12 Jul 2026, 06:21 UTC37 views4 reactionsread 8 August 2026 ኦሮማን
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰሞኑን እንደ አዲስ አስቴር አወቀን ሳደምጥ፣ በአሉ ግርማ ትዝ አለኝ፤ የበአሉን ኦሮማይ ታስታውሱታላችሁ ? ፀጋየ ሀይለማርያም ጋዜጠኛ ነው፤ ሮማን የተባለች ውብ ኩሩ እጮኛ አለችው፤ ሊጋቡ ጥቂት ወራት ሲቀራቸው በቀይ ኮከብ ጥሪ አስመራ ለግዳጅ ተላከ፤ በዚያም በዘመቻው መሀል ፊያሜታ የተባለች ያስመራ ሴት ተዋወቀ፤ ከባድ ፎንቃ ገባለት፤ ባስመራይቱና በሸገሪቱ ሴቶች ፍቅር መሀል ተወጥሮ በታሪካዊው ዘመቻ ላይ ተሳተፈ ፤ በመጨረሻ ሮማን አስመራ መጥታ ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር አንደያዘው ተረዳች፤ ፊያሜታ ለሱ ብላ ህይወትዋን ትሰጣለች፤ በመጨረሻም ፊያሜታን በሞት ሮማንን በቅያሜ አጥቶ አጥቶ ብቻውን ሲቀር ልቦለዱ ይጠና…
❤4
12 Jul 2026, 06:21 UTC34 viewsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
1 Jun 2026, 15:38 UTC80 viewsread 8 August 2026 Photo
እንባ እንባ ይለኛል
ይተናነቀኛል ...
ግን እንባ የታባቱ
ደርቋል ከረጢቱ
ሳቅ ሳቅ ይለኛል
ስቆ ላይስቅ ጥርሴ
ስቃ እየነደደች
መከረኛ ነብሴ።
አይ ኢትዮጵያ😓
23 May 2026, 16:44 UTC90 viewsread 8 August 2026 በየቦታው ዜጎች ያለቅሳሉ ፤ በየቦታው ሰው ይታገታል ፤ በየቦታው መፈናቀል አለ ፤ በየቦታው የሰው ልጆ ይታረዳል ፤ በየቦታው የሰው ልጅ በርሃብ ይሞታል ፤ በየቦታው ተንቀሳቅሶ መስራት አይቻልም አሁን አሁንማ ስለ መብላት ትተን ስለ ነብሳችን መጨነቅ ጀምረናል። "መሀይም ማዳመጥ አይችልም ማውራት ብቻ ነው የሚችለው..." ያለው ማን ነበር?
23 May 2026, 16:23 UTC88 viewsread 8 August 2026 ስለ ማህበረሰቡ የማያስብ፣ ሰራተኞቹን በስርዓት የማይቆጣጠር፣ ለመታየት ብቻ የሚሰራ ፣ ከሰው ነብስ ይልቅ የ አንድ ሳር መረገጥ የሚያሳስበው፣ በግ መስሎ ተኩላ የሆነ በዘመኔ አንድ አብይን አህመድን አየው። አይ ኢትዮጵያ አንድ የሚያረግሽ ጠፍቶ የሚገነጣጥልሽ በዛ😔😓
7 Mar 2026, 14:08 UTC158 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
ፈሪሳ.... ምን ይሆን?
ለማንኛውም ጋሼ ሌላ ሀሳብ ሊያስኮመኩመን ነው😍
@art_love_12
🥰3
13 Feb 2026, 07:53 UTC194 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
ደስታንም እንደቆሎ ቅሜአለሁ። ፍስሃ ደጋግማ የተባረከውን የቤቴን በር አንኳኩታለች። ችግርም በፈንታው የተለያየ ክብደት ባለው ኮቴው ወጥቶብኛል፣ ወርዶብኛል። በአዲስ አበባም ራስ ወዳድ ጎዳናዎች ላይ እስኪሳቅብኝ ቼ ቼ ብሎኛል። አንዳንዴም የአለም ችሎታዋ መቆንጠጥ ብቻ እስኪመስለኝ ተቆንጥጫለሁ። እንዲህ ሲሆን እንደ ጌታዬ 'ተፈፀመ' አላልኩም።
የተሳሳትኩትን አረምኩ።
ከአሳሳቾችም ራቅኩ።
ጥንካሬዬንም አየሁ።
ስህተት የማይፈፅም የሰው ልጅ የለም!።
ዛሬ የለበስነው ንፁህ ነገር ከትላንት ወዲያ ቆሽሾ ትላንት የታጠበ ቢሆን እኮ ነው።ታዲያ ቆሻሻው ወጥቶልን ነፍሳችን የምትፀዳው ሒስ ወይ ግለ ሒስ ስናደርግ ነው። ከሁሉ ከሁሉ ግን እልሃለሁ፤ ራስን ማጠብ ይመረጣ…
❤3
3 Feb 2026, 10:16 UTC155 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
የሚገርመኝ ነገር ነበር
ኢትዮጵያ ውስጥ በአንዳንድ የገጠር አካባቢወች ይደረጋል...ስም ሁሉ አለው ጠፋኝ እንጅ! ጭራሽ ዛሬ ህንድ አካባቢ ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርጉ አየሁ። አንዲት ላም ከወለደች በኋላ ጥጃዋ በሆነ ምክንያት ከሞተች ወተቷ ይደርቃል። ጠባችም አልጠባችም ጥጃዋ በአካባቢው ካለች ግን ሰውነቷ ወተት ማምረት ይቀጥላል። (የተፈጥሮ ተዓምር፣ የእናትና ልጅ ትስስር) ስለዚህ ባለቤቶቹ የሞተችዋን ጥጃ ቆዳዋን በሳር(ጭድ) ይሞሉና እንዲህ ጥጃ አስመስለው እናቷ አጠገብ ያቆሟታል። ሚስኪን ላም ገና ለገና ልጀ ታድጋለች ብላ በሰው ስትታለብ ትኖራለች። ትልሳታለች ታሸታታለች...ምን ልላችሁ ነው? ለመሆኑ ዋጋ እየከፈላችሁለት ያለው ነገር በህይወት …
👍1
21 Jan 2026, 07:50 UTC143 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
"ከቤታችን ሞልቶ!!"
ሁለት ሰዎች በአንዲት ሴት ይጣሉና አንዱ ሌላኛውን በመጥረቢያ ቀልቶ ይገድለዋል።
በአንዷ ሴት የተጣሉት ሁለቱም ወንዶች ደግሞ ባለትዳሮች ነበሩ።
እናም ባሏ የተገደለባት የሟች ሚስት በቀብሩ ላይ ስታለቅስ፤
"ገዳይ ሸሽቶ ሄደ ሟችም ተቀበረ፤
የተጣሉበትም ብቻውን አደረ..."
እያለች ሙሾዋን ስታወርድ፤ የገዳይ ሚስት ሰምታ ኖሮ እሷም ቀበል አድርጋ፤
"እሱስ ምን ሲል ገድሎ እሱስ ምን ሲል ሞቶ፤
የተጋደሉበት ከቤታችን ሞልቶ።
አለች ይባላል"
ቸር ይግጠማችሁ!!
🔥3
28 Nov 2025, 17:18 UTC185 views0 reactionsread 8 August 2026 https://vm.tiktok.com/ZMAKV4uaU/
28 Nov 2025, 17:15 UTC167 views2 reactionsread 8 August 2026 ልብሱ
ጫማው
ጌጡ ቀርቶ
እህል እንኳን ሳልገዛልሽ ፤
ስለ ዐይኖችሽ
ስለ እጆችሽ
ስለ እግሮችሽ ሳልፅፍልሽ ፤
ሳልጎበኝሽ
ሳልሰልልሽ
የኾንሽውን ሳልጠይቅሽ ፤
እንዲሁ . . . እንዲያው . . . እንደማንም ፤
እንደ ተራ . . . እንደ ምንም ፤
ድምፄን ውጬ ዝም ስልሽ ፤
ረስቼሽ እንዳይመስልሽ ።
ባይልልኝ ነው አበባዬ ፤
ባይሆንልኝ
ባይሞላልኝ ፤
ከዕንባ በቀር በልቤ ላይ
ሌላ ገንዘብ ባይቆይልኝ ፤
እንጅማ አንቺን ፤
እመቤቴን ፤
እንዴት ብዬ እረሳለሁ !?
ቀን በውኔ
ሌት በሕልሜ
ትዝ እያልሽኝ አለቅሳለሁ ፤
ብቻ አንድ ቀን
ሞት ካልለየኝ ፤
ያ ጨለማ ካልቀደመኝ ፤
ዕምባ አርግዤ ብቅ እላለሁ፤
እጆችሽን
እግሮችሽን
ዐይኖችሽን እስማለሁ ፤
ከአንቺ …
❤2
27 Nov 2025, 15:51 UTC112 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
አሁን ከሆነ...የምንኖረው እንጂ የምናወራበት በቂ እድሜ የለንም። ነገር ግን... ሞት አፍንጫችን ስር አለ ብለን እያመንን በቅፅበት እንደምንሞት እንዘነጋዋለን። ቆይ ግን አሁን ብንሞትስ? ለምሳሌ እኔ እንዲህ እያልኩ አስባለሁ...የፃፍኳቸው ግጥሞች እኔን ሲያጡ ይበርዳቸው ይሆን? ልክ እንደፍጡር ባልተፈጠርን ብለው ያማርሩ ይሆን(የኔ ፍጡሮች)...የሰካካኋቸው ቃሎች እናታችን ሞተች ብለው ያነቡ ይሆን?... ቲሽ የቀሽም ሰው ሀሳብ! ጥያቄው...ሳልሞት በፊት እየኖርኳቸው ነበር ወይ በሚል መስተካከል አለበት። ቆይ ቆይ... ለምሳሌ ቅድም ከምወደው ልጅ ጋር ነበርኩ። አሁን ብሞት እድሜ ልኬን ማለቴ ሙተ ልኬን...ሀሀሀ ሳቅ! ለካ ከሞቱ ወዲያ ማሰብ ፥ መጨነቅ አይቻል…
❤2👍1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Art_love_12. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.