10 Aug 2026, 15:49 UTC516 views7 reactionsread 12 August 2026 ከራሴ የማልወደው አንድ ነገር ቢኖር አስራ ስድስት አመት ዘግይቼ መፈጠሬን ነው። በቻልኩት አቅም ላስተካክለው እሞክራለሁ። ጂንስ አልለብስም። ካኪ ሱሪ በወፍራም ሹራብ ለብሼ ጥግ ላይ እቀመጣለሁ። የዘወትር ፀሎቴ ሌላ አይደለም። "እባክህ ጌታዬ እኩያዋ አርገኝና አግብቻት ከዚህ መርዛማ ህዝብ ነጥቄ ወደ ሸዋ ልውሰዳት!!" ነው።
በዚህ አመት ነው ከባለቤቷ እና ከሁለት ልጆቿ ጋር እኛ ወደምንኖርበት አከባቢ የመጡት። መልኳ፣ ፀባዩዋ እና አለባበሷ አንድ አይነት የሆነላት ሴት የማውቀው እሷን ነው። እንዲሁ ቀልብን የሚሰልብ ርግት ያለ ድባብ አላት። መንገድ ላይ ስታልፍ አባውራው ሁላ ምናምኑን በጋቢው እየሸፈነ ነው የሚያያት።
ራሷን ልታጠፋ ሞክራ ከተረፈች ቡኃላ ግን…
❤5😍2
Signed Wasye
9 Aug 2026, 10:13 UTC714 views3 reactionsread 12 August 2026 ሰሞንኛ
(በእውቀቱ ስዩም)
በአገራችን በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ ወጣቶች የአካል ብቃት ፉክክር ሲያደርጉ በቲክቶክ ሳይ ደስ ይለኛል ፤ የሆነ ቦታ ጡንቻቸውን በስሚንቶ በተበጀ ዳምቤል ያጠጠሩ፣ ከወገባቸው በላይ የተራቆቱ ጎረምሶች ወደ ካሜራው አየሾፉ እንዲህ ይላሉ፤ ‘ ኢስቲ ወንድ ናን የሚል ካሌ ኢሂንን ቻሌንጂ ይሞኪር፤ የኛ ጀማ! ማኒንም አይሰማ ! “
ስክሮል ሳደርግ ሌላው ቡድን ከሆነ አካባቢ ብቅ ይላል፤ የቡድኑ መሪ በዳጉሳ ቂጣ ዳጎስ ያለውን ደረቱን እየመታ ‘’ እስቲ ይህንን ደረት አጣብረው፤ ሰባ አመት ብትማስን ምታመጣው ይመስልሀል፤ የልምጥ ልይ ! የኛ ዠማ ! ማንንም አያምጥ፤ ደሞ ሸር ኮቢሊንክ ማረግ እንዳይዘነጋ” የ…
❤2👌1
Signed Wasye
7 Aug 2026, 15:50 UTC905 views5 reactionsread 12 August 2026 የመጻተኛው አገር
አገር ድንኴን ት'ኹን
ጠቅልዬ የማዝላት
ስገፋ እንድነቅላት
ስረጋ እንድተክላት
✍️በውቄ
@WAS143
@WAS143
❤5
Signed Wasye
6 Aug 2026, 18:30 UTC≈1,110 views16 reactionsread 12 August 2026 «የምር? የምርህን ነው?!»
«ምን ልበልሽ?»
«መልስልኝ የጠዬቅኩህን!»
«አዎ የምሬን ነው። እስከሞት ድረስ ነው የምወድሽ!»
«ቆይ...መቼ ነው የወደድከኝ?...ማለቴ ኤግዛክትሊ ምን ሳደርግ አይተኸኝ ነው ልሙትላት ያልከው? የትኛው ጨዋታዬ ነው በሌላ ነገር እንድታስበኝ ያደረገህ? የትኛው ቀሚሴ ነው ምኞት የቀሰቀሰብህ?»
«ኧረ እኔ የመጀመሪያ ቀን እንዳዬሁሽ ነው የወደድኩሽ።»
«ስለዚህ በመልኬ ነው ማለት ነው?»
«አላዬሁትም ነበር ፊትሽን።»
«ሰውነቴን አይተህ ነዋ? በአቋሜ?!»
«የለም። ተቀምጠሽ ነበር።»
«እና ምኔን ነው የወደድከው?»
«ፀጉርሽን! ፀጉርሽ ነው ጠልፎ የጣለኝ።»
እጇ የቻለላትን ያህል ዘግና እየተመለከተች...«ያን ያህል ራሱ'ኮ አልን…
❤9👍6👌1
Signed Wasye
5 Aug 2026, 22:15 UTC≈1,100 views8 reactionsread 12 August 2026 እኔ እንደሁ ስወድ አያምርብኝም። መጥኜ ማፍቀር አልችልበትም። እሷን ደግሞ መጎተት ሳቆም ነው የምስባት። ቀለል ስል ነው የምከብዳት። በድን ስሆን ነው ስሜት የምሰጣት።
ስኖር አልጥማትም። ስሞት ነው የምትወደኝ።
እኖራለሁ ብዬ ፍቅሯን ማጣት አልሻም! እስከሞት ድረስ ነው የምወዳት!!
@WAS143
@WAS143
❤6👌1🥰1
Signed Wasye
4 Aug 2026, 20:39 UTC≈1,250 views28 reactionsread 12 August 2026 «ናፈቅሽኝ አቦ !» ብዬ የፃፍኩት
ኩራት ሲሰማኝ - ቀድጄ ጣልኩት ።
«ናፈቅከኝ በጣም» ብለሽ የፃፍሽው
ልምምጥ መስሎሽ
ወርውረሽ ጣልሽው ።
የፍቅር ብርሃን እንዳልተሰማን
ቅር እንዳላለን እንዳልናፈቅን
በአዲስ ወረቀት - ፀብ ተላላክን ።
እንበልና ...
እኒያ ወረቀቶች ...
ቀደን የጣልናቸው
የክረምት ጎርፍ አገናኛቸው ።
እስኪ አስቢያቸው ...
ደራሽ ተሳፍረው
ሆነው ጎን ለጎን
እርስ በርሳቸው ተያይተው ቢሆን ?
ምን ይሉን ይሆን ?
ሀብታሙ✍️
@WAS143
@WAS143
❤15👌7😍4👏2
Signed Wasye
4 Aug 2026, 14:55 UTC≈1,260 views20 reactionsread 12 August 2026 ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል።
«ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?» ትላለች አንደኛዋ።
«እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!» ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች።
እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል።
ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው።
«ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?» ይለኛል።
«ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?»
«አይ ሻማው ይሁን በቃ!» ይላል እየተቅ…
❤10👏6👌3🥰1
Signed Wasye
28 Jul 2026, 09:26 UTC≈1,960 views25 reactionsread 12 August 2026 እስቲ ዛሬ ደግሞ ለለውጥ ያክል አለቃ ክንፌ የላኩልኝን ግጥም መሳይ ምክር ልጋብዛችሁ!
(ለለጅ ምክር የአባት መታዘቢያ)
ልዠ ሆይ!
ሙቫይልህን አስቀምጥ
ምክሬን አድምጥ !
ጦርነትን የሚጠምቀው
እድሜውን ብትጠይቀው
የማቱሳላ ገራዥ
የአብርሀም ዣንጥላ ያዥ
በጎሽ ያረሰ
አዳምና ሄዋን ገምጠው የተፉትን በለስ አንስቶ የጎረሰ
የሎጥን ሚስት ሀውልት የላሰ
ሆኖ ታገኘዋለህ ፤
ልዠ ሆይ!
ጦርነትን የሚያውጀው
ያረጀው ነው የጃጀው
ግና ጦርሜዳ ላይ የሚዋጋው
ያንተ ብጤ ነው ለጋው፤
ሜሲ አንደመታት ኩዋስ ወደ መቃብር የሚልለጋው፤
ልዠዋ!
በጀግኖች ዘመን እንኩዋ-“ከመሞት መሰነበት” ይባላል
የሰማእት ሀውልት ሆኖ ተመቆም
ህያው ሆኖ መተኛት ይሻላል
ልዠ ሆይ!
በሀያ…
❤20👌3👏1🥰1
Signed Wasye
23 Jul 2026, 18:44 UTC≈2,340 views11 reactionsread 12 August 2026 ወጣቶች ነበርን
በእውቀቱ ስዩም
ጊዜ ሲራመድ ኮቴው ድምጥ አልባ
ከየት ተነስቶ ወደ የት ገባ
ከየት ተነስቶ ወዴት ደረሰ
ጠጉር መንጥሮ፣ ፊት እያረሰ፤
ወጣቶች ነበርን
ቅጽር የሰራን ፤ አምባ የሰበርን
ኮካ ኮላውን ባሲድ በርዘን
ብንጎነጨው፤ የማይመርዘን፤
በራዱን ያጋልን፣ ሙት ልብ ያስነሳን
ግራዋ በልተን ፤ ሎሚ ያገሳን፤
ተስፋችን ብዙ፤ እድሚያችን ለጋ
ስንሰማራ፣ ትርጉም ፍለጋ
ገላችን አይፈዝ፣ ጭቃ ቢለሰን
የማናስቀይም፤ ቡትቶ ለብሰን
ገጻችን ብሩህ፤ ልባችን ሽፍታ
ስንመነጠቅ፤ ወደ ከፍታ
የስኬት ገነት፣ ደጃፏን ከፍታ
ምትቀበለን ፣ እየመሰለን
ከቁመታችን በላይ፣ የዘለልን፤
ወጣቶች ነበርን
ዛሬ እንደዋዛ
ዘንድሮን ምሰን፤ ታችአምናን ቀበርን፤
@WA…
❤7👏3🥰1
Signed Wasye
20 Jul 2026, 09:28 UTC≈2,530 views12 reactionsread 12 August 2026 የጋራ ድል
(በእውቀቱ ስዩም)
የስፔን ደጋፊ ብሆን ምን ያስገርማል? ስፔን በስነፅሁፍ አክብራ የጋበዘችኝ አገር ናት፤ ስፔን ሁለተኛ አገሬ ናት ብል ኩሸት አይሆንም፤
ስፔን እንድታሸንፍ ፈልጊያለሁ፤ ያም ሆኖ፣ ከጉዋደኛየ ከካሳ ጋራ አር-ጄንቲና ታሸንፋለች ብየ በአራት ሺ ብር ተወዳደርሁ፤ ስፔን ካሸነፈች እፈነጥዛለሁ፤ አርጄንቲና ካሸነፈች ደግሞ ላብ ያልገነፈለበት ፣ እንቅልፍ ያልተሰዋበት አራት ሺ ብር አካውንቴን ያጠበድላል ብየ አሰብኩ፤ በሁለቱም በኩል አሸናፊው ነኝ የሚል መላ መጣልኝ፤
በመጨረሻ እንዳያችሁት ስፔን፣ በረኛ ሳይሆን በር የሆነውን የአርጀንቲናን ግብጠባቂ ጣጥሳ አገባች፤ ዋንጫውን ጨበጠችው፤ደስ አለኝ፤ግን ደስታየ…
❤5🤣3👏2😁2
Signed Wasye
19 Jul 2026, 20:23 UTC≈2,380 views20 reactionsread 12 August 2026 "ባጭር ቀረን" ስንል - እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
።።።።
ፊታችንን ዐይተው
እንደተቸገርን - ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን
እስክንለምናቸው - ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
።።።።
ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ፣ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፣ ፈጥነው ለሚረሱ😉
ቺርስ!!!!
።።።።።።
ላባ ላረጉልን ፣ የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን ፣ ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ...
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
።።።።።።።።።።።
(✍️ Bewketu Seyoum )
መልካም ልደት በውቄ!!!
@WAS143
@WAS143
❤18😍2
Signed Wasye
11 Jul 2026, 16:23 UTC≈2,870 views20 reactionsread 12 August 2026 ኦሮማን
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰሞኑን እንደ አዲስ አስቴር አወቀን ሳደምጥ፣ በአሉ ግርማ ትዝ አለኝ፤ የበአሉን ኦሮማይ ታስታውሱታላችሁ ? ፀጋየ ሀይለማርያም ጋዜጠኛ ነው፤ ሮማን የተባለች ውብ ኩሩ እጮኛ አለችው፤ ሊጋቡ ጥቂት ወራት ሲቀራቸው በቀይ ኮከብ ጥሪ አስመራ ለግዳጅ ተላከ፤ በዚያም በዘመቻው መሀል ፊያሜታ የተባለች ያስመራ ሴት ተዋወቀ፤ ከባድ ፎንቃ ገባለት፤ ባስመራይቱና በሸገሪቱ ሴቶች ፍቅር መሀል ተወጥሮ በታሪካዊው ዘመቻ ላይ ተሳተፈ ፤ በመጨረሻ ሮማን አስመራ መጥታ ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር አንደያዘው ተረዳች፤ ፊያሜታ ለሱ ብላ ህይወትዋን ትሰጣለች፤ በመጨረሻም ፊያሜታን በሞት ሮማንን በቅያሜ አጥቶ አጥቶ ብቻውን ሲቀር ልቦለዱ ይጠና…
❤20
Signed Wasye
Showing the 12 most recent of 22 posts we hold for @was143. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.