26 Sept 2025, 11:02 UTC331 viewsread 7 August 2026 አንዳንድ ህመሞች መልካቸውን ሳይለውጡ ሁሌም ራሳቸውን ሆነው ማሳመማቸው ይገርመኛል! ውስጤም ለምን እንደማይለምዳቸው አይገባኝም!
ከውስጤ መብሰልሰል ያባነነችኝ ትህቱ ከፊቴ ያለውን ወንበር ስባ ስትቀመጥ ነበር።
"ይህን ያህል ምን ሀሳብ ገዛክ? ፊትህ የሚናገረው ውስጣዊ ህመምን ጭምር እንዳዘለክ ነው።" አለችኝ።
"አያናድም ግን?" አልኳት እይታዬን የመንገዱ ወከባ ላይ ጥዬ።
"ምኑ?" አለችኝ አይኔን ተከትላ ወደውጪ እየተመለከተች። ያናደደኝ ከጎዳናው ያለ መሰላት።
"ይህ ፊት ተብዬ ነው። ሰው ራሱን ሸሽጎ ራሱን ማስታመም እየፈለገ ግን አደባባይ የሚያሰጣን ባላንጣችን" አልኳት አይኗን እየሸሸሁ። ካየኋት አይኖቼ እንባን መገደብ ይሳናቸዋል፣ …
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
22 Sept 2025, 21:08 UTC287 viewsread 7 August 2026 አዛኝ ደግ ናት ጨካኝ!
ወድጃታለሁ! ይህን ቃል ከሰየምኩለት በላይ ቃላት በማይለኩት መጠን በእኔነቴ ውስጥ ትልቅ የተደላደለ ቦታ አላት!
ሳውቃት ዛሬ ላይ አይደለም! ከሁለት ዓመት በፊት እንጂ፤ ምን እንኳን እርሷ ባታስተውለኝም በሰዓቱ! በጊዜው በጣም እየታመምኩ ያለሁበት የስቃይ አምስት ዓመትን ባስቆጠረ የፍቅር (ልበለው መቼስ) ሕይወት ውስጥ ነበርኩኝ! አብርያት ካለዋት ሴት ጋር የተዳከመ አብሮነት በትግል የምመራ የመፈቀር ራብተኛ ነበርኩኝ።
በሰበብ አስባቡ ውሃ ቀጠነ አመል ግጭት ውስጤ የተሰበረ ተስፋ ቢስ በነበርኩበት መሰላቸት፤ ድንገት በሕዝብ መጓጓዣ አየኃት። ከሁለት ዓመት በፊት!
ዳግም ያየኃት እንሆን በትግሌ ላቆየው ከማልችለው የፍቅር ሕይወት ተሰ…
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
7 Sept 2025, 20:34 UTC250 viewsread 7 August 2026 Photo
ምናልባት አባትህ ፈገግታው ምጥን ይሆናል! በቀለድከው በተጫወታክ እንዳሰብከው አልሳቀልህ ይሆናል! ያም ደግሞ ስሜትህን ሰብሮት ቅር ተሰኝተኽ ይሆናል!
ምናልባት ያለሽ ጫማ ሰለቸሽ እናም አባትሽን ብር ጠየቅሽው ከጠየቅሽው ብር ላይ ቀንሱ እርሱንም ደጅማስጠናት በመሰለ ልምምጥ ሰጠሽ! ስለዚህ ከፍቶሽ ይሆናል!
እርሱ ግን...
ፈገግታውን የቆጠበው ሀሳብ ይዞት እንጂ ቦታ ሳይሰጥህ ቀርቶ አልነበረም፤ የሰጠሽ ብር ምናልባት ከትራንስፖርቱ ቀንሶ አልያም ምሳውን ዘሎ ይሆናል!
በስራው ላይ
ለነፍሱ ትልቅ risk ወስዶ፣ አላፊ አግዳሚው ከፍ ዝቅ እያደረገው፣ አለቃው የቤቱን መከፋት እያራገፈበት፣ የውስጥ ህመሙን ሸሽጎ፣ ረሀቡን አታሎ፣ ድካሙን አሳስቆ.... ነው ለመኖር…
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
26 Aug 2025, 05:19 UTC268 viewsread 7 August 2026 ሰላም-ለኪ እም!
"ልጄ ትወደኛለህ?"
"ይህ የሚጠየቅ ነው? አተሽው ነው?"
"መስማት ፈለኩኛ..." በስስ ቁጣ።
"እሽ ህይወቴ! ከአለም ውድ መውደዶች ሁሉ አብልጬ እወድሻለሁ!" እቅፏ ውስጥ እንደሚሰማኝ ሰላም፤ ሳቅፋት ይሰማት ይሆንን?
"ስታገባ ግን ጥለኸኝ ትሄዳለህ?" በፍርሃት እያየችኝ።
"እናስ! ከሚስቱም አንድ ይሆናል ይልስ የለ? ግን አረሳሽም! ከፍቅሬ ላይ አንዲት ዘለላ ስንዴ መጠን እንኳን አልቀንስም!" ከልቤ ነው አንደበቴ!
"አንበሳ የኔ መልዓክ! አየኽ ካንተ በፊት አባትህን ነው የማውቀው! አንተን ለማፍቀሬ መጠን ባይኖረኝም እንዳትቀየመኝ የእኔ ውድ፤ የእርሱን ያህል ግን አይሆንም"
ዝም አልኳት! ውስጤ ሀሴት ያደርጋል! ለአባቴ ስላላት መውደድ ስ…
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
29 Jul 2025, 19:22 UTC277 viewsread 7 August 2026 [ፊታውራሪ ደጉ ፯]
ፊታውራሪ ደጉ እንደ ስማቸው ደግ ናቸው! የሰፈሩ አድባር! የሰፈር ሰው ሲምል በስማቸው ነው። "እውነትም ስምን መልዓክ ያወጣል" እየተባለ፤ ምሳሌው ለፊታውራሪ እንደተተረተ የሚነገርላቸው ጉምቱ ሰው።
ፊታውራሪ ይህ የደግነታቸው ዝና ረፍት ነሳቸው! ፓፓራዚ* ሲወጡ ሲገቡ መዳረሻቸውን እየዘገበ ረበሻቸው! በተለይ ደግሞ ሕይወት የከበዳቸው በእፍረት የሰው ፊት ማየት የሸመማቸው* አንድ ታዋቂ መፅሔት፤ የመፀዳጃ ቤት አጠቃቀማቸው ላይ በሚያሳዩት ኩሩነትና አልሞ ተኳሽነት በፎቶ አስደግፎ እንደማደናነቅ ሰራርቶት ያሰራጨው ወቅት ነበር።
በመፅሄቱ የፊት ገፅ ላይ ቁጢጥ ብለው በሚታየው የሙገሳ ልጥፍ ላይ፤ ምንሽራቸው ጎምለል ብሎ ጦር ሜዳ እንዳለ ወታ…
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
28 Jun 2025, 21:15 UTC285 viewsread 7 August 2026 ስልብ ምኞት!¡
....
መሰልቸት ታውቃለህ?
መሰልቸት ታውቂያለሽ?
ተስፋ ከውስጥ ነጥፎ
መኖር ወዙ እስኪሸሽ?
ሳቅን መሳቅ ሽተን
ማንባት ፈለገነው
ሁለቱም ከብዷችሁ
አንዱንም ሳንይዘው?
???
??
?
.........
እንዲያ ያለ ህመም
ይህን ባሉት ስቃይ
ሕይወት ትወና ናት
መኖር ህልም መሳይ
ሰውን እየናፈክ...
ደግሞም በመከለል...
እንባን ሳቅ ይተካል
ከሰው ፊት ለይምሰል
!!!
!!
!
.........
እናም...
...
የቀረፋን ተስፋ
የጠቆረን ምኞት
ለማ…
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
27 Jun 2025, 19:22 UTC246 viewsread 7 August 2026 እህህህ....
ሰው በመናፈቅ ስቃይ
ሰው በመናፈቅ ህመም
መርገጫዬን አሳጣኝ
ባዘንኩ በመዋተት ድካም
..........
ብርታቴን፣ ተስፋን ነሳኝ
መወደድ መሻት ቀጣኝ
.......
...
"እንዴት ነህ?" መባል ስሜት
እንባን እንደ ፀጋ
ይመስል የተቸርኩት
ፍለጋው አከሰረኝ፤
ለማይሞላኝ ምኞት!!!
✍ካህሊል ጂ. (fanuel a.)
@zikiretibeb
@zikiretibeb
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
15 May 2025, 10:50 UTC318 viewsread 7 August 2026 Photo
እንዴት ብዬ ልውረድ?
አቅም አነሰኝ እንደ ሰው
እንደ-እጄ ፍጥረት ተረታው
-------------
ወኔ ከዳኝ ድፍረት አጣሁ
ረቂቅነት ጠፋኝ ተሸነፍሁ
-------------
እንደ መልኬ ያበጀሁት
በፍቃዴ የሰራሁት
አወረሰኝ ግብሩን
እኔው እርሱን መሰልኩ ውሉን
-------------
ፍርሃትም እየናጠ
እንደ ሰብ አሽመድምዶ
የሰነፍ ምሱን ገቢር
ተዋሕዶኝ ለምዶ
አካል ነፍስ ሰርቶ
ካ'ምላክነቴ ወሰን
ዳግም እንዳልሸጠ
ሰጋሁት መምጣትን
-------------
ሲቃ በበዛባት ሕመም በጠናባት
ድምጿ ቢጎረንን በ'ንባ ጣር ጩኸት
የጠወለገ አካል ደም …
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
19 Apr 2025, 07:49 UTC318 viewsread 7 August 2026 Photo
አንዲት ጠጠር ወደ ጥልቅ ባህር ውስጥ ብንሰዳት ከኢምንትነት የገዘፈ ተፅእኖ የላትም።
ይህቺኑ ጠጠር ለመያዝ ባነሰች ውሃ መቋጠሪያ ብንወረውራት ብርታቷ ከተቀባይዋ ያየለ ነውና፤ እንደ ጎረምሳ ክንድ ብርቱነቷን "ይታይልኝ" በሚል፤ የጠብታ ፍንጥቅጣቂዎችን ትፈጥራለች።
አዕምሮም እንደዛው ነው ስለ ፈጣሪ ሕላዌነት ስብከት፤ ከውቅያኖስ ሰፍቶ እና መጥቆ፤ ከእውነቱ አድማስ ካልተስተካከለ "እንደምን ያለ ነው አምላክ?" በሚል ትርጓሜ መሻት፤ በሃያልነት የሚያጠይቅ፤
ነገር ግን፤ አዕምሮን ስራ በነፈግነውና እና ባሰነፍነው ወቅታት፤ በቃላት ጥበብ መጎልበት የገዛው ሲገኝ "እንሆን አምላኬ" በሚል አማኝነት የሚጣባው።
ብቻ አማኝነት እና ኢ-አማኝነት የወቅት ሚዛናዊነት ስ…
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
15 Apr 2025, 17:31 UTC290 viewsread 7 August 2026 Photo
የአንዲት ቢራቢሮ ድምቀት አንድ ቀለም ብቻ አይደለም! ህብር ነው ውበቷ!
ቀልብን ምትገዛበት እና እይታን ምትማርክበት ትልቁ ሃይሏ ጉራማይሌ ውህደቷ ነው!
ይህን የቀለም ስብጥር የሚመትረውና የውበቷን መወድስ የሚዘርፈው የሰው ልጅ አዕምሮ ነው!
ይኽ ስለመሆኑም አንድ ሰው "የቀለሟ ስብጥር ለኔ ውበትን ሳይሆን፤ መጠንን የተሻገረ ልኬት ያልተሰመረለት መክሰር ነው።
መክሰር ደግሞ ለእኔ ውበት ሊሆን አይቻለውም" ማለት ይችላል። ችሎም አንዲትን ቢራቢቶ በመኃል ጣቱ ጥገት ሊያከስማት ይቻለዋል!
አምላክና መናፍስትም በሰው ልጅ አዕምሮ እንደ ቢራቢሮዋ ስሪት፤ ድርሳን እና መሻት ናቸው!
አእምሮው፤ ስለመኖራቸው እንደ-ቢራቢሮዋ ቀለም ፀዳል ዜማ ሰድሮ ከተቀኘ የሚገኙ…
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
5 Apr 2025, 13:10 UTC279 viewsread 7 August 2026 " ሀገር ማፍረስ ከፈለጋችሁ አህዮቿን ከታሰሩበት ፈታችሁ ልቀቁ
ሰይጣን ከግንድ ጋር ታስሮ ያገኘውን አህያ እንዳሻው እንዲቦርቅ ቋጠሮውን ፈትቶ ለቀቀው። ነፃነቱን ያገኘው አህያም ወደ አንድ ሰው ማሳ ዘልቆ ከእርጥቡም ከደረቁም በጥርሱ ይግጠው ጀመር።
የአትክልቱ ባለቤት ሚስት በመስኮት በኩል ዘልቃ ስትመለከት ማሳው በአህያው ጥርስ ታጭዶ አገኘችውና ደነገጠች። ማሳቸው በአንዴ እንዲህ መሆኑ እያበገናት መሳርያዋን አቀባብላ ተኮሰችበት። በተደጋጋሚ የተለቀቀው ጥይት ሆዱን ዘርግፎ ከመሬት አጋደመው።
የአህያው ባለቤት የተኩስ ድምጽ ሰምቶ ከቤት ሲወጣ ከግንድ ጋር ያሰረው፣ በጀርባው ተሸክሞ ከወዲህ ወዲያ እያመላለሰ የሚያገለግለው አህያ በደም ተጨማልቆ ከመሬት መዘረሩ…
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
4 Apr 2025, 21:24 UTC229 viewsread 7 August 2026 ''.....ሰው ሲታመም የምንጠይቀው ከቋጠሮ ሰሐን ጋር ነው...
ሰው ሲታሰር ' እግዚአብሔር ያውጣህ ' የምንለው ከፍትፍት አገልግል ጋር ነው ....
አራስ የምትጠይቀው ከፔርሙዝ አጥሚት ጋር ነው ...
የክርስትና አባታችን ለፋሲካ አክፋዩን የሚጠብቀው ድፎ ዳቦ ና አረቄ ነው ...
እዝንተኛ የምናስተዛዝነው ሰባት እንጀራ ከአንድ ሰሐን ወጥ ጋር ነው ...
ሟች የምንሸኘው ከገንቦ ጠላና ከለምለም እንጀራ ጋር ነው ...
የቅዱሳንና የመልአክታት ተራዳኢነት የሚጎበኘን በስማቸው ከዘከርን ነው...
ሰዕለታችን በሬ ወይም በግ ነው ...
ሰርጋችን ፣ ልደታችን፣ እርቃችን፣ ሹመታችን፣ አምልኳችን፣ የሚበላ ነገርን ሙጥኝ ያሉ ናቸው ... ...
ሌላው ቀርቶ አ…
Signed ፌዮዶር. ዶስቶዬቭስኪይ🤦♂
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @zikiretibeb. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.