6 Aug 2026, 11:18 UTC249 views14 reactionsread 7 August 2026 Photo
በዚህ ዘመን ያሉ ወጣቶችን እንደማውራት ደስ የሚለኝ ነገር የለም። ለምን? ከልብ ካወራሀቸው ከልብ ያደምጡሃል። የውሸት ከዘባረቅክባቸው ይከሽፉሃል? ወልይ ናቸው እንዴ?!
ስለ እሴት ለአንድ ወጣት እየመከርሁ ነበር ....
ለአንዳንድ ሰዎች እንዲጠቅም ወደ ጽሑፍ ቀየርኩት እንዲህ ይነበባል።
እንደ ተራ የመንገድ ላይ ፌስታል፣ ነፋስ እንደሚያወዛውዘው ክብደት አልባ አትኹን። በእሴት፣ በሥነምግባር፣ በዕውቀትና በክህሎት ክብደት ይኑርህ። ይህን ጊዜ ማንም ወደፈለገው ሊወስድህና ሊስብህ አይችልም። በዘመናችን ምንም ዋጋ፣ እሴት(ክብደት) የሌላቸው ሰዎች በየቀኑ አንተን የሚጎትቱት አንተ ለራስህን እሴት ከሌለህ ብቻ ነው። ሁሉንም ነገር የመከታተል ግዴታ የለብህም፣ …
❤11🔥3
6 Aug 2026, 03:22 UTC295 views11 reactionsread 7 August 2026 Photo
«አላፊው (ጠፊው) በሚጠፋ ነገር ልቡ የተንጠለጠለ ጊዜ ያጠፋዋል፤ አላፊው በዘላቂው (በማያልፈው) ልቡ ሲንጠለጠል ግን ያኖረዋል። ስለሆነም ቁርኝትህ ከአላህ ጋር መሆኑ መዳን ነው፤ ከአላህ በስተቀር የሚያድንህስ ማን ነው?»
ሸምስ ተብሪዝ ( ቁዲሰ ሲረሁ)
በተለያዩ ቁሳዊ ነገሮች ልብን ማንጠልጠል የልብ መጥፊያዋ ነው። በአላህ ላይ ልብን ማኖር ሕያው መሆኛዋ ነው። ልባችን ንጉሥ ነው። ጥበቃ ይፈልጋል።
ካዕብ አል-አሕባር እንዲህ ማለቱ ተዘግቧል፦ ወደ ዓኢሻ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ዘንድ ገብቼ እንዲህ አልኳት፦
«የሰው ልጅ ዓይኖቹ መሪ (መሪ መንገድ የሚያሳዩ) ናቸው፣ ጆሮዎቹ ማፍሰሻ (መቀበያ) ናቸው፣ ምላሱ አስተርጓሚ ነው፣ እጆቹ ክንፎች …
❤11
5 Aug 2026, 19:25 UTC338 views19 reactionsread 7 August 2026 የመጀመሪያውን ለሊት ማለትም ከ 4:00 በኃላ እስከ 7:00 ድረስ ግድ ካልኾነ በስተቀር እንዲሁ ያለምንም ጥቅም በተለይም በስክሪን ላይ ረጃጅም ሰአታት ማሳለፍ ጥቅም የሌለው በረከት የሚያሳጣ ልማድ ነው። ውጤታማ እንቅልፍ የሚገኝበት ሰአት ነው። ለሊትም ለመንቃት፣ የፈጅር ሰላትም በንቃት ለመስገድም ወሳኝ ነው። በተለምዶ ያለምንም ጥቅም የምናመሽበት ይህ ሰአት ለማረም መሥራት ተገቢ ነው። ይህን ለማሳካት ወደ ከመግሪብ ጀምሮ ወደ ቤት የመሰብሰብ ልማድ የግድ ይላል። በተለያየ ምክንያት ሰዎች ከዚህ ልምድ ቢሸሹም ከባድ ግን አይደለም። ለራስም ጊዜ ለመስጠት ይህን መተገበር ላይ እናተኩር።
ሰላም ለይል ♥
❤19
4 Aug 2026, 09:30 UTC421 views5 reactionsread 7 August 2026 ዘመናዊ መዝናኛ ወይስ የትኩረት ስርቆት (ጘፍላ)
"ሰው ሁልጊዜ የሚያየውን ይመስላል" ይባላል። በዘመናችን ለየት ባለ መልኩ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ የሚደረጉ የድብድብና የሁከት መድረኮች (በተለይ ድራማዊ የሪንግ ድብድቦች/ሬስሊንግ እና መሰል ትርኢቶች) ከስፖርትነት ይልቅ ዓላማቸው ምን እንደሆነ ጠይቀን እናውቃለን?!
እንዲህ አይነት ፕሮግራም አዘጋጆች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን አእምሮ በደስታ፣ በቁጣ እና በከፍተኛ ውጥረት (Adrenaline) አስረው የሚያቆዩት በምክንያት ነው፡
ዋናው ትኩረትን መስረቅ (ጘፍላን) ማስፋፋት ነው። የሰው ልጅ አእምሮ በጊዜያዊና ከንቱ ውጥረቶች ሲጠመድ ከዋናው የዐለም ህይወቱ ዓላማ፣ ከፈጣሪው፣ ከስራው እና ከዕድገቱ እንዲዘ…
❤3👍2
4 Aug 2026, 09:30 UTC357 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
25 Jul 2026, 07:57 UTC731 views8 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤7👍1
25 Jul 2026, 07:57 UTC631 views8 reactionsread 7 August 2026 ባሌ አልሰማኝም፣ ሚስቴ አላዳመጠችኝም በሚል ቁጣና እልኽ ወደ ክፉ እሳቤ፣ ተፈጥሮኣዊ ወዳልኾነ ስሜት አትገስግሱ። ፍጹም ከሰዋዊነት የሚያስወጧችሁ የ "ዘመናዊ" ዳዕዋ ተጽእኖ አይደረስባችሁ። ሁሌም በስሜቶች በመጎዳት ወደ ውሳኔ ከመድረሳችሁ በፊት ከፈጣሪያችሁ አላህ ጋር በቁርኣናዊ መርህ ላይ ቆዩ።
ወሃ^ብያ ስላናደደህ በእልህ ፈረስ ሱፍያ መኾን የለብህም። እልህ፣ ሕመም፣ ብስጨት፣ በደል ሌላ ሳጥን ውስጥ ናቸው። የአንተን ትክክለኛ ማንነት የሚያሳጡ መሳናክሎች ናቸው። ባይኾን እነዚህን በአግባቡ ከተጠቀምክባቸው የለውጥህ ነዳጅ ናቸው።
ይኽን ኹሉ የማወራው፤ በጠዋቱ ከአንድ የምወደው ዳዒ ጋር በስልክ ስለ መደማመጥ ባህላችን ከቁርኣንና ሐዲስ አንጻር ለአንድ ሰዓ…
❤6👍2
23 Jul 2026, 19:56 UTC615 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
23 Jul 2026, 19:56 UTC596 views9 reactionsread 7 August 2026 የሰው ልጅ እንደ አህያ ጅራትና እንደ መልአክ ክንፍ ተቀላቅሎ የተሰራ ነው። አህያዋ ወደ መሬትና ወደ ሳር (ወደ እንስሳዊ ፍላጎት) ትጎትተዋለች፤ ክንፉ ደግሞ ወደ ሰማይ (ወደ አላህ ዕውቀት) ይስበዋል። አህያዋ ካሸነፈች ሰውየው ጭቃ ውስጥ ይወድቃል፤ ክንፉ ካሸነፈ ግን ወደ መንፈሳዊው ዓለም ይበራል።
ይህ ሐሳብ ከሰይድና ሩሚ (ቁዲሰ ሲረሁ) "መስነዊ" ላይ የተወሰደ ሐሳብ ነው። የሰው ልጅ ከእንስሳና መላእክት ባሕርይ የተሰራ ልዩ ፍጥረት ነው። መላእክት በመንፈሳዊ ቅናት የሚቀናበትና የሰገደለት፣ ሰይ^ጣን ደግሞ በቅናቱ እብሪቱ የአላህን ትዕዛዝ ተላልፎ ለሰው ልጅ አልሰግድም ብሎ ከአላህ እዝነት ተባረረ።
የሰው ልጅ እንደ የሁለቱ ጥምር ባህርያት ውጤት ነው።…
❤8🥰1
23 Jul 2026, 07:10 UTC617 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👏3
23 Jul 2026, 07:07 UTC477 views7 reactionsread 7 August 2026 መንፈሳዊነት፣ ዘመናዊ የከባቢ ጥበቃ እና የሱፊዮች ጥበብ
በአውሮፓው ድንቅ መስጂድ ጀርባ ያለው ባለራዕይ!
በእንግሊዝ አገር የሚገኘው የካምብሪጅ ማዕከላዊ መስጂድ በዓለማችን ልዩ እና የመጀመሪያው ሥነ-ምህዳር ወዳድ (Eco-friendly) መስጂድ በመሆን ትልቅ ታሪክ ሰርቷል። ኪንግ ቻርለስ ሣልሳዊ በጎበኙበት ወቅትም ትኩረታቸው መሳቡን ሚድያዎች ዘግበዋል።
ይህ 100% አረንጓዴ መስጂድ በጸሐይ ብርሃን ኤሌክትሪክን የሚያመነጭ፣ የዝናብ ውሃን አጣርቶ የሚጠቀም እና የካርቦን ልቀት የሌለው (Zero-Carbon) ነው።
የተፈጥሮ እና የእስልምና ጥበብ ውህደት ጥበባት የሚታይበት ይህ መስጂድ ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮ እንጨት የተገነባ፣ በቀን የኤሌክትሪክ መብራት የ…
👍6❤1
23 Jul 2026, 04:53 UTC409 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Showing the 12 most recent of 16 posts we hold for @Bestkerim. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.