17 Dec 2022, 09:59 UTC≈1,560 viewsread 7 August 2026 Photo
አንድ የስነ-ሰብ (Anthropology) ተመራማሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገጠራማ መንደር ለስራ ያቀናል። በቆይታውም ከህጻናት ጋር መግባባትን ይፈጥራል። እናም ሕጻናቱን ለማስደሰት አንድ ሽልማት ያለው ጨዋታ ያዘጋጃል።
ጨዋታውም፣ በማንጎ የተሞላ አንድ ቅርጫት ከዛፍ ስር ያስቀምጣል፣ ህጻናቱን ከዛፉ አንድ መቶ ሜትር እንዲርቁ አደረገ፣ ከዛም እንዲህ አላቸው:-
"እኔ ጀምሩ ስል ቀድሞ ቅርጫቱ ጋ የደረሰ የፈለገውንና የሚችለውን ያህል ማንጎ ይበላል:: "
ጨዋታው ተጀመረ።
ህጻናቱ ግን ከጨዋታው ህግ ውጪ ያልተጠበቀ ነገር አደረጉ።
ይህም ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል ወደ ቅርጫቱ ሮጡ። ከዚያም አንድ ላይ በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ማንጎ በአሸናፊነት መንፈ…
Signed Teddy
27 Nov 2022, 21:34 UTC≈1,030 viewsread 7 August 2026 ስህተት እና ትክክል
ብዙ የተሳሳቱ ሰዎች ባሉበት ፣ ስህተት ራሱ ትክክል የመሆን አቅም አለው ። በዚህ ሁኔታ የተሳሳተ ሰው ትክክል የሚሆነው በራሱ ብቃት ሳይሆን እንደተሳሳተ ማወቅ ባልቻሉ ደካማ ሰዎች ስህተት ነው ። ለምሳሌ ፦ የቁስ ሀብት የሕይወት ትርጉም መለኪያ መሆኑ የተሳሳተ ነው ነገር ግን ብዙ የተሳሳቱ ሰዎች ስለተቀበሉት ትክክል ነው ። ከቁስ ሀብት ውጪ ሌላ የመኖር ዓላማ እንደሌለ አለማወቅ የሚያሳየው የሕይወት ትርጉምን ከቁስ ሀብት አንፃር መውሰድ ስህተት አለመሆኑን ሳይሆን ትክክለኛውን የሕይወት ትርጉም መረዳት ያለመቻልን ስህተት ነው ።
ሕይወት የእንቁራሪት ኩሬ አይደለችም ። አንተ ካለህበት ጠባብ የኩሬ ሕይወት በመነሳት የውቅያኖሱን ሰፊ ሕይወ…
Signed Teddy
30 Jul 2022, 07:15 UTC≈1,470 viewsread 7 August 2026 አንዲት ሴት ወይዘሮ በባቡር ጉዞ ላይ ሳሉ አጠገባቸው ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠ ሻንጣአልተፈቀደምና ስለነበር አንድ ሠራተኛ መጥቶ ይህ ወንበር ለሰው መቀመጫ እንጂ ለዕቃ ማኖሪያ እባክዎ ያንሱ ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡
‹‹ቢያነሱ ይሻላል እምቢ ካሉ ላለቃዬ እነግራለሁ›› ቢላቸውም ‹‹ሂድ ንገር›› አሉት፡፡ ሂዶ ሲነግረው አለቅየው መጥቶ "ያንሱ እንጂ ለምን አላነሳም ይላሉ?" ብሎ ቢነግራቸው ‹‹አላነሳም›› በሚለው ሐሳባቸው ጸንተው የማይበገሩ ሆኑበት፡፡
በመጨረሻም ለዋናው ኃላፊ ተነግሮት ይመጣና ‹‹ይህን ሻንጣ ያንሱ›› ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡ ዋና ኃላፊውም ‹‹ለምን?›› ሲላቸው ‹‹ገና አሁን አዋቂ ሰው መጣ፡፡ እኔ የቸገረኝ እኮ እስካሁ…
Signed Teddy
20 Jul 2022, 19:22 UTC≈1,250 viewsread 7 August 2026 File
Rophnan ft Julian marley
Merkeb
(አርምሞ)
🎵🎵🎵🎵
የልቦናን መቅረፅ አብርቶ
የሚጓዝ መች ይሰምጣል ከቶ
ወደ ውስጥ ላየ ለገባው
መርከቡ ሰፊ ነው ከውሀው
🎵🎵🎵🎵
ሰው ራሱን ካዳመጠ ከራስ ከታረቀ
የመኖርን ሚስጢር እውነት አወቀ
ልብ ላይ ሁሌም ድምፅ አለ እሱን ተከተለህ
በሶስተኛው በሙሉ አይንህ ታያለህ
🎵🎵🎵🎵
@yehasab_menged
@yehasab_menged
Signed Teddy
8 Jul 2022, 04:09 UTC≈1,260 viewsread 7 August 2026 ባውንድሪ ማለት ጨዋነትና ሚዛናዊነት ማለት ነው!
የአብዛኛው የግንኙነት ቀውስ የሚከተለው ሰዎች የራሳቸውን ባውንድሪ (ቀይ መስመር) በሚዛናዊነት ሳያስክብሩ ሲቀሩና ሰዎች እንደፈለጉ እንዲያደርጓቸው ሲፈቅዱ ነው፡፡ እነሱም ቢሆኑ የሰውን ባውንድሪ ካላከበሩ ለግንኙነት ቀውስ ምክንያት መሆናቸው አይቀርም፡፡
የራሳችንን ባውንድሪ አስከብረንና የሰውን አክብረን ልኩን ያወቀ ሕይወት እንዳንኖር የሚያደርጉን ደግሞ በሕብረተሰቡ መካከል የሚዘዋወሩ አፈ-ታሪዎች ናቸው፡፡
አፈ-ታሪክ #1:- “የቀይ መስመር ወሰን ማበጀት ማለት ራስ ወዳድነት ነው”፡፡
እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ የቀይ መስመር ያለው ሰው ራስ ወዳድ ሳይሆን ራሱን በሚገባና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የሚያከ…
Signed Teddy
1 Jul 2022, 03:32 UTC≈1,190 viewsread 7 August 2026 መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ!
• ፈራችሁም አልፈራችሁም መኖራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እሞታለሁ በሚልፍ ፍርሃት ታስራችሁ ከምትኖሩ ቀና ብላችሁ ብትኖሩ ይመረጣል፡፡
• ፈራችሁም አልፈራችሁም መነገዳችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እከስራለሁ በሚል በፍርሃት ታስራችሁ ከምትነግዱ በአዎንታዊነት ተነቃቅታችሁ በትነግዱ ይሻላል፡፡
• ፈራችሁም አልፈራችሁም መማራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና ፈተና እወድቃለሁ በሚል ፍርሃት ታስራችሁ ከምትማሩ እችለዋለሁ በሚል እምነትና ትጋት ብትማሩ የላቀ ነው፡፡
• ፈራችሁም አልፈራችሁም አንድን ሰው ማፍቀራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና ይገፉኛል በሚል ፍርሃት ታስራችሁ ከምታፈቅሩ ጤናማ በራስ መተማመን ይዛችሁ ብታፈቅሩ እጅግ ተመራጭ ነ…
Signed Teddy
6 Jun 2022, 18:49 UTC≈1,150 viewsread 7 August 2026 አለመጣደፍ….!!!
የጥድፊያ መንፈስ ይታይብናል፡፡ በብዙ ነገሮች መረጋጋት የከዳን ይመስላል፡፡ ሰከን ማለትን ሳንጠላው አልቀረንም… ጥቂት አፍታ ወስዶ የሰዎችን የልብ መሻት፣ ወይም የነገሮችን ስረ-ግንድ ለማስተዋል የተዘጋጀን አልሆንም…፤ እጅግ ጥቂት የበለጡን ግለሰቦች ይኖራሉ፤ እነሱን አይመለከትም ጉዳየ፡፡
በብዛት ግን… የተጣደፈ ወጨፎ አይነት ባህሪ እየናጠን ነው……
ሳስብ የሚሰማኝ፤ ሰው ስሜቱን ሳይሻገር የሚያቀርበው አስረጂ ሁሉ ወደ ልክነት የመድረስ ንጥረቱ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው፡፡ ስሜቱን መሻገር ከቻለ እንደጥላቻ፣ ንቀት፣ ማጥላላት፣ ማኮሰስ ወዘተ አይነት አሉታ አጸፋዎችን አያስተጋባም፡፡ ሰዎች በሚኖሩት ህይወት፣ በሚያነሱት ሀሳብ ወይም ባላቸው ማን…
Signed Teddy
17 May 2022, 06:23 UTC≈1,150 viewsread 7 August 2026 መነጠል እና መጀመል
... ይልቅ አንድ ታሪክ ልንገርህ፡፡
እ.ኤ.አ በ1750ዎቹ በለንደን ከተማ ጎዳናዎች የሆነ የሚያስገርም ሰው ብቅ አለ፡፡ ስሙ ጆናስ ሀንወይ (712-1786 እ.ኤ.አ) ይባላል፡፡ የሆነ ቀን ከጨርቅና ከቆዳ ቀጣጥሎ የሠራውን ዘባተሎ ግዙፍ ጃንጣለውን ይዞ ብቅ ሲል "ምን ጉድ ነው? "በሚል ስሜት ሰዎች ተከተሉት፡፡ ጃንጥላውን ይዞ በወጣ ቁጥር አንድ ገበያ ሕዝብ ያጅበው ጀመር፡፡ ምናልባት የሚሸነቁጥ የሚያዋርድ ስድብም ይከተለው ይሆናል፡፡ ለሠላሳ ዓመታት ይሄው ምቾት የሚነሳ አጅብ አልቀረለትም፡፡
እነሆ ዛሬ በአሜሪካ ብቻ በዓመት 33 ሚሊዮን ጃንጥላዎች ይሸጣሉ፡፡ 365 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ለግብይቱ ይውላል፡፡ ከኛም ሀገር የመከላከያ በ…
Signed Teddy
16 May 2022, 17:32 UTC928 viewsread 7 August 2026 ....
ብዙ የማውቃቸው ሰዎች ሀይማኖት ያላቸው ሲኦል እና ገነት አለ ስለተባሉ ነው። ከክፋት የሚቆጠቡት ሲኦልን ፍራቻ እንጂ መልካም መሆን ምንም ሽልማት የለውም ክፉ መሆንም ምንም ቅጣት የለውም ቢባሉ ለክፋት የሚግደረደሩ ናቸው። በሰውነት ሰው ስለመሆን ሳይሆን እግዚአብሔር ወይም አላህ ወይም ሌላኛው አምላክ በክፋታቸው ይቀጣናል ፤ በመልካም ስራቸው ይሸልመናል ብለው ስለሚያምኑ ነው ሚዛን የሚሰሩት። እስኪ እውነት እናውራ ከተባለ የብዙ ሀይማኖቶች መደምደሚያ ከሞት በኋላ ያለ ሽልማት ወይ ቅጣት ባይሆን ምን ያህል ሰው ሀይማኖት ይኖረው ነበር? ምን ያህል ሰው ቅዱስ የሚለውን ስራ ለመስራት ይጋጋጣል? ምን ያህሉስ ሰው ወደሀይማኖት ተቋማቱ እየሄደ አቴንዳንስ ያስመዘ…
Signed Teddy
8 Apr 2022, 15:18 UTC≈1,140 viewsread 7 August 2026 #ታካችነት_ኃይልህን_አሳልፈህ_የምትሰጠው_ጠላትህ_ነው
"ታካች ሰው። አንበሳ በሜዳ ነው ሲባል በመንገዱ ላይ እሞታለሁ ይላል።" (መጽሐፈ ምሳሌ 22:13)
የሆነ ሰው አእምሮህን በመጠቀም ከካንሰር ጭምር መፈወስ እንደምትችል ቢነግርህ፤ ታምነዋለህ ወይስ ትስቅበታለህ?
አእምሮ ሃይል አለው!!!
በጭንቀት፣ በስጋት ውስጥ ከቶ ከሰውነት ተራ እስክትወጣ ድረስ ያከሳሃል…
በተስፋ እና በሃሴትም ሞልቶ ህይወትህን ያበራልሃል።
የምትችላቸው እና የማትችላቸው ነገሮች ያሉት አእምሮህ ውስጥ ብቻ ነው።
በቀጣዮቹ ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ የምትችለውን ሁሉ አድርገህ አስር ሺ ብር ይዘህ ና ብልህ ‘አልችልም - ገንዘቡን ከየት ማምጣት እንዳለብኝ ምንም ሃሳቡ የለኝ…
Signed Teddy
5 Feb 2022, 18:10 UTC≈1,270 viewsread 7 August 2026 የአሪስቶትል ምናባዊ ሰው (Aristotle's Imaginary Man)
፨ " በአለም ላይ ለመኖር የሚያስፈልጉት ነገሮች እጅግ በጣም ጥቂቶች
ናቸውና አላስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ራሱን አያጋልጥም፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ
እራሱን ቢያገኝ እንኳን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀና ቆራጥ ነው።
በእንዲህ ያለ ኑሮ ውስጥ ሕይወት አላስፈላጊ መሆኗን አምኖ ተቀብሏል።
ለታይታ ሲል አይኖርም፤ የሚወደውንና የሚጠላውን ነገር መደበቅ አይችልም፤
ሲናገርም ሲያደርግም በግልጽ እንጂ በድብቅ አይደለም፤ በእርሱ አይኖች
የሚደነቁ ነገሮች የሉምና ስለምንም ነገር አይደንቅም፤ ብዙ አያወራም፤ ሰዎችን
ለማስደሰት ሲል የማይገባውን አያደርግም፤ በሌሎች ይመሰገን ወይም ይደነቅ
ዘንድ ግድ የ…
Signed Babi
30 Jan 2022, 05:29 UTC≈1,200 viewsread 7 August 2026 • በህይወቴ ዘመን ሁሉ ቤተሰቦቼ እንደ ልጅ ቆጥረዉኝ አያዉቁም፡፡ ጠንቋይ ቤት ሄደዉ ያላቸዉን ሀብት 'እኔ ላይ ካፈሰሱ ዉድቀትና ድህነት ቤታችን ዉስጥ እንደሚገባ ነገር ግን ወንድሜ ላይ ካፈሰሱ ቤታችን በበረከት እንደሚሞላ' ዘባረቀላቸዉ፡፡
ይህን ካዘዛቸዉ ቀን ጀምሮ እኔን እንደለማኝ ወንድሜን ደግሞ እንደንጉስ አሳደጉን፡፡ ወንድሜ 'አለ የተባለ ትምህርት ቤት' ሲያስገቡት እኔን ግን የመጨረሻ የድሃ ትምህርት ቤት ወረወሩኝ፡፡ ግን ምን እንደሆነ ልንገርህ ተከተለኝ...
• አስተማሪዎቼ ቤተሰቦቼን ጠርተዉ 'ደደብ ተማሪና ተደብዳቢ እንደሆንኩና ለዚህም እንደመቀጫ የትምህርት ቤቱን ሽንት ቤት ማፅዳት እንዳለብኝ' መወሰናቸዉን ነገሯቸዉ፡፡ ቤተሰቦቼ ደስ አላቸዉ...…
Signed Babi
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @yehasab_menged. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.