30 Jul 2026, 14:49 UTC25 views3 reactionsread 8 August 2026 Video
✨🎉🎉🎉🎉🎊🎇🎆የኔ ገብርኤል 💕🎉🎉🎉🎊🎊🎆🎇✨
አባቴ ነው ለኔ......
የመንገዴ መሪ
ማይጠፋ ከጎኔ
ሞት እንኳን ቀላል ነው
ካለልኝ መድህኔ
ረስቶ አያቅም
የልመናየን ቃል
እንኳንስ ምሕረቱ
ስሙ ለኔ ይበቃል
ከስንቱ አወጣኝ
ከእሾህ ከጋሬጣ
ስንክልክል አይኖርም
ገብርኤል ሲመጣ
መመኪያየ ነው
የነፍሴ ጠበቃ
ተስፋ ቢጎል እንኳን
ትዕግስቴ ቢያበቃ
አዲስ ምዕራፍ አለው
ዘወትር ለደስታየ
አፍሬ አላውቅም ድረስልኝ ብዬ☺️
…
🙏3
4 Jul 2026, 10:54 UTC71 views2 reactionsread 8 August 2026 Photo
አሜን 🙏💕
አያልፍም ያልኩት ባንተ አለፈ
አዲስ ታሪክ በስምህ ተፃፈ
ወድቄ ነበር መንበርከኬ
ለካስ ለስራህ ነው ላንተ አምላኬ
ለፀሎት ሆነ ለምስጋና
የሰበሩኝ ላልል ቀና
እንድቀርብህ ዝቅ ብዬ
ለካስ በደል ክፍያዬ
እግሬን መተው እንደጣሉኝ
ለጉልበትህ አቀረቡኝ
ተንበርክኬ እንዳነባ
ለምህረትህ ላንተ መባ
ቀና እስከምል ተሸልሜ
በንስሐ አለምልሜ
እዛው ልቆይ ከእግሮችህ ታች
ይሁን ያልከው እስኪመቻች
አሜን ይሁን ለኔ ያልከው
አንተ አምላኬ የፈቀድከው
✍️ያቡ 💕
https://t.me/yabupoem
❤1👏1
12 Jun 2026, 20:09 UTC241 views4 reactionsread 8 August 2026 ⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️
ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ የከበረ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ
ዛሬ አንድ የጥንቃቄ ⚠️መልዕክት ልነግራችሁ ነው የመጣሁት ቴሌግራም በብዛት ሃክ እየተደረገ ስለሆነ የሚላኩላችሁን ሊንኮች ሳታዉቁ አትክፈቱ እዚህ ቻናል ወይም ግሩፕ ላይም ሊገጥም ስለሚችል ከወዲሁ እንድትጠነቀቁ እያሳሰብኩ ያቡ ነኝ የናንተው ሰላማችሁ ይብዛልኝ 🙏💕
👍4
Channel photo updated
10 Jun 2026, 12:28 UTC190 views4 reactionsread 8 August 2026 #የልብ አኬልዳማ 💔
እስከመጨረሻው አንብቡት ያልተመቸው የመዉጣት መብቱ እንደጠበቀ ነው መቼም እውነት ጠላታቺን ሆኗል😄😒.......ብልህ ከሆንክ ተማር ተመለስክ አይ ካልክ ገደሉም ፈረሱም ያው 🙌
ምናልባትምኮ የኛም ፍቅር እንደተገባበዝነው ሙዚቃ ወይም ፊልም ቢሆን መቼም መለየት ባልኖረ ነበር..........
መዉደዴን ነግሪያት ትቀበለኝ ይሆን ብለህ የተጨነቅህበትን ጊዜ ብታስብ ስታገኘኝ አልቀልብህም ነበር
የሕይወቴ ህይወት እንዳልክ ሕይወትህ ብሆን መቼም የኔ ያንች ሚባል ሕይወት ባልኖረን ነበር
በብዙ ስቃይ እና መከራ መሃል ስንት ነገር እንዳለፍንና እንዳገኘከኝ ብታስብ የትኛውም ስሜትና ችግር ከፍቅራችን በልጦ ባላለያየን ነበር
አሜን ባልህበት አፍህ ቸልታህን…
🔥4
1 Jun 2026, 06:38 UTC218 views10 reactionsread 8 August 2026 Photo
እዉነት እስኪጣራ
እስኪያልፍ መከራ
ነፍስ ይማር እያልን ስንሸኝ በተራ
ሀዘን ሰሚ ጠፍቶ ፍትህ ከኛ ርቃ
ነፍሳችን ረክሳ በክፉዎች ወድቃ
እገሌኮ ሞተ አወይ ሰው ከንቱ
በእንባ እየተራጩ በድን መሸኘቱ
እልፍ ቁስል ይዞ የማይሽር ጠባሳ
አፈሩ ይቅለልህ ወጋችን ሆነሳ
በምድር ፍርድ የለም እንባችንን ሚያብስ
አምላክ ተው ታረቀን ፊትህንም መልስ
ተው ቅዱስ ጊዮርጊስ.... 🥹
አንተ ባለፈረስ
በተባልነ ጊዜ ማተብህን በጥስ
ከፊትህ እንደመራህ በዛ በደግ ጊዜ
አሁንም ቅደምና አዉጣን ከትካዜ
ተው ቅዱስ ገብርኤል...... 🥺
እንዳወጣሃቸው ደቂቃንን ከእሳት
ይቺን ቅድስት ምድር በምህረት ዳብሳት
የሃዘን እሳት ነው በኛ የነደደ
በግፍ በግዞት ነው ካህን የታረደ
መጣሁ ልጄ …
😢6❤4
31 May 2026, 21:35 UTC164 views4 reactionsread 8 August 2026 Yabupoem (✍️ያቡ💕)
🎤 እስኪ የልብ ስብራታችንን እንፈውስ🥰
ሙሉውን አንብቡና ስሜታችሁን አጋሩን💕 እወዳችኋለሁ🫶🫡
እንደምን አላችሁ የዚህ ውብ ቤተሰብ አባላት እና ታዳሚዎች? ዛሬ አንድ ነገር ልበላችሁ እስኪ ሁላችንም በውስጣችን የምናውቀውን ነገር ግን ጮክ ብለን ለመናገር የምንፈራውን አንድ እውነት ላካፍላችሁ ነው።😊
ለመሆኑ... ቅንና መልካም ልብ ያላቸው ሰዎች በፍቅርና በትዳር ሕይወታቸው ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ዕድል የሌላቸው እንደሚሆኑ አስተውላችኋል?
እኔ በዚች የሕይወት ጉዞዬ ብዙ ሰዎች በቅርበትም ሆነ እንዲሁ በዙሪያዬ ተቀምጠው የልባቸውን ስብራትና እምባ ሲያፈሱ ተመልክቻለሁ። ብዙ የሕይወት ወቅቶች ሲያልፉና ሲተኩ አስተውያለሁ፤ በዚህ …
❤3👏1
27 May 2026, 07:44 UTC193 views5 reactionsread 8 August 2026 Photo
ከተለያየን ምን አደርጋለሁ ሚለውን የማዲንጎ ሙዚቃ እያዜምኩ ሳላያቺሁ ልሸኛችሁ መሰለኝ........ 🥹
ዉድ በተባለ እንቁ ጓደኝነት
ስንት ቀን አልፈናል ስንስቅ ስንጫወት
አበባየሁሽ ብለን መስከረም ሲጠባ
ደግሞ ተመልሰን ዞረን እስክንገባ
ደህና ሁኑልኝ ..............
ስቀን ተጨዋውተን በእቅፍ ባንለይም
የዓመት ሰው ይበለን ያገናኘን ዳግም
ላሳለፍነው ጊዜ በክፉም በደጉ
ባየነው ለሁሉም ጓደኝነት ጥጉ
አይጉደል እና ደርሶ መላሽ ያርገን
እንድንስቅ ያብቃን በአንድ ተሰባስበን
አላዉቀዉምና የመንገዴን ነገር
ይቅርታ አድርጉልኝ ቂም በልብ እንዳይቀር
ከግቢ እየወጣችሁ ላላችሁ መልካም መንገድ ሰላም ግቡልኝ💕🙏
✍️ያቡ 💕
https://t.me/yabupoemeth…
👏2🥰2❤1
19 May 2026, 22:39 UTC245 views3 reactionsread 8 August 2026 Video
Video, posted without a caption
❤2👏1
19 May 2026, 21:53 UTC208 viewsread 8 August 2026 https://vt.tiktok.com/ZSxhUcqDM/
Yabu_ poem✍️ pinned «እኔን ላወድስ.........😊 ይ=ይመስገን ማይጠፋ ዘወትር ካንደበቷ ች=ችላ የማትጨክን የዋህ ሰዉነቷ ነ=ነገሯን የማትጥል በዋዛ ፈዛዛ ች=ችላን የማታውቅ መኖር እንደዋዛ የ=የቀረባት ሁሉ ቅኔ ነሽ የሚላት አ=አብስራ ማለት …»
13 May 2026, 20:19 UTC304 views4 reactionsread 8 August 2026 Photo
ለምን እንደው እንጃ......
አብሬ ቆይቼ ስለያቸው ገና
ሚያወሩ አይመስለኝም ስለኔ ገመና
ትንሽ ያወቋትን ሽራፊ ገፅታ
ህቡዕ ማንነቴን የዉስጤን ሁኔታ
ሚያዉቁት አይመስለኝም
እንዲህ ብለው አሙኝ ልልም አልመኝም
ብቻ...........
እሷ እንደዚህ ናት ብሎ ለማጣጣል
ለመንገዴ እሾህ አሜኬላ ማብቀል
ላልችለው መምሰሉን ለወጉ ለመፍገግ
ባልቆጠር እንኳን ከዛ ከቅዱስ በግ
እየሰማሁ ትቸው ደግ ባልደረግ
እንጃ...........
ብቻ አይመስለኝም ዞር ስል ሚያወሩ
ሀሜት በኔ ሹመው ቃል ሚሰነዝሩ
ላለማመን ይሁን ወይም ላለመክፋት
ለኔ አይታየኝም የወዳጄ ሀሜት
ታዲያ የቱ ይሻላል.........
በክፉ እያሰቡ ሰወችን መጠርጠር
ወይስ ከሰው…
🔥4
Showing the 12 most recent of 19 posts we hold for @yabupoemethiopia. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.