27 Aug 2026, 17:19 UTC≈1,560 views8 reactionsread 3 September 2026 Forwarded from @getem
🔔 ውድ የቻናላችን አባላት፣ አዲስ የምስራች አለን!
የተመረጡ ግጥሞችን እና ሀሳቦችን, ወጎችን የምናጋራበትን ጉዞአችንን የበለጠ ለማሳደግ እና ጽሁፎቻችንን ባማረ ሁኔታ ለማቅረብ አዲስ Substack ገጽ ከፍተናል!
📌 ግጥሞች ለማንበብ እና አዳዲስ ጽሁፎቻችን በኢሜይል እንዲደርሷችሁ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው Substack ገጻችንን Subscribe ያድርጉ፡
https://substack.com/@getembicha
@getem
❤7🔥1
Signed Leul Mekonnen
26 Aug 2026, 10:21 UTC≈2,760 views61 reactionsread 3 September 2026 ፋርማሲ ኮንዶም ሊገዛ ዘው ብሎ ሲገባ ፋርማሲስቷ ትልቅ ሴትዮ ሆነው ያገኛቸዋል
ሽሮፕ አለ እማማ?
አለ ግን ለማነው?
ለብል.... ለልጄ... ለልጄ ነው
ምን ሆኖብህ ነው?
ከባድ ሳል ይዞት ምንም አላስተኛ አለው ለሊቱን ሙሉ ቀጥ እንዳለ ነው ያደረው
ለሱ ግን ከሽሮፑ ይልቅ ሌላ የምትቀባ መድሀኒት አለች እሷ ናት የምትሻለው
ቢቻልማ የሚጠለቅም ቢኖር ደስ ይለኝ ነበረ
ሰውዬ ግን እርግጠኛ ነህ ሽሮፕ ነው የፈለከው? ኮንዶም ነው አደል የፈለከው? መጠየቅ አፍረህ ከሆነ አትፈረኝ
ኧረ በስማም እማማ ትልቅ ሰው አይደሉንዴ? እኔ እንዲህ ያለ ነገር አርጌም አላውቅም
እና ልጁን በንፋስ ነው የወለድከው? በል አሁን የትኛው ይሁንልህ?
ካሉ ምን ይደረጋል መቼ…
😁59👍2
Signed Papi
5 Aug 2026, 07:56 UTC≈6,750 views181 reactionsread 3 September 2026 ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል። «ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?» ትላለች አንደኛዋ። «እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!» ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች።
እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል።
ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው።
«ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?» ይለኛል።
«ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?»
«አይ ሻማው ይሁን በቃ!» ይላል እየተቅ…
❤152🔥29
Signed Papi
29 Jul 2026, 07:03 UTC≈5,860 views1 reactionsread 3 September 2026 https://t.me/boost/getem
❤1
Signed Leul Mekonnen
21 Jul 2026, 07:41 UTC≈7,810 views99 reactionsread 3 September 2026 «ዛሬ አትመጭም?»
«ዛሬ ማርያም ናት አልነካም!»
«ነይ እኔም አልነካሽም!»
«አንተማ ወንድ አይደለህ እንዴት ብሎ ያስችልሀል?»
«ወንድ ልጅ አያስችለውም ያለሽ ማነው?»
«ቢያስችላችሁማ መች ከፍላችሁ ትተኙን ነበር?»
(ዝም ብሎ ትንሽ ማሰብ...ከአባባሏ ላይ ስትህት ማጣት...ልመናውን መቀጠል...)
«ቆይ እኔ ብዙ ቀን ሳልነካ አልመለስኩሽም?»
«እና በራስህ ፍላጎት ነዋ! ቤትህ መጥቼ 'አትንካኝ' ብልህ ግን ለራሴም አያሳምነኝ...አንተም የሌለብህ ሰይጣን መውጣቱ አይቀርም።»
«እእእ እና ያሁኑንን ወር ስራ ብትገቢባት ማሪያም ትቀይምሻለች?»
«በሀይማኖቴ አታሹፍ!»
«አንቺ ነሽ'ኮ እያሾፍሽ ያለሽው። ገላሽን ሽጠሽ እያደርሽ ማሪያምን አልነካም ስትይ አታፍሪም…
❤84😁15
Signed Papi
14 Jul 2026, 08:50 UTC≈7,100 views103 reactionsread 3 September 2026 ትንሹ ጆኒ ለአስተማሪዉ እየነገረዉ ነዉ ።
እኛ ቤት በጣም ትንሽ ናት ቤታችን እና እናቴ አባቴ እኔ ሁላችንም ምንተኛዉ አንድ አልጋ ላይ ነዉ ። እና ሁሌ ማታ ላይ አባቴ እንደተኛሁ እና እንቅልፍ እንደወሰደኝ ቼክ ያደርገኛል “ ተኝተሀል ?” ብሎ ሲጠይቀኝ
“አይ አልተኛሁም “ እለዋለሁ። ከዛ በጥፊ ያጠናግረኝ እና ይገላምጠኛል ብሎ ነገረዉ። አስተማሪዉ ሰማዉ እና “ይኸዉል ዛሬ አባትህ ቼክ ሊያደርገህ ተኝተሀል ብሎ ሲጠይቅህ ዝም በል ትንፍሽ ሳትል እንደተኛ ሰዉ ጨፍነህ ምንም መልስ እንዳትሰጥ “ ብሎ መከረዉ ።
ከዛ በሶስተኛዉ ቀን አስተማሪዉ ህፃን ጆኒን ፊቱ አባብጦ ቀይ ሆኖ ጥግ ቆሞ ያየዋል ።
አስደንግጦ “ እረ ምንጉድ ነዉ ፊትህ ምን ሆነህ ነዉ እንዲህ…
😁86❤17
Signed Papi
14 Jul 2026, 08:50 UTC≈5,440 views145 reactionsread 3 September 2026 ከራሴ የማልወደው አንድ ነገር ቢኖር አስራ ስድስት አመት ዘግይቼ መፈጠሬን ነው። በቻልኩት አቅም ላስተካክለው እሞክራለሁ። ጂንስ አልለብስም። ካኪ ሱሪ በወፍራም ሹራብ ለብሼ ጥግ ላይ እቀመጣለሁ። የዘወትር ፀሎቴ ሌላ አይደለም። "እባክህ ጌታዬ እኩያዋ አርገኝና አግብቻት ከዚህ መርዛማ ህዝብ ነጥቄ ወደ ሸዋ ልውሰዳት!!" ነው።
በዚህ አመት ነው ከባለቤቷ እና ከሁለት ልጆቿ ጋር እኛ ወደምንኖርበት አከባቢ የመጡት። መልኳ፣ ፀባዩዋ እና አለባበሷ አንድ አይነት የሆነላት ሴት የማውቀው እሷን ነው። እንዲሁ ቀልብን የሚሰልብ ርግት ያለ ድባብ አላት። መንገድ ላይ ስታልፍ አባውራው ሁላ ምናምኑን በጋቢው እየሸፈነ ነው የሚያያት።
ራሷን ልታጠፋ ሞክራ ከተረፈች ቡኃላ ግን…
❤133😁12
Signed Papi
8 Jul 2026, 10:45 UTC≈6,360 views107 reactionsread 3 September 2026 "ካብ ለካብ"
++++++
(በአንድ የፈረንጅ ቲክቶክ ቪዲዮ መነሻነት የተጻፈ ቀላል ታሪክ)
------------
አልጋው ላይ ተኝቶ አጫጭር ቪዲዮዎችን እያፈራረቀ ሲመለከት ስልኩ ጠራ።
የደዋይዋን ስም ሲያይ ፈገግ አለና በሁለተኛው ጥሪ አነሳው።
«ሄይ የኔ ፍቅር። እንዴት ዋልክልኝ? የት ነህ?» አለችው።
«ሄይ ማሬ... ቤቴ ነኝ» ብሎ መለሰላት።
«ቤትህ ምን እያደረግክ?»
«ምን አደርጋለሁ?…ዝም ብዬ ስልኬ ላይ ያው በቲክቶክ እየዛግኩ»
«ውይ…ደብሮሃል እንዴ የእኔ ፍቅር?»
«አይ ብዙ አልደበረኝም…»
«ኦኬ…እኔማ የደወልኩልህ ዓለም ሲኒማ ቴአትር ልንገባ እንደሆነ ልነግርህ ነው.. ከዛ በኋላ ደሞ እራት እንበላለን ብለናል፣ ስለዚህ ዛሬ አልመጣም። አርብ ስ…
😁74❤33
Signed Papi
8 Jul 2026, 08:44 UTC≈5,280 views82 reactionsread 3 September 2026 "ፖስት ፒል ግዛልኝ" የሚል የጽሁፍ መልእክት ላከችልኝ። የታዘዝኩትን ልፈፅም ፋርማሲ ተገኘሁ።
ፓራስታሞል ፋላጊው ፥ ኮንዶም ሸማቹ ፥ ቬርሞክስ ገዢው... ከፋርማሲው የሚፈልጉትን ሲወስዱ ከሻጩ ፊትለፊት አቀርቅሬ ቆምኩ። "ምን ልታዘዝ?" ሲለኝ ነበር የባነንኩት። እያማጥኩ "ፖስት ፒል" አልኩ።
ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ፖስት ፒል ገዛሁላት።
አፈቅራታለሁ። ስለ እኔ ስታወራ "የቅርብ ጓደኛዬ ነው" ትላለች። "እንደ ወንድሜ ነው የማየው" ትላለች። "ከንፁህ ጓደኝነት የዘለለ ነገር የለንም" ትላለች። እኔ ግን አፈቅራታለሁ።
እንደማላገኛት እያወቅኩ ሳልማት ኖርኩ። የእኔ ላደርጋት እየተመኘሁ የሌላ ስትሆን አየሁ።
ናቲ በድን እንዳየ አው^ሬ ሲያንዣብብባት "ተጠን…
😢54❤28
Signed Papi
5 Jul 2026, 09:14 UTC≈6,100 views177 reactionsread 3 September 2026 በወጣቶች የተቋቋመ Christ way የሚባል International church ቃል ልካፈል ገባሁ።
ሙሉ ለሙሉ ወጣቶች ናቸው። ሙዚቀኞቹ ፣
ሰባኪዎቹ ፣ ዲያቆናት ፣ ዘማሪዎች ሁሉም ወጣቶች ናቸው።
በየወንበሩ ተመስጠው በሚፀለዩ ሴቶች ውብት እየተዋከብኩ አንዲት የማለዳ የምንጭ ውሀ የመሰለች ልጅ ጎን ለፀሎት በተነጠፈ ጅባ ላይ ቁጢጥ ብዬ የሚካሄደውን ማስተዋል ጀመርኩ።
አንድ ስድስት ሰባት መፅሀፍ ቅዱስ የያዙ ወጣቶች በየረድፉ እየዞሩ ምእመኑ ላይ እጅ እየጫኑ ይፀያሉ።
አንዱ በልሳን እያወራ ወደኔ ቀረበ።እጁን ጭኖ ሊፀልይብኝ ነው ገብቶኛል። ባልወድም ልታገሰው ወሰንኩ። ግምቴ ልክ ነበር!
"ዛሬ በእግርህ ትሄዳለህ" ሲል ግንባሬን ይዞ ጸለየልኝ።
ምን ሆኖ…
😁149❤28
Signed Papi
4 Jul 2026, 07:23 UTC≈6,170 views81 reactionsread 3 September 2026 መንገድ ላይ የጀበና ቡና የምትሸጥ ሴት ማፍቀርኮ ችግር የለውም። ችግሩ ፉክክርህ ከግንበኛ፣ ከተራ አስከባሪ፣ ከአናፂ ምናምን ጋር ነው።
የማስተርስ ዲግሪ ሰርቼ...ስምንት አመት ሙሉ የባንክ ስራን ቀጥቅጨ...ያሰብኩትን ሁሉ ጨብጬ...የአልማዝ ልብ ግን ከመንገድ ወያላዎች ለይቶ አያዬኝም።
«የሴት ልጅን ልብ የሚያሸንፈው ያልተጫወተ ነው» የሚለው የእማዬ ምክር እዚህ ላይ አይሰራም። በኑሮ ሰባት እጥፍ የምበልጣቸውን ሰዎች በምላስም በልጨ መገኘት አለብኝ። ችግሩ መሰሎቼ ስላልሆኑ ያ ባለጌ ሽመልስ እንደ ኮሜዲያን የሚታይበት ዳስ ውስጥ የኔ ቀልድ እጅ እጅ ይላቸዋል።
አንዳንዶቹማ እያወራሁ በፈጠጣው አቋርጠውኝ ሁላ ሌላ ወሬ ይጀምራሉ። ሽመልስ ማውራት ሲጀምር ግን…
😁49❤32
Signed Papi
2 Jul 2026, 08:34 UTC≈5,680 views112 reactionsread 3 September 2026 ታክሲ ውስጥ ስለገጠመኝ ሰውዬ እያዋራኋት ነው። በጣም ስላሳቀኝ መስማት እንዳልፈለገች እያወቅኩ ነው የማወራት። ለንቦጯን ብትጥልም በጨዋታው ላይ ስለተማመንኩ ወሬዬን ቀጠልኩ።
ረዳቱ «ለህፃኑም ትከፍላለህ!» ሲለው ሰውዬው «አልከፍልም» ይላል!
«ትከፍላለህ!»
«አልከፍልም!»
«ካልከፈልክ ወንበር አይዝም።»
«ይይዛል!»
«ከያዘ ክፈል!»
«አልከፍልም!!»
«ካልከፈልክ እቀፈው?!»
«ይከብደኛል!»
እኔ 😂
እሷ 😑
«በቦታው ብትኖሪ በጣም ነበር የሚያስቅሽ» አልኩ ሀፍረቴን እያፋፈስኩ።
«ብታይ ረዳቱ ራሱ ሰውዬው እንደዛ ሲል ዙሮ ሁላችንም አዬን...የታክሲው ሰው እንዳለ አፍሮ ዝም አለ...እኔ ነኝ ያቃተኝ...'ቡፍፍፍ' ብዬ መሳቅ ስጀምር ሁሉም ያፈነውን ሳቅ ለቀቀው…
❤77👏35
Signed Papi
Showing the 12 most recent of 21 posts we hold for @wegoch. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.