28 Sept 2026, 16:12 UTC150 viewsread 3 October 2026 Forwarded from @AleHigPhoto
ለፌዴራል ጠበቆች መልካም ዜና የ2018 ዓ.ም. የግብር አከፋፈል አሰራር ተመቻቸ🙏🙏🙏✍️✍️
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር (EFAA) ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጋር ባደረገው የጠበቀ ውይይትና ጥረት፣ ለአባላቱ የተሻለና የተቀናጀ የግብር አከፋፈል አሰራር እንዲዘረጋ ማድረጉን አስታወቀ።
የ2018 ዓ.ም. የግብር ክፍያ አፈጻጸም በ2017 ዓ.ም. በነበረው የግብር አከፋፈል መመሪያና አሰራር መሠረት እንዲስተናገድ ተደርጓል።
የጠበቆችን የሥራ ባህሪ ያገናዘበ አሰራር እንዲዘረጋ የተደረገውን ጥረት አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በመረዳት አሰራሩን ያቀለለ ሲሆን፣ የማኅበሩ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና የቀረበላቸው መሆኑ ተገልጿል።
ማኅበሩ…
Signed Advocate Mikias Melak ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ
10 Aug 2026, 10:27 UTC920 viewsread 3 October 2026 Photo
"በችኮላና በጥድፊያ" የሚዘጋጁ ህጎች፣ በህግ አወጣጥ ስርዓቱ ላይ አለመረጋጋት እየፈጠሩ መሆኑን በጥናት ተመላክቷል።
👉 አንዳንድ መመሪያና ደንቦች ከመውጣታቸው በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የማይገመገሙ መሆኑ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ተብሏል።
👉 ህጎች በወጡ በሳምንት እና በአመታቸው ማሻሻያ የተደረገባቸውም እንዳሉም ተገልጿል።
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)
በኢትዮጵያ የህግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎች፣ የአዋጅ መሻሮችና መጣረሶች እየታዩ መሆኑን፣ ይህንንም መረጋጋት ለማምጣት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ፖሊሲም ሆነ ወጥ የህግ ማዕቀፍ በሀገሪቱ አለመኖሩን ፌደራል የህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩት ያካሄደው ጥናት አመለከተ።
ጥናቱ "የህግ አወጣጥ…
Signed Advocate Mikias Melak ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ
2 Aug 2026, 17:33 UTC924 viewsread 3 October 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Advocate Mikias Melak ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ
11 Jun 2026, 09:08 UTC≈1,390 viewsread 3 October 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Advocate Mikias Melak ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ
11 Jun 2026, 09:08 UTC≈1,290 viewsread 3 October 2026 Photo
#የግብር_ጉዳይ
የኢትዮጵያ የፌደራል #ጠበቆች ማህበር ዝማኔ ኩነት ወይም Update on Current Affairs በሚል ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መደብዳቤ ማህበሩ ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጋር የጠበቆች ግብር አከፋፈልና ከሙያው ልዩ ባህርይ ጋርየተጣጣመ የግብር ማዕቀፍ እንዲኖር በተከታታይ ውይይቶች ማድረጉን አስታውቋል።
በእነዚህ ውይይቶች በተደረሰው መግባባት እና በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 በተደነገገው መሰረት ሊዘጋጅ የሚገባውን እና የባለሙያዎች የተቀናሽ ወጪ መመሪያ ለማዘጋጀት የሚረዳውን የፖሊሲ ግብዓት ሰነድ ማህበሩ የጥናት ቡድን በመመደብ ባለፉት አራት ወራት ሲሰራ ቆይቶ ስራውን አጠናቆ ሰነዱን ለገንዘብ …
Signed Advocate Mikias Melak ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ
7 Jun 2026, 20:05 UTC≈1,080 viewsread 3 October 2026 File
#ለመረጃ፡ ጥሬ ገንዘብ ያላቸው ግለሰቦችና ተቋማት ገንዘባቸውን በማዋጣት በጋራ በተቋቋመ ፈንድ አማካኝነት በተለያዩ የትርፍ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ የሚያስችል “የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ” ረቂቅ መመሪያን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ተዘጋጅቷል ሰነዱን በማንበብ አስተያየት መስጠት ለምትፈልጉ ከላይ ተቀምጧል!
Signed Talk To Lawyer
25 Apr 2026, 07:45 UTC≈1,600 viewsread 3 October 2026 Photo
ለተከታታይ አምስት (5) ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት ነው።
ከእረፍትና ልዩ ልዩ ፍቃዶች ውጭ አንድ ሰራተኛ ለአምስት (5) ተከታታይ ቀናትና ከዚያ በላይ ከስራ የቀረ ሰራተኛን ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውልን ማቋረጥ የሚያስችል አዲስ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በሰበር መዝገብ ቁጥር 249795 ላይ አንድ ሰራተኛ በተከታታይ ከአምስት (5) ቀናት በላይ ከሥራ ከቀረ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የሥራ ውልን ማቋረጥ እንደማይችል ጠቅሶ የሕግ ትርጉም ሰጥቶ ነበር።
ሆኖም ሰበር ሰሚ ችሎቱ አሁን ላይ አሰሪው ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ከስ…
Signed Advocate Mikias Melak ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ
22 Apr 2026, 13:50 UTC≈1,370 viewsread 3 October 2026 👉 ቃብድ ✍️
ቃብድ ማለት ተዋዋይ ወገኖች ውላቸው እንዲጸናላቸው ያላቸውን ፍላጎት ለማሳየት እና ሽያጩን ለማረጋገጥ አንዱ ወገን ለሌላኛው የሚሰጠው የማስያዣ ገንዘብ ነው።
በኢትዮጵያ የውል ሕግ ሥርዓት ውስጥ ቃብድ ከመደበኛ የውል አፈጻጸም ለየት ያሉ የሕግ ውጤቶች አሉት።
1. የቃብድ የሕግ ውጤት በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885
እንደ ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885(1) እና (2) ድንጋጌ፣ በቃብድ የታሰረ የሽያጭ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለየው በሚከተሉት ነጥቦች ነው፦
ተቃራኒ ስምምነት እስካልተደረገ ድረስ፣ ቃብድ የሰጠው ወገን የሰጠውን ቃብድ በመተው፣ ቃብድ የተቀበለው ወገን ደግሞ የተቀበለውን ቃብድ እጥፍ አድርጎ በመመለስ ውሉን በፈቃዳቸው ማፍረስ ይችላ…
Signed Advocate Mikias Melak ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ
3 Apr 2026, 19:54 UTC≈1,330 viewsread 3 October 2026 Photo
#ethiotelecom
ኢትዮ ቴሌኮም በኦንላይን ሰነዶችን ለማረጋገጥ የሚያስችል የዲጂታል ፊርማ አገልግሎት አስጀምሯል።
ኢትዮ ቴሌኮም ተገልጋዮች በአካል ሳይገኙ ሰነዶችን በዲጂታል መንገድ እንዲፈርሙና ህጋዊ ማረጋገጫ እንዲያገኙ የሚያስችለውን "ቴሌሳይን" (teleSign) የተሰኘ ሶሉሽን በይፋ ስራ አስጀምሯል።
- ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣
- ከፍትህ ሚኒስቴር
- ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በመተባበር የቀረበው ይህ ሲስተም፣ ተገልጋዮች ካሉበት ሆነው የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን እንዲያገኙ ለማስቻል ያለመ ነው።
በተለይ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአካል ኤምባሲ ወይም የውክልና መስጫ ቢሮዎች ሳይገኙ የህጋዊ ውክልና ለመ…
Signed Lawyer Mikias Melak ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ
24 Mar 2026, 15:24 UTC≈1,770 viewsread 3 October 2026 File
File, posted without a caption
Signed Talk To Lawyer
15 Feb 2026, 11:57 UTC≈2,220 viewsread 3 October 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Lawyer Mikias Melak ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ
Showing the 11 most recent of 11 posts we hold for @AboutJustices. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.