19 Nov 2023, 07:51 UTC≈1,630 views10 reactionsread 7 August 2026 ፍጡር መሆን እዳ
(አልታየህ ኪዳኔ)
ውድነህ ክፍሌን አብዛኞቻችን የምናውቀው በፀሀፊ ተውኔትነቱና በሬድዮ ድራማ ደራሲነቱ ነው። ነገር ግን አንድ ረዥም ልቦለድ መፅሀፍም ፅፏል። "ላማ ሰበቅታኒ" ይሰኛል። ከአራት አመት በፊት ነበር ያነበብኳት። ድብን ያለች ፋንጣዚ (የአዳም ረታ ቃል ናት ይህቺ) እና ሳታየር ናት።
ታሪኩ እንዲህ እንዲህ ላሳጥርላችሁ... ወታደሩ ሀገሬን እከላከላለሁ ብሎ ጦርነት ሄደ። ሲመለስ አንድ አይኑን ፣ አንድ እጁን እና አንድ እግሩን እዛው ጦር ሜዳ ሰውቶት መጣ። ሞቷል ተብሎ ታምኖ ነበር። ታዲያ ሲመለስ ሚስቱ ሌላ ባል አግብታ ጡረታውን እየበላች ጠበቀችው።
አማራጭ አልነበረውም መንገድ ላይ ወጣ። አንድ ቀን ምሽት መንገድ ዳር ቁጭ…
❤8👍2
19 Nov 2023, 07:51 UTC≈1,190 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
11 Sept 2023, 16:01 UTC≈1,340 views7 reactionsread 7 August 2026 አዲሱ አሮጌ ነው እንደማለት
(አልታየህ ኪዳኔ)
ወደፊት እንደው የዚህ ዘመን መልክ እንዴት ያለ ነበር? ብሎ ጥያቄ ለሚያነሳ ሰው የበእውቀቱ ስዩም ግጥሞች የሆነ አይነት የተለየ ምስል የሚሰጡት ይመስለኛል።
ከያኒ ዘመኑን ይዋጃል ወይንም ይገልፃል።
የትኛውም ዘመን ነቅ አልባ አይደለም። ችግሮች በየአይነቱ አሉ። ተፈጥሮ ከሰጠችን የፉክክር አለም አልፎ ብሶትና መከራ በላያችን ይዘንባል። ፖለቲካው ሌላ የመከራናየግጭት ፈጣሪ ነው።
በዚህ ሁሉ ውስጥ በእውቀቱ ዘመኑን እየዋጀ ነው። በስራዎቹ ጥብቅ የትላንት ታሪክ ሃሳሳ ላይ ነው። ማህበረ ፖለቲካውን፣ የዘመኑን ስንስል በተለየ አውድ ይመለከታል። ለተጠየቅ ያቀርባል። በእውቀቱ የሰው ልጆች ምድራዊ እድል እና እጣፋ…
❤5👍1👏1
11 Sept 2023, 16:01 UTC866 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
3 Sept 2023, 16:05 UTC908 views5 reactionsread 7 August 2026 ነገረ ሙዚቃ
(አልታየህ ኪዳኔ)
አንዳንድ ሙዚቃ አለ ገና ዜማውን ማድመጥ ስጀምር ሰውነቴን ይወርረኛል። ይሄን ስሜት የሚፈጥሩብኝ ሙዚቃዎች ጥቂት ናቸው። ዜማዎቹ የሆነ መንሳፈፍ ውስጥ ይከትቱኛል። እንግዳ እኔም የማላውቀው አይነት ስሜት እንዲሰማኝ ያደርጋሉ።
ገና በለጋነቴ ያ ጥቁር ቦርጫሙ ሶኒ ቴሌቪዥን ፊትለፊት ቆሜ በግርምት ካየኋቸው የማይረሱኝ ፤ የተለየ ስሜት እና ድባብን ከሚፈጥሩብኝ መሃል እነኚህ 3 የተለዩ የኦሮምኛ ቋንቋ አቀንቃኝ ስራዎች አሉ።
፩) የመጀመሪያው ታደሰ ፊጤ ነው። ታደሰ እንዳሁኑ ቴክኖሎጂ የሙዚቃውን ኢንደስትሪ በብዙ መልኩ ሳይቀይረው በፊት ፣ በዛ ሶኒ ቦርጫም ቴሌቪዥን "Booruu Booruu jedhaa" እያለ ሲዘፍን ያየሁት አእ…
❤5
3 Sept 2023, 16:05 UTC703 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤1
3 Sept 2023, 06:18 UTC723 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
ስመ ደብሩ ሰው
(አልታየህ ኪዳኔ)
አንዳንድ አስፈሪ ነገሮች አሉ። እስኪ ይልማ ገብረአብ የሚባል ሰው በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ባይኖር ብላችሁ አስቡ። አያስፈራም? ለኔ አስፈሪ ነው።
ግን ይልማ ኖረ። ከአራት አስርት አመታት በላይ የዘለቀ የሙዚቃው አለም ተሳትፎው ለቁጥር የሚያዳግቱ የሙዚቃ ግጥሞችን እንዲደርስ አስችሎታል።
ስራውን በታላቅ መውደድ የሰራ ፣ የለፋ ፣ የተጋ ፣ ለሞያው ዋጋ የከፈለ ነው። ከልጆቼ እናት ጋር እንኳ የተለየሁት በሙያው ምክንያት ነው ሲል ተናግሯል።
ቁጥራቸው እጅግ ለበዙ አቀንቃኞች የስኬት መሰላል የሆነ የሙያ ባለቤት ነው።
ደግሞ ትህትናው ሲያስቀና። "በኢትዮጵያ ሙዚቃ ያለህ ቦታ" ሲባል "ተዉ እነ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐ…
❤1
18 Aug 2023, 17:48 UTC713 views1 reactionsread 7 August 2026 ተንቀሳቃሹ ቤተ መፅሀፍ
(አልታየህ ኪዳኔ)
ጋሽ አስፋው ጎበዝ አንባቢ ነው። ስብሃት ይሄን ይናገራል። አስፋው ለኔ የተሟላ ቤተ መፅሀፍ ነው ይል ነበር ስብሃት።
ጋሽ አስፋው አንድ ጊዜ ከወይ አዲስ አበባ ጋር ቆይታ አድርገው በነበረ ጊዜ ይህንን ብለዋል።
"ለእኔ ንባብ መዝናኛዬና ሳላቋርጥ የምማርበት የእውቀት መገብያዬ ከመሆኑም ባሻገር ከእኔነቴ ጋር እጅጉን ተቆራኝቷል። አላነብም የሚል ሰው ሲገጥመኝ 'ሰው እንዴት ሳያነብ ውሎ ያድራል' የሚል መገረም እስኪፈጥርብኝ ድረስ"
ጋሽ አስፋው የፃፉት ብቸኛ መፅሀፍ "አንድ ለ አምስት" የሚለው ረዥም ልቦለድ ነበር። ካነበብኩት ቆየሁ።
መፅሀፉን ጣዕም የሰጠው ገፀባህርያቱ የሚያደርጉት ክርክር ነው። የሚያነሱት ተቃ…
❤1
18 Aug 2023, 17:48 UTC637 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤1
31 Jul 2023, 17:26 UTC720 views3 reactionsread 7 August 2026 የወግ ፀሀፊዎች ትውስታ
(አልታየህ ኪዳኔ)
ጊዜው ተለዋውጧል። በነበረበት የቀጠለ የለም። ባለፉት አራት አምስት አመታት ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል።
እንዳሁኑ የፖለቲካ አጀንዳዎች እለት ተእለት መነታረኪያ ሰበብ ሳይሆኑ በፊት ፤ ሚም ባልገነነበት ጊዜ ፤ ፅንፍ የወጣ ብሄርተኝነት እየገነገነ በመጣበትም ሰዓት ፤ እነዚህ ፀሀፊዎች የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ያለመታከት ይፅፉ ነበር።
ወጎችን ፣ አጫጭር ታሪኮችን ፣ ማህበራዊ ትዝብቶችን አዋዝተው ይፅፋሉ። በተለይ ወግ የመፃፍ ክህሎታቸው የተለየ ነበር።
● ህይወት እምሻው ፦ ልከኛ ወግ ፀሀፊ ነች። ወጎቿ ውስጥ ሳቁም ፣ ጨዋታውም ፣ ቁምነገሩም አንድ ላይ አለ። ህይወት ከማህበራዊ ትስስር ገፅ ፀሀፊነት እራ…
👍2❤1
31 Jul 2023, 17:26 UTC540 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤1
29 Jul 2023, 04:54 UTC563 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
አለማየሁ ገላጋይን ስንጠራ "ደራሲ" የሚለውን ቅጥያ ማስቀደም አይኖርብንም። ስሙ እራሱን በደምብ የገለጠ ይመስለኛል።
አለማየሁ ገላጋይ አዲስ ስራ ይዞ እየመጣ ነው !
መንገዱ የራሱ ነው። ሹፌሩም ጭምር። በእርግጥም መልካም ዜና ይመስላል።
@yebirhan_fiker
@yebirhan_fiker
❤1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @yebirhan_fiker. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.