6 Feb 2025, 17:34 UTC≈1,310 views7 reactionsread 30 September 2026 File
የጸሎቴ ርዕስ ነህ
መድሃኒት ነዉ ስምህ
ጥዑመ ስም ኢየሱስ
ሀሌ ሉያ ስምህ ይቀደስ
መልቅ የሆ-ንካት ለነፍሴ
መሰማሪያ ለምለም መስኬ
በጨለማ ብርሃኔ
መታመኛ መድህኔ
ዋስትናዬ መድህኔ
በኔ ቦታ አንተ ገብተህ
መከራዬን ተቀብለህ
መታያዬ ብርቱ አለቴ
አንተ እኮ ነህ መሰረቴ
ጌታ እኮ ነህ መሰረቴ
መጀመሪያ መጨረሻ
ብርቱ አለቴ የኔ ጋሻ
የነፍሴ ነፍስ እስትንፋስ
ታሪኬ ነህ ኢየሱስ
ሞገሴ ነህ ኢየሱስ
ያየሁብህ አዲስ ቀን
ስለ ሁሉም ተመስገን
ደምህ አለ በመቃኔ
አያየኝም ሞት ኩነኔ
ገላገልከኝ ከኩነኔ
ዘማሪት ጽጌረዳ ጥላሁን
@Beza_Gospel_Ministries
@Beza_Gospel_Ministries
❤4👍3
28 Jan 2025, 15:45 UTC≈1,170 views1 reactionsread 30 September 2026 File
🔴 አልተወኝም ጌታ ለካ ይወደኛል
ዛሬም ስበድለው ልጄ ነህ ይለኛል 🔴
@Beza_Gospel_Ministries
@Beza_Gospel_Ministries
👍1
15 Jan 2025, 11:06 UTC≈1,260 views6 reactionsread 30 September 2026 ከሥስሉሱ አምላክ ውጪ መዳንን ማሰብ አይቻልም፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ፣ ከአብ የሚወጣው አጽናኙ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፣ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል።" (ዮሐንስ 15:26) በማለት ተናገረ።
ይህ ክፍል መንፈስ ቅዱስ በመጣ ጊዜ ወደ ክርስቶስ እንደሚመራን ይናገራል፤ እርሱ እውነተኛና ብቸኛ ወደ አብ መግቢያ ነው። ወደ ሕጉ ብንመለከት እግዚአብሔርን በራሳችን ጽድቅ መቅረብ እንደማንችል ያሳየናል። እኛ እጅግ ክፋ ኀጢአተኞች ነን፤ እግዚአብሔር ደግሞ ቅዱስ ነው። መልካም የምንናለቸው ነገሮቻችን ራሱ በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ናቸው። የሰው ልጅ በአዳም ጽድቅ ከተሸፈነ ፈጽሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም። ሕግን ለመ…
❤6
9 Jan 2025, 18:31 UTC934 views9 reactionsread 30 September 2026 File
በክብር ወዳረከው አሳባችን እየሄደ
መዝገባችን ወዳለበት ልባችን እየነጐደ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን ማራናታ ኢየሱስ (2)
አሜን ቶሎ ና
የኛ ጌታ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና
ማራናታ ቶሎ ና
የመለከት ድምፅ እስክንሰማ
ስትወርድ ልናይህ በክብር በደመና
በጥልቅ ናፍቆት ወደላይ እናያለን
መሲሀችን ሆይ እባክህ ቶሎ ናልን
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታችንን ማራናታ ኢየሱስ (2)
አሜን ቶሎ ና
የኛ ጌታ ቶሎ ና
አሜን ቶሎ ና
ማራናታ ቶሎ ና
ከሙታን መንድር ልጆህን የጠራህ
የንጋት ኮከብ ለጠፋነው የበራህ
በመደላደል ረስተንህ አንቀመጥ
መድሃኒታችን ዳግመኛ እስክትገለጥ
እስክትመጣ እስከምናይህ ድረስ ድረስ
አናቆምም ማለታ…
❤7👍2
3 Jan 2025, 20:49 UTC977 views6 reactionsread 30 September 2026 Our Greatest Need!
የሰው ልጅ ትልቁ ችግር ኀጢአት ነው፤ ትልቁ መፍትሄ ደግሞ ክርስቶስ። በሕይወታችን እጅግ የሚያስፈልገን እራሱ እግዚአብሔር ነው። ከክርስቶስ ውጪ ያገኘናቸው ነገሮች ከንቱ ናቸው። ሰው በክርስቶስ ሆኖ ሁሉን ቢያጣ አትራፊ ነው፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ሁሉ በሁሉ ነውና።
የጌታችን የመጀመሪያ ፈተና በዲያብሎስ የቀረበ ነበር፤ ጌታችን ይህን ፈተና የተጋፈጠው ለአርባ ቀንና ሌሊት ከጾመ በኃላ ነበር፤ እነዚህን አያሌ ቀናት ያለ ምግብ ያሳለፈ ሰው የሚፈልገው የመጀመሪያ ነገር ምግብ ነው፤ ለዚህም በሚመስል ሁኔታ ሰይጣን ድንጋይን ወደ ዳቦ የመቀየር ሀሳብን ያቀርብለታል።
ጌታችን ከሰይጣን ለቀረበለት የመጀመሪያ ፈተና ምላሹ እንዲህ የሚል ነ…
⚡2👍2❤1🔥1
25 Dec 2024, 23:13 UTC770 views8 reactionsread 30 September 2026 ምነው ዘግይቼ አንተን ማፍቀሬ!
ምነው ዘግይቼ አንተን ማፍቀሬ! ኦ ጥንታዊም አዲስም የሆንክ ውበት፥ ምነው ዘግይቼ አንተን ማፍቅሬ! እነሆ አንተ በውስጤ እያለህ እኔ ከራሴ ውጭ ነበርኩ። የማስጠላው እኔ፥ ውብ አድርገህ በፈጠርካቸው ነገሮች መካከል ያለ ማስተዋል ስጣደፍ አንተ ከእኔ ጋር ነበርክ፤ እኔ ግን ካንተ ጋር አልነበርኩም። እነዚህ ነገሮች ካንተ አርቀውኛል፥ ሆኖም እነርሱም ባንተ ባይሆኑ ኖሮ መኖር ባልቻሉ ነበር። ድምፅህን ከፍ አድርገህ ጮህክልኝ፤ ጠራኸኝም። ድንቁርናዬንም በኃይልህ ከፈትከው። ጸዳልህን ልከህ ሸፈንከኝ፤ አበራህልኝም፤ ዓይነ ሥውርነቴንም ገፈፍከው። መዓዛህን ለእኔ ተነፈስክ፤ ተንፍሼም ሳብኩት፤ ተከትዬህም ቃተትኩ። ቀመስኩህ፤ ተራብኩ፤ ተጠ…
❤7👍1
22 Dec 2024, 20:37 UTC832 views5 reactionsread 30 September 2026 በአንተ ማረፍን ማን ይሰጠኛል? ልቦናዬ ይጥለቀለቅ ዘንድ፥ ክፋቴን እረሳ ዘንድ፥ አንተን ብቸኛው ሀብቴን አቅፍ ዘንድ! ወደ እኔ መግባትህን ማን ይሰጠኛል?
አንተ ለእኔ ምንድነህ? እንድናገር በርኅራኄህ አንደበቴን ዳስሰው፥ እንዳፈቅርህ ግድ የምትለኝ፥ ምላሽ ባልሰጥ ቁጣህ የሚነደውና ከለላ የሚያሳጣኝ፥ እኔ ለአንተ ምንድነኝ? አንተን አለማፍቀር ራሱ ጉስቁልና አይደለምን? ኦ! አቤቱ ጌታዬ አምላኬ፥ በርኅሩኅነትህ መልስልኝ፥ አንተ ለእኔ ማን ነህ? "ለነፍሴ፥ እኔ መድኃኒትሽ ነኝ፥ በላት" እሰማህ ዘንድ ተናገረኝ፥ እነሆ በፊትህ የልቦናዬ ጆሮዎች ተከፍተዋል፥ አቤቱ ጌታዬ፥ ክፈትና "ለነፍሴ፥ እኔ መድኃኒትሽ ነኝ፥ በላት" ይህን ድምጽ በሩጫ ተከትዬ በመጨረሻ አንተን…
❤3👍1🥰1
21 Dec 2024, 22:22 UTC748 views3 reactionsread 30 September 2026 File
O come, all you unfaithful
Come, weak and unstable
Come, know you are not alone
O come, barren and waiting ones
Weary of praying, come
See what your God has done
Christ is born, Christ is born
Christ is born for you
O come, bitter and broken
Come with fears unspoken
Come, taste of His perfect love
O come, guilty and hiding ones
There is no need to run
See what your God has done
Christ is born, Christ is born
Chris…
❤3
18 Dec 2024, 17:08 UTC701 views4 reactionsread 30 September 2026 File
ይራራልናል፣ ያስብልናል፤
በጊዜው ሰርቶ ደግሞም ያስቀናል።
ይመጣል 'ነገ' ዛሬም ያልቅና
ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናትና
ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና በአዲስ ዝማሬ በአዲሱ ዜማ
Hanna Tekle " እንደ ሰው" //Endesew// ሀና ተክሌ 2022
@Beza_Gospel_Ministries
@Beza_Gospel_Ministries
🥰4
14 Dec 2024, 13:36 UTC793 viewsread 30 September 2026 Photo
የጣቶችህን ሥራ፣
ሰማያትህን ስመለከት፣
በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣
ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣
በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ
ሰው ምንድን ነው?
ትጠነቀቅለትም ዘንድ
የሰው ልጅ ምንድን ነው?
መዝሙር 8:3-4
@Beza_Gospel_Ministries
@Beza_Gospel_Ministries
12 Dec 2024, 20:39 UTC692 views2 reactionsread 30 September 2026 File
ልቤ ተሰብሮብኝ ሳቃስት
መንፈሴ ሲሞላ በጭንቀት
መፍትሔ ከሰው አልሻ
ጌታዬ እያለ ወገሻ
ከእግሩ ስር ወድቄ አነባለሁ
ኋላ በፈውስ እመለሳለሁ /2
ልንበርከክ ሁሉን ልንገረው
ልገስግስ ውስጤን ላሳየው
መሰውያዬ ስር ነውና
ነገሬ ሁሉ የሚያልቀው /2
የተቀጠቀጠን ሸንበቆ
ሳይሰብር የሚጠግን አለኮ
ማንም የማይዘጋው በር አለኝ
ላራግፍ ገብቼ ሸክሜን
ስለእኔ የሚሰማው ኢየሱስ ነው
በጸሎት ነገሬን ላጫውተው /2
ልንበርከክ ……
ለኑሮዬ ትርጉም ሲጠፋ
ሲጨላልምብኝም ተስፋ
በመጠበቂያዬ ላይ ሆኜ
መጠበቅ አውቃለሁ ታምኜ
ሁሉንም ያደርጋል ለበጎ
ብዙ አሳልፎኛልኮ /2
ልንበርከክ ….
የነፍሴ የስጋዬንም ቀንበር
ሰብሮ ይጥለዋል እግዚአብሔር
ቃሉ አይሻርም እውነት ነው
ትላንት…
🔥2
11 Dec 2024, 11:27 UTC786 viewsread 30 September 2026 Photo
@Beza_Gospel_Ministries
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Beza_Gospel_Ministries. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.