12 May 2026, 17:11 UTC≈1,350 views21 reactionsread 7 August 2026 በቃ ስትስቅ ታምራለች
ከብርሀን ጡት ጠብታ ያደገች ትመስላለች ፤ ቀጥታ ከአማልክቱ የተተነፈሰ ዛት አላት። ወለም ዘለም ሳያረግ ላጀብ የፈጠራት ምናብ እንጂ ሰብ የማትመስል አይነት ናት።
ታዲያ እንዴት ከዚች አይነት ፍልቅልቅ ይህ ሰውነቴ ፍቅር አይወድቅም አረ እንደውም የምን መውደቅ መሰበርም ነው። 24 ሰዐት የሷን ውበት ይቆጥራል። ልቤ ውበቷን ከክፉ ነገር ይሰውርልሽ እያለ እንደ ፀበል ደም ይረጫል። ውበቷን እኮ ለመናገር የጎርፍም የወንዝም ጉልበት ይጨርሳል። ፊት ለፊቷ ማንነት እንደ ልብስ ይጣላል ፤ ዛፍ ቅጠሉን ያረግፍላታል። በዚ ላይ ፈገግታዋ ሲታከልማ ሞትን ደርሶ የዶክተር ሚና ያላብሰዋል።
በቃ ስትስቅ አትዪዋት ጥርሷ መጀመሪያ ላይ ነጭ ነበር የሚመስ…
❤12🤗6😘2👍1
8 May 2026, 17:45 UTC≈1,490 views8 reactionsread 7 August 2026 እንደ ብሌን በውሀ ሰርክ እያነፃው አጥሬ ባኖርኩሽ በወደድኩ። ስቀሽ ፈግታሽን ከደዌዬ እንደ ክንፍ በተነሳሁበት ፤ መራመድ እየተራመድኩ አጠረኝ! የቆጠብሽው መራመድ አለ እስቲ አውሺኝ? ልንቀሳቀስ በፍቅርሽ ዛቢያ መዞሬን እንደ ምድር ሳይንሳዊ ላርገው እስቲ ይለይልኝ እወድሀለሁ በይኝና ከመለኮት ተቃቅሬ መንደሬን በዕብደት ፉርጎ ልንከባለለው! እራፊ ከገላዬ ለጥፌ በመንገድ በህፃናት በውሾች ይጮህብኝ ማንም መብቱ ሆኖ አብዷል ይበል ልፋቴን አብዷል በቃ በሚል አስትዪኝ። 😒
ኢስማኤል✍
❤5🌚3
17 Apr 2026, 19:02 UTC≈2,090 views58 reactionsread 7 August 2026 ሴቶች እንዳትቆጡና እንደሀሳብ እንደጻፍኳት ካራክተር እንዳንሆን ለምን ሱሰኛ ወንድ አናፈቅርም 🤔ከሱሱ ውጪ ሌላ ነገር ስለማይታየው አይማግጥብንም፣ አንካድም.....ያው ቢማግጥብን ሲጃራይቱን በመሳም ነው ያ ደግሞ it's normal😌🫠
(እንቅልፌ እንቢ ሲለኝ የማስበው ሀሳብ)
😁35🤣11🥴7👀5
17 Apr 2026, 18:20 UTC≈1,900 views50 reactionsread 7 August 2026 "አልቀረበትም አሁን በሱ ቤት እኔን ለማስቀናት ነው ይሄ ሁሉ ማሽካካትና ማግጠጥ"...ደግሞ'ኮ አይቶኛል ..ሳይታወቀኝ ከንፈሬን በጥርሴ እየነከስኩ እንደሆነ ያስተዋልኩት የሚያሽኮረምማት ሴት(ስታስፈራ..እንዴት እንደቀረባት ባይገባኝም) እኔን እያየች ቅንድቧን ስታኮመሽሽ ነው።
ምንም እንዳልመሠለው ሰው ሻዬን እየጠጣሁ አይኔን ከነሱ ላይ አንስቼ ትኩረቴን ሌላ ቦታ ላይ አሳርፋለሁ...
የአይኔ እረኛ ሁኜ ድጋሜ ወደእነሱ እንዳይመለስ እየከለከልኩ ያገኘሁትን ለማየት እሞክራለሁ...የሰወቹን ግርግር...ሻይው እንዳይበላው እየሰጋ ኡፍፍፍ እያለ አብርዶ የሚጠጣውን ሽማግሌ....ኬክ ካልገዛችሁልኝ እያለ የሚያለቅሰውን ህጻን....የአስተናጋጇን መቀመጫ እያየ የፈዘዘውን…
❤29💔16🔥3❤🔥2
16 Apr 2026, 21:12 UTC≈1,320 views17 reactionsread 7 August 2026 እና ምን ለማለት ነው ነገ እጠር ያለች ድርሰት post አድርጊ አድርጊ ብሎኛል ጠብቁኝ ለማለት ያህክል ነው😁
😁14👍2🥰1
16 Apr 2026, 21:10 UTC≈1,290 views14 reactionsread 7 August 2026 ከእኔነቴ ከሚያናደኝ ነገር ምን መሠላቹ ልቤ አድርጊው ያለኝን ነገር ካላደረኩ ሰላም አይሠማኝም🤦♀
👍12😁2
15 Apr 2026, 18:42 UTC≈1,360 views35 reactionsread 7 August 2026 ስለምርቃት ቅድም tik tok ላይ እያየሁ የሆነ ነገር ትዝ አለኝ።
የምር ከቤተሰቦቼ ከምወደው ነገር ምርቃታቸውን ነው ።በተለይ ከአያቴ....ምርቃቶቿ ማር ናቸው... እና ከምትመርቀኝ ምርቃት ከማር ይበልጥ የሚጣፍጥ አንድ ምርቃኗ አለ "ያመንሽው አይክዳሽ"የምትላት ነገር አለች።ታዳ እንደዚ ብላ በመረቀችኝ ቁጥር ልቤ ምን ይለኛል መሠላቹ "ያመንኩት አንድ ጌታዬን ነውና እሱ አይክዳኝጂ ሌላው ትርፍ ነው"ይለኛል።ለዛ ነው መሠል ተንሰፍስፌ ነው "አሚን" የምላት።
👍16🔥8❤7🥰4
3 Apr 2026, 19:06 UTC≈1,950 views37 reactionsread 7 August 2026 Photo
ዛሬም የዘኪን ድርሰት ነው በscreenshort ተከሽኖ🙂↔️
ጋበዝኳቹ።በዛውም follow እያደረጋቹሁት😊
🔥20❤10🤯6❤🔥1
31 Mar 2026, 14:53 UTC≈1,990 views33 reactionsread 7 August 2026 የጠንቋይ ልጅ!
(አሌክስ አብርሃም)
የሰርግ ፎቷችን ያለበት ቦርድ እየዞረ ተጋባዥ እንግዶች ሁሉ ይፈርሙና መልካም ምኞታቸውን ያሰፍሩ ነበር። ቆይቶ አንድ ጽሁፍ አየሁ፤ "መልካም ድህነት" ይላል። ብልግና አይደል? ጽሁፉን ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፤ የእርሱ ነው። ለዓመታት ፍቅረኛዬ የነበረው የያሬድ እጅ ጽሁፍ! "ምነው ፀባዩ እንደ እጅ ጽሁፉ ቢያምር ኖሮ!" እላለሁ።
አፈቅረው ነበር፤ እርሱም ያፈቅረኝ ነበር (ወይም ይመስለኛል)። "የሱቄ ጠባቂ ናት" የሚላት ሴት ጋር ተኛ። እዛ መገናኛ የልብስ ሱቅ አለው። ይቅርታ ላደርግለት ሰበብ ፈለግኩ። ጎበዝ ነው፤ በጥረቱ ኑሮን ያሸነፈ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ ቢባል አንድ ሁለት ብሎ ደረጃውን የሚያስቆጥር። ደስ የሚል ሕይወት…
❤17😁12🔥2👍1🤔1
29 Mar 2026, 18:10 UTC≈1,450 views17 reactionsread 7 August 2026 Photo
ፁሁፉ የሱ ነው ድንቅ ፀሀፊ👌
ውዶቼ Please አታሳፍሮኝ follow እያደረጋችሁት😊
🥰11❤3👍3
29 Mar 2026, 16:35 UTC≈1,500 views35 reactionsread 7 August 2026 ውለጅልኝ🙏
"ዚኑዬ!ውለጅልኝ?"
"ዘኪዬ ምን ተይዞ?"
"ይሄማ የፈጣሪያችንን ሪዝቅ መኮነን ነው...ሁሉን አሲዞ ፈጥሮን"
"አታነካካኝ.....እኔ ያልኩት..."
"ገብቶኛል ዚኑ...ድንገት ተነስቶ (አባቴ) መባል አማረኝ"
"እሺ ስንት ልውለድልህ?"
"ብልጥ የያዘውን ይዞ ነው የሚያለቅስ...ለአሁኑ አንድ ይበቃል"
"ዘኪዬ እንደምወድህ ታውቃለህ አይደል?"
"አታረሳሽ.."
እህ...ላረሳሳህ አይደለም....ግን ዘኪ...ልጅ'ኮ ብዙ ፍላጎቶች ይዞ ነው ሚመጣው...እንደድሮው የራሱን "ሪዝቅ"የሚባለውን ነገር ይዞ መምጣት ትቷል....እኔ ወልጄ ልጄን መበደል አልፈልግም"
"እኔን አታምኒኝም ማለት ነው?...አንቺ ላይ ያጎደልኩብሽ ነገር አለ?...ወንድነቴ…
❤21🥰7💔5🔥2
28 Mar 2026, 09:38 UTC≈1,610 views20 reactionsread 7 August 2026 ለምን ጠላሁት?
ከመሬት ተነስቼ ምክኒያት ሳላስቀምጥ እንዳፈቀርኩት ሁሉ ድንገት ተነስቼ ጠላሁት ብል ማን ያምነኛል....?
" ፍቅር ሲበዛም እንደሎሚ እየሆመጠጠና እየደረቀ ይሄዳል መሠለኝ...."ከመቼ ወደሽው ከመቼ ጠላሽው?..."ለሰሙኝ የሚያስብል ጥያቄ አስኪፈጠር...."አይ አይ ችኩል ነኝ ነገር ላይ ብቻ አይደለም ችኩልናዬ ፍቅር ላይም ችኩል ነኝ ለመውደድም ለመጥላትም"ብዬ መመለስ እስኪያምረኝ ጠያቂ ፈለኩኝ።
ውይ አፈር በበላሁ! የችኮላየ ለካስ እንደወደድኩትም የሰማ አልነበረም።ወይስ በራሴ እጅ ሂጄ ቸኩዬ አፈቀርኩት እጅ እጅ ሲለኝ ጠላሁት ብዬ ልናገር? መቼስ ከንግዲህ ልቡን አምኖ የሚሰጠኝ የለ...
"አፈቅረሀለሁ'ኮ ካንተ መለየት አልችልም"…
❤15👍3🔥2
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @wlbta. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.