንቅመስለት ብለንኮ ነው!» ብሎ አስቀያሚ ሳቅ እየሳቀ ከእናቴ ላይ መነሳት ሲጀምር ሰውየውን በልቤ አመስግኜ ሳልጨርስ እሱም የአጋንንት ሳቅ የመሰለ ቃጭል ማስካካት አስካክቶ
«እንዲያ ነው …..» ብሎ ሱሪውን መፍታት ሲጀምር ከእኔ የሚበልጥ እልህ እና መጠቃት ሰውነቴ ውስጥ ነደደ። ወዲያው ከውጪ የሆነ ሰው ተጣራ
«ሙሉሰው? ሙሉሰው?» ይሄኔ ሊፈታ የጀመረው…
Signed Melat
28 Oct 2024, 16:13 UTC36 viewsread 8 August 2026 #የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ ሁለት)
(ሜሪ ፈለቀ)
ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ ለደቂቃዎች ቆየሁ። ምን ያህሉን እንዳስታወስኩ ባላውቅም ደጁን እያየሁት ምስሎቹ ጭንቅላቴ ውስጥ ቅርፅ እየሰሩ ተደረደሩ። ከቤት ተንደርድሬ ስወጣ በዛ ያሉ መሳሪያ የታጠቁ ወንዶች በድል አድራጊነት እየተወጣጠሩ ጊቢያችንን አልፈው እየወጡ፣ የመጨረሻው ሰውዬ አባቴ በወደቀበት ተራምዶት ሲያልፍ ፣ ዘልዬ አጠገቡ ስደርስ የቱጋ እንደተመታ እንኳን እንዳይለይ ሆኖ ልብሱ በደም ርሶ በእጁ የያዛትን የሲጋራ መለኮሻ መጨበጥ አቅቶት እጁ ሲዝል፣ እሪሪሪ ብዬ ስጮህ እንኳን መንደርተኛው ባለመሳሪያዎቹን ፈርቶ ስለተሸሸገ ብቅ ያለልኝ ጠፍቶ ባለመሳሪያ…
Signed Melat
28 Oct 2024, 15:59 UTC28 viewsread 8 August 2026 *ፀጉረ ልውጡ*
ክፍል አስራ ዘጠኝ
፡
...የዋሻው ሰዎች ደማቸውን ለመበቀል እንደመጡ ተሰማኝ የዋይታና የደስታ
በሚመስል ጩኸት ወደ ጎሳው መንደር ተቃረቡ በግራ እና በቀኝ ቀጥ ባለ
ረድፍ እሳት የያዙ ሰዎች ይታያሉ መሀል ላይ ከወገብ በላይ እርቃናቸውን የሆኑ
እዘለሉ እየተንከባለሉ ወደ መንደሩ መቅረብ ጀመሩ ከጎሳው አባል አንዱ
ድምፁን ከፍ አርጎ በማላስተውለው ቋንቋ ተናገረ አንደኛው ከሱ ተቀብሎ
አስተላለፈ ሙሉ ጎሳው የተፈጠረውን ሰማ ሁሉም ከመኝታው ተነሳ
ሚመጣውንም ለመቀበል ተሰናዳ በድንገት የጎሳው መሪ ጣቱን ወደኔ ቀስሮ
የሆነ ነገር አለ ሶስት ሰዎች ጦራቸው ቀስረው እንድነሳ አዘዙኝ እኔም ተነሳሁ
ከጎሳው መንደር መውጫ ወደ ሚታየው ድንበር ጠቆሙኝ የዋሻው…
Signed Melat
28 Oct 2024, 15:57 UTC37 viewsread 8 August 2026 ፀጉረ ልውጡ *** ክፍል 18
፡
....ነጩ ፈረስ ከበላዬ ቆሞ ቁልቁል ይመለከተኛል አይኑ ከአይኔ ተጋጥሞ
ሳለ....ከመቅፅበት ወደ ጥቁር አስፈሪ ዘንዶ ተቀየረ ከጭራው ተጠቅልሎ ቀጥ
ብሎ ቆሞ አፉን ከፍቶ ቁልቁል ወደኔ መምዘግዘግ ጀመረ...ፈርቼ መሞቴን
ተውኩትና ጫካ ውስጥ ከዛፍ ላይ ተሰብሮ በወደቀ እንጨት ከዘንዶው ጋር
ትግል ልጀምር ወሰንኩ...እንጨቱን ፍለጋ ጫካ ውስጥ ስርመሰመስ የዛፍ ስር
ጠልፎኝ ከቅጠል ርጋፊ መሀል ወደኩኝ....የቅጠሉ ርግፊ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ
መላ አካሌን ጋርዶታል....ዘንዶው በመጣሁበት አቅጣጫ ተከተለኝ ነገር ግን
ሊያገኘኝ አልቻለም በንዴት ያወጣው እጅግ ሰቅጣጭና ቀጭን ድምፅ
አሸበረኝ በጣም ፈራሁ እርቄ እንዳልሄድኩ የተረዳ ይመ…
Signed Melat
26 Oct 2024, 16:21 UTC43 viewsread 8 August 2026 * ፀጉረ ልውጡ *
ክፍል አስራ ሰባት
፡
....ነጭ ፈረስ ይዛ "አካባቢውን ዞር ዞር ብለህ ተመልከት የተመረጡ ሰዎች ሚቀመጡት ክቡር ፈረስ ነው" አለችኝ አይኑ የእንስሳም አይመስልም አተኩሮ ተመለከተኝ ሙሉ አይኑ ደም የለበሰ ነው ቀጥ ብሎ መጥቶ አጠገቤ ቆመ እመቤቲቱ እንድቀመጠው በዓይኗ ምልክት ሰጠችኝ የእንስሳውና የእሷ ጥምረት እጅግ አስደንግጦኛል ግን ድንጋጤዬን ለመደበቅ ፈጠን ብዬ ከኮርቻው ላይ ጉብ አልኩኝ እሱም ወደ መውጫው በሚመራው አቅጣጫ ያለ ልጓም ምሪት አመራ የዋሻውን ስራ የሚከውኑ ሎሌዎች በሙሉ ስራቸውን ትተው ከወገባቸው ዝቅ ብለው በረከት እንደሚቀበል መዳፎቻቸውን አጋጥመው በማላውቀው ቋንቋ ይለፍፋሉ ፈረሱ እንደ አንዳች በሁለት እግሮ ቀጥ ብሎ…
Signed Melat
26 Oct 2024, 16:19 UTC39 viewsread 8 August 2026 * ፀጉረ ልውጡ *
ክፍል አስራ ስድስት
....ስንብታቸው እጅግ አስፈራኝ እግሮቼ ወደ ፊት ለመሄድ ፈሩ እዚ ዋሻ ውስጥ እንደምቀር ተሰማኝ..."አይዞህ አትፍራ"አለች እመቤቲቱ አይኖቿ እንደፈጠጡና ከናፍርቶቿ በደም እንደጠቆሩ ሳይ እጅግ ፈራው አገልጋዮቹ ወደፊት ይገፉኝ ጀመር ወደ ሗላዬ ዞሬ ባሪያዎቹን ስመለከት የሁሉንም አይን እንባ ጋርዶት በሀዘን አቀርቅረው ነበር ...እመቤቲቱ አንዱን አገልጋይ በምልክት ጠርታ በጆሮው ሹክ አለችው ግን ምን እንዳለች ለማወቅ አልቻልኩም አገልጋዩም እርምጃውን ፈጠን አርጎ ተመለሰ ወደ ውስጥ ይዘውኝ ገቡ እርቃኔን አስቀሩኝ አንዳች እራፊ ጨርቅ እንኳ አላኖሩብኝም ሞቴ እንደቀረበ እርምጃው ይሰማኛል ግን የስቃይ ሞት እንዳይሆን ለራሴ…
Signed Melat
26 Oct 2024, 16:17 UTC39 views2 reactionsread 8 August 2026 « የእኔ አበባ አባትሽን የገደሉትን ሰዎች አድገሽ አንድ በአንድ ተበቅለሻቸዋል። አታስታውሺው ይሄ ይቅርብሽ!! » አለችኝ በልመና።
«አባቴ ሲሞት ስንት ዓመቴ ነበር?» አልኳት ውስጤን የአባቴን መልክ የማስታወስ ከፍተኛ ፍላጎት እያተራመሰው። ወዲያው ቀጥዬ «አባቴ ምን ይመስል ነበር?»«13 ዓመትሽ ነበር። አባትሽ ሲሞት 13 ዓመትሽ ነበር። አባትሽ አንቺን ነበር የሚመስለው። መልካችሁ ብቻ መሰለሽ? ቁመትሽ ሳይቀር የሱ ነው። ነገረ ስራሽ የእርሱ ቅጂ መሆንሽ አይጣል ነው።» አለችኝ ለቅሶዋን ገታ አድርጋ። ከዚህ በኋላ የምጠይቃት ነገር ሁሉ ከእርሱ ሞት ጋር የተያያዘ እና የሚያስለቅሳት ስለመሰለኝ ምን ዘልዬ ምን እንደምጠይቃት ግራ ተጋባሁ።
«ኪዳን የዘጠኝ ዓመት…
❤1👍1
Signed Melat
26 Oct 2024, 16:17 UTC33 viewsread 8 August 2026 #የመኖር አካፋይ ፣ የመ ፤ ሞ ፣ ት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አስራ አንድ)
(ሜሪ ፈለቀ)
ጭንቅላቷ ከአልጋ ልብሱ ወጥቶ ባይታይ ኖሮ የደቀቀ ሰውነቷ ከአልጋው ተጣብቆ አልጋው ላይ ሰው የተኛ አይመስልም ነበር። ፊቷ አጥንቱ ቢገጥም መልኳን የት እንደማውቀው ለማስታወስ አልተቸገርኩም። ስልኬ ውስጥ ካገኘኋቸው ፎቶዎች ውስጥ አይቻታለሁ። እናቴ ትሆናለች ብዬ ጠርጥሬም ነበር። አጠገቧ ከተቀመጥኩ ደቂቃዎች ቢያልፉም ከጥቂት የ<ደህና ነሽ?> ቃላት ልውውጥ ውጪ ከምን ጀምሬ ምን እንደምነግራት ወይም ምን እንደምጠይቃት ግራ ገብቶኝ ተጎለትኩ። እሷም እንደእኔ ግራ ገብቷት ይሆን ወይም ስትናገር እያማጠች በመከራ በመሆኑ ደክሟት አላውቅም ዝም ብላለች። በዝምታዋ…
Signed Melat
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Dilosann. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.